Estifanos Dereje
994 subscribers
407 photos
6 videos
4 files
22 links
"ማስተማርንም ሆነ መማርን እድሜ አይወስናቸውም፣ ዕውቀት በማንም ሊሰራጭ፣ ለማንም ሊበረከት ይችላል፡ በዘመናችን ቴክኒካዊ ክህሎት ከታች ወደ ላይ ነው የሚፈሰው። "
እጓለ ገብረ ዮሐንስ ዶ/ር
@RW16T
+251912087083
Download Telegram
ሁለተኛው የሐገር ፍቅር ፕሮግራም እጅግ ውብ ሆኖ አልፏል:: ጸሐፊና ደራሲ ህይወት እምሻውን በጣም እናመሰግናለን:: ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን የያዘ ልዩ ንግግር (Presentation) እና ውይይት( Discussion with questions ) ነበር:: እንግዶቻችንም እንዲሁ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን:: ደራሲና ጸሐፊ ህይወት እምሻው ከተለየ እይታ(Angle) የሐገር ፍቅርን ሀሳብ አሳይታናለች:: 1:45 የፈጀ ዝግጅት ነበር:: ህይወት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በፖለቲካ ሳይንስ( Political Science) ሁለተኛ ዲግሪዋን በአለም አቀፍ ግንኙነት ( International Relations) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጨርሳለች::

ደራሲ ህይወት እምሻው: 'ባርቾ': 'ማታ ማታ' እና 'ፍቅፋቂ' ለአንባቢ ያበቃቻቸው ስራዎች ናቸው:: በተለያዩ የግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በሀላፊነት አገልግላለች : አሁንም እንዲሁ አገርና ህዝብ የሚጠቅም ስራ እየሰራች ትገኛለች:: ህይወት Save the Children በተባለው NGO ድርጅት ግንኙነት ክፍል (Communication office) ለ16 ዓመታት የሰራችና አሁንም እየሰራች ሲሆን ከስራዋ: ከጽሁፍ ሙያዋ: ከሙዚቃ እውቀትና ምርጫዋ ጋር ተያይዞ ሰፊ ልምድና እውቀት አካፍላናለች:: ደራሲና ጸሀፊ ሐይወት እምሻው ካነሳቻቸው ዋና ዋና ሀሳቦች መሀከል የሚከተሉት ይገኙበታል::

''የሐገር ፍቅር በሙዚቃ ውስጥ ያለው ጉልበት: ትስስርና ትርክት:: ሙዚቃዎቹ አደራን: ቁጭትን: ወኔን: መውደድን: አብሮ መስራትን: ሀገር መከላከልን ይመለከታሉ::''

''አብዛኛው የሙዚቃ ስራዎች ግን መከላከልን ትኩረት ያደርጋሉ: ስለዚህ መሻሻል(መራመድ) ሊታይባቸው ይገባል::''

''የሐገር ፍቅር በተሻለ መንገድ እንዲራመድ እንዲተረጎም ሁለት መንግዶች ቢኖሩ መልካም ነው:: እነርሱም:- 'አገራዊ አጀንዳ' (ህዳሴ ግድብ: ኦሎምፒክ: ...ወዘተ እና 'ብሔራዊ አገልግሎት' ናቸው''

''የሐገር ፍቅር ማለት አገርን ሁልጊዜም መግስትን ደግሞ በተገቢው መንገድ መደገፍ ነው::''

''ሐገርና መንግስትን ለይቶ ማየት ተገቢ ነው::''

''የኢትዮጵያ ሕዝብ ብልህ ነው''

''ኢትዮጽያ አንድ ነገር አላት''

ህይወት እምሻውን እጅግ በጣም እናመሰግናለን!

ይህ ፕሮግራም በየወሩ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅና ቀጣይነት ያለው ነው::

ጥያቄ አስተያየቶቻችሁን ጻፉልን!

መልካም ቀን!
የቀበና ቤት ቻናልን ይቀላቀሉ! በየጊዜው ያሉ መረጃዎችንና ፕሮግራሞችን ለማየት ይችላሉ::

https://t.me/Qebena
የቀበና ቤት ኢንስታግራም (Instagram) በዚህ ሊንክ ያገኛሉ።

Follow us on Instagram & Don't forget to share.
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአሜሪካ ሀገር ጉብኝታቸው:: - ታሪክ ማለት በጽሁፍ ያለ የተነገረ (አፈታሪክ) ብቻ ሳይሆን ዜማው: ፎቶው: ዕቃዎቹ: ትዝታው ... ነውና ለማስታወስ ያህል ይሄንን አካፍለናል::

አገራችን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን! ካለንበት ችግርም እንወጣ ዘንድ ሰላም: ፍቅር አንድነት ይስጠን!
🚩Assisting sellers in how to best promote their properties to attract advantageous offers

🚩Advertising properties through a variety of marketing techniques

Please join though the link below.

https://t.me/addisassets
Estifanos Dereje
https://forms.gle/TgZaLaPpijp3YB5eA
እንዴት አረፈዳችሁ!

ሶስተኛው የሐገር ፍቅር ልዩ ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 15 ነው። እንግዳችን ደግሞ የአሀዱ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ዋና ሥራአስኪያጅ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ነው።

እእዳያመልጥዎ!