ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ሶስት 🦅

........... ከልጅ ጋር መሆን እንዴት ሕይወት ያድሳል። ሁሉንም ነገር እነሱ የሚያዩበት እይታ ተስፋ ያዘለና እምቅ ኀይልን የሚለቅ ነው። ደስታም ሩቅ አይሆንም ። ጉጉትና ደግነት ፣ ፍቅርና ወዳጅነት በልጆች ዓለም ሳይበረዝና ሳይለዝዝ ይኖራል ። .............
.............. ልጅ ለማወቅ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አዋቂዎችን ለምን ይሆን የሚያውኳቸው። በተደጋጋሚ መልስ ያጣች ልጅ ደግሞ ቀስ በቀስ ያላዋቂ አዋቂ ወደ መሆን ትቀየርና እሷም መጠየቅ ታቆማለች ።ደርሳ የራሷ ልጅ ሲኖራት እሷም ሌላ ያላዋቂ ልጅ ታፈራለች ።በዚህ መሠረት በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ዕውቀትን የተራቡ ልጆችኝ ተቀብለን ዕውቀት ብለን በምንሰጣቸው የተዛባ መረጃ ተብትበናቸው ያላዋቂ አዋቂዎችን እናፈራለን ። እነሱንም እንደኛ ።
ያላዋቂ አዋቂነትም ተብትቦ ማኅበረሰብ በሚኮራበት ባህል በተባለ ባቡር ሁላችንንም ፍፃሜ ወደሌለው እንጦሮጦስ ይዞን ይወርዳል ። ጥቂት ደፋርና እምቢ ባይ በጥያቄ አስጨናቂ ከዚህ ወረርሽኝ የተረፉ ነፍሶች እስኪገኙ ። ማኅበረሰብን ካላዋቂ አዋቂነቱ የሚያባንኑ ። ነገርግን ልጆች አላዋቂዎች ስለሆኑ ማን ይሰማቸዋል ? አላዋቂ የሚባለው ጠያቂ ፣ አዋቂው ደግሞ የማይጠይቅ መሆኑ አንዱ የህይወት አሳዛኝ ገጽታ ሳይሆን አይቀርም። በርግጥም ድንቅ ነው !! ጥያቄ አቁመው በቁመት ስላደጉ ብቻ አዋቂ የሚል የክብር ስም በዕድሜያቸው ብቻ ለገፉ ህፃናት እንደ ካባ ሲደረብ።..............
ገፅ 100

~~~ይቀጥላል ~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ።
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም።
አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ ይያዛል።
ጥያቄውን ለመመለስ
ይህን👉 @R_e_a_d_e_rs ይጠቀሙ👍 and don't delete your answer since it helps us to count
መልካም እድል!!
መልዕክቱ ላልደረሳቸው አካፍሉ 👍
From
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🌼 ስነ-ግጥም 🌼

የሞላ ማድጋ ከጀርባ ካዘሉ ፤
ጎደሎ እንስራ ያዘሉት ተሻሉ ፤
ሙሉ ያዘሉቱ ከላይ ያፈሳሉ ፤
ጀርባቸውን ከታች ያበሰብሳሉ ፤
ጎደሎ ያዘሉ ምን ቢንገላጀጁ፣ ምን
ቢንገዋለሉ ፣
መሙላትን ይሻሉ ።
ምሉዕ ነን የሚሉ፣
እያደር ሲጎሉ፣ ይንቦጫቦጫሉ ።

ምንጭ:- የቀንድ አውጣ ኑሮ፣ 2002፣ የተሻሻለ
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም። አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ…»
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል አንድ 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

📚 ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡

📚 ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡

📚 1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡

📚 በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡

~~~ይቀጥላል~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም። አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ…»
​​በአርቲስት ተዘራ ለማ ሞት ከልባችን አዝነናል። ነፍሱን በገነት ያኑርልን።
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል ሁለት 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

☞☞ የጳጉሜን 5 ምስጢር
📚 አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡

📚 ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡

📚 ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ማግስተ ሰኞ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2012 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ማግስተ ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡

📚 በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል፡፡

~~~ይቀጥላል~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል ሶስት 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ
📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡

📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል፡፡

~~~ይቀጥላል~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም። አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ…»
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል አራት 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

☞☞ ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ
📚 የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡

📚 ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡

📚 ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡

📚 ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡

📚 በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

📚 ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
🌼
ለመጪው ዘመን ከቁጥር ሳንጎድል በሰላም በፍቅር ያድርሰን!

~~~ ተፈፀመ ~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ጷግሜን 6
የመጨረሻዋ የ2011 ቀንን ከተቀያየማችሁት ሰው ጋር ይቅርታ እንድትጠያየቁ፣ አሮጌውን ወደጎን እንድትጥሉ በቻናላችን ስም እንጠይቃለን!
የነገ ሰው ይበለን!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Readers_To_Know
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
​​አሸናፊ አግኝተናል! አሸናፊው በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር 15 ነጥብ አግኝቷል።
🗓 የዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ 🗓

ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::
ዕለት ፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ
የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::
ወር ፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::
ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀም 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና 5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::
ምንጭ – መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ 🌼
🌼ዮሐንስ በሰላም አደረሳችሁ 🌼
🌼 አደረሰን! 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😁 ለፈገግታ 😁

A: ሄሎ
B: ማን ልበል
A: ደውለሽ ማንልበል💁‍♂? ማን ብለሽ ነው የደወልሽው?
B: ሰማይ ቤት
A: ኦ! አዳም በአንቺ ምክንያት ከገነት ስለተባረረ እስቲ
ምድር ቤት አጠያይቂ
B: ኧረ ባክህ! ቆይ አንተ ማነህ?
A: ዲያቢሎስ 🧟‍♂
B: ለነገሩ ከሱ አትሻልም (ጥርቅም😳!)

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አራት 🦅

............ ሽታ ከሌሎቹ የስሜት ህዋሳቶቻችን ይልቅ ለአእምሮአችን በተለይ ስሜታችንን ለሚቆጣጠረው ክፍል እጅግ ቅርብ ነው ። ለዚህም ነው ጠረን ከፍቅርና ከፍርሀት ስሜቶቻችን ጋር ያለው ቁርኝት ዘመናት ያልሻረው ሐቅ የሆነው ። እንኳን በሰው በእንስሳውም ዓለም ጠረን ሀይለኛ የስሜት ቆስቋሽ ነው። የሽቶ መዐዛና የጽጌረዳ ለዛ የማይገዛው ማን አለ ? ክፉ ጠረንም ቢሆን ጉልበቱ ቀላል አይደለም ። ምራቅ የሚያዝረበርብ የምግብ ሽታ ፣ ስሜት የሚኮረኩር የፍቅረኛ መዐዛና ነፍስ ያላወቀን ሕፃን የሚያስፈነድቀውን የእናት ጠረን የሚበልጥ ግን የለም።.................
ገፅ 111
........... ድኻ ድኻ የሚሆነው ገንዘብ ስለሌለው ሳይሆን ፣ ገንዘብን ከማሳደር ማውደም ስለሚቀናውም ነው። የድኻ ድኻነቱ ደስታውንና ኀዘኑን ፣ የትኛውንም ጠንካራ ስሜቱን ተቆጣጥሮ ከስሜቱ በላይ መኖር አለመቻሉም ነው ። ከለመደው የዕጦት ኑሮ ላለመውጣትም ይመስል ፣ ያገኛትን በአንድ ቀን ባለው ኃይል ከዘመድ ከጎረቤት ጋር ተባብሮ ያወድማታል ። ድሀ ብድር መውሰድና ፍቅር መስጠት አይፈራም ። ጥላቻና ሞትም ከድሃ ያን ያህል የራቁ ነገሮች ናቸው ማለት አይደለም ። ብዙ መገዳደልና መደባደብም እዚህ ይበዛል ። ድኽነት የተወሳሰበ ያስተሳሰብና የአኗኗር ውጤት ነው። የማይዳሰስ ግን በቀላሉ የማይገፋ ..... አሳዛኝ ሰዎች የሰፈሩበት የመከራ ተራራ ነው። ..............
ገፅ 119

~~~ይቀጥላል ~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ።
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
Forwarded from Quality ButtonSCAM
Horoscope and zodiac information
የሕብራተ-ክዋክብት በ12 ይከፈላል ።
የመጀመሪያዉ የzodiac ምልክት Aeris ይባላል ።ብዙዎቹ "the infant" ይሉታል። አንዳነዶች ደግሞ ጠቦቱ እና ወጠጤው በግ ሲሉ ፀበኛ አና ተዋጊ መሆኑን ለመግለፅ ይጠቀሙታል። የኤሪስ የልደት ሰንጠረዥ ከመጋቢት 12-ሚያዝያ-12 ድረስ የሚቆይ ነው ።
እነዚንና የመሳሰሉትን ለማየት👇