Read Revive
342 subscribers
131 photos
5 files
49 links
Reviving the reading culture – one book, one youth, one story at a time.

Reading. Sharing. Connecting
Download Telegram
Read Revive pinned «ስንቶቻችን አንብበን ጨረስን?»
የግድግዳው ላይ ጽሑፎችን ተከትለን የምናደርገው ጉዞ ቀጥሏል •••

[5]

«እየተበላሸ እንደሆን እንዲገለጽልህ፥ ዘወትር አይቡን አሽትት!»

አይቡ ሲበላሽና ሲወሰድ፥ እኛ ከዓይቡ በቅርብ ርቀት ላይ ነበርን። ነገር ግን አላስተዋልንም!... ለምን ቢባል... አይቡን በንቃት በመከታተል ላይ ስላልነበርን ነው። አይቡእየተበላሸ እንደሆነ እኔዲገለጽልን፥ አይቡን ማሽተት ግድ ነበር...

[6]

«በአዲስ አቅጣጫ መንቀሳቀስ አዲስ አይብ ለማግኘት ይረዳል!»

አይቡን ወደማጣት ያደረሰን ሁኔታ ሳይቀየር፥ አይቡን ስለማግኘት ማሰባችን አይገርምም?! ... አይቡን ለማግኘት ወደ አይቡ መጓዝ ያስፈልገናል። ያላዋጣውን መንገዳችንን እንገምግም፥ አዲስ አቅጣጫ ካስፈለገን በተሰላ ድፍረት መራመዳችንን እንቀጥል። የ Haw (አሃ) ከ
አዲሱ መንገድ በርግጥም ይኼው ነበርና...

[7]

«ፍራቻን ተሻግሮ ማለፍ ደስተኛና ነጻ ያደርጋል!»

የተሳሰርንበት ምክንያት አልባ ፍርሃት ስንት አይቦችን ከማግኘት ከልክሎን ይሆን?! የፈለግነውን ባለማግኘታችን የምናስተናግደው ደስታ ማጣት የፍርሃታችን ውጤት ቢሆንስ?!... ፍርሃት እስር ቤት ነው፥ እርሱን በመሻገር ውስጥ ነጻነት አለ።... እስኪ ደግሞ ሳንፈራ እንሞክረው!

[8]

«ከማግኘቴ በፊትም ቢሆን አዲሱን አይብ ሳጣጥመው በምናቤ መቅረጼ ወደ አዲሱ አይብ ይመራኛል!»

ምናብ... አይባችንን የማግኘት ቁልፍ! መለስ ብለን ራሳችንን እንመልከት። አይቡን ባጣንም ሆነ ባገኘን ጊዜ፥ አዕምሯችን ምን ላይ ነው?! የሚታሰበን፤ የምንፈልገው ወይስ ባልሆነብን የምንለው?! የምናብ ዓለምን መቆጣጠር፤ በራስ ላይ ያለን ቁጥጥር ይጠቁማል። ወደ አይባችን እንቅረብ ... በምናብ ... ከዚያም በዕውን!

የሆነው ሆኖ ግን ••• ወደ አይቡ መጓዛችንን ቀጥለናል!!!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
🔥2
🧀📚 Every Reader Sees a Different Story.

The same pages. The same characters. The same journey.
Yet no two readers walk away with the same lessons.

In 4 days, we'll come together to hear the perspectives, reflections, and insights that made this book meaningful in different ways.

One conversation might change the way you see the entire book.

📅 4 days to go.
See you at the Read & Revive Book Review!


Date: Sunday, July 19
Time: Morning, 02:30 – 05:00 LT
Location: Tor Hayloch, Ethiopian Muslim Youth Council (EMYC) Office


Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
🔥2
"What would you do if you weren't afraid?"


Perhaps the most powerful question in Who Moved My Cheese? isn't asked by the characters—it's asked of us.
In 3 days, let's explore that question together.

🧡 See you at the Read & Revive Book Review

Date: Sunday, July 19
Time: Morning, 02:30 – 05:00 LT
Location: Tor Hayloch, Ethiopian Muslim Youth Council (EMYC) Office

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
3🥰1
🧀 Every perspective matters.
Every voice adds value
.

Interested in being part of our community-led review session?

Complete the short form below👇

Click here to participate

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
👍21
የጉዞው መጨረሻ •••

[9]

«የድሮ አይብን ቶሎ ከረሳህ ሳይረፍድብህ አዲስ አይብ ታገኛለህ!»

ስንቶቻችን ትላንት ላይ ቆመናል?! የነበረንንና ያጣነውን አይብ እያሰብን ስንት ዛሬያችንና አዲስ አይብ የማግኘት ተስፋችን ባክኖ ቀርቷል?! ማለፍ... መራመድ... መቀጠል... ባለመቻላችን ስንት ዕድል አስመልጠናል። ከህይወት በብዙ አረፈድን... በድሮ የአይቡ ሃሳብ፥ አዲስ አይብ ይገኝ ይመስል... ! አሁን እንደ Haw (አሃ) አንድ የገባን ዕውነት አለ። መሻገር... ወደ ብሩህ ነገ!

[10]

«ወሰብሳባው ቦታ ውስጥ አይብ መፈለግ አይብ በሌለበት ሁናቴ ውስጥ ከመቀመጥ በላይ አደጋ የለውም!»

እጅግ ከሚማርኩ የHaw (አሃ) መረዳቶች ውስጥ አንዱ ይህ ነው። የቱ አደጋ እንደሚብስ መረዳት! እርግጥ ውስብስቡ መንገድ አደገኛ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አይቡ ተወስዶ ዝም ብሎ መቀመጥ ይበልጥ አደገኛው ነገር ነው። እኛ የቱን አደጋ መረጥን?! በመፈለግ ውስጥ ያለን አደጋ ወይስ በመቀመጥ ውስጥ ያለውን አደጋ?!... ላስተዋለ ሰው፤ አይቡን ማጣትን ያህል አደጋ የለም!

[11]

«የድሮ አስተሳሰቦች አዲስ አይብ አያስገኙም!»

ያ... የበፊቱ... አይባችንን የነጠቀን አስተሳሰብ፥ አዲስ አይብ እንዲሰጠን እንጠብቃለንን?! ነባር አካሄድ ነባር ውጤትን እንጂ ሌላ ምን ይወልድና?!... አሁን ደግሞ እስኪ ቀና እንበል። ከነበርንበት ሁኔታ የሚያወጡ ሃሳቦችን ለማስተናገድ አዕምሯችንን ክፍት እናድርግ። አዲስ አይብ፥ አዲስ ሃሳብን ይፈልጋል፡ መጓዝ... ወደነገ... በአዲስ አስተሳሰብ... ወደ አዲሱ አይብ! ... ከሁሉም በፊት፦ አዲስ አይብን የሚያስገኝ አዲስ አስተሳሰብን ከደገነባ ሰውነት!

[12]

«አዲስ አይብ አግኝተህ እንደምትደሰትበት ስታውቅ አካሄድህን ትለውጣለህ!»

ስለመጣንበት መንገድ ምን እናስባለን?! ስለምንሄድበትስ?!... አይቡን ለመፈለግ በውስብስቡ መንገድ ላይ መጓዝ ምንም ያህል አድካሚ ቢሆን አይቡን በማግኘት ውስጥ ያለውን እውነተኛ ደስታ ስናስበው፥ የመንገዱ አስቸጋሪነት በርግጥም ቀለል ያለ መልክን ይይዛል። የተለመደው የስንፍናና የመሰላቸት አካሄድ፥ አዲሱን አይብ የማግኘትን ደስታ በማወቅ ውስጥ ይቀየራል። ለአይቡ መጓዝ፥ አይቡን ለማግኘት ተገቢ ነው። ስለዘላቂ ደስታችን አካሄዳችንን እንቀይር።

[13]

«ጥቃቅን ለውጦች ሲከሰቱ ልብ ማለቱ፥ በኋላ ላይ ትልቅ ለውጥ ሲመጣ ለመቀበል ያስችላል!»

ያስደነገጠን ድንገተኛ ለውጥ አለ አይደል?! ዱብ ዕዳ የሆነብን፥ ሳይታሰብ የህይወት አቅጣጫችንን የቀየረው?! - ከምን የመጣ ይመስለናል?! የመጀመሪያዎቹን ጥቃቅን ለውጦች ካለማስተዋል ነው። እኛ ይመስለናል እንጂ፥ ያጋጠመን ለውጥ ድንገተኛ አይደለም። ማስተዋል ብንችል፥ የሚታዩ ትንንሽ ለውጦች በየቦታው ነበሩ። የተበላሸውን አይብ ማሽተት በመቻል ውስጥ፥ ለውጡን በግልጽ መመልከት ነበር። ማስተዋል! ማስተዋል!! ማስተዋል!!!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
👌3🥰1
🧀 The countdown continues...

Just 2 days until we come together to reflect, share, and uncover the lessons hidden between the pages of Who Moved My Cheese?

The journey doesn't end with the last page—it comes alive in the conversation.


📚 See you in 2 days!

Date: Sunday, July 19
Time: Morning, 02:30 – 05:00 LT
Location: Tor Hayloch, Ethiopian Muslim Youth Council (EMYC) Office


Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
👏3🤗1
የግድግዳው ላይ ጽሁፍ

ለውጥ አይቀርም!

አይቡን ሁሌም እንዳንቀሳቀሱት ነው!

ለውጥ እንደሚመጣ ጠብቅ!

አይቡ ለሚንቀሳቀስበት ቀን ሁሌም ዝግጁ ሁን!

ለውጥን ተከታተል!

እየተበላሸ እየሄደ እንደሆነ እንድታውቅ አይቡን ሁሌም አሽትተው!

ለውጥ ሲመጣ ቶሎ ተላመድ!

የድሮ አይብን በፍጥነት በረሳህ ቁጥር አዲስ አይብ ሳይረፍድብህ ታገኛለህ!

ተለወጥ!

ከአይቡ ጋር ተንቀሳቀስ!

በለውጥ ተደሰት!

አዲሱ ጉዞህን ተደሰትበትና በአዲስ አይብ እርካታህን አጣጥም!

ዳግም ለመለወጥ እና ለውጡን ለማጣጣም ሁሌም ዝግጁ ሆነህ ጠብቅ!

አይቡን ሁሌም እንዳንቀሳቀሱት ነው!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
3🔥2
Read Revive
የግድግዳው ላይ ጽሁፍ ለውጥ አይቀርም! አይቡን ሁሌም እንዳንቀሳቀሱት ነው! ለውጥ እንደሚመጣ ጠብቅ! አይቡ ለሚንቀሳቀስበት ቀን ሁሌም ዝግጁ ሁን! ለውጥን ተከታተል! እየተበላሸ እየሄደ እንደሆነ እንድታውቅ አይቡን ሁሌም አሽትተው! ለውጥ ሲመጣ ቶሎ ተላመድ! የድሮ አይብን በፍጥነት በረሳህ ቁጥር አዲስ አይብ ሳይረፍድብህ ታገኛለህ! ተለወጥ! ከአይቡ ጋር ተንቀሳቀስ! በለውጥ ተደሰት! አዲሱ…
Haw (አሃ) ወደ አዲሱ አይብ ባደረገው ጉዞ ላይ፥ በውስብስቡ መንገድ ውስጥ የቀሰማቸውን አያሌ እውቀቶቾ በዚህ መልኩ አጠቃልሎ አቅርቦልናል።... እኛም አመስግነናል።... ወደ አይቡ የተደረገው ጉዞ በርግጥም አስደሳች ነበር!!!

የሆነው ሆኖ ግን ••• አይቡን ፈልጎ የማግኘቱ ጉዞ እጅጉን ባለብዙ ትርጉም ሆኖ አግኝተነዋል።

Haw (አሃ) አብቅቷል!!!
እኛ ደግሞ ልንጀምር ነው ••• !!!

የረጅሙን ግን አስደሳቹንና አዲሱን አይብ ለማግኘት ወደምንችልበት ማንነት የሚቀይረንን ጉዞ በይፋ ለማስጀመር ••• በመጪው እሁድ - ሐምሌ 12 - 2018 ዓ.ል ••• መቃጠሪያችንን ጦርሃይሎች ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ቢሮ ውስጥ አድርገናል!

ከጠዋቱ 02፡30 ላይ...

ጥያቄዎቻችንን፣
ሃሳቦቻችንን፣
ትችቶቻችንን፣
የወሰድናቸውን ትምህርቶች፣
የሚወክሉንን ገጸ ባህሪያት፣
ያለፍንባቸውን መንገዶች... ይዘን እንገናኝ።

ጉዟችን በርግጥም ዋጋ ይኖረዋል።

መጽሐፉንን ያነበበና መውሰድ ያለበትን ትምህርት የወሰደ ሰው ያረፍዳል ብለን አንጠረጥርም!!!

የእሁድ ሰው ይበለን!!!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
2🔥2
📖 Have thoughts about Who Moved My Cheese? We'd love to hear them!

Whether it's a lesson that stayed with you, a favorite quote, or a personal reflection, your perspective could inspire someone else.

Register through the form below and be part of our community-led review session.

Click here to register

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
የእሁድ ቀጠሯችን እንደተጠበቀ ነው አይደል?!

እስኪ በተከታዩ ፎርም አረጋግጡልን።

ይህንን ይጫኑ

"አይቤን ማን ወሰደው?" በተሰኘው ተወዳጅ መጽሐፍ ዙሪያ ያላችሁን ሃሳብ፣ አስተያየት... ከታሪኩ የቀሰማችሁትን ትምህርት፣ የወደዳችሁትን ጥቅስ፣ የግል ምልከታችሁንና ሌሎች ቢሰሙት መልካም ነው ብላችሁ የምታስቧቸውን ነገሮች ሁሉ ለመስማት እጅግ ጓጉተናል።

ይመዝገቡ!
በሰዓቱ ይገኙ!!
የጋራ ጉዟችን አካል ይሁኑ!!!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
1🔥1
🧀📚 Tomorrow is the day!!

Every page has led to this moment.
Tomorrow, we'll come together to reflect on Who Moved My Cheese?, exchange perspectives, and celebrate the journey we've shared through reading.

Whether you finished the book or are still making your way through it, we'd love to have you with us.

If you'd like to participate in the discussion, please register using the link below:
[ https://forms.gle/Gmscb4ev1PK1UtPu5 ]

Only 1 day to go!
We can't wait to see you there!!


Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
4
🧀📚 The deadline is over and it's finally happening tomorrow!!

Whether you finished the book or are still making your way through it, we'd love to have you with us.

If you'd like to participate in the discussion, please register using the link below:
[ https://forms.gle/Gmscb4ev1PK1UtPu5 ]

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
🔥21🥰1
🧀📚 TODAY'S THE DAY! 🎉


The wait is over!!

Today, we gather to celebrate our reading journey through Who Moved My Cheese?—a journey of reflection, growth, and meaningful conversations.

Come ready to:
• Share your insights
• Hear fresh perspectives
• Connect with fellow readers
• Reflect on the lessons that stayed with you

📍 Venue: Tor Hayloch, Ethiopian Muslim Youth Council (EMYC) Office

🕒 Time: Morning, 02:30 – 05:00 LT
🗺Location Map: https://maps.app.goo.gl/B5P1ov5dQ7gmW9HHA

We can't wait to welcome you all!
See you there, in shaa Allah!
🔥53
ከላይ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተመልከቱት!

ላነበባችሁ ክለሳ!
ላላነበባችሁ ጥቅል መልዕክቱን ለመረዳት!
Who is ready for our next book?🔥🔥

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
🔥15🥰3👏1🫡1
📚 Our Who Moved My Cheese? Review Session was an inspiring reminder that every book has the power to change the way we think.

Led by Huda from the Anbabi Team, the session brought together meaningful reflections, engaging small-group discussions, and practical lessons on embracing change, letting go, and moving forward with confidence.

This is what Read & Revive is all about—turning books into conversations, conversations into insights, and insights into action.

📖 Stay tuned for our next book!

Anbabi  Read & Revive
Reading Sharing Connecting
5🔥5👎1🥰1🤔1