ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
🧞‍♂👣 ከዚም ከዛም👣 🧞‍♂

1. ድመቶች🐈 110 ያህል የድምፅ አይነቶችን ማውጣት ይችላሉ።

2. ሰው ከ5-10 🕑 ደቂቃ ያለ ዓየር መቆየት ይችላል ተብሎ ይገመታል።

3. የሴቷ ዘር (እንቁላል🥚) የእስክሪቢቶ ጫፍ ያክላል ተብሎ ይገመታል።

4. አንጎል🧠 አንስተን ብናነጥፈው 24 m^2 የሚያክል እርዝማኔ አለው።

5. አባባል:- የትላንቷ ፀሐይ🌞 አቃጠለችኝ ተብሎ የዛሬዋን ፀሐይ አልሞቅም አይባልም።

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
😂🌍 ለፈገግታ 🌎😂

ጨርሰው ያንብቡት

“ጦር አውርድ”
ከበዕውቀቱ ሥዩም
.
… ከዘመናት ባንዱ ዘመን የሀበሻ መዲና በነበረችው አክሱም በጐረቤቶቿ በኑብያና በየመን ሰላም ነገሠ …
ይልቁንም በአክሱም ብልፅግና ሰፈነ፤ ሁሉም እንጀራና ወይን ጠገበ።
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከተመሰገኑት ያክሱም ሊቃውንት አንዱ ንጉሡ በተገኙበት ጉባኤ ‘ልቦናዬ ያሳየኝን ልናገር’ አሉ። ተፈቀደላቸው።
“ግርማዊ ጃንሆይ” አሉ ባማረ ድምፃቸው …
“ግርማዊ ጃንሆይ አክሱም የምትገኝበት ሁኔታ ለረጋው ሕሊናየ ሥጋት ፈጥሮብኛል፤ ይሄ ሥጋት ደግሞ ቀስ በቀስ ወደ ወገኖቼ መጋባቱ አይቀርም።”
“ምንድን ነው የሥጋትህ ምንጭ?” አሉ ንጉሡ።
ሊቁ ማብራራት ጀመሩ።
“እንደምናየው በመንግሥታችን ሰላም አለቅጥ ሰፍኗል … የባሩድ መዓዛ ከሸተተን ብዙ ዘመን ሆነን … የሽለላ
የፉከራ ዜማዎቻችን ተዘነጉ። እረኞቻችንን ስሟቸው …
በዜማዎቻቸው ውስጥ የብልግናና የፍቅር እንጂ የጉብዝናና የጀግንነት ስንኝ አይገኝም። ጋሻዎቻችን በተሰቀሉበት ድር አደራባቸው … ጦሮቻችን ዶልዱመዋል … ሀኔዎቻችን ዛጉ … ነጋሪቶቻችን ዳዋ
ዋጣቸው … ሰላም ልማዶቻችንና ትውፊታችንን አጠፋብን። ሕንፃ ያለ ጡብ ያለ ጣሪያ ሕንፃ እንደማይሆን እኛም ያለ ነውጣችን ያለ ሽለላችን ያለ ድላችን እና ያለ ሽንፈታችን እኛ አይደለንም።
“ግርማዊነትዎ እንደሚያውቁት አንበሳ ከሚዳቋ ጋር ተኝቶ ማየት ለጊዜው የሚያስደስት ትዕይንት ሊሆን
ይችላል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ይሰለቻል። የሁሉም ዓይን አንበሳው ሚዳቆዋን ሲያሳድዳት … ሰብሮም
ሲገነጣጥላት ለማየት ይናፍቃል።
“ጃንሆይ … ‘እርግቦች በሰገነቶቻችን ላይ ሰፍረዋል፤ የዘንባባ ዛፎች በጓሮአችን በቅለዋል’ ብለው የሚያዘናጉትን አይስሟቸው! … ብርቱ መንግሥት
ከርግቦች ላባ ፍላፃ ያበጃል … ከዘንባባዎች ዝንጣፊ የጦር ሶማያ ይሰራል። “ለራሳችን ብርቱዎች ነን ብለን እንጃጃላለን … ካልታገሉ ሀቅንም ማወቅ አይቻልም። ጐረቤቶቻችን ከፈገግታቸው ባሻገር ምን እያሴሩ እንደሆኑ
አናውቅም። የጐረቤቶቻችን በር ተዘግቷል … በዚህ ምክንያት በእልፍኛቸው ውስጥ ምን እየተሰራ እንደሆነ አናውቅም … የጐረቤቶቻችንን ልክ አለማወቅ በቤታችን ላይ ሥጋት እንዲያንዣብብ አድርጓል።
“ጃንሆይ! የምንኖረው ፈተና በሌለበት ዘመን ነው። ፈተና የሌለበት ዘመን የተፈጥሮን ሕግ ያዛባል። እስቲ
ጐረምሶቻችንን እይዋቸው! … እንደ ሴት ዳሌና ጡት ማብቀል ጀምረዋል … በምትኩ ፂማቸውን ካገጫቸውና ከከንፈራቸው ጠርዝ አርግፈዋል …
መዳፎቻቸው ከሐር ጨርቅ ይለሰልሳሉ … እግራቸውን ዘርግተው የባልቴት ተረት በመተርተር ጊዜያቸውን ያጠፋሉ … የደም ቀለም አያውቁም!
“አያቶቻችን ፍላፃ የወጠሩባቸው ደጋኖች የሴት ልጆቻችን የጥጥ መንደፊያ ሆኑ … ስለዚህ የምንለብሰው ሸማ በውርደት አድፏል። ይሄን እድፍ ከደም በቀር የሚያነፃው ምን አለ?”
ንጉሡ ከመኳንንቱ ጋር ይሄን አድምጠው፣ “ታዲያ ምን ይሻላል?” አሉ።
“ኑብያዎችን ለምን አንወጋም?” አሉ ሊቁ።
“ኑብያዎች ምን አደረጉን?”
“ሁለታችንን በሚለየው ድንበር ላይ ዋርካ ተክለዋል!”
“እና ቢተክሉስ?”
“ዋርካዎች እየሰፉ በመጡ ቁጥር የኛን መሬት መውሰዳቸው አይቀርም!”
“እና ምን ይሻላል?”
“እናቅምሳቸው!” አሉ ሊቁ።
“እንበላቸው!” አሉ መኳንንት።
“በሏቸው” አሉ ንጉሡ።

ሁኔታዎች ተቀያየሩ። ሴቶች ቆሎ በማመስ ጭብጦ በማሰናዳት ተጠመዱ። ወንዶች ኢላማ ልምምዱን አጣደፉት። አሮጌ ጋሻዎች
ከተሰቀሉበት ወረዱ። ደጋኖች ተወለወሉ። ፍላፃዎች ተሳሉ። የጐበዞች አረማመድ ተለወጠ። የእረኞች
የፍቅር ዘፈን አንደበታቸው ላይ ሟሟ።
የደም ቃና ያላቸው ዜማዎች መስኩን ዱሩን ጋራውን ሞሉት። የአክሱም ባንዲራ ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች።

ጥቂት ወራት አለፈ። ከወደ ኑብያ ግድም ደብዳቤ መጣ።
“ዛቲ ጦማር ዘተፈነወ ትኀበ ንጉሠ አክሱም …
… የየመን ሊቃውንት አንድ መረጃ ነገሩን … እናንተ አክሱሞች በኛ ላይ ሠራዊት ልታዘምቱ እንደተሰናዳችሁ ሰምተን አዝነናል። ይሁን እንጂ የጠባችን ምክንያት በድንበሮቻችን ላይ የተተከሉት
የዋርካ ዛፎች መሆናቸውን በማወቃችን ለሰላም የሚበጀውን አድርገናል። ከዛሬ ጀምሮ ዋርካዎች እንዲቆረጡ ትእዛዝ አስተላልፈናል … ይቅርታ አድርጉልን !”
የሚታይ ማህተም ደብዳቤው ከደረሳቸው በኋላ ንጉሡ ሊቁን አስጠሩ።
“ምን ይሻለናል? ኑብያዎች ሳንወጋቸው ዋርካዎችን ቆረጡ! እንግዲህ ምን ሰበብ እንፈጥራለን?” አሉ
በቅሬታ።
“ግርማዊ ሆይ!” አሉ ሊቁ “የሰማነው ዜና በእውነቱ የሚያስቆጣ ነው። እንደሚያውቁት ሠራዊት ለማደራጀት ብዙ ገንዘብ ብዙ ጉልበት ብዙ ጊዜ
ፈጅተናል። ጐበዞቻችንን ከሙያቸው አፈናቅለን አስታጥቀናቸዋል። ሴቶቻችን ቡሃቃቸውን አሟጠው ስንቅ ሰርተዋል። ይሄ ሁሉ ያለ አንዳች ተግባር ብላሽ
መሆን የለበትም ጃንሆይ!” አሉ በመማፀን ድምፅ።
“ታድያ ምን አድርግ ነው የምትለኝ?”
“የዘመቻችንን እቅድ ሰልሎ ለኑብያዎች የነገራቸው የየመን መንግሥት ነው።”
“እናስ?”
“በዚህ ምክንያት የመኖች የኛን ሉዐላዊነት ደፍረዋል።
ስለዚህ ለምን ዘመቻውን ወደ የመን አናዛውረውም?”
አማራጭ አልተገኘም። በማግስቱ አዋጅ ተነገረ፤
“ጠላታችን ወደሆነው ወደ የመን ሀገር ዝመቱ። በዚያ ሕያው የሆነውን ሁሉ ፍጁ ! … ከተሞቻቸውንም ወደ ፍርስራሽ ለውጡ ! …”.
.
ምንጭ – “በራሪቅጠሎች ”። 1996 ገጽ 76-81
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📜 ከታሪክ ማህደር 📜

የአየር መንገድ ሥራ ከተጀመረበት ጊዜ ሳያቋርጡ ለመንገደኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አየር መንገዶች ሥራ የጀመሩበት ዘመን (እ.ኤ.አ)
1. ኬ.ኤል.ኤም 17 ሜይ 1920
2.አቪያንካ 19 ሴፕቴምበር 1921
3.ኳንታስ 2 ኖቬምበር 1922
4.ኤሮፍሎት 15 ጁላይ 1923
5.ሲ.ኤስ.ኤ 28 ኦክቶበር 1923 በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ተቋርጦ (1939-45) እንደገና የጀመረ

6.ፊን ኤይር 20 ማርች 1924 በጦርነቱ ተቋርጦ በ1945 የጀመረ

7.ሳቢና 1 ኤፕሪል 1924

👉👉8.አቪዬሽን ወደ ኢትዮጵያ የገባው 18 ኦገስት 1929 ወይም ነሐሴ 12 1921 ዓ.ም

ምንጭ 'አቪዬሽን በኢትዮጵያ' በካፕቴን መኮንን 1995... ገጽ 21

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አምስት 🦅

........ ደመነፍስ እንግዲህ ከንቁ አእምሮአችን ሥር ያለው የተንጣለለው ከፊል ንቁና ድብቁ አእምሮአችን ነው የሚባለው። አንዳንዴ በደመነፍስ ኖረን በደመነፍስ መሞትም አለ። ደመነፍስ ስንል በርግጥ አንዳንዴ የሰውን እንስሳዊ የፍላጎት ግፊትንም ለመግለጽ እንጠቀምበታለን ።........ ነቅቶ የሚንከላወሰውን አእምሮአችንን በጥልቅ የማንነታችን ውቅያኖስ ውስጥ ተወሽቆ እሱ ነው አሉ የሚያሾረው የሚያሽከረክረውም ።
ደመነፍስ የነፍስ ደም ነው፤ መልኩ ግን ቀይ አይደለም ፤ የነፍስ ነገሮች በቀለም ሳይሆን በሀሳብ ደርዝ ነው የሚገልፁት። ደመ ሥጋ የሥጋ ህልውና እንደሆነ ሁሉ ደመነፍስም የነፍስን አኗኗር ይወስናል። ደመ ስጋ ለሰውነት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብና ኦክሲጅን ያደርሳል ። ብሎም ካንዱ ክፍል ወደ ሌላው ጠቃሚ መልዕክተኛ ንጥረ ነገሮችንና ተወጋጅ ቆሻሻዎችን በልብ እየተገፋ ያመላልሳል ቀን ከሌት። እሱ በቆመበት ቀን ሕይወትም ትቆማለች ።ደመነፍስም በነፍስ አለም ያንኑ ሳይሠራ ይቀራል? ቀን በውን .... ሌት በህልም .... አውቀን በንቃት .... ሳናውቅ በፍዘት ....የቀዳነውን ሐሳብ አመላላሽ .... ባቡራችን .... ቧንቧችን ነው።...........
ገፅ 206

~~~ይቀጥላል~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate


📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

ኤድያ ጨርቅን ማመን የሚያምን ይመነው ፤
ሲነጋ ቢደምቅ ሲመሽ ወላቂ ነው ፤
ድሎቴን ለማይወድ ጠቦኝ ለሚቀረው ፤
ብሰፋው ባሰፋው ለሚተረተረው ።
ደካማ ነውና ሳውቀው መቀደዱን ፤
ዋ! በተውኩት ኖሮ ብጥስጣሽ መውደድን ።
እንደሱማ ነበር ብልጭልጭ ፍልቅልቅ ፤
ሲነጋ ጠላቂ ሲመሽ ሊወላልቅ ።
እብድ ይበሉኝ እንጂ በቃኝ የሱ ነገር ፤
ዛሬም ነገም ማጠብ መቆሸሹ ላይቀር ።

ምንጭ:- ከታገል ሰይፉ፣ ቀፎውን አትንኩት፣ አ.አ ብርሀንና ሰላም
#share #participate #comment


📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ስድስት 🦅

ስለ ኦቲዝም አጠቃላይ መረጃ ታገኙበታላችሁ ፤ትወዱታላችሁም።
ክፍል ስድስትPage 2
ክፍል ስድስትPage 3
ክፍል ስድስትPage 4
​​ጥሩ እውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ እናረጋለን ቆይታችሁ ከኛ ጋራ ዘወትር ይሁን!
~~~ ይቀጥላል ~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ሰባት 🦅

.......... ልቦናችን ከእውነቱ ይልቅ እውነት ነው ብለን የያዝነው ፣ ያመነው ጉዳይ ይገዛዋል። የውሸት ሀይል ደግሞ እውነት መስሎት በተቀበለው አእምሮ ላይ ነው። ምድር በውሸታሞች የተሞላች ከመሆኗም ባሻገር ውሸትን በቀላሉ እውነት አድርገው የሚቀበሉ ሰዎችም ከዚያው አይተናነሱም ። ስሜታችን የተጠመደበት ጉዳይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ለውሸት የተጋለጥን ያደርገናል ። ይህም ምናልባት ስሜት ከምክንያትና ከማስረጃ ይልቅ በእምነትና በግንኙነት ላይ ስለሚደገፍ ይሆናል ። ያመነውና የተጠጋነው ሰው ደግሞ የስሜታችን ሹፌር መሆኑ አይቀርም። ........... የብዙ ሰው አስተሳሰብ ለስሜታዊው የልቦና ክፍል ማይም ነው። ሦስት አራት ዲግሪ ይዘውና ስልሳ ሰባ ዓመት ኖረው እንኳ ቢሆን የራሳቸውን ስሜት በመረዳትና በመምራትም ሆነ የሌላውን ሰው የስሜት አለም በማንበብ ችሎታ ከዜሮ ክፍል ፈቀቅ ያላሉ ሰዎች አያሌ ናቸው ።................
ገፅ 218

......... የሰው ልጅ መቼም ሊሰራ ያሰበውን ክፋት የደግነት ቀለምና የቅድስና ቅባት ቀብቶ ራሱን ሲያታልል የልቡናው አይን መታወሩን እንኳ አያውቅም።..........
........ ኅሊናውን አሽከሩ ያደረገ ሰው ክፋቱ ጌታው መሆኑ አይቀርምና።............
ገፅ 229

~~~ይቀጥላል~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

1. አባባል : ሴት👱‍♀ ካላበለች ባሏን👱‍♂ ትወዳለች❤️

2. In 1819 France🇫🇷 citizen Laennec invented stethoscope👨‍⚕.

3. Quote :- Anyone can make you smile😁, many people can make you cry😭, but it takes someone really special to make you smile with tears in your eyes😂.

4. ይሄን ይሞክሩት🤷‍♂🤷‍♀!
በአምስት ቁጥር የሚያልቅ ባለ ሁለት አሐዝ ቁጥር ማባዛት ስኩዌር ማድረግ። የመጀመሪያ ዲጂት ቁጥር ሲደመር አንድ ከዛም በራሱ ዲጂት ማባዛት። ከዛም አባዝተው ያገኙትን ከፊቱ 25 መቀጠል ነው።
ለምሳሌ :- 95*95 ?
9(9+1) = 90 ይሆናል። ከዛም 90 ላይ 25 መጨመር፤ የመጨረሻ መልሱም 9025 ይሆናል።

#share #participate #comment
እናንተም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉትን👇
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​🎥📻 ከታሪክማህደር 🎙🎞

🏅ኖብል ፕራይዝ 🎖
ኖብል ፕራይዝ እ.ኤ.አ በ1895 በስዊዲሹ ኬሚስት፣ ኢንጂነር እና ኢንደስትሪያሊስት አልፍሬድ ኖብል ነበር። አምስቱ ሽልማቶችም በኬሚስትሪ ፣ በስነ ጽሑፍ ፣ በሰላም ፣ በፊዚክስ እና ፊዝዮሎጂ ወይም በሜዲስን ዘርፎች ለመጀመሪያ ጊዜ በ1901 ተሰተው ነበር። ሽልማቶቹም በስዊድንና በኖርዌይ ይሰጣሉ። ሁሉም ሽልማቶች ከሰላም ሽልማት ውጪ በስዊድን ሲሰጡ የሰላም ሽልማት በኖርዌይ ይሰጣል።
ሽልማቱን የሚሰጡትም Nobel Assembly at the Karolinska institute በፊዚዮሎጂ ወይም በሜዲስን ፣ Norwegian Nobel Committee በሰላም ዘርፍ ፣ Royal Swedish Academy of Sciences በኬሚስትሪ ኢኮኖሚክ ሳይንስና በፊዚክስ ዘርፍ ፣ Swedish Academy በስነጽሑፍ ዘርፍ ናቸው። የሚሰጠው ሽልማትም 986,000 us Dollar እንዲሁም ሜዳሊያ፣ ዲፕሎማ ናቸው።
- Wilhelm Röntgen የመጀመሪያውን የፊዚክስ ዘርፍ ተሸላሚ ሲሆን ፤ የተሸለመውም x-ray በማግኘቱ ነበር።
- Jacobus Henricus van't Hoff የመጀመሪያው የኬሚስትሪ ዘርፍ ተሸላሚ ነበር።
- Emil Adolf von Behring የመጀመሪያው የፊዚዮሎጂ እና የሜዲስን ዘርፍ ተሸላሚ ነበር።
- sully Prudho የመጀመሪያው የስነ ጽሑፍ ዘርፍ ተሸላሚ ነበር።
- Jean Henry Dunant እና Frédéric Passy የመጀመሪያዎቹ የሰላም ዘርፍ አሸናፊዎች ነበሩ።

በሰላም ዘርፉ ዘንድሮ ማለትም በ2019 እ.ኤ.እ. የተሸለሙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አቢይ አህመድ ናቸው። የተሸለሙበትም ምክንያት ቃል በቃል እንደሚከተለው እናየዋለን
The Nobel Peace Prize 2019 was
awarded to Abiy Ahmed Ali "for his
efforts to achieve peace and
international cooperation, and in
particular for his decisive initiative to
resolve the border conflict with
neighbouring Eritrea."
እንኳን ደስ አላችሁ አለን!

#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ❤️
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ስምንት 🦅

........... በትክክል ያላደጉ ልጆች እንዴት ጥሩ ወላጅ ሊሆኑ ይችላሉ? ሰዎች ሙዚቃና ስፖርት ፣ እጅ ስራና እርሻ ከልጅነታቸው ሲማሩ ፣ ወላጅነትንና የትዳር አጋርነትን ግን በግምትና በመላምት የሚገቡበት መሆኑ አስገራሚ ነው ። አውሮፕላን አብርሮ በማያቅ ፓይለት በሚበር አውሮፕላን ውስጥ ማንም አይሳፈርም። ብዙ ልጆች የሚወለዱት ግን ትዳርና ቤተሰብ እንዴት እንደሚመራ በማያውቁ አዲስ ለማጆች ባቋቋሙት ቤት ውስጥ ነው። ...........
ከጎዳና ተዳዳሪው እስከ ሚሊየነሩ ፣ ከገበሬው እስከ ሳይንቲስቱ ፣ ከየኔ ብጤው እስከ ሀገር መሪው አብዛኛው ያገባል ይወልዳል ። ከዘጠና እጁ በላይ ግን ለትዳርም ሆነ ለወላጅነት ማይም ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። በምድር ላይ ካሉ ስራዎች እጅግ አስቸጋሪ ለሆነው ሥራ እንዴት ይሆን ሰው ሁሉ እንዲህ ደፋርና ግድየለሽ ሊሆን የቻለው? በዚህ በማይማን ህብረት በተቋቋመ ተቋም ውስጥ እንደሚወለዱ ልጆች ምን አሳዛኝ ፍጥረት ሊኖር ይችላል? እንደ ትዳር የዕድሜያችንንና የሕይወታችንን ብዙ ድርሻና ዘመን የሚወስድ ምን አለ? ሰውን የማያህል ነገር ወልዶ እንደማሳደግስ ምን ከባድ ኀላፋነትስ አለ? ታድያ የትዳርና የወላጅነት ማይማን የተመሳቀለ ኑሮ ኖረው ወደዚህ አለም ያመጡትንም ሰው ህይወት እና አስተሳሰብ ቢያመሳቅሉ ይገርማል ? አስተሳሰብና አእምሮም በከፍተኛ ደረጃ የሚቀረፀውና የሚወሰነው ትምህረት ቤት ሳይሆን በልጅነት እድሜ በቤተሰብ ውስጥ ነው።..............
ገፅ 261
....... ለተሰበረ እግር መዳን ጄሶ እንደሚያስፈልግ የተሰበረ ልብንም ያለ እውነተኛ ጓደኛ መጠገን አይቻልም ። .......
ገፅ 269

~~~ይቀጥላል~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

አማርኛ ከሌሎች ቋንቋዎች የተዋሳቸው ቃላት

በዋናነት ከ 4 ቋንቋዎች የተዋሳቸው ቃላት ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ እነርሱም ዐረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛና እንግሊዝኛ ናቸው፡፡ የቱርክ እና የጀርመን ቋንቋዎችም ጥቂት ቃላትን ለሀገራችን ቋንቋዎች አበርክተዋል፡፡

 🇸🇦🇩🇿 ከዐረብኛ የተዋሳቸው ቃላት
ሀዋላ፣ ጉምሩክ፣ ሰንዱቅ፣ ሱቅ፣ መጋዘን፣ ሽርክና፣ ወኪል፣ ሰነድ፣ ደላላ፣ መሃለቅ ወዘተ 

🇫🇷🇫🇷ከፈረንሳይኛ ከወረስናቸው ቃላት መካከል ደግሞ “ኦፊሴል”፣ “ሞኖፖል”፣ “ሌጋሲዮን”፣ “ኮሚስዮን”፣ “ፔኒስዮን”፣ “ዲክላራሲዮን”፣ “ኦፕራሲዮን”፣ “ካሚዮን”፣ “ፍሪሲዮን”፣ “ሬኮማንዴ”፣ “ለገሀር (ላጋር)፣ “ቡፌ”፣ “ሌሲ ፓሴ”፣ “ዴኤታ”፣ “ ካፌ”፣ “ራንዴቩ”፣ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

🇮🇹🇮🇹ከጣሊያንኛ ከወረስናቸው ቃላት መካከል እነዚህ ይገኙበታል “ፓስታ”፣ “ማካሮኒ”፣ “ላዛኛ”፣ "መኪና"፣“ስፓጌቲ”፣ “ስልስ” (ሳልሳ)፣ “አሮስቶ”፣ “ፋብሪካ”፣ “ጋዜጣ”፣ “ሊቼንሳ”፣ “ፉርኖ”፣ “ቪያጆ” (በመኪና የሚደረግ ጉዞ)፣ “ላቫጆ”፣ “ካሮሴሪያ”፣ “ካምቢዮ”፣ “ሞቶሪኖ”፣ “ፍሬን”፣ “ፊልትሮ”፣ “ሳልቫታዮ”፣ “ፖርቶ መጋላ”፣ “ፒንሳ”፣ “ቺንጊያ” ፣ “ፈረፋንጎ”፣ “ኩሽኔታ” “ኪያቤ”፣ “ካቻቢቴ” “ባሌስትራ”፣ “ቸርኬ” “ፒስታ” “ኮማርዳሬ” “ጎሚኒ” “ሮንዴላ” “ዲፍረንሻሌ” “ስፒናታ” “ሳልዳሬ” “ቡኮ”፣ “ፖምፓ” (ቧንቧ)፣ “አውታንቲ”፣ “ማኖ”፣ “ኢሊ ጎሬ”፣ “ቴስታ”፣ “ፑንቶ”፣ “ቦጦሎኒ”፣ “ካምቦ” ወዘተ…. የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

🇬🇧🇬🇧ከእንግሊዝኛም እንደ “ፖሊስ”፣ “ባንክ”፣ “ሚኒስቴር”፣ “ካፒታል”፣ “ኤሌክትሪክ”፣ “ኮሌጅ”፣ “አካዴሚ”፣ “ኤክስፐርት”፣ “ዲሬክተር” ፣"ክሊኒክ" የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ዘጠኝ 🦅

..... " ይገርማል! ግን እኔ እምልሽ ባለማወቄ አትታዘቢኝ ..... ፌስቱላ ሲባል ከወሊድ ጋር የተያያዘ ችግር እንደሆነ ምናምን አውቃለሁ። ግን ምን ማለት ነው ..... እንዲያው የህክምና ቋንቋ በማይገባው ሰው ቋንቋ ብታስረጂኝ "......👇👇👇
ክፍል ዘጠኝPage 2