ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
​​​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አስራ ሶስት 🦅

" የሶለን ማስታወሻ "
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
​​"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
👆 share this to your friends
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

1. Quote:- A girl looks more beautiful when she knows she doesn't need to expose to look beautiful.

2. Salt food is the major cause of many disease including diabetes.

3. Adults, above 11 years, should not use 1500 mg sodium.

4. If you mix a little salt and olive oil, you will not feel pain in the next 5 years.

#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

እማምዬ የፍቅር ጥግ፣ የእናትነት አልፋና ኦሜጋዬ። እናንተ "ሴት እናት ናት! ሴት እህት ናት! " የምትሉ 'በደፈናው ኃይማኖተኛ ሁሉ መነኩሴ ነው' እያላችሁ ነውና ይቅር ይበላችሁ፤ ሴትነት እናትነት አይደለም። "ሴት ከውስጧ የወጣ ገዳም ውስጥ ስትመንን እናት ትሆናለች" ሴት.... "ልጅ" የሚባል መስቀል ተሸክማ የሕይወትን ቀራንዮ ስትወጣ 'እናት' ትባላለች፤ ሴት ልጅ የራሷን ዘመን ይቅርብኝ ብላ የልጆቿ የዘመን መስቀል ላይ በፍቅር ስትቸነከር ወደ እናትነት ከፍታ ታርጋለች።

ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም፡ ከአሌክስ አብርሃም , ገጽ 52


#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

ሞት ብትፈራውም ብትርቀውም የማይቀር እዳ ነው ወይም መንገድ ነው።
የዕድሜህ ማጠር ወይም መርዘም አያስጨንቅህ። የፈጣሪ ፈቃድ ነውና። ይልቁንም በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካም እና በደስታ ለመኖር ስጋህን ተጠንቀቀው። ነፍስህን ቁጠራት እምነትህን ጠንቅቃት።

ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ፡ ዝጎራ


#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

በሀገራችን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የፊልም ታሪክ አለ ቢባልም ፊልሞቻችን ግን "ባለበት እርገጥ" አካሄድ ላይ የተዘፈቁ ናቸው ። ከ1970 ዎቹ አንስቶ ወደዚህ ያለውን ጊዜ እንኳን ብናጤን ፊልሞቻችን በጊዜው የነበረው የቅርጽ(form) ችግር በተነጻጻሪ እየተፈታ ጠንካራ የነበረው የጊዜው የይዘት (content) አጠቃቀም እየፈረሰ መጥቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰሩ ፊልሞች ይዘታቸው ልል ሆኖ በቧልት የተዘፈቁ እየሆኑ መጥተዋል። ለዚህ ዋናው ችግር ደግሞ የፈጠራ ዕጦት ነው። ብዙዎቹ ታሪኮች ተመሳሳይ ናቸው። ብዙዎቹ ገፀ-ባሕርያት ተመሳሳይ ናቸው። የብዙዎቹ የሤራ፣የትልም፣የመቼት አመራረጥ ሳይቀር ተመሳሳይ ናቸው ። ይህን የፈጠራ እጦት ለመቅረፍ አዳዲስ ብስል የፈጠራ ታሪክ ከማቅረብ ባሻገር መጽሐፍት፣የታላላቅ ሰዎች የህይወት ታሪክ፣እውነተኛ የህይወት ታሪክ መሰረት ያደረጉ ፊልሞች አሁን ያለውን ችግር ይፈታሉ ብዬ አምናለሁ።

ጥናታዊ ፅሁፍ ፡ በምህረቱ መንግስቱ

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫

መጽሐፍ
ዶክተር አሸብር እና ሌሎች
በአሌክስ አብርሃም የተደረሰ
ሃያአምስት አጫጭር እና ረዘም ያሉ ታሪኮችን በ237 ገፆች በውስጡ አካቷል.
በውስጡም ብዙ ማህበራዊጉዳዮች ደስ በሚልና ፈገግ በምያሰኝ መንገድ ተዳሰዋል ።
ብያነቡ ይወዱታልና እንድያነቡት ጋብዘኖታል
soft copyውን በpdf ከፈለጉ
👉 @zhangidaa

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አስራ አራት 🦅

" የሶለን ማስታወሻ "
👆👆👆👆👆👆👆👆
​​"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌲🎄 ገናችን 🎄🌲

“በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” እየተባለ እንደሚጨፈረው ሁሉ፣ ቂምና በቀል በገና ጨዋታ አይታሰብም፡፡ ከጨዋታው በኋላ መብል መጠጡ ተሰናድቶ፣ ድግሥ ላይ ጌታውም ሎሌውም እኩል ይቀጣሉ፡፡ አብረው ይበላሉ። አብረው ይጠጣሉ፡፡ ይህን ልምድ ደራሲና ጋዜጠኛ መምህር ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር፤ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት ጋር በማቆራኘት ያብራሩታል፡-
“የኢየሱስ ውልደትም የሰውን ልጅ እኩልነት ለማወጅ፣ ኃጢያተኞችን ይቅር በማለት ከሌላው ጋር ያዋሀደ ክስተት በመሆኑ፣ በገና ጨዋታም አሽከርና ጌታው እኩል ይጫወታሉ፤ ይራገጣሉ”
መልካም የገና በዓል!   

ምንጭ ፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ


🌟
🎄 。。
🎄🎄。 。
🎄🔴🎄
🎄🔴🎀🎄
🎄🎀🎄🔴 🎄。。
🎄🎄🎀🎄🎄
。。🎄🎄🔴🎄🎄
🎄🎄🎀🎄🔴🎄
🎄🔴🎄🎄🎀🎄🎄
🎄Happiness 🎄
🎄 🎄 And luck 🎄🎄
🎄🎄🔴🎄🎄🎀🎄
🎄🔴🎄🎀🔴🎄🎄🎄
📝 Merry Christmas 📋

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

"መግባትና መውጣት" ከተሰኘው የ 'በዕውቀቱ ሥዩም' መጽሐፍ የተቆነጠረ...

📖📖📖

ቀኑ ደመናማ በመሆኑ፣ ፀሐይዋ ያለውትሮዋ በመራቋ አውሮፕላን ጀርባ ላይ ካልተሰጣ በቀር የረጠበው ልብሴ እንደማይደርቅ ገባኝ ይሁን እንጂ ወዲያው ብልሃት መጣልኝ ። መንገዱ ዳር ወደሚገኝ ካፌ ገብቼ ትኩስ ነገር ለመውሰድ ለመውሰድ አሰብሁ። ሆዴ በጣም ከሞቀ ቢያንስ ካናቴራዬ ይደርቃል። ገባሁና አስተናጋጇን ጠርቼ ጦመኛ ስለ ሆንኩ ሻይ እና ችብስ እንዲያመጣልኝ ነገርሁት። አሻግሬ ወደ ውጭ መመልከት ጀመርሁ ። ማዶ ካለው አሮጌ አጥር ሥር አንድ መጽሐፍ አዟሪ ጎረምሳ ብልቱን በጳውሎስ ኞኞ መጽሐፍ ጋርዶ ሽንቱን ይሸናል ። እየሸና ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ሲገላመጥ ከእኔ ጋራ ተገጣጠምንና በእጄ ምልክት ጠራሁት ። ሽንቱን ሳይቋጭ ተንደርድሮ ገባ ። አንዱን መጽሐፍ እየመዘዝሁ ፣ "በቢንላደን ላይ መጽሐፍ ጽፈውበት ነው?" ብዬ ጠየቅሁት ።



"ቢንላደን አይደለም፤ ኦሾ ነው!" አለኝ አዟሪው እየሳቀ ። ከኦሾ መጽሐፍ ለናሙና ሁለት አንቀጽ አንብቤ የእግዜርን ህልውና ስለ ተጠራጠርሁ፣ አስተናጋጁ ችብሱን ትቶ ጥብስ እንዲያመጣልኝ ነገርሁት ። ጥብሱ በጣም ጥሩ ነበር ። ብዙ ሬስቶራንቶች ውስጥ እንደሚታየው በጥብሱ ውስጥ ፀጉር አላገኘሁም ። ጥብሱን ያዘጋጀው ሼፍ መላጣ ሳይሆን አይቀርም ።



ከካፍቴርያው ከወጣሁ በኋላ ሳልፈልግ ራሴን ከአስተናጋጁ ጋር ማነጻጸር ጀመርሁ ። ልጁ በመልኩ እና በዩኒፎርሙ ጥራት ይበልጠኛል ። በተጨማሪም ኮካ በትከሻው ላይ አስቀምጦ መክፈት ይችልበታል ። በርግጥ ኮካን ትከሻህም ላይ ክፈተው፣ ጠረጴዛ ላይ ጣዕሙን አይቀይረውም ። ግን በቃ ተስተናጋጁ ኮካ አዝዞ የሰርከስ ትርኢት ይመረቅለታል ። አስተናጋጁ በዚህ ረገድ ሊደነቅ ይገባል ። በሒሳብ ግን አይደርስብኝም ፤ የእኔን ጨምሮ የሦስት ደንበኞችን ሒሰብ ሲሳሳት አይቻለሁ ። ይህ ሰው በባቄላ ፍሬ ሲያሰላ ያደገ ሳይሆን አይቀርም ብዬ አሰብሁ ። ጓደኛዬ ... እንደነገረኝ የጥንት ኢትዮጵያውያን በጦርነት የተሞላ ኑሯቸው የሒሳብ ዕውቀታቸውን ለማዳበር ጊዜ ስላልሰጣቸው መደመር እና መቀነስን የሚሰሩት የባቄላ ፍሬን በመጠቀም ነበር ። ነገሩ እውነት ከሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የባቄላ ዝምድና ከአተር ጋር ብቻ ሳይሆን ከካልኩሌተር ጋር ጭምር ነው ።

📄📄📄

ምንጭ 📚 "መግባትና መውጣት" ገጽ 10-12
ደራሲ 🖊 በዕውቀቱ ሥዩም

THANK YOU
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/Readers_To_Know/281
🦅🖊 ስነ_ግጥም 🖌🦅

ጐጆ ቤት
....
ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
መሪዋም ምሰሶ
ሹማምንቷም ማገር
አንዳንዶቹም ቋሚ
ሌሎቹም ወጋግራ
ሰራዊቷም አጥር!
ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
ሕዝቡም ክዳን ሆኖ
ጐጆውን አልብሶ
እንደሳር ቢቀጥን፤ ቢኖር ተራ መስሎ
ከዝናብ ያድናል፤ ውርጩን አሰናብቶ
ፀሃይን ይከላል፤ በጥላው ከልሎ…
ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
እውነትም ጐጆ ናት
ሊቃውንቷም እሣት
ላንዱ ጭስ ሲደርሰው
ለሌላው ትኩሣት፡፡
ምሰሶው ቢተልቅ - መሪው ገዝፎ ቢታይ
ጐጆው ከቶ አይሞቅም - ካልጫሩበት እሣት
ጐጆው ቤት አይሆንም - ሳር ከሌለው በአናት…
… ሀገርስ ጐጆ ናት !!!...
..
(እንዳለጌታ ከበደ፣ልብ ሲበርደው፣2000)

❣️ THANK YOU ❣️
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/Readers_To_Know/281
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
በአብዲሳ ቶላ የተተረጎመው " ሳፒያንስ "

ከጦር ውርወራ እስከ ተወንጫፊ ኒዩክለር ሚሳይሎች የተደረገ የዘረ ሰብ ጉዞ

የሰው ልጆች ሥነ ልቦና፣ ኢኮኖሚ፣ ሐይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ሳይንስ… ከጥንታዊው የአደንና ቅርሚያ ህይወት እስከ ዘመናችን የካፒታሊስትሥርዓት የተዳሰሰበት፡፡
---------------!!----------------------------
ከዛሬ 3.8 ቢሊየን ዓመታት በፊት፣ መሬት በምትባል ፈለክ ላይ፣ አንዳንድ ሞለኪሎች ውህደቶችን በማካሄድ ውስብስብ የሆነ ዘአካል ወይም ኦርጋኒዝም አስገኙ፤ የነዚህ ዘአካሎች አፈጣጠርና እንቅስቃሴ ሥነ-ህይወት ወይም ባዮሎጂ ይባላል፡፡
ሰው በታሪክ ሂደት ውስጥ ሦስት ወሳኝ የሚባሉ አብዮቶችን አካሂዷል፡፡ እነኝህም ከ70,000 ዓመታት በፊት ሰው ከልምዱ እየተማረና እያወቀ - ይህንን እውቀቱን ደግሞ ማከማቸት የጀመረበት ኮግኒቲቭ ሪቮሊሽን (Cognitive Revolution) የሚባለው፣ ከ12,000 ዓመታት በፊት የጀመረው የግብርና አብዮት (Agricultural Revolution) እንዲሁም ከ500 ዓመታት በፊት ጀምሮ ማካሄድ የጀመረው የሳይንስ አብዮት (Scientific Revolution) ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ እነኝህ ሦስት አብዮቶች በዘረ ሰብና ሌሎች ዘአካሎች ላይ ስላደረሱት ተጽእኖ የሚተርክ ነው፡፡
አንብቡት ብዙ ቁም ነገር አለው።
❣️ THANK YOU ❣️
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚