ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫
የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ የቀይ መስቀል መስራች ደራሲ ገጣሚ አርበኛ
ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ቅምሻ💫
ክፍል አንድ
" አሁን የሰው ምንነት ግልጽ ብሎ ታየኝ። ሰው ማለት የተፈጠረ መፍጠር የማይችል የሚመግበውና የሚጠብቀው ያለው ነፍስና ሥጋ ያለው ከነፍስ ከሥጋ አንድ የሆነ በነፍስ አካልነት የቆመ የሚያስተውል ፣ የሚያስብ ፣ የሚናገር ፣ የሚንቀሳቀስ ፣ ሥጋ ብቻ ያልሆነ ፣ ነፍስም ብቻ ያልሆነ ፣ ፍፁመ ሥጋ ወነፍስ ፣ ፍፁመ ጸጋ ፣ ምሉዐ ጸጋ ፣ መንግል ያለው ፍጥረት ነው። "
ገፅ 94

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ቅምሻ💫
ክፍል ሁለት
" ኤርሚያስ ሲመራመር እግዚአብሔር አንድ ትዕዛዝ ሰጠው። ኤርምያስ ተመልከት አለው ኤርሚያስም እሺ ብሎ ሳለ አንድ ፈጣን ፈረሰኛ በፊቱ በታላቅ ፍጥነት እየጋለበ አለፈ። ፈጣሪም ኤርሚያስን 'ኤርምያስ ይህን ፈረሰኛ ተከተል' ብሎ ባዘዘው ጊዜ ኤርምያስ እንደነገረኝ ለመከተል ሞክሬ ነበር አለኝ። ከዚያስ ብለው አልቻልኩም አለኝ። ሌላ የሚገርም ነገር ልንገርህ፥ ፈጣሪዬም አዘዘኝ። አሁን ደግሞ ሌላ ፈረሰኛ መጣና ተከተለው አለኝ። ያሁኑ ፈረሰኛ ደግሞ ነፋስ ነበር። በሰንጋ ፈረሱ ተቀምጦ ለማየት በማይቻል ፍጥነት አለፈ። አሁንም ፈጣሪዬ ኤርምያስ ተከተለው አለኝ። እኔም አምላኬ ሆይ እንኳን የነፋስ ጋላቢውን የመጀመርያውን የሰው ጋላቢ መከተል አልቻልኩም ብዬ ብመልስ ፈጣሪዬም መለሰልኝ የሰው አቅምንም አስታወቀኝ።
🤔 እንቅልፍ ሲወስደው ራሱን ስለማያቅ የሰውነት ማንነት አቅምን ተረዳሁ። ፈጣሪዬም አየህ ኤርምያስ የመጀመሪያው ፈረሰኛ ያንተ ሐሳብ ነው። ሁለተኛው እኔ ነኝ። አንተም ለመከተል ሞክረህ የነበረው ደግሞ ያቃተህ እንኳን የኔን ነገር የራስህን ሐሳብ እንኳ ልትመረምርና ልታውቀው እንደማይችል ነው ፤ ብሎ አምላክ ገለጸልኝ ያለውን ካወጋኝ በኋላ ተለየኝ። "
ገፅ 119

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከላይ የምናያቸው
ሰው ምንድን ነው? (ምንትኑ ውእቱ ሰብእ?)
የማንነትን ትርጉም ፍለጋ ከሚለው የዶክተር ዘበነ ለማ መጽሐፍ የተወሰዱ ናቸው።
© 2011
ዋጋ 99.99 ብር

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​​​​​ይህን መጽሐፍ የፃፉት
​​ዶክተር ዘበነ ለማ በነገረ መለኮት ትምህርት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪ በማስተርስ ዲግሪ ስለአለም እምነቶች ጥናትና ፍልስፍና በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በዶክትሬት ዲግሪ በሥነ አመራር እና አንትሮፖሎጂ ጥናት ከሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ ተምረው ፈጽመዋል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
😂😂😂ለፈገግታ 😂😂😂
ወንዱ :- ይሄንን ቀን በጉጉት ስጠብቅ ነበር
ሴቷ :- ትቼህ እንድሄድ ትፈቅድልኛለህ ?
ወንዱ :- በፍፁም
ሴቷ :- ትወደኛለህ ?
ወንዱ :- አዎን
ሴቷ :- በላዬ ላይ ከሌላ ሴት ጋር
ታመነዝራለህ ?
ወንዱ :- በፍፁም አላደረገውም
ሴቷ :- ትስመኛለህ ?
ወንዱ :- ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ
ሴቷ :- ትመታኛለህ ?
ወንዱ :- ምን በወጣኝ
ሴቷ :- ልመንህ ?
ወንዱ :- Yes
ሴቷ :- የኔ ፍቅር
” ከጋብቻ በኋላ ከታች ወደ ላይ አንብቡት ”

ምንጭ:-http://www.yasekal.com

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫የእለቱ ጥቆማ💫
👉የ ወንድ ልጅ ምጥ
፩.አይነት፡የግጥም መድብል
፪.ደራሲ:ይስምዕከ ወርቁ
፫.የ መጀመርያ እትም:ሀምሌ 1999 ዓ.ም
፬.ገፅ ብዛት:80
፭.የግጥም ብዛት:60
፮.ልዩ ጥቆማ:
1.ፈሶሎጂ(ገፅ 35)
2.የወንድ ልጅ ምጥ(ገፅ75)

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
#coming soon
👉የ አጭር ልብወለድ ፬ቱ ምሰሶ ፀሐፍት
ባለ 4ክፍል ህይወታዊና ጥበባዊ ዳሰሳ👓

@Readers_To_Know
​​📺👉ከታሪክ ማህደር 👈📺
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም በስልጣን ዘመናቸው ከተናገሯቸው በቴሌቪዥን መስኮት ከቀረቡት ውስጥ በጥቂቱ
📺 "እያንዳንዱ ደቂቃና ሴኮንድ በእያንዳንዱ ወገናችን ህይወት ላይ ይወስናል።እና ቅድም እንዳልኳቹ እነሱ ከእረኛ እስከ ምሁር ተነስተው ለእኩይ አላማቸው ተሰልፈው ሲያበቁ ይህን ያደርጋሉ።ንቀውናል ደፍረውናል ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል። ውይይት ነው ሰላማዊ ሰልፍ ነው ወይስ እንደወያኔ ወጣቶች ታጥቃቹ ትሰለፋላቹ።"
📺 "አብዮታዊ ሰራዊታችን ከሕዝብ እንዳልተወለደ እና የሕዝብ ወገን እንዳልሆነ ሁሉ ፤ ይህንን ገበሬ እየሞተ ባለመሬት እንዳላደረገ ሁሉ ፤ እየለመነ ብስኩትና ዱቄት እንደማያድል ሁሉ ፤ ዛሬ በአክሱም በአደዋ በሽሬ ወዘተርፈ እንደ ጠላት ጦር ይሀው እርሱ ገበሬው እንደ አንበጣ ተሰባስበው እየተከተከው ነው። ......... ኋላቀሮች ረሀብተኞች ችጋራም የምንባለው ከዚሁ ክልል በሚመነጭ ችግር ነው።"
📺 "እንግዲ ሁሉም ለከትና መቼም ወሰን አለው። እኔ ግራህን ሲመቱህ ቀኙን ስጥ የሚባል እምነት የለኝም። በተለይ እንደንደዚህ አይነት የአካባቢያችን እብሪተኞች ደግሞ የሚገባቸው ቋንቋ ዲፕሎማሲ ሳይሆን አፍንጫቸውን ማለት ነው።"
📺 "ሁሉም አኩራፊ፤ ሁሉም ነፃ አውጪ ነኝ ባይ ፤ ሁሉም ተሳዳቢ እና ተቺ ፤ ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንዲያ ነው የሚል ፤ ምን አደረጋችሁልኝ እንጂ እኔ ምን አደረኩ የማይል ቁጥር ጥቂት ባልሆነበት ሁኔታ ውስጥ ምን ተዓምር እንድንሰራ ይጠበቅብናል።"
📺 "እኔ በበኩሌ እኔ ብሎ መናገር ልምዴ እንዳልሆነና እንደማልወደውም ታውቃላችሁ። በዚህ የታሪክ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና ፈቃድ በተሰጠኝ ሀላፊነት እና በተጣለብኝ እምነትና አደራ ለእናት ሀገሬና ወገኔ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር ምን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ በሚል እንጂ ከዚህ በተረፈ ቅንጣት ታህል እደግመዋለሁ ቅንጣት ታህል የሥልጣን ጥማትና ምኞት የለኝም።"

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከዚም ከዛም💫
#1. ሉሲ (ድንቅነሽ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘችው በታዋቂዎቹ ሳይንቲስቶች ዶናልድ ጆሀንሰን እና ይቬስ ካኘንስ ነበር።
#2. አሜሪካ ስያሜዋን ያገኘችው አሜሪጎ ቬስፑቺ ከተሰኘውና በ1499 ሀገሪቱን ካገኘው ኢጣሊያዊ የባሕር አሳሽ ነው።
#3. የመጀመሪያዋ የሴት መንኮራኩር አብራሪ የ26 አመቷ ቫለንቲና ተሬሽኮቫ ትባላለች።
#4. ከኢትዮጵያ አንደኛ ከአፍሪካ አራተኛ የሆነው ራስዳሽን 4620m ከባሕር ጠለል በላይ እርዝማኔ አለው።
#5. ንብ አንድ ፓዎንድ የሚመዝንን ማር ለመስራት 55,000 ማይል እና 2,000,000 አበባዎችን መቅሰም አለባት።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ለፈገግታ 💫
ጓዶቼ አንብቡ ምን አልባት አይታወቅም 😂😂😂 see the pic below

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ጥቆማ 💫
ሮሜዎና ዡልዬት
ቴአትር
ከከበደ ሚካኤል
ይህ መጽሐፍ አርተር ብሩክ የሚባል አንድ የእንግሊዝ ባለቅኔ መዠመሪያ በግጥም ጻፈው።ቀጥሎ ሼክስፒር ይህን ቅኔ መሠረት አድርጎ በመከተል ቴአትር አድርጎ አቀረበው።ከበደ ሚካኤልም በዚህ መጽሐፉ በግጥም ዘውግ ወደ አማርኛ ለመግለጥ እንዲመቸው አድርጎ አቅርቦታል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫
ከበደ ሚካኤል በኢትየጵያ ስነጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ገናና ከሆኑት ደራስያን አንዱ ናቸው። ጥቅምት 23፣ 1909 የተወለዱት ባለቅኔ የቤተክህነትን ትምህርት ካገባደዱ በኋላ በአሊያንስ ፍራንሴዝና በላዛሪስት ሚስዮን ዘመናዊ ትምህርትን ተከታትለዋል።
የግሪክ፣ የሮማውያን፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የሩስያና የጣልያንን በርካታ መፃህፍት ከመረመሩም በኋላ 26 መፃህፍትን ለወገኖቻቸው አበርክተዋል።
የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ለዚሁ አስተዋፅኦዋቸው የክብር ዶክተርነት ዲግሪን በ1990 ሰጥቷቸዋል።
በሜጋ አሳታሚ ድርጅት ታትመው ለአንባብያን ከቀረቡት መሀከል
1. ታሪክና ምሳሌ (፩ኛ መጽሐፍ)
2. ታሪክና ምሳሌ (፪ኛ መጽሐፍ)
3. የቅኔ ውበት
4. ሮሜዎና ዡልዬት
5. የዕውቀት ብልጭታ
6. ጃፓን እንደምን ሠለጠነች
7. ታላላቅ ሰዎች

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ቅምሻ 💫

ወንዙን ከላይ ገደብነው፣
ምንጩንም ወትፈን አቆምነው፣
ዝናቡን በድግምት ሰማይ አስቀረነው፤
የሴቱ ነገር ነው እኛን እንቢ ያለነ፣
ተስማምተው ቢሸኑ አጥለቀለቀነ።
...... አዳም ረታ፡ ግራጫ ቃጭሎች ገጽ 29

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫

አሌክሳንደር ፑሽኪን (1799-1837)

በ1977 ተወለደ። በጊዜው ተራማጅ አስተሳሰብ የነበረው ፑሽኪን: ሕይወቱን ለሩሲያ ስነ-ፅሁፍ ዕድገት ያዋለ በመሆኑ: የሀገሪቱ የመጀመሪያው የፈጠራ ፅሁፍ ጠቢብ ለመባል በቅቷል። የፑሽኪን የስነ-ፅሁፍ ውጤቶች የምዕራባውያን ባለ ቅኔዎች እና የብእር ሰዎች ተፅዕኖ የዳሰሳቸው ቢሆንም አርአያና ምሳሌ ለመሆን በበቁት በቅኔው፡ በተውኔቱ፡ በልብወለድ እና አጫጭር ድርሰቶቹ ጥልቀት እና ምጥቀት ብሔራዊ ባለቅኔነቱን ለማስመስከር ችሏል። ፑሽኪን በሰፊ የስነ-ፅሁፍ እና የስድ ፅሁፍ አዝመራው አማካኝነት ዘመናዊውን ስነ-ፅሁፋዊ ቋንቋ ለሩሲያ ያበረከተ ታላቅ የፈጠራ ሰው በመሆኑ፡ 'የሩሲያ ስነ-ፅሁፍ ታላቁ ጴጥሮስ' እያሉ የሚጠሩትም አልታጡም። የዛሬዋ ሶቪዬት ኅብረት ደራሲያንም፡ 'የሕዝባችን ነፍስ' የሚል ስያሜ የሰጡት ያለ ምክንያት አይደለም። የአርበኝነትን ባሕርይ፡ ጠንካራ ብሔራዊ ኩራትንና ለሩሲያ አፈር ያለውን ጥልቅ ፍቅር ከአብዮታዊ ስሜት ጋር በማዋሀድ በቅኔዎቹ ይገልጥ ስለነበር ነው። ይህም ስለ ስራው እና ስለ ህይወቱ በሚተርኩ ገድሎች ውስጥ ተመዝግቧል። በተለይም በከፍተኛ ስሜት ይደግፈው በነበረው፡ "የታኅሣሣዊያን ንቅናቄ" እየተባለ በሚጠራው፡ የ1825 እንቅስቃሴ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ላደረጉት አርበኞች ጓደኞቹ መታሰቢያነት የፃፋቸው ቅኔዎች ለዚህ ቋሚ ምስክር ናቸዉና ሊጠቀሱ ይገባል።

ፑሽኪን ኢትዮጵያዊ ደም ነበረው። በሀገራችን በይበልጥ የሚታወቀውም በኢትዮጵያዊው ቅድመ አያቱ በአብርሃም ሃኒባል ታሪክ እንጂ፥ እምብዛም በኪነታዊ ስራዎቹ አይደለም። ወደ አማሪኛ ከተመለሱት ጥቂት አጫጭር ታሪኮቹ በስተቀር ዋነኛዎቹ የፑሽኪን የጥበብ ውጤቶች፡ በተለይም ድንቅ ቅኔዎቹ እስከ ዛሬ በሀገራችን ልሳናት አልተተረጎሙም።

የፑሽኪን መጨረሻ ድንገተዊ እና የሚያሳዝንም ነበር። በአንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ፡ ዳንቴስ ከሚባል ሰው ጋር የከረረ አለመግባባት ይፈጠርና ሁለቱ ጠበኞች በተኩስ ለመፋለም ይወስናሉ። እኒሁ ግለሰቦች የካቲት 8 ቀን 1837 ባደረጉት የተኩስ ፍልሚያ የ38 ዓመቱ ጎልማሳ ደራሲ በለጋነቱ ተቀጨ።

[ካፖርቱ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች (ትርጉም) በመስፍን አለማየሁ፡ገጽ 7 እና 8፡ 1978 ዓ.ም ]


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫

ጥቂት ስለ ንግሥተ ሳባ

አባቷ ንጉሥ ተዋስያን ሲሆን እናቷ ደግሞ እቴጌ ኤስሜኒ ይባላሉ

ንግሥተ ሳባ የነገሰችው ከክርስቶስ ልደት በፊት 1013 ዓመት (በ 3,987 ዓመተ ዓለም) ሲሆን በጽሑፍ ከተገኙ መረጃዎች የኢትዮጵያ ነገስታት ተርታ 52ኛዋ በጠቅላላው ከነገሡት ነገሥታት ተረታ ደግሞ 98ኛዋ ነበረች።

ንግሥተ ሳባ ሰሎሞንን የጎበኘችው 'ታምሪን' በተባለ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ አማካኝነት ነበር።

ከንጉሥ ሰሎሞን የወለደችው ልጇ ስሙ 'እብነ እልኪምን' ይባል ነበር። ትርጉሙም 'የብልሃተኛ ልጅ' ማለት ነው።

-በኋላም ንግሥተ ሳባ ለ31 ዓመት ስታስተዳድር ቆይታ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ982 ዓመት(በ3,518 ዓ.ም) መንግሥቷን ለልጇ ስታወርስ ስሙ 'ቀዳማዊ ምኒልክ' ወይም 'ዳዊት' ነብሎ ነግሷል

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከዚም ከዛም💫

-በዓለማችን በኢንተርኔት ግብይት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸጠው የማሪዋና እፅ ነው፡፡

-የአለማችን 10% ህዝብ ግራኝ ነው።

-ዶልፊን ከ እንስሳት ሁሉ የማስታወስ ችሎታ አለው።

-አንድ ሰው በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት በእንቅልፍ ያሳልፋል።



👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ቅምሻ 💫
የ አጤ ኅይለስላሴ አሟሟት
"ነሃሴ 20 ቀን 1967 ዓ.ም ተረኛ አልባሻቸው ስለነበርኩ
ከንጉሱ ማደሪያ ለማደር ስሄድ ሻለቃ ዳንኤል አስፋው ለዛ
ቀን ማደሬ እንደማያስፈልግ ነገረኝ፡፡ ወደ ንጉሱ ቀርቤ
የተባለውን ስነግራቸው፣ ንጉሱ ተንበርክከው እንባቸውን
እየጠረጉ፣ አይ አንቺ ኢትዮጵያ! እውነት በድለንሻል?
አልደከምንልሽም? ብለው እምባቸውን ፈነጠቁ፡፡
እኔም አማራጭ ስላልነበረኝ ጌታዬን ትቼ ወደ ቤቴ ሄድኩ፡፡
ንጉሱ ሞተው የተገኙ እለት የመኝታ ክፍላቸው የመድሀኒት
ጠረን ይሸት ነበር፡፡ በንጉሱ አንገት አካባቢ ለአንገት
ማሰሪያ የሚያገለግል ፋሻ ተቀምጦ ነበር፡፡ ንጉሱ
የተገደሉት ነሃሴ 20 ቀን 1967 ዓ.ም ሲሆን የተቀበሩት
በማግስቱ ነሃሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም ነው፡፡
ግድያው የተፈጸመው ከደብረብርሃን የመጣውን ልዩ ጦር
በሚመራው በሻለቃ ዳንኤል አስፋው አማካኝነት ነው፡፡
ንጉሱ ሰመመን አምጪ መድሃኒት በአፍንጫቸው
እንዲያሸቱ ከተደረገ በኋላ በትራስ ታፍነው ተገድለዋል፡፡
ንጉሱን እንዲያፍን የታዘዘው ወታደር ህሊናው እምቢ
ብሎት በመርበትበቱ፣ እራሱ ሻለቃ ዳንኤል አፈናውን
ፈጽሞታል፡፡
ነሃሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም የሬሳ ሳጥንና የከፈን ጨርቅ
እንዳቀርብ ታዝዤ ሰጥቻለሁ፡፡ በ7 ሰአት ላይ በሻለቃ
ዳንኤል ትእዛዝ 4 ጉርጓዶችን በ3፣ በ3 ሜትር አስቆፍሬ፣
በኮንክሪት ዘግቻለሁ፡፡ በአጭር ጌዜም በጉርጓዶቹ ላይ
ቤት ተሰራ፡፡ ኢህአዲግ ሲገባ ኮሎኔል ሲለሺ መኩሪያ
በሰጡት ጥቆማ፣ ከነዚሁ ጉርጓዶች የንጉሱ አጽም ተገኝቶ
ወጣ፡፡" - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አሟሟት
በማስመልከት ከተሰጡ ምስክርነቶች
Peter Marlow Photographs/Pitt Rivers
Museum/Oxford University/Exhibition 2010:
https://www.prm.ox.ac.uk/event/the-burial-
of-emperor-haile-selassie
'Emperor Haile Selassie was finally buried in
2000, 25 years after his tragic death. He was
deposed in 1974 by the military government
the 'Derg', and died a year later while still
under house arrest
Despite Haile Selassie's undeniable
historical importance, the new government
that replaced the Derg refused to give Haile
Selassie's reburial the status of a state
funeral ...'

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
የባዕድ ሐገር ስሞች ትክክለኛ የግዕዝ ትርጓሜያቸው።
-------------------------
፩. ኮሌጅ ------ መካነ ትምህርት
፪. ዩኒቨርስቲ ------ መካነ አምሮ
፫. ሌክቸር ------ ትምህርተ ጉባኤ
፬. ሌክቸረር ------ መምህረ ጉባኤ
፭. ዲን ----- ሊቀ ጉባኤ
፯. ቢሮ ------ መስሪያ ቤት
፰. ባንክ ------ ቤተ ንዋይ
፱. ሲቪል ሰርቪስ ------ ሰላማዊ አገልግሎት
፲. Custom ------ ኬላ
፲፩. ኮምፒተር ------ መቀመሪያ
፲፪. ድግሪ ------ ማዕረግ
፲፫. ሚኒስተር ------ ምሉክ
፲፬. Mass media ------ ምህዋረ ዜና
፲፭. ፎቶ ግራፍ ------ ብራናዊ ስዕል
፲፮. ራዲዮ ------ ንፈሰ ድምፅ
፲፯. ፖሊስ ------ የህግ ዘበኛ
፲፰. ኢንተርኔት ------ የህዋ አውታር
፲፱. ሎሬት ------ አምበል ፣ ተሸላሚ የቅኔ
፳. ዶክተር ------ ሊቀ ሙህር
፳፩. ኢምባሲ ------ የእንደራሲ ፅ/ቤት
፳፪. ዲፕሎማት ------ የመንግስት መልክተኞች
፳፫. ኢኮኖሚክስ ------ ስነ ብዕል
፳፬. ሀዋላ ------ ምህዋረ ንዋይ
፳፭. ሳሎን ------ እንግዳ መቀበያ
፳፮. ቱሪዝም ------ ስነ ህዋፄ
፳፯. ስካን ------ ምክታብ
፳፰. ፕሬዝዳንት ------ ሊቀ ሀገር / ሙሴ
፳፱. ቴሌኮሚኒኬሽን ------ ምህዋረ ቃል
፴. ቪዛ ------ የይለፍ ፍቃድ
፴፩. ፓስፖርት ------ የኬላ ማለፊያ
፴፪. ቴሌቪዥን ------ ምስለ መስኮት / መቅረፀ ትይንት
፴፫. Voice Recorder ----መቅረፀ ድምፅ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ምንጭ ፡- TIKVAH-ETH

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫