ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
👆👆👆👆👆👆👆👆
​​"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​​​🎥📻 ከታሪክማህደር 🎙🎞

👇👇ሮማነወርቅ ካሳሁን..... በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ 👇👇

ደራሲ ከበደ ሚካኤል በትምህርትና ስነ-ጥበብ ሚኒስቴር ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በ1948 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ባደረጉት ንግግር ስለወይዘሮ ሮማነወርቅ (የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት ጋዜጠኛ) እና ሌሎች በአርዓያነት ስለሚጠቀሱ ሴቶች እንዲህ በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተው ነበር …

‹‹…ከጦርነቱ ወዲህ ግን በአዲስ አበባም ሆነ በየጠቅላይ ግዛቱ የሚታየው የሴት ተማሪዎች ቁጥር አስደሳች እየሆነ መጥቷል፡፡ እነስንዱ ገብሩ፣ እነሮማነወርቅ ካሳሁን (ሬዲዮ አንባቢዋ) እነ ዮዲት እምሩ፣ እነአልማዝ ፋሲካ ከማዕድ ቤት ወጥተው በማኅበረሰቡ መካከል በመገኘት አገር እየረዱ ነው:: በተለይም የሮማነወርቅ ካሣሁን የሬዲዮ ትምህርት አቀራረብ የመማር እድል ላላገኙት ሴቶች ጭምር ተስፋ የሚሰጥ ስለሆነ የኅብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ የሴቶች ትምህርት በብዛት እንዲቀጥልና ለትምህርት የሚመደበውም ገንዘብ ከፍ እንዲል በትህትና አሳስባለሁ …››


አዲስ ዘመን ረቡዕ ነሐሴ 8 / 2011

አንተነህ ቸሬ

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አስራ ስድስት 🦅

" የሶለን ማስታወሻ "
"............ ብዙ ሰዎች ባሕርይና ችሎታ ግንኙነት የላቸውም ብለው ማሰባቸው ትክክል አይመስለኝም። ይህ ውሀውን የያዘው ጠርሙስ ከውሀው ጋር ያለው ግንኙነት ያን ያህል ጠቃሚ አይደለም እንደ ማለት ነው። ይዘቱ በመያዣው በብዙ መንገድ ይወሰናል። ለምሳሌ የመያዝ ዐቅሙ (ጭላጭ ውሀ ብቻ መያዝ የሚችል እቃና 100 ሊትር ሊይዝ የሚችል እኩል አይደለም)፣ ውበቱ (በወርቅ ብርጭቆ ወይም በቅል ሽክና መጠጥ ቢሰጠን እኩል ደስታ አይሰማንም) ፣ ንፅህናውና ጥራቱ (በቆሻሻ እቃ ተቀድቶ ንፁሕ ውሀ ቢሰጠን ልዩነቱ ሰፊ ነው) ፣ እንዲሁም በጥቅም ላይ ለማዋል ማስቻሉ ( እንደ ወንፊት በሚያፈስ ወይም በታሸገና ከጠብታ በላይ በማያሳልፍ ዕቃ የቀረበ ውሀ እንደሌለ ነው) ። ይህ ሁሉ ከይዘቱ እኩል መያዣውም አስፈላጊ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። ታዲያ የሰውን ችሎታ የሚሸከመውን ባሕሪይ እንዴት ነው አስፈላጊነቱን ለማየት የሚያዳግተው? ባህርይ እኮ ችሎታን ተሸካሚ መያዣ መሆኑን ማንም ሊክድ አይችልም። ስለዚህም መልካም ባሕሪይ የሌላቸው ጎበዝ ሰዎች ባጭር ቃል የባከኑ ችሎታዎች ከመሆንም ዐልፈው ጎጂ ስጦታዎችም ሊሆኑ ይችላሉ። ........."

~~~~ ይቀጥላል ~~~~

​​"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

የአብርሀም ሊንከን መሳጭ ንግግሮች

🔸 ጠላቶቼን ጒደኞቼ ባደርጋቸዉ በዘዴ አጠፋዋቸዉ ማለት አይደል?
🔹በዝግታ የምራመድ ብሆንም በፍፁም ወደ ኋላ አልመለስም።
🔸ስለ ወደፊቱ መልካሙ ነገር አንድ ቀን በሆነ ሰዓት መምጣቱ ነዉ።
🔹እዉነት በስም ማጥፋት ላይ ከሁሉ የበለጠ በቀል ነዉ።
🔸ዛፍ እዉነተኛ ነገር ሲሆን፣ጥላዉ ደግሞ ስለ
እሱ የምናስበዉ ነገር ነዉ።
ዛሬ መስራት የምችለውን ነገር ለነገ አታሳድር
ነፃነት የምድር የመጨረሻዉ ተስፋ ነዉ!!

ምንጭ: ከመጽሐፍ ዓለም የፌስቡክ ግሩፕ



THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

ጥቂት ስለ እንስሳት

🔸ሰጎን በፍጥነት ከፈረስ ይበልጣል ፣ ወንዱ ሰጎን የአንበሳን ድምፅ አስመስሎ ማግሳት ይችላል።
🔸 ካንጋሮ ጅራቷ ሚዛን መጠበቂያዋ ነው፣ ጅራቷ መሬት ካልነካ መዝለል አትችልም።
🔸 ነብር ላይ የምናየው መስመር የተሰመረው ፀጉራቸው ላይ ብቻ አይደለም። መሥመሩ እስከቆዳቸው ይዘልቃል፣ ሆኖም የአንዱ ነብር መስመር ከሌላኛው ነብር ጋር በጭራሽ አንድ አይሆንም።

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🔘ሕይወት ባለብዙ አቅጣጫ ስለሆነች በአንድ መንገድ ብቻ አይተህ ተስፋ አትቁረጥ።
🔘 ሕይወትና ፍላጎት እንደ ተቆራኙ ወፎች ናቸው፤ ተያይዘው ይበራሉ። አንዱ እስካለ ሌላው ይኖራል።
🔘ሕይወት ጣፋጭነትንም ሆነ ጎምዛዛነቷ የሚታወቀው ቀምሰን ስናጣጥመው ብቻ ነው፡፡
🔘ለአመንው ለአቀድነው ነገር ህወታችንን መስዋት ማድረግ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡
🔘በሕይወታችን የአንድ ደቂቃ ትዕግስት ማጣት የዘላለም ጸጸት ያስከትላል።
ምንጭ: በዓሉ ግርማ, ከአድማስ ባሻገር

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አስራ ሰባት 🦅

የሶለን ማስታወሻ
.......... አብሮ ከመብላት ይልቅ አብሮ መሥራት መቻል ብስለትን ይጠይቃል። በሰው ሐዘን አብሮ ከማልቀስ ይልቅ በሰው ደስታና ስኬት አብሮ መደሰት የትልቅነት እና የቅንነት ምልክት ይመስለኛል። ምቀኝነት አብሮ መስራትን ሲከለክል ክፉ ቅናት ደግሞ ለሌላው እንዳንደሰት እንቅፋት ይሆንብናል።
* * *
ሰዎች በበታችነት ስሜት የሚያሳዩት ባሕሪይ ከትሕትና ጋር በቀላሉ ሊያምታታ ይችላል ። በትዕቢትም ተወጥረው የበላይነት ስሜታቸው የነፋፋቸውን ሰዎች በራሳቸው የሚተማመኑ ጠንካራ ሰዎች ሊመስሉ ይችላሉ። የበታችነት ስሜት ቆስሎ የተሰባበረ ትዕቢት ሲሆን ትዕቢት ደግሞ እንደተወጠረ ፊኛ ጥቂት ነገር ጠቅ ብታደርገው የሚፈነዳ በፍርሀትና በባዶነት የተሞላ ማንነት ነው። ትሕትና ራስንም ሰውንም በተገቢው ደረጃ ማየትና ለራስም ለሰውም ትክክለኛውን ክብር በመስጠት፣ ከሌሎች ጋር ራስን ከማነፃፀር ተላቆ፣ ሰው ከራሱ ችሎታና ራዕይ ጋር በመወዳደር የተረጋጋ ኑሮ መኖር ሲችል የሚያሳየው ባሕሪይ ነው።.........
* * *

~~~~ ተፈፀመ ~~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

እስካሁን ይህን መፅሀፍ እንደ ቅምሻ ያክል ያስተምራሉ ያልናቸውን በ17 ክፍላት አይተናል፤ ቀሪውን ደግሞ ለእናንተ ትተናል። በጣም ስለቆየ ይቅርታ🙏 እንጠይቃለን ትንሽ ተጨናንቀን ነበር። ያመለጣቹን ክፍል ወደላይ በመሔድ ማየት ትችላላችሁ።


እናመሰግናለን !!!
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🎥📻 ከታሪክ_ማህደር 🎙🎞
ጳውሎስ ኞኞ (1926 - 1984)
-----------------------
ጳውሎስ ኞኞ ከእናቱ ከወይዘሮ ትበልጫለሽ አንዳርጌና ከግሪካዊ አባቱ ሚስተር ኞኞ ህዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም. በቁልቢ ከተማ ተወለደ። ትውልዱ ቁልቢ ይሁን እንጂ የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው በድሬዳዋ ነው። እድሜው አስር ዓመት ገደማ ሲሆነው ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ክርስቶስ ትምህርት ቤት ገብቶ የቀለም ትምህርቱን ጀመረ።

በትምህርት አቀባበሉ ፈጣን ስለነበር 'ደብል' እየመታ በአጭር ጊዜ ወደ አራተኛ ክፍል አለፈ። ነገር ግን ትምህርቱን ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለም። ወላጅ እናቱ ምንም ገቢ ስላልነበራቸው ገና በመማሪያ እድሜው እናቱን ለመርዳት ደፋ ቀና ማለት ጀመረ። ስዕል በመጠጥ ቤቶች አዙሮ በመሸጥ ራሱንና ደሀ እናቱን ያስተዳድር ነበር።

ጳውሎስ ኞኞ በ1943 ዓ.ም. ገደማ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ሳለ በእርሻ ሚኒስቴር ተቀጠረ። በሚኒስቴሩ የእንስሳት ህክምና ክፍል የእንስሳት መርፌ ወጊ ሆኖ በወር ስምንት ብር እየተከፈለው በጊዜው አጠራር ሀረርጌ ክፍለ ሀገር ጨርጨር አውራጃ ለሶስት ዓመታት ሰርቷል።

በ1946 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል በሰማንያ ብር ወርሀዊ ደመወዝ በድሬሰርነት፣ በፀሀፊነትና በሂሳብ ስራ አገልግሏል።

ጳውሎስ በአጭር የትምህርት ቤት ህይወቱ እንኳ ለተማሪዎች ግጥም እየፃፈ ያነብ ነበር። ትምህርቱን ቢያቋርጥም ከንባብና ከፅሁፍ አልራቀም። የኑሮ እጣ ፈንታው ገና በጠዋቱ ከትምህርት ቢያሰነባብተውም ከስራ መልስ ረፍት የሚያደርገው በመፃፍና በማንበብ ነበር። ለጋዜጠኝነት ህይወቱ መሰረት የሆነውም ይህ ነው።

ጳውሎስ ኞኞ ሲነሳ ጋዜጠኝነቱ፣ ከጋዜጠኝነቱም እያዝናኑ በሚያስረምሩ መጣጥፎቹ ይታወቃል። በተለይም "አንድ ጥያቄ አለኝ" በሚለው የጋዜጣ አምዱ በይበልጥ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አስገኝቶለታል።

ጳውሎስን ከህዝብ ያስተዋወቀችው "የኢትዮጵያ ድምፅ" ጋዜጣ ናት። በጋዜጣዋ ከሪፖርተርነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሰርቷል።

በ1957 ዓ.ም. "የኢትዮጵያ ድምፅ" ጋዜጣን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተዛወረ። ከጥቂት ወራት በኋላም ወደ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ተዛወረ። በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከየካቲት 2 ቀን 1957 ዓ.ም. እስከ መስከረም 1970 ዓ.ም. በምክትል አዘጋጅነት እንዲሁም በተለያዩ ዓምዶች በዋና አዘጋጅነት ሰርቷል። . . . . .

ጳውሎስ ከጋዜጠኝነት ሙያው በተጨማሪ የአጫጭር ልብወለዶች ደራሲ፣ የታሪክ ተመራማሪና ፀሀፊ ነው። ግጥሞችንም ይሞካክራል።

ከልብ ወለድ ስራዎቹ መካከል፦
> የጌታቸው ሚስቶች
> የኔዎቹ ገረዶች
> የአራዳው ታደሰ
> የሴቶች እንባ
> ድብልቅልቅ
> እንቆቅልሽ
> ምስቅልቅል
> ቅይጥ ይጠቀሳሉ።
> በአምስት ቅፆች የቀረቡት "አስደናቂ ታሪኮች" ከኢ-ልብወለድ መፅሀፎቹ መካከል ናቸው።

ከጋዜጠኝነቱ ባልተናነሰ በታሪክ ፀሀፊነቱም ይታወቃል ጳውሎስ ኞኞ። በርካታ የታሪክ መረጃዎችንና ሰነዶችን አሰባስቦ አጠናቅሯል። በ1981 ዓ.ም. በጡረታ ከተገለለ በኋላ የታሪክ ምርምሩን አጠናክሮ በመቀጠል መፅሀፎችም ፅፏል።

ከበርካታ የታሪክ መፅሀፎቹ መካከል፦
> የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት
> አጤ ቴዎድሮስ
> አጤ ምኒልክ
> አፄ ምኒልክ በአገር ውስጥ የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች
> አፄ ምኒልክ ከውጭ ሀገራት ጋር የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች
> የኢትዮጵያ ታሪክ ኢንሳይክሎፒዲያ
መጥቀስ ይቻላል። ለህትመት ያልበቁ በርካታ የታሪክ መፃህፍትም አሉት።

ከ1983 ዓ.ም. በኋላ በርካታ መፅሄቶችና ጋዜጦች ለህትመት ይበቁ የነበረበት ጊዜ ነበር። ከነዚህም አንዷ "ሩህ" መፅሄት ነበረች። ጳውሎስ ኞኞ ደግሞ ዋና አዘጋጇ። ነገር ግን ከሦስት እትም በላይ ከመፅሄቷ ጋር መዝለቅ አልቻለም። ምክንያቱም ባደረበት ህመም ይሰቃይ ስለነበር።

ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና የታሪክ ተመራማሪ ጳውሎስ ኞኞ በመጨረሻም በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ግንቦት 29 ቀን 1984 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
---------------------------------------
ምንጭ፦ የሥነ ጽሁፍ ሰዎችና ሥራዎቻቸው
ልቦለድ፣ የተውኔት ድርሰት እና ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ
[ከ1850 - 1960ዎቹ]
✍️ ሀብታሙ ግርማ ደምሴ

እናመሠግናለን
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ጥቆማ

ለዛሬ ስነፅሁፍ በስስት የምታያቸውና ምትዘክራቸው እነ ቶልስቶይና ቸኮቭን ካፈራችዉ ሩስያ የተገኘው ድንቅ ደራሲ ኒኮላይ ጎጎል የደረሰውን "dead souls-ሙት ነፍሳት " የተሰኘውን ግሩምና ዘመን አይሽሬ መፅሀፍ ለጥቆማ መርጠነዋል።

በብዙ አንባብያን እና ሀያስያን" a masterpice from a master mind "እየተባለ ሚሞካሸው ይህ መፅሀፍ በ ፊውዳል ዘመን ሩሲያ ከሀገር ሀገር እየዞረ የሞቱ ጭሰኞችን ነፍስ የሚገዛ ቺቺኮቭ የተሰኘ ገፀባህሪይ ላይ ያጠነጥናል።በቺቺኮቭ ጉዞ ውስጥ ጎጎል የሩሲያን ዉበትና ድሀ ገፅ፣የሰውን ልጅ ጥልቅ ማንነትና የህይወትን ወጣገባ በአስደማሚ ትረካ ያስቃኘናል። ለዚህም ይመስላል በብዙወች ከቶልስቶይ"war and peace" ቀጥሎ የሩስያን ጥጋጥግና የሰዉን ልጅ ውስብስብ ባህሪይ ቁልጭ አርጎ ሚያሳይ ድርሰት እየተባል የሚወደሰው።

ትደሰቱበት ዘንድ በአክብሮት ጋበዝን።መልካም ንባብ!!
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ጥምቀት የክርስቶስን መገለጥ የምስራቅ አብያተክርስትያናት በዮሀንስ እጅ መጠመቁን፣የምዕራቡ ደግሞ የሶስቱን ሰብዓሰገል መምጣት በማሰብ የሚያከብሩት በዓል ነዉ።መልካም በዓል እየተመኘን የተለያዩ ሀገራት ጥምቀትን እንዴት እንደሚያከብሩት በጥቂቱ እናስቃኛችሁዋለን።

፩ ስፔን፦ የ ስፔን ህፃናት ለእየሱስ ስጦታን ያመጡት ንጉሳን ለነሱም እንደሚያመጡ በማመን የዋዜማው ቀን ጫማወቻቸዉን ወልውለው ያስቀምጣሉ።በበዓሉ ቀን ደግሞ የካርኒቫል ፈረስ በመጋለብና ባህላዊ ምግቦች በመመገብ ያሳልፋሉ።

፪ ታላቋ ብሪታንያ፦ የዋዜማዉ እለት 12ኛዉ ምሽት ለበዓሉ ሚዘጋጀዉ ግዙፍ የፍራፍሬ ኬክ ደግሞ 12ኛው ኬክ ይባላሉ።ውስጡ የገባዉን ባቄላ ያገኘዉ ሰው ለበዓሉ እንደ ንጉስ ተመርጦ ልዩ ክብር ይሰጠዋል።የቀረውን የበዓሉን ክፍል ሰብዓሰገል ጋር በሚገናኙ ተግባራት ያሳልፋታል።

፫ ሩስያ፦በዓሉ የክርስቶስን ጥምቀት ያስባል።ሊቃነ -ጳጳሳት ውሀውን ከባረኩ ቡሀላ ሁሉም ህዝብ እንደ በረዶ ሚቀዘቅዘው ውሀ ውስጥ ገብቶ ሶስቴ ብቅ ጥልቅ ይላል።ይሄም የጌታ ጥምቀት ተምሳሌት ነዉ።................

መልካም በዓል🍋
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
 🌫🌊የጥምቀት በዓል 🌊🌫

ጥር 10 ቀን በዋዜማው ከተራ በሚል ስያሜ በሚታወቀው በዚሁ ዕለት ባሕረ ጥምቀት ከተዘጋጀ በኋላ በመላዋ ኢትዮጵያ በከተማም በገጠርም በመሐል አገርና በጠረፍ ጭምር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙት ታቦታት ሁሉ ከመንበራቸው ተነሥተው ወደተዘጋጀው ባሕረ ጥምቀት በመውረድና በተዘጋጀላቸው ድንኳን ውስጥ በማደር በዚያው በአደሩበት ድንኳን ውስጥም ማኅሌቱና ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በኋላ ባሕረ ጥምቀቱ ተባርኮ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ የበረከቱ ተሳታፊ ከመሆናቸውም በላይ በዓሉ ከዋዜማው (ከከተራው) ቀን ጀምሮ ታቦታቱ ወደየአብያተ ክርስቲያናቱ ተመልሰው በመንበራቸው ላይ እስኪያርፉ ድረስ ሁለት ቀን መሉ በየባሕረ ጥምቀቱና በየመንገዱ ሁሉ በድምቀት የሚከበር በዓል በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለማትን የፈጠረና ሁሉንም ያስገኘ ልዑል አምላክ ሲሆን ለእኛ አርአያና ምሳሌ ይሆን ዘንድ በተዋሐደው ሥጋ ትኅትናን ገንዘብ በማድረግ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ በአገልጋዩ በዮሐንስ መጥምቅ እጅ የመጠመቁ ምሳሌ መሆኑን ያስረዳል፡፡

ከሊቀ ብርሃናት ኢሳይያስ ወንድምአገኘሁ

🍀🍀🍀🍀🍀 🍀🍀🍀🍀

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

ጠቃሚ ምክሮች
1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።
2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ
ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡
3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።
4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።
5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።
6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።
7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም
የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

እናመሠግናለን
#share #participate #comment

@zhangidaa
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
"ፍልስፍና ከምንም ተነስቶ ወደ
ምንም የሚያደርስ መንገድ ነው"
---------------------------------------
የፍልስፍና መምህሩ ወደ ክፍል ውስጥ ይገባና ለተማሪዎቹ የመጨረሻውን ፈተና ሊሰጥ ተዘጋጀ። አንድ ወንበር በማንሳት ከጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና፦
"እስከዛሬ በዚህ ኮርስ የተማራችሁትን ቁም ነገር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይኽ ወንበር አለመኖሩን አረጋግጡልኝ" አለ።

በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የዚያን ወንበር አለመኖር ወይም መኖሩ እውነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ መፃፍ ጀመሩ። ብዙዎቹ ለሰዓታት የፈጀ ጥናታቸውንና ማብራሪያቸውን ሲፅፉ አንድ ተማሪ ግን በሰላሳ ሴኮንድ ውስጥ መልሱን ፅፎ ለመምህሩ በማስረከብ ክፍሉን ለቅቆ ሄደ።

በነጋታው ፕሮፌሰሩ የተማሪዎቹን ውጤት ይዞ መጣ። ከሁሉም ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያገኘው በሰላሳ ሴኮንድ ፈተናውን ጨርሶ የሄደው ተማሪ ነበር።

ፕሮፌሰሩም "ብዙዎቻችሁ የወንበሩን አለመኖር ለማሳየት ብዙ ደክማችኋል። ይኽ ተማሪ ግን ከሁላችሁም በላቀ መንገድ ወንበሩ አለመኖሩን አረጋግጦልኛል" አለ።

ተማሪው ለጥያቄው የሰጠው ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር።
"የቱ ወንበር?"።
----------------------------
"ጥ በ ብ" - ከጲላጦስ
(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)
📖 📖 📖 📖 📖 📖 ❣️ እናመሠግናለን ❣️
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
ፍልስምና ፩+፪+፫ የሚለው የደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ መጽሐፍ ላይ ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር እና ቴዎድሮስ እንዲህ ሲሉ ያወጋሉ...
ከመጽሐፉ የተቀነጨበች ጽሑፍ...

፨፨፨

ቴዎድሮስ ፦ የወንድና የሴትን ትተን በተመሳሳይ ጾታዎች መሀል እኩል የሚባል ነገር ይኖራል? አንድ ወንድ ከሌላው ወንድ ጋር...?

#ስብሃት ፦ የውልህ..እኩል የሚለው እኮ ስታትስቲክስ ነው። #ሀሳብ ነው እንጂ እኩል የሚባል ነገር የለም። አንድ ሰው የማንም እኩል አይደለም። እያንዳንዳችን ራሳችንን የቻልን ዩኒቨርስ ነን። እኛ ብቻ ሳንሆን እያንዳንዷ የሰውነታችን ሴል ልዩ ናት። እኩል..ምናምን የምንለው ሃሳብ ነው እንጂ የለም።



ቴዎድሮስ ፦ የሰው ልጅ መሞት የሚጀምረው መቼ ነው?

#ስብሃት ፦ የውልደቱ እለት ነው መሞት የሚጀምረውማ። ጥፍርህ ያበቅላል አይደለም? ግን ደግሞ እንደበቀለ ይሞታል። ተቆርጦ ሲሔድ አይሰማህም። ሞት እኮ ሁሌም አብሮህ ነው። ስትታጠብ ቆዳህ በመጠኑ እየተላጠ ይሄዳል። እየሞትክና እየተወለድክ ትኖራለህ ማለት ነው ።

ምንጭ ፦ / ፍልስምና ፩+፪+፫……ገጽ 77 /
ደራሲ ፦ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

ጋሽ ስብሃት ምን ለማለት ፈልጎ ይሆን...?
❣️ እናመሠግናለን ❣️
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

🔴 ከሁለት ቢልዮን ሰዎች አንድ ሰው ብቻ 116 👩‍🦳👨‍🦳 ዓመትና ከዛ በላይ የመኖር እድል አለው። አይዞአችሁ የላቹበትም 😜😜😜

🔷 በ1926 ቴሌ ቪዥንን ( Television )📺 የፈጠረው ሰው እንግሊዛዊው Baird ነበር።

🎥 Quote :- What lies ahead will always be a mystery. Do not be afraid to explore.

🔶 ባሕረ ሀሳብ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን በአረብኛ አቡሻከር በአማርኛ የዘመን አቆጣጠር 📆ይባላል። የቀመረው 12ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ድሜጥሮስ 👳‍♂ነበሩ።

🔷 ይህን ይሞክሩ!
ባለ ሶስት አሐዝ ቁጥር ይምረጡ። ከዛም በ 7፣ በ 11 እና በ 13 ያባዙት። የሚያገኙት ውጤት የባለሶስት አሐዙን ሁለት ጊዜ የተደገመ ይሆናል።
ለምሳሌ :- 574 ብንወስድና በ 7፣ በ 11 እና በ 13 ቢያባዙት የመጨረሻው መልስ 574,574 ይሆናል።🎞🎞🎞

እናመሠግናለን
#share #participate
for any comment 👇

@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
"........ሺህ ምሁር ብትሆን መዋደድ ግድ ነው።
የተያያዝንበት ላስቲክ በመለጠጡ የተራራቅን ይመስለናል እንጂ የመያያዝ ባርነት ውስጥ ነን።

አዕምሮአቸው ብሩህ ባህላቸው ግን የባርያ የሆኑ ስንት አሉ በእግዜር። ባላምንበትም ልማልበት።

አይ አም ኢንተለጀንት ብሎ የሚናገር ግን ዘር ማንዘሩ በቁንጫ የሚበላበት፣ በጎጥ ብራንድ የነደደ ሰው አያበሽቅህም?

በ'ነኝ' ሰው የሚበላለጥ ቢሆን የአለም ጌታዋ ብዙ ነበር።

'ውበት ሃሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው' እንደሚባለው አዕምሮም ሃሰት ነው ብልጥነትም ከንቱ ነው።

ሁሉ ረጋፊ ነው። መደ'በር ደሞ የጋራችን ነው።......"

***
#ከ'አፍ መጽሐፍ የተወሰደ / አዳም ረታ/ ❣️ እናመሠግናለን ❣️
#share #participate #comment
@infho
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

💫በቀን፣ በሳምንት፣ በወር፣ በአመት ምን ያህል ሰው እንተዋወቃለን? ምን ያህሉንስ ጠብቀን አቆይተናል?

አንዳንዶች በህይወታቸው ውስጥ ሰው በየጊዜው ያስገባሉ። ነገር ግን ግንኙነታቸውን እንደነበረ ጠብቆ ማቆየት ላይ ደካማ ናቸው። እየቆየ የተበላሸ ግንኙነት ይሆናል። በግንኙነታቸው ውስጥ አንዱ ብቻ ጠንካራ ሆኖ አንዱን ላለማጣት ሲል ይበረታል በዚህም ምክንያት ወደ አንድ ጎን አድልቶ መሰለቻቸት ሊመጣ ይችላል ፤ ወይ ደግሞ ሁለቱም ደካማ ይሆኑና የነበራቸውን ደስ የሚል ነገር ረስተው ይለያያሉ። አንዳንዶች ደግሞ አጠገባቸው ስላለው ወዳጃቸው ግድ አይሰጣቸውም። እነሱ የሚጨነቁት ስለራሳቸው የግል ደስታና ስሜት ብቻ ነው። አንዳንዶች ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በውሸት ማስቀጠል ይፈልጋሉ። ከዛ ሰው ጋር መለያየት፣ መቀያየም ወይም መጣላት አይፈልጉም። ነገር ግን ደግሞ ብዙ መቀራረብም አይመቻቸውም፤ ግንኙነታቸውን ያዝ ለቀቅ ያደርጋሉ። አንዳንድ ሰዎች ከዚህ በፊት በነበራቸው ያልሰመረ ግንኙነት ላይ በመናደድ ቀጣይ ጉዞአቸው ላይ ለነሱ የማይታወቃቸው ነገር ግን የበቀል በሚመስል ሁኔታ ኑሮአቸውን ይቀጥላሉ። በዚህ ሂደት ምንም የማያውቀው ተጎጂ ይሆናል። ያለፈውን ህይወታቸውን እንደ ትምህርት የሚጠቀሙትም ቁጥራቸው ትንሽ የሚባል አይደለም። አንዳንዶች መጀመሪያ ላይ ጥሩ ግንኙነት ይጀምሩና እየቆየ ሲሄድ ሆን ብለው ግንኙነታቸውን ማላላት ይፈልጋሉ። ምክንያታቸው ቢለያይም እነዚህም ሰዎች ስለራሳቸው እንጂ ስሌላው ስሜት ብዙም ግድ አይሰጣቸውም ማለት ነው፤ ወይ ደግሞ በቂ ምክንያት አላቸው፤ ሰው በማማረጥ ላይም ሊሆኑ ይችላል። አንዳንዶች ደግሞ ገና ትውውቃቸውን ሲጀምሩት የተበላሸና መስመር የሳተ በመሆኑ ዘላቂ ግንኙነት ለመጀመር ይከብዳቸዋል ። አንዳንዶች በዙሪያቸው ብዙ ሰው ካለ አጥብቆ የሚፈልጋቸውን ሰው ሳያውቁም ይሁን በቸልተኝነት ይጎዱታል። እዚጋ ለዛ ሰው እንዲከብድ የሚያረገው ግንኙነታቸው እንደ ዲምላይት በርቶ የሚጠፋ ስለሆነ ለመቁረጥና ለመተው ይከብደዋል። የአንዳንድ ሰዎች ወዳጅነት በእኩይ ተግባር በተጠመዱ ሰዎች ምክንያት እንዳልነበረ ሆኖ ሲበላሽ እናገኘዋለን።አንዳንዶች ደግም ከትውውቃቸው እስከ ፍፃሜያቸው የሚያስቀና ግንኙነት ይኖራቸዋል። እርስ በእርስ ካለፈው እየተማሩ፤ ዛሬን አብረው እየኖሩ፤ ነገን አብረው በተስፋ የሚጠባበቁ ወዳጆችም ጥቂት አይደሉም። ለዚህም ምስጢሩ መዋደዳቸው(መፋቀራቸው)፣ መተማመናቸው፣ ይቅር መባባላቸው፣ መተሳሰባቸው፣ መቻቻላቸው፣ በሀሳብ መደጋገፋቸው፣ አልፎ ተርፎም ግጭታቸውን አብረው የመፍታት ችሎታቸውና ሌሎችም ...... ወደ ህይወታችን ሰዎችን ስናስገባ ጥንቃቄ ማድረግ አንርሳ። ለምናረጋቸው ነገሮች ምክንያታዊ ለመሆን እንሞክር። ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!!!
ፀሐፊ: - ©D.Ys

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

🔶 Quote:- live as if you were to die tomorrow learn as if you were to live forever.

🔷 Diabetes is hereditary because our food habits are hereditary.

🔴 Smallest bone of body is in ears👂.

🔶 Human body needs natural sodium not sodium chloride salt.

⚪️ Largest muscle in your body is one on which you are sitting on. Don't see it pls 😂😂😂

እናመሠግናለን
#share #participate #comment

@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

ዓለማችን የሰለጠነች እንዳይመስላችሁ። የመጀመሪያው ዋሻ ቆፍሮ ይኖር የነበረው ሰው ከሥልጣኔ ቁንጮ ላይ እንደደረሰ ተሰምቶ ይሆናል። እሳትን የፈጠረውም እንደዛው። አሁን የተፈጠሩትን ውስብስብ መሣሪያዎች ስናይ ከሥልጣኔ ጫፍ የደረስን ሊመስላችሁ ይችላል። ነገርግን ዓለም ማብረቅረቅ ጀመረች እንጂ ገና አልሰለጠነችም። ... የሰው ልጅ የአዕምሮውን የመፍጠር እና የማሰብ ችሎታ ገና ምንም አልነካውም ማለት ይቻላል። የዛሬ መቶ ዓመት ከመቃብራችሁ ብትነቁ ይህን ታረጋግጣላችሁ። የሰው ልጅ የአእምሮ ህዋስ በብዙ ሚሊዮን እጥፍ ሊበለፀግ ይችላል።
ራማቶሓራ, ይስማዕከ ወርቁ፡ ገፅ 69

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን ዕድል እንድትጠቀም ያደርግሃል፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ያረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ። ባለቀ ትናንት አትታሰር፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን፣ ይልቅ ወደማይታየው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ። አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።


#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚