Estifanos Dereje
994 subscribers
407 photos
6 videos
4 files
22 links
"ማስተማርንም ሆነ መማርን እድሜ አይወስናቸውም፣ ዕውቀት በማንም ሊሰራጭ፣ ለማንም ሊበረከት ይችላል፡ በዘመናችን ቴክኒካዊ ክህሎት ከታች ወደ ላይ ነው የሚፈሰው። "
እጓለ ገብረ ዮሐንስ ዶ/ር
@RW16T
+251912087083
Download Telegram
Forwarded from Kebena House
አራተኛው ዙር የሐገር ፍቅር ፕሮግራም በጣም ውብ ነበር። ታላቅ የኪነጥበብ ሰው አቶ አገኘሁ አዳነ ብዙ የገዘፉ ሐሳቦችንና የህይወት ልምዱን አካፍሎናል። ካነሳቸው ነጥቦች መሀከል:-

# የሐገር ፍቅር ማለት ኢንቨስትመንት ማለት ነው። በእያንዳንዱ ሰው ስራ፣ ትዳር፣ ሐሳብ፣ ኑሮ፣ ... ወዘተ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የሐገር ፍቅርን ያመጣል።

# የኢንቨስትመንት ዋነኛ መሳሪያ ትርክት (Narration) ነው። ትርክትን መቆጣጠር ቢቻል እጅግ ትልቅ ኢንቨስትመንት ማድረግ ያቻላል።

# የሐገር ፍቅር ስሜት እንደዘመኑ የሚቀያየርና አይነቱ ብዙ አይነት ሊሆን ይችላል። ዘመኑ የሚፈልገው የኢንቨስትመንት አይነት ሐገር ፍቅርን ይወስናል። ይህ ደግሞ የሀሳቡ ባህሪው ሳይሆን አይቀርም።

# የሐገር ፍቅር ለመግለጽ ከኢንቨስትመንት የተሻለ ቃል ወይም ገለጻ ላገኝለት አልችልም። ኢንቨስትመንቱ እንዳይከስርና ተገቢውን ሀብት እየተጠቀመ መሆኑን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብሏል።

አቶ አገኘሁ አዳነን በቀበና ቤት ስም በጣም እናመሰግናለን።

ለተፈናቀሉ ዜጎች ለተደረገው ገቢ ማሰባሰቢያ ላደረጋችሁት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።

በ5ኛ ዙር የሐገር ፍቅር ዝግጅት እስከምንገናኝ ቸር ያቆየን!

ለበለጠ መረጃ
Info@kebenahouse.com
+251903048787
@kebenahouse
Forwarded from Kebena House