ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
😂🌍 ለፈገግታ 🌎😂

"......አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ። በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ። ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ። በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ዳቦ አምራች ነጋዴው ገበሬው የሚልክለት የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሔዱን አየ። በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው። በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም። ገበሬውንም አስጠራው። ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ' ከተስማማነው ውጪ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው? ' ሲል ጠየቀው። ገበሬውም ' እኔ ፈፅሞ አልቀነስኩትም ' ሲል በአግራሞት መለሰ። ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው። 150 ግራም ነው። ገበሬውም አዘነ። ' እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም። አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሀን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዛም ቂቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ። ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሀለው ' አለው። ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው። ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው። ነጋዴው አፈረ።.........."
የምናገኘው የሰጠነውን ያህል ነው!!!
ምንጭ:- "ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች" በዲያቆን ዳንኤል ክብረት 2012 ገፅ 125-126

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

".....' ባልቻ አባ ነፍሶን እድሜዎት ገፍቷል፤ መሞትዎ ካልቀረ ለልጆችዎ የሚሆን፤ ለትውልድ የሚተርፍ ሀብት፤ ቅርስ አትርፈው ቢሞቱ ይሻሎታል። ' ብለው እጅግ ብዙ ጊዜ ለምነዋቸዋል። በተደጋጋሚ መሳሪያ አጥተው፣ ስንቅ ጨርሰው በልዩ ልዩ ምክንያት ተዳክመው ተሸንፈው ያውቃሉ። ይህንን ግን ለመቀበል አልሆነላቸውም። በመጨረሻ የነበሩበትን ስፍራ አገምጃን ጣልያኖች ከበቡት። ሰዎቻቸው ሁሉ ጥለዋቸው ሔዱ። እርሳቸውና ሁለት ወዳጆቻቸው ቀሩ። ጣልያኖች ወደ አባ ነፍሶ ሔዱ። ለዚያውም ባልቻ የእምነት ሰው ናቸው ተብሎ፤ የእምነት ሰዎች ሁሉ ከፊት እንዲቀድሙ ተደርጎ ነበር የሔዱላቸው። ባልቻ አባ ነፍሶ በቤታቸው እንደተቀመጡ ጣልያኖች ወደእሳቸው መጡ።
' አንተ ማነህ? ' ብለው ጠየቋቸው።
' ባልቻ አባ ነፍሶ ' አሉ።
' እጅህን ስጥ፤ መሳሪያህንም ፍታ? ' አሏቸው።
ባልቻ አባ ነፍሶ መልሰው፤
' እኔ እጄን መስጠት አላውቅም። ብቻዬን በቆም እንኳን ለሀገሬ የሚያስፈልጋትን አደርጋለሁ። አሉና፤ ካባቸውን ገለጥ አድርገው መሳሪያቸውን አውጥተው በፊታቸው የነበሩትን የጣልያን ወታደሮች ገድለው እራሳቸውም ሞቱ። ባልቻ አባ ነፍሶ በዚያን ጊዜ ዐሥር፤ ዐሥራ አምስት ወታደሮች ስለገደሉ፤ ' እኔ ገድዬ ሀገሬ ነፃ ትወጣለች ወይ? ምን እጠቀማለሁ? ' ቢሉ ኖሮ ባልቻን ከነ ክብራቸው ዛሬ አናስታውሳቸውም ነበር። በዚያን ሰዓት የቆሙት ብቻቸውን ነው። ......"

~~~~~~ ይቀጥላል ~~~~~~

ምንጭ:- "ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች" በዲያቆን ዳንኤል ክብረት 2012 ገፅ 192-193

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🎥📻 ከታሪክ_ማህደር 🎙🎞

🏃‍♂ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ያስመዘገበው አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰን 2:15:16:2 ነበር። በባዶ እግር ሮጦ ማራቶንን ያሸነፈ ብቸኛ የፕላኔታችን ሰው ነው። ድርብ ድርብርብ ድል ነው። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሊካሔድ 40 ቀናት ሲቀረው የትርፍ አንጀት መታወክ ደርሶበት ቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በኋላ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ተወዳድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የድልን አክሊል ከእነ ክብረ ወሰን ጨበጠ! ያስመዘገበውም ክብረ ወሰን 2:12:12:11 ነበር። ከተናገራቸው መካከል
" ለምወዳት ሀገሬ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ የሺህ ዓመት መኩሪያ እና መከበሪያ ታሪክ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሠራሁ ከእንግዲህ በኋላ የምመኘው ነገር የለም። "
" የወርቅ ሜዳልያ ለእኔ ባያስፈልግም ለአገሬ ግን ያስፈልጋታል። "
" እኛስ ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ምን አደረግንላት?"

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🎬 ሰኔ 30 🎬
ሰኔ ሰላሳ ከሚለው ፊልም የተወሰዱ አስተማሪ ንግግሮች

....."አንዳንድ እውነቶች ኑሮህን ሰውተው ይገቡሀል። ብልህ ከሆንክ ግን በኑሮ ከገባቸው ትማራለህ።".....
....."ህይወት ተቃራኒ የላትም፤ ዘላለማዊ ነች። ስጋዊ መገለጫዎች ይቀራሉ እንጂ ከሞት በኋላ እንኖራለን።"....
......"ሰው ሀገሩን ማህበረሰቡን ለመግለፅ፣ ለመዳኘት ከመሞከሩ በፊት ሰውነቱን እራሱን ማወቅ አለበት። አለም ሰው ውስጥ ነው ያለው። የውስጡን አለም ያወቀ የሚታየውን አለም መግለፅ አይቸግረውም። ሰው ሰውነቱን ቢረዳ ይሄ ሁሉ ችግር አለምን ሁሉ ባላመሰ፤ ከዜግነትም ከሀይማኖትም ሰውነት ይቀድማል። ሰውነታቸው ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው ሀገር ማለት ይገባቸዋል። እኔ ማነኝ እያልን ከራሳችን ጋር እናውራ ተፈጥሮ መልስ እየሰጠ ወደ እውነቱ ያደርሰናል። "......
......."ፈሪ ምን ጊዜም ይቀጣል። ሂድ ሴቶች ብልሆች ናቸው፤ ችግኝ ነኝ ብትልም ጎጆ ሰርታ ታሳይሀለች። ሰው ሙሉ የሚሆነው አጋር ሲኖረው ነው።"......
......"እንግዲ ሰው አንዴ ከአምሮው አንዳንዴ ከልቡ ነው። አእምሮ ምድራዊ ሲሆን ልብ ደግሞ መንፈሳዊ ነው። እግዚአብሔር ልብሽን አእምሮሽ ላይ ካሰለጠነው የወጣትነቱ እሳት አይነካሽም። ከልብሽ ከሆንሽ እዚህም ሆነሽ ትመነኩሻለሽ።"......
....."ቅን ሁኚ የተወደደ ሰው ነው መወደዱን የሚያጣው፤ የወደደማ መውደዱ ሁሌም ከእርሱ ጋር ነው። ነገርሽን ለእግዚአብሔር ስጪ ጊዜ ያልፋል፤ አንቺነትሽን ማፍቀር ነው ፍቅር ማለት አይደል?"......
....."ህይወት ብርቱ ቅኔ ነች። ሰው ለመቀየር አንድ ቀን ይበቃታል። በትናንትና እና በዛሬ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ።"....
......"ወይ ጊዜ ይቆጣጠርሻል ወይ ጊዜን ትቆጣጠሪዋለሽ። ያለ ፍርሀት የወሰኑት ውሳኔ ነው ትክክል። ለራስሽ አንድ እድል ስጪው። በጊዜ የወሰንሽው ሳይሆን በፍቅር የወሰንሽው ይበልጣል።"....

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 via @like
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓 ".....' ባልቻ አባ ነፍሶን እድሜዎት ገፍቷል፤ መሞትዎ ካልቀረ ለልጆችዎ የሚሆን፤ ለትውልድ የሚተርፍ ሀብት፤ ቅርስ አትርፈው ቢሞቱ ይሻሎታል። ' ብለው እጅግ ብዙ ጊዜ ለምነዋቸዋል። በተደጋጋሚ መሳሪያ አጥተው፣ ስንቅ ጨርሰው በልዩ ልዩ ምክንያት ተዳክመው ተሸንፈው ያውቃሉ። ይህንን ግን ለመቀበል አልሆነላቸውም። በመጨረሻ የነበሩበትን ስፍራ አገምጃን ጣልያኖች ከበቡት። ሰዎቻቸው ሁሉ ጥለዋቸው…
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

ከባለፎው ክፍል የቀጠለ
"........ባልቻ አባ ነፍሶ በዚያን ጊዜ ዐሥር፤ ዐሥራ አምስት ወታደሮች ስለገደሉ፤ ' እኔ ገድዬ ሀገሬ ነፃ ትወጣለች ወይ? ምን እጠቀማለሁ? ' ቢሉ ኖሮ ባልቻን ከነ ክብራቸው ዛሬ አናስታውሳቸውም ነበር። በዚያን ሰዓት የቆሙት ብቻቸውን ነው። ንጉሡ የሉም። የሚሸልማቸው ማንም የለም። የሚያከብራቸው የለም። ወዳጆቻቸውም ሸሽተዋል። ወዳጆቻቸው ብቻ ሳይሆኑ እድሜና ጉልበትም ሸሽቷቸዋል። ምንም አይነት የሚያገኙት ሹመትና እርስት የለም። ለመርሐቸው ግን ብቻቸውን ነበር የቆሙት። ይሄ ነው ዛሬ የሚያዋጣን። ብቻን መቆም።
አብዲሳ አጋን እዚህ ላይ ማስታወስ ተገቢ ነው። በጣልያን ሀገር ብቻውን እንዴት እንደቆመ። ከጣሊያን ከሚያገኘው ጥቅም ይልቅ ከእውነት ለሚያገኘው ክብር ሲል ብቻውን ቆመ። ምንም ለማድረግ አይቻልም በሚባልበት ቦታና ዘመን ዘርዐይ ደረስ እንዴት ብቻውን ቆመ? የጣሊያን ወታደሮች በሞዐ አንበሳ ሐውልት ላይ ሲሳለቁ፣ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማም ሲዘባበቱ አየ። ማንም በሌለበት፣ ብቻውን ለሀገሩ ክብር ቆመ።......."
~~~~~ || ~~~~~ || ~~~~

ምንጭ:- "ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች" በዲያቆን ዳንኤል ክብረት 2012 ገፅ 193

"ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎችም"
ጥር ወር 2012 እትም
ደራሲ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
መፅሐፉ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያጠነጠነና ብዙ ነገሮች የሚዳስስ በመሆኑ ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
ደራሲው የፃፋቸው መፃሕፍት በቁጥር 33 ይደርሳሉ። ከነዚህም መካከል
1.የኔ ጀግና እና ሌሎች
2. የሰርቆ አደሮች ስብሰባና ሌሎች
3. ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት እና ሌሎች
4. የአዲስ አበባ ዎሾች
እና ሌሎች ሀይማኖታዊ መፃሕፍትንም አበርክቷል።

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
#ሰሞነኛ ቅምሻ#

አንዳንዴ ለዘመናት ታስበው እና ተደክሞባቸዉ ከተሰሩ ስራወች በላይ እጅግ የጠለቀ ደስታ፣ሀዘን ወይም መከራ ከውስጥ ፈንቅለው የሚያወጡዋቸዉ ቅፅበታዊ ፈጠራወችና ተግባራት የአለምን የታሪክ መስመር ሲለውጡና ይህ ነዉ የማይባል ተፅዕኖ ሲፈጥሩ ኖረዋል።በታላቁ የቪክቶሪያን ዘመን እንግሊዛዊ ባለቅኔ እና ገጣሚ ዊልያም ኧርነስት ሄንሌ የተፃፈችው "invictus " የተባለች ግጥምም እዚህ ውስጥ ትመደባለች።
invictus ቃሉ ላቲን ነው።በ እንግሊዘኛ " invinsible" ወደ አማርኛው ስናስጠጋው ደግሞ 'አይበገሬው" ሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። ገጣሚዉ ገና በ25 አመቱ ያሣለፈውን ስንክሳር ዘካሪ ናት።እጅግ ፅኑ ህመም ግራ እግሩን ካሣጣው ቡሀላ ብዙወች ቀኙም እንደሚደገምና ብዙም ሳይቆይ እንደሚሞት ቢገምቱም ይህ ተዐምረኛ ሰው ግን ተስፋ ሳይቆርጥ በዘመኑ ዝነኛ ወደነበረዉ ዶክተር ጆሴፍ ሌስተር በማምራት ለመቀበል አይደለም ለማሰብ በማይችሉት ስቃይ ዉስጥ ሆኖ ከሀያ በላይ ቀዶጥገናወችን አካሄደ። እነዚህ ጥቂት ስንኞች በነዛ ብዙ ከባድ የመከራዉ ቀናት በአንዱ ድንገት ህመሙን፣ምሬቱን ፣ፅናቱን እና ተስፋዉን በአንድ ለውሶ የቋጠራቸው ናቸው።

ወራት አልፈው ብዙወችን ባስደመመ ሁኔታ እግሩንም ህይወቱንም ይዞ ከህክምናው ወጣ።በ 1888 ዓ.ም ባሣተመው 'Book Of Verses' በተሰኘው የግጥም መፅሀፍ ዉስጥም ይችን ግጥም አካተታት። እነሆ ከዛ ጊዜ ጀምሮ እኒህ ስንኞች ከቅዱስ መፅሀፍት ጥቅሶች ዕኩል በሰወች ልብ ውስጥ ነግሰዋል።ከቸርችል የሁለተኛው አለም ጦርነት ንግግር እስከ ኖርማንዲ ወታደሮች ዝማሬ፣ከማንዴላ የሮቢን ደሴት እስር እስከ ኦባማ የምርጫ ድል ብሎም ስፍር ቁጥር በሌላቸው ስራወች ውስጥ ተስተጋብተዋል።የማይደፈረውን ለሚደፍሩ ሁሉም የተስፋ ሰንደቅና የፅናት መዝሙር ናቸው። መንግስቱ ወ/ማርያም በ1882 ዓ.ም ካሳተመዉ ብልጭታ ከተሰኘው መፅሀፍ ውስጥ 'አይበገሬው' ብሎ የተረጎማትን ይችን ግጥም ለዚህ ከባድ ወቅት የ መንፈስ ስንቅ ትሆናችሁ ዘንድ እነሆ፦
Invictus(አይበገሬው)

'በድቅድቅ ፅልመቱ ካሰጠመኝ ሌሊት
ከእንጦርጦስ ጨለማ ፥ መድረሻ አልባ አዘቅት
ባማልክትሀይል ይሁን በምን ይሁንበምን
አልጠራጠርም በድል መወጣቴን።
የዕጣ ፋንታ ፍርጃ በጥፍሩ ቢያንቀኝም
ግንባሬን አልቋጥር ሙሾም አላወርድም
ህሊናየ ቢቆስል በክፋ ዕጣ ናዳ
እኔ እንደሁ ወይ ፍንክች ያበጠዉ ይፈንዳ
ከስቃይ ማዕበል ከዕንባ ጎርፍ ጀርባ
የጳዕረሞት ጥላ ሊያፍነኝ ቢያደባ
ያመታት መከራ ቢከመር ለትንግርት
ይየኝ አየዋለሁ አልበገርለት።
ጉዞየ ቢያስመርር ሆኖ የዳበሳ
የታሪክ ማህደሬ ፍዳየን ቢያወሳ
የዕጣየ ባለቤት እኔ ነኝ ራሴው
እኔው ነኝ መንፈሴን አቅጣጫ ማስይዘው'
ቸር ያሰማን🙏
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

🤷‍♂ ሁሉም ለውጥ እድገት አይደለም፤ ሁሉም እውቀት ጥበብ አይደለም።

🧪 በ1781 ፋራናይት ( Fahrenheit ) የተባለ ፈረንሳዊ ተርሞ ሜትርን ( thermometer with mercury ) ፈጥሮ ነበር።

🌴 የአለማችን አጭሩ እንጨት ድዋርፍ ዊሎው 5 ሴንቲ ሜትር እርዝመት ያለውና በግሪንላንድ የሚገኝ ነው።

🌳 ገዳ የኦሮሞ አስተዳደር ስርዓት አስተዳደሩ ጊዜውን ጠብቆ በየስምንት ዓመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሚቀያየርበት ስርዓት ሲሆን ከዓለም ኢትዮጵያን የመጀመሪያው የዲሞክራሲ ሀገር ያደርጋታል ተብሎ ይታመናል።

🧞‍♂🧞‍♀ Quote :- Who you are is what makes you special. Don't change for anyone.

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
😂🌍 ለፈገግታ 🌎😂

ከሕፃናት ለፈጣሪ የተላኩ ደብዳቤዎች
_______________

1. ጌታ ሆይ፤ ቀጭኔ እንደዚያ እንድትመስል ፈልገህ ነው ወይስ በድንገት የሆነብህ ነው? ~ ኖርማ

2. ጌታ ሆይ፤ ሰዎችን እንዲሞቱ እየፈቀድክ አዳዲስ ሰዎችን ከምትሰጥ ይልቅ፤ ለምን ያሉትን በሕይወት አታቆያቸውም? ~ ጄን

3. ጌታ ሆይ፤ በአንድ ሰርግ ላይ ተገኝቼ ነበር፤ እናም ሰርገኞቹ በቤተክርስቲያን ውስጥ ነበር የተሳሳሙት፡፡ ችግር ይኖረው ይሆን? ~ ኔሊ

4. ጌታ ሆይ፤ ሀገራትን የሚለያየውን መስመር ያሰመረው ማነው? ~ ናን

5. ጌታ ሆይ፤ ስለታናሽ ወንድሜ አመሰግናለሁ፡፡ ግን እኮ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ የነበረው ቡችላ ነበር፡፡ ~ ጆይስ

6. ጌታ ሆይ፤ በመዝናኛ ወቅታችን ዝናብ በመጣሉ ምክንያት አባቴ ተናዶ ነበር፡፡ እናም ሰዎች አንተን ሊሉህ የማይገባውን ነገር ብለውህ ነበር፡፡ እንደማትጎዳው ተስፋ አደርጋለሁ ~ ያንተው ወዳጅ ( ማንነቴን የምነግርህ አይሆንም )

7. ጌታ ሆይ፤ እባክህ ድንክዬ ፈረስ ላክልኝ፡፡ መመልከት ትችላለህ፤ ከዚህ በፊት ምንም ነገር ጠይቄህ አላውቅም፡፡ ~ ብሩስ

8. ጌታ ሆይ፤ ወደ ሆነ ነገር ተቀይረን የምንመለስ ከሆነ፤ እባክህ ጄነፈር ሆርቶንን አታድርገኝ፡፡ ምክንያቱም እጠላታለሁ፡፡ ~ ዴነስ

9. ጌታ ሆይ፤ በዓለም ላይ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ማፍቀር ይከብድሃል ብዬ እገምታለሁ፡፡ እኛ ቤት ያሉት ሰዎች አራት ብቻ ቢሆኑም፤ እኔ አልቻልኩም፡፡ ~ ናን

10. ጌታ ሆይ፤ ላንተ ከሰሩልህ ሰዎች መሐከል ኖህን እወደዋለሁ፡፡ ዳዊት ደግሞ ምርጡ ነው፡፡ ~ ሮብ

11. ጌታ ሆይ፤ የሰንበት ቀን በቤተክርስቲያን ውስጥ የምታየኝ ከሆነ፤ አዲሱ ጫማዬን አሳይሃለው፡፡ ~ ማይኪ

12. ጌታ ሆይ፤ ቶማስ ኤዲሰን ብርሃንን እንደሰራ እናነባለን፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤት ስንማር ግን ይሕንን ያደረግከው አንተ ነህ፡፡ ቶማስ ኤዲሰን ሃሳብህ ሰርቋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ትክክል ነኝ ኣ? ~ ዶና

13. ጌታ ሆይ፤ የተሻለ አምላክ መሆን የሚችል አለ ብዬ አላስብም፡፡ ይሄን የምለው ቀድሞውንም አንተ አምላክ ሆነህ ስለተገኘህ አይደለም፡፡ ~ ቻርለስ

14. ጌታ ሆይ፤ የማክሰኞውን ዕለት አድማስ እስካይ ድረስ፤ ብርቱካናማ ከሀምራዊ ጋር የሚስማማ አይመስለኝም ነበር፡፡ የሚገርም ነበር፡፡ ~ `ጄን

15. ጌታ ሆይ፤ አንዳንድ ጊዜ ስላንተ አስባለሁ፡፡ በማልፀልይበትም ጊዜ ጭምር፡፡ ~ ኢልዮት

16. ጌታ ሆይ፤ ስቴፕለር መምቻ ከምርጥ የፈጠራ ውጤቶችህ መሐከል አንዱ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ~ ሩት

17. ጌታ ሆይ፤ ምናልባት ቃየንና አቤል የየራሳቸው ክፍል ቢኖራቸው ኖሮ እርስ በእርሳቸው አይገዳደሉም ነበር ፡፡ ለእኔና ወንድሜ ሰርቶልናል፡፡ ~ " "

18. ጌታ ሆይ፤ ያንተ ዕድሜ ላይ ስደርስ፤ ልክ እንዳንተ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ~ ቶም
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ቆንጆዎቹ ከ ሠርቅ ዳ. 1989 ዓ.ም.pdf
6.8 MB
ድንቅና ዘመኑን የዋጀ ሀገርኛ መጵሀፍ👌
ሠርቅ ዳ. እጅህ ይባረክ🙏
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🤰👩‍👦መልካም የእናቶች ቀን👩‍👦🤰

እማምዬ የፍቅር ጥግ፣ የእናትነት አልፋና ኦሜጋዬ። እናንተ "ሴት እናት ናት! ሴት እህት ናት! " የምትሉ 'በደፈናው ኃይማኖተኛ ሁሉ መነኩሴ ነው' እያላችሁ ነውና ይቅር ይበላችሁ፤ ሴትነት እናትነት አይደለም። "ሴት ከውስጧ የወጣ ገዳም ውስጥ ስትመንን እናት ትሆናለች" ሴት.... "ልጅ" የሚባል መስቀል ተሸክማ የሕይወትን ቀራንዮ ስትወጣ 'እናት' ትባላለች፤ ሴት ልጅ የራሷን ዘመን ይቅርብኝ ብላ የልጆቿ የዘመን መስቀል ላይ በፍቅር ስትቸነከር ወደ እናትነት ከፍታ ታርጋለች።

ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም፡ ከአሌክስ አብርሃም , ገጽ 52

እናመሰግናለን

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
መልክአ እናት

ሰላም ለኪ እናታችን ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ።

ሰላም ለአይኖችሽ
ከጭስ ጋራ ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቀበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮየን ከምገፋ
ምነው እንባሽን ባረገኝ ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ

ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትናንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት ሞልቶ በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንችን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
ለካ በእርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ።

ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
ሰላም ለኪ!
ባለሽበት እንዳለሽ።

( በእውቀቱ ስዩም፡ ኗሪ አልባ ጎጆዎች እና ሌሎችም የግጥም ስብስብ, ገፅ 32)
መልካም የእናቶች ቀን❤️🙏
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
እናት
-----
በአሐቲ ግብሩ፣እግዜር ተሳሳተ
ለልጆች አድልቶ፣ለ'እናት ሰሰተ
በዝቶ ካልጠቀመ !
መናኛ ከሚያበጅ ፣ እየደጋገመ
ከሚባክን ጭቃ…
ልጆችን ቀንሶ ፣ እናት በደገመ
እንደ ሮሐ ውቅር
እንደ ደብረ ኤረር
እንደ ዙፋንህ አምድ፣አንተን ተሸካሚ
ዘላለም 'እማ' ቶድቅ
ባደረ'ካት እሷን ፣ ..እንደ ኪሩብ ቋሚ
.
« ሚኪ እንዳለ »
እናመሠግናለን
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🦅🖊 ስነ_ግጥም 🖌🦅

ሲጎል እያንኳኳ ግብር የጠየቀ፤
ማን ሊኖር እንደሆድ መብቱን ያስጠበቀ?
አሻፈረኝ ቢሉት ጦርነት አውጆ፤
አካላትን ማርኮ እሚያውል ከጎጆ።
በቀን ሶስት አራቴ እያንደረደረ፤
ንጉሥ ድሀ ሳይል ሁሉን ያስገበረ።
ጀግናስ ማለት እሱ ማንንም ማይፈራ፤
በመኖሩ ብቻ
ግብር የሚያስከፍል ከሰራም ካልሰራ ።

ምንጭ:- አለሚቱ ዳመና ፤ተስፋ አብ ዳካ ፤ 2004 ፤ ገጽ 93

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

📣 Quote :- Don't let yourself be controlled by three things:
🤦‍♂people🤦‍♀,
💸money💰, or
🔙past experiences.


🌈 The largest cave in the world, Hanson Doong, is in vietnam. It's over 200 meters high and has it's own climate⛅️, jungles🏞, rivers, and clouds☁️ inside.

🌡. በ1643 terriceli የተባለው ኢጣሊያዊ ባሮሜትርን (Barometer) ፈጥሮ ነበር።

🌊 በ1849 እ.ኤ.አ 6 ሜትር ቁመት ያለው በረዶ በስኮትላንድ ከሰማይ ወርዶ ነበር።😳🤷‍♂

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫

" እኔና ቹ "
ደራሲ ፍስሐ
ድርሰቱ በእሱና በቻይናዊቷ ፍቅረኛው መካከል በነበረው ግንኙነት አብረው ስላሳለፏቸውና ስለተጨዋወቷቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ ብዙ አገራዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ችግሮችን እያሳዘነም፤ እያዝናናም፤ እያስገረመም ለማሳየት ይሞክራል። ቢያነቡት ብዙ ጥቅም እንደሚያገኙበት እኔ ምስክር ነኝ።
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

.......ኢትዮጵያ 11.5 በመቶ እድገት ባስመዘገበች ቁጥር አንድ ምግብ ላይ 11.50 ጨምሮ ያድራል። ገቢው ግን ከማደጓ በፊት የነበረው ገቢ ነው። ምንም አይነት የኢኮኖሚ ሳይንስ ውስጥ መግባት ሳያስፈልግ የእያንዳንዱ አገር እድገት ከነዋሪው ህዝብ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መገናኘት ካልቻለ እንዴትም ሆኖ እድገት መባል እንደማይችል መከራከር ያስችላል። እኔ በግሌ "ኢትዮጵያ ልታድግ ነው" ሲባል ፍርሀት ይወረኛል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ባደገች ቁጥር መብላት እያቃተኝ እንደምሔድ አውቀዋለኋ! ......
ምንጭ:- እኔና ቹ ገፅ 175
ደራሲ ፍሰሀ
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

.........ኢትዮጵያ ውስጥ በየቢሮው ዛሬ ከምሳ በፊት ምን ሲሰራ ዋለ ብትይኝ፤ የምሰጥሽ መልስ ማናጀሮች የኮምፒውተር ጌም ሲጫወቱ፣ ፀሐፊዎች ተሰብስበው ተራ የመንደር ወሬ እያወሩ፣ የበላይ አለቃቸው ሊያሽኮረምማቸው መፈለጉን ሲተርኩ፣ ሌላው የቢሮ ሰራተኛ በቢሮ ስልክ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር ረጅምና እርባና ቢስ ወሬ ሲያወራ፣ የቀረው እንደኔና እንደአንቺ ሲሟገት፣ ሌሎቹ በስብሰባ ሰበብ እሽግ ውሀ ሲጎነጩ... ወዘተ ነው። ስልክ እያወራ ወይም ቢሮውን ዘግቶ የእኔ አይነት የኮምፒውተር ጌም ሲጫወት የነበረ ማናጀር በጌሙ በጣም ከመመሰጡ የተነሳ ባለጉዳይ መምጣቱ በፀሐፊው በኩል ሲነገረው "ስብሰባ ላይ ነው" በያቸው ብሎ ሲመልስ ነው የምሳ ሰዓት የሚደርስለት። ከሰዓትም እንደዚያው። ወይኔ ቹ የኢትዮጵያን ቢሮክራሲ ተዟዙረሽ የማየት እድል ቢገጥምሽ ከመገረም አልፈሽ ጨርቅ ወደመጣል ታመሪያለሽ። እንዲያውም በአጭሩ ይችን አገር ያደቀቃት ሌላው ችግር ስብሰባ ነው። ስብሰባና ጭብጨባ የዚች አገር አንኳር ችግሮች ናቸው። ታምኛለሽ .... በየመንግስት መስሪያ ቤቱ ቢያንስ በሳምንት አራት ቀናት የሙሉ ቀን ስብሰባ አለ። ከስድስቱ ቀናት ወይም ከአምስት ቀን ተኩል ውስጥ አራት ቀናት በስብሰባ ያልቃል! ከስብሰባ ይልቅ ግምገማ ቢባል ይሻላል። በዚህ ምክንያት ብቻ በየዘርፉ ያሉ ባለጉዳዮች ለአንዲት ፊርማ ልክ እንደ ኢሚግሬሽን ሦስት ወር ይጉላላል! ለአንዲት ፊርማ! ለምን?.... ፈራሚው ስብሰባ ላይ ነዋ! በዚህም ላይ በእያንዳንዷ ስብሰባ ለተሰብሳቢው በመስሪያ ቤቱ በጀት እሽግ ውሀ ይቀርብለታል። ለ30 ደቂቃ ስብሰባም ቢሆን የ30ሺ ብር ውሀ ሊቀርብ ይችላል። ያውም ላይጠጡት ከፍተው ተጎንጭተው ትተውት ለሚወጡት ውሀ! ደንብ ነውና ይቅርብኝ የሚል የለም። ስለዚህ ሳይጠማቸው ይጠጡና አስተርፈውት ይወጣሉ። ከዚህ ቢሮ ወተሽ ጥቂት መቶ ኪሎሜትር ስትጓዥ አንዲት ዳቦ አጥተው በረሀብ የሚሞቱ ልጆች ታገኛለሽ። በስብሰባው ላይ ግን ስለ ረሀብ አይነሳም። እድገት ነው የሚተነተነው። ኢትዮጵያውያን ዜጎች ምንም አይነት ጉዳይ ይኑራቸው ያለወረፋ ሊፈፅሙት የሚችሉት አንዳችም ጉዳይ የለም። ቴሌ ወረፋ፣ ፍርድ ቤት ወረፋ፣ ሆስፒታል ወረፋ፣ መሬት አስተዳደር ወረፋ፣ መንገድ ትራንስፖርት ወረፋ፣ መዘጋጃ ቤት ወረፋ፣ ፖስታ ቤት ወረፋ፣ መብራት ሀይል ወረፋ፣ ውሀ ልማት ወረፋ በቃ ሁሉም ቦታ ወረፋ! ለምን?....ስብሰባ!....። ከዚያስ? ጭብጨባ!.... ከዚያስ? የባለጉዳይ መጨናነቅ። ከዚያስ? ወረፋ የሰለቻቸውን ሰዎች ለማበርከት መጣር። ከዚያስ? ባለጉዳዩን ለጉቦ ማመቻቸት። ከዚያስ? በጎን እያስጨረሱ መዝረፍ! ይህ ነው ትክክለኛው አሰራር።
ገፅ 178-179 እኔና ቹ

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ!

🌿🌿🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿 🌿 🌿🌿
🌿🌿🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿🌿 🌿 🌿
🕌 ሙባረክ 🕌

በዓሉ የሰላም የፍቅር ያድርግልን! መጪው ግዜ ከገባንበት ችግር ተላቀን ደማቅ ደማቅ በዓሎችን እንደድሮው ተሰባስበን የምናከብርበት ያድርግልን!
ሰላም ፍቅር ለሁላችሁ ተመኘሁ!

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
@Readers_To_Know
🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

........" 'ዓለማችን ውስጥ ካሉ ሰባት ቢሊዮን ህዝቦች ውስጥ ሞትን የማያውቅ የለም። ስለ ሞት የማያውቅ ሰው የለም። ሞት መኖሩን ሁሉም ያውቃሉ። በትክክል ሞት መኖሩን የተረዱት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው ብዬ አምናለሁ። ሞት መኖሩን ማወቅ ብቻውን ማወቅ አይባልም። ሞት መኖሩን አውቃለሁ፤ ስለዚህ እንዴት መኖርና እንዴት መሞት ነው ያለብኝ? ብሎ ራሱን የጠየቀና ምላሹንም ያገኘ፣ ምላሹን አግኝቶም በተግባር ሞት ከመኖሩ ጋር በተገናዘበ መልኩ ህይወቱን የሚመራ ብቻ ነው ሞት ስለመኖሩ ያወቀ ሰው የሚባለው። ይህን የተረዳ ሰው ምንግዜም ለህሊናው ተገዢ ሆኖ ይኖራል። አለአግባብ ለመበልፀግ ሲል የሚሮጠውን ሩጫ ያቆማል፤ ለገዘፈ ሀብት ብሎ በግፍ የሰው ነፍስ ከማጥፋት ይቆጠባል። ሞትን ማስቀረት ከማይችል ከባዕድ አምልኮ ራሱን ያገላል። በዚህም ከመጥፎ ተግባር ይቆጠባል። አሟሟቱን አሳምሮ ኑሮውን በአግባቡ ይመራል። ወራሽ ሳይኖረው በዘጠና ዓመቱ ሲዘርፍ በኖረው ገንዘብ ረጅም ህንፃ መስራቱን ያቆማል። ሊሰራ የሚችለው በሀቅ ገንዘቡን ብቻ ይሆናል። ሞት መኖሩን የተረዳ ባለስልጣን በይው አገር መሪ ህዝቦቹን እያስራበ በውጪ አገር ባንኮች ቢሊዮን ዶላሮችን ማስቀመጡን ይተዋል። ስለዚህ በኔ ፍልስፍና የሰው ልጅ የመጨረሻው የጥበብ ጣሪያው ላይ ደረሰ የሚባለው ሞት መኖሩን ሲያውቅና ሲረዳ ነው ባይ ነኝ። ታውቂያለሽ እኔ በእያንዳንዷ የህይወት ጉዞዬ ላይም ሆነ እለት ተእለት የምፈፅመውን ማናቸውንም ተግባር ከመጨረሻዋ ህይወቴ ጋር አገናኛታለሁ። እኔ ለመሞት እያጣጣርኩ በህመም ይሁን በእድሜ ማብቃት ምክንያት አልጋ ላይ ተኝቼ ማሰብ የምፈልገው ያለፈ የህይወት ጉዞዬን ነው። ያንን አስቤ ምንም አይነት የሚፀፅት መጥፎ ስራ አለመስራቴን ከተረዳሁ በቃ! ፈገግ እንዳልኩ እሞታለሁ ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ሞትን መፍራት አይታሰብም። ከሞት በኋላ ስላለው ነገር መጨነቅም አይኖርም። አየሽ ለህሊና ተገዢ መሆን የፈለኩትም ሆነ የሆንኩት ለጥቅሜ ስል ነው። ይህችን ጥቅም ማጣት አልፈልግም። ይህንን በመረዳቴ ነው ራሴን እንደ እድለኛ የቆጠርኩት።'

'ፍፁም ሆነህ ግን መሞት አትችልም።'

'አልችልም። የአቅሜን ያክል ነው የምጠነቀቀው። ከአቅም በላይ ሆኖ ለፈፀምኩት ተግባር ልፀፀት አይገባኝም ይቅርታ ልጠይቅ ብቻ ነው የምችለው።'' ......"

ምንጭ:- እኔና ቹ ገፅ 165
ደራሲ ፍሰሀ
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂
🥀ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰብ አባላት እንደምን አላችሁ! የቤት ውስጥ ቆይታ እንዴት ይዞአችኋል? መፅሐፍትን እያነበባችሁ ግዜያችሁን የምታሳልፉ እንዳለችሁ ተስፋ እናደርጋለን። እናም ካነበባችሁት በጥቂቱ ማካፈል ለምትፈልጉ 👉 @R_e_a_d_e_rs ላኩልን።

🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠
🦠አንገብጋቢ ካልሆነ ከቤት አንውጣ
🦠ርቀታችንን እንጠብቅ
🦠እጃችንን እንታጠብ
🦠የእኛ ጥንቃቄ ለወገኖቻችን መሆኑን
🦠እናስብ።
🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠

እናመሰግናለን
የቤተሰባችን ቁጥር እንዲጨምር #share ማድረግ እንዳይረሳ

@Readers_To_Know
📓📓📓📓📓📓📓📓