ቄራ ሰላም መስጂድ kera Selam Mesjid
773 subscribers
411 photos
54 videos
9 files
120 links
አህለን

       ይህ የቄራ ሰላም መስጂድ ቻናል ነው

🔸ስለ መስጂዱ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች መረጃ
🔸መልዕክት አዘል አጫጭር ፅሁፎች
🔸የተለያዩ የድምፅና የምስል ፕሮግራሞች


          💎ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን💎
Download Telegram
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
በስራ ላይ
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የወንድማችን ሙባረክ ኽይሩ ወይም የዳሩሰላም የዳእዋ አስተባባሪ (አስተዋዋቂ) እናት ለተከታታይ ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኺራ ሂደዋል
ቀብር ዝዋይ ከተማ ላይ የሚሆን ሲሆን መሄድ የምንችል ስዎች በጊዜ ብንነሳ
Forwarded from ቄራ ሰላም መስጂድ ዳሩሰላም ዛሬ በእግርህ ስትሄድ ከከበደህ ወደ መስጂድ መምጣት ነገ በ 4 ሰዉ ጀናዛ ተብለህ ትመጣለህ
''እኔ ለመስጅዴ ፅዳትና ውበት ባለቤት ነኝ'' በሚል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

በዛሬው ቀን ግንቦት 18/2016 ዓ/ል ከፈጅር ሰላት በኋላ በዳሩ ሰላም ዳዕዋ ተቋም አስተባባሪነት የመስጅዱን ግቢ የማፅዳት ስራ ተከናውኗል። ይህንንም የፅዳት ዘመቻ በየወሩ ለማስቀጠል ተቋሙ ስራውን በዛሬው እለት ጀምሯል።

ስለሆነም የመስጅዱን ውስጣዊና ውጫዊ ፅዳቱን ለማስቀጠል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንዲሳተፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ግንቦት 18/2016 ዓ/ል
ዳሩ ሰላም ዳዕዋ ተቋም
ቄራ ሰላም መስጅድ
ማሳሰቢያ :- 1, ተማሪዎች ወደ ቲቶር ሲመጡ ማስታወሻ ደብተርና እስክሪፕቶ መያዝ 2,  ተማሪዎች ከቲቶሩ በፊት ዘወትር ከሰኞ- አርብ ከ10:00-12:00 ቤተ-መፅሀፍ መጥቶ መመዝገብ 3, በቲቶሩ እለት በጊዜና በሰአቱ ቦታው መገኘት
Audio
ነገን ማሥቀደም.m4a
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Eliyah Mahmoud
መተበይ (ego)
…..

ዛሬ ላይ እጅግ ከተበተቡን በሽታዎች መካከል ለራስ የሚሰጥ አጓጉል ቦታ ኣንዱ ነው፡፡ ዕውነት ነው ሰው ራሱን ከማንም በላይ ይወዳል፡፡ ለዛም ነው ነገ በትንሳኤ ቀን ወንድም ከወንድሙ ከእናቱና ከአባቱ እንዲኹም ከባለቤቱ የሚሸሸው፡፡ ምድር ላይ ግን አንድ ሙስሊም የመተበይ ችግር ውስጥ እንዲኖር ኢስላም በቀጥታም በተዘዋዋሪም ይከለክላል፡፡

የስነ-ልቦና ልሒቃን አንድ ሰው ለራሱ እጅግ ትልቅ ቦታ የመስጠት ችግር ውስጥ ከወደቀ (ego problem) የሚያሳያቸው ምልክቶች እንዳሉ ይገራሉ፡፡ ለአብነት ያህል እነዚህን መጥቀስ ይቻላል፡፡

1ኛ) ትችትን አለማስተናገድ (inability to accept criticism)
…….

በግዙፍ የመተበይ ችግር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች በነሱ ላይ ለሚነሱ ትችቶች ምንም ዓይነት ቦታ የላቸውም፡፡ ትችቶቹ ተገቢና ከራሳቸው ክፍተት የመነጩ እንኳ ቢኾኑ ለራሳቸው ምክንያት ከመስጠትና ተቺዎቹን በሌላ አግጣጫ ከመመልከት በዘለለ ትችቶቹን እንደ መልካም ግብዓት መጠቀም አይፈልጉም፡፡

ወዳጄ ልብ ይበሉ! ትችት በተለይ ደግሞ በትክክል ላለና ለተፈጠረ ስህተት ሲኾን ከተቺው በኩል የሚለገስ ስጦታ ነው፡፡ ኸሊፋው ዑመር (ረ.ዐ.) “ ነውሬን እንደ ስጦታ የለገሰኝ ሰው ኣላህ ይዘንለት” ይል እንደነበረ ያስታውሷል፡፡ ፈለጎቻችን ሰለፎች ክፍተቶቻቸው ሲነገራቸው እንደ ስጦታ ይቆጥሩት እንደነበር ላነበበ፣ ዛሬ እኛ ምን ኾነን ነው በዚህ ልክ ራሳችንን ፍጹማን ያደረግነው? ማለቱ አይቀርም፡፡ ልቦና ካለው፡፡

በግሌ እምነት ከሌላቸው አውሮጳውያን የተማርኹት የኾነ ፕረዘንቴሽን ቢቀርብና በዛ ላይ ሒስ (ኮሜንት) ቢሰጥ ምንም እንኳ የተሰጠው ሒስ አግባብነት እንኳ ባይኖረው በተሰጠው ሒስ ላይ መልስ አይሰጡም፤ተማሪዎችም መልስ እንዳይሰጡ ይከለክላሉ፡፡

2ኛ) ቦታ መፈለግ (validation)
….

ግዙፍ መተበይ ውስጥ ያሉ ኣካላት በሚፈጽሟቸው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ዋጋ ማውጣትን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በየትኛውም ስሌት ለነርሱ ቦታ እንዲሰጡ ለማድረግ ስራዎቻቸውን አጉልተው ማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ የዕውቅና አባዜ ውስጥ ስለሚቆዩ ምኞታቸውን የሚያመክን የትኛውንም ሐሳብ መስማት አይፈልጉም፡፡ ይልቁንም በቆሙበት ኮረብታ ላይ ኹሉ ማንነታቸውን ማወጅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰለፎቻችን ራሳቸውን ይደብቁ እንደ ነበር ታሪኮቻቸው ዛሬም ሕያው ኾነው ይናገራሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሰሞኑን ሰሒሕ ሙስሊም ላይ ያለ ኣንድ ድንቅ ታሪክ በድምጽ ይዤ እቀርባለኹ፡፡ ኢንሻኣላህ!!!

3ኛ) የመወደድ አባዜ (Grandiosity)
….

የክፉ መተበይ ባለቤቶች ሰው ኹሉ በሚሰሩት ነገር ሊወዳቸው እንደሚገባ ያምናሉ፡፡ እነሱ የሰሩትን ሰው ኹሉ እንዲያይና እንዲስማማባት ይፈልጋሉ፡፡ አቤት ምን ዓይነት በሽታ ነው ጃል!? ነብያት እንኳ በኹሉም ሰው ዘንድ አልተወደዱም፤ በሕዝቦቻቸው የተገደሉም አሉ፡፡

ላይ ከጠቀስናቸው መገለጫዎች ኹሉ ይህ ሶስተኛው በሽታ እጅግ አደገኛ እንደኾነ ማስተዋል ያሻል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በሌሎች እምብዛም ተቀባይነትን ካጡ ራሳቸውን እስከማጥፋት ይደርሳሉና፡፡
…..

ወዳጄ ከዘረዝርናቸው ሶስት መሰረታዊ ችግሮች ምን ያሕሉ በኔ ላይ አለ የሚለውን ለርሶ ተውኹ፡፡ ቸር እንሰንብት!!!
https://t.me/E_M_ahmoud
በዚህ አመት ሐጅ ላልተሳካለት
~

ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–


★ በዐረፋ መቆም ላልቻለ ከአላህ ወሰኖች ዘንድ ይቁም።

★ በሙዝደሊፋ ማደር ላልቻለ ወደ አላህ ያቃርበው ዘንድ ለትእዛዙ ይደር።

★ ሀድዩን ሚና ላይ ማረድ ያልቻለ ከምኞቱ ይደርስ ዘንድ ስሜቱን ይረድ።

★እሩቅ በመሆኑ ቤቱ (በይተል ሐራም) መድረስ ያልቻለ የቤቱን ባለቤት ያስብ። ወደሱ ከደም ጋኑ የቀረበ ነውና።"


(ለጧኢፉል መዓሪፍ: 633)
ማሻአላህ ቲቸር ነስረዲን በማስተማር ላይ

ኢስላምን በተሰጠህ ኒእማ መርዳት እጅግ ወሳኝ ሀላፊነትን መወጣት እንደሆነ አይዘንጉ
በቄራ ሰላም መስጂድ ኢቅራ ቤተ-መፅሀፍ ለ12ኛ ተፈታኞች በEnglish ት/ት በዛሬ እለት የተሰጠ ቲቶር
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
አስደሳች ዜና ለክልላዊና ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
ኢቅራ ቤተ-መፅሀፍ ለ8ኛ ክልላዊ እና ለ12ኛ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ይረዳል እና ያግዛል ያለው የቲቶር ፕሮግራም በብቁ መምህራን መስጠት ጀምሯል፡፡ ለበለጠ መረጃ ማስታወቂያውን ማንበብ ይቻላል!