Purity Tube
10.7K subscribers
133 photos
22 videos
33 files
85 links
መፅሀፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያላቸው
👉 የስነ-ፆታ (sexual )
👉 ወሲባዊ ንፅህና
👉 የእጮኝነት
👉 የትዳር
👉 ወጣት ተኮር ጉዳዮች ይዳሰሳሉ
We discuss sexual , family and relationship issues from biblical point of view

Contact us @Appeal4purity_bot
💯 #ቅድስና_ለእግዚአብሔር 💯
Download Telegram
Purity Tube pinned a file
#ወቅታዊና_ጠቃሚ_ምክር ወደ ዩኒቨርስቲ ለምትገቡ ተማሪዎች

👉ዩኒቨርስቲ ማለት የለውጥ ቱቦ (a vessel of change ) ነው፡፡

💢በብረት ማቅለጫ በአንደኛው ጫፍ ውስጥ የገባ ማንኛውም አይነት ቅርፅ የነበረው ብረት በሌላኛው ጫፍ ሲወጣ ቀድሞ የነበረውን ቅርፅ ለቆ ፈሳሽ ሆኖ እንደሚወጣ ሁሉ ዛሬ ዩኒቨርስቲ ገብታችሁ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ተመርቃችሁ ስትወጡ ዛሬ ላይ ያላችሁን ማንነት ይዛችሁ እንደማትወጡ እወቁ

👉ለውጥ ስንል ሁለት አይነት ለውጦች ናቸው
󾠮 አዎንታዊ Positive
󾠯 አሉታዊ Negative

ሁለቱም ለውጦች እንዲከሰቱ ከኋላ የሆነ አምጪ ሃይል (Driving Force) አላቸው፡፡

💢አሉታዊው ለውጥ ከሚያመጡ ሃይላት በዋናነት የሚጠቀሱት
1)የአቻ ግፊት (peer pressure) እና
2)'ነፃነት' (freedom) ወይም ከቤተሰብ ተፅእኖ ውጪ መሆን ናቸው፡፡

💢አዎንታዊውን ለውጥ የሚያመጣው በዋናነት መንፈሳዊ ህብረት ነው፡፡
ይህም በፌሎሺፕ መሳተፍና
በsmall teams ውስጥ መሳተፍ ናቸው፡፡

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 133)
----------
1፤ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

2፤ ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።

3፤ በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።

💯ዛሬ ላይ በሱስና በተለያዩ የህይወት ዝቅጠት ውስጥ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የኋላ ታሪክ ብታጠኑ አብዛኞቹ ጊቢ ከመግባታቸው በፊት "ጨዋማ ከእሱ ወዲያ የለም" የተባለላቸው ናቸው፡፡

💯ለውጥ የማይቀር ነው፡፡
💯አለመለወጥ ምርጫችሁ አይደለም፡፡ 💯የለውጡ አይነት ግን የእናንተ ምርጫ ነው፡፡

#ትክክለኛውን_ምረጡ👍

@Appeal4Purity
@Appeal4Purity
👉👉ውብና ልዩ👈👈

󾠬አስቀያሚ የሚባል የጣት አሻራ የለም
👉የጣት አሻራ ልዩ ነው ተመሳሳይም የለውም፡፡
ይህ አያስደንቅም

💢አስቡት ከአዳምና ሄዋን ጀምሮ እስካሁን ስንት ሰው በምድር ላይ ኗሯል ቁጥር የለውም፡፡

👉ሁላችንም ደግሞ የተለያየ የጣት አሻራ ነው ያለን፡፡ ማለትም ያንተን ወይም ያንቺን አይነት የጣት አሻራ ያለው ሰው ኖሮ አያውቅም ወደፊትም አይኖርም፡፡

ልክ እንደ ጣት አሻራ ሁሉ ሁለት አንድ አይነት ትዳር ሊኖር አይችልም፡፡

👉ሁሉም ትዳር ልዩ ነው የራሱ ብቻ የሆነ ውበትም አለው፡፡
እንደ ባለትዳር የኛ ስራ በትዳራችን እግዚአብሔር የሰጠውን ልዩ ውበት መፈለግ ነው፡፡
💢የራሳችንን ትዳር ልዩ ውበት ፈልገን ማግኘት ካልቻልን ትዳራችንን ከሌሎች ትዳሮች ጋር በማወዳደር ድብርትና መመሰቃቀል ይሰማናል፡፡

ደግሞም የእግዚአብሔርን አሰራር ተፈጥሮን ብቻ በማየት ምንያህል ብዝሃነት እንጂ አንድ ወጥ የሆነ አሰራር እንደማይከተል መረዳት እንችላለን🐦🐏🐢🐕🌱🍁፡፡

👉የኛ ስራ እግዚአብሔር የሰጠንን መፈለግና በእርሱም ደግሞ መደሰት ነው፡፡

" ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።"
(መዝሙረ ዳዊት 19:1)

#Married

@Appeal4purity
@Appeal4purity
ሴት የማገኝበት የተሻለው መንገድ


👤እንግዳ ፦ 26 አመቴ ነው እና ፆታዊ ስሜቴን መቆጣጠር አድክሞኛል፡፡ ከቤተክርስቲያናችን በጣም ደካማው ሰው እንደሆንኩ ነው ሚሰማኝ፡፡

ምንም እንኳን ያላገቡ ወንዶችም ሴቶችም በዚህ ዙሪያ ትግል እንዳለባቸው ባውቅም የእኔ በጣም የበዛ እንደሆነ ነው ሚሰማኝ፡፡

ስለዚህ ጥያቄዬ ይህ ነው ለትዳር የምሆነኝን ሴት የማገኝበት የተሻለው መንገድ ምንድነው?

A4P ፦ ዋው፤ ስለዚህ ጥያቄህ ይህ ነው ማለት ነው
👤እንግዳ፦ አዎ ምነው ምን አጠፋሁ?

A4P ፦ ጥያቄህ የሚመስለው ወደ ትዳር መግባትህ ከፆታዊ ሃጢያት እና ተያያዥ ሱሶች ነፃ ሚያወጣህ እንደሆነ ነው፡፡

👤እንግዳ ፦ አይደለም እንዴ?

A4P ፦ ቆይ የጠየቅከኝ እንዲገባህ በዚህ መልኩ ላስረዳህ

ጎረቤትህ ሲጋራ ማጨስ እንዲያቆም የጉንፋን ክትባት እንድትከተብ መጠየቅ እንደማለት ነው፡፡

በዚህ አረዳድ እንድትረዳው እፀልይልሃለው፡፡
ማለት እንዴት አንድ ሴት ወደ ህይወትህ ስለመጣች ህይወትህን ልታነፃው ትችላለች ? በፍፁም አትችልም

💯1ኛ ቆሮንቶስ 7፥2 ላይ አንዲትን ሴት ስላገባህ ከዝሙትና መሰል ሃጢያቶች ነፃ ትወጣለህ አይደለም የሚለው፡፡


በጊዜው የዝሙት ሃጢያት ስለነበረ ሁሉም ወንድ ከገዛ ሚስቱ ጋር ብቻ ሴትም ከባሏ ጋር ብቻ ወሲባዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚያስተምረው፡፡

ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 7፥1-2 ላይ በቆሮንጦሶ ቤተክርስቲያን ያሉ ያላገቡ ሰዎች ራሳቸውን ከዝሙት ስለጠበቁ እያበረታታ በተጨማሪም እንዲያገቡና ከሚስታቸው ጋር ፆታዊ ግንኙነት እንዲፈፅሙ እየመከረ ነው፡፡

👉እዚህ ቦታ ላይ ወሲብን ለመፈፀም ብቸኛውን የተቀደሰ መንገድ ትዳር መሆኑን እናያለን፡፡

🛑እንጂ "ካገባህ የዝሙትን ሃጢያት ሰንሰለት ትበጥሳለህ ፣ ፖርኖግራፊ ማየት ታቆማለህ፣ masturbation ትተዋለህ " ማለት አይደለም፡፡

💢ስለዚህ በጥንቃቄ አድምጠኝ
ፆታዊ ስሜትህ ከእግዚአብሔር የተሰጠህ አንደኛው ተፈጥሮህ ሲሆን በዚህ ተፈጥሮህም እንዴት ▶️በእግዚአብሔር መደገፍ ፣
▶️በእርሱና በትዕዛዛቱ መደሰት ፣
▶️በእርሱ ታምነህ ውጊያዎችህን ሁሉ ማሸነፍ ፣
▶️መልካም ባህሪያትን መላበስ እንደምትችል የምትማርበት ድንቅ ተፈጥሮህ ነው፡፡

👉ይህ ተፈጥሮህ ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል ጉዞህ ላይ ጠላትህ ሳይሆን ረዳትህ ነው፡፡

👉ስለዚህ ይህን ስሜትህ ዲያቢሎስ እንዳይጠልፍብህ ልትጠብቀው ይገባል፡፡ ደግሞም እግዚአብሄር ለዚህ ተፈጥሮህ ይዋጋልሃል፡፡ ምክንያቱም ፆታዊ ስሜትህን ገዝተህ ንፁህ መሆን ከቻልክ መንፈሳዊ ህይወትህን ይጠብቅልሃል፡፡

💢በነገራችን ላይ ያላገቡ ብቻ አይደሉም ያገቡም ጭምር ናቸው በዚህ አይነት ትግል ውስጥ የሚታገሉት፡፡

💠" እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:5)
💠 " ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:22)


#General

@Appeal4purity
@Appeal4purity
Forwarded from Purity Tube
👉“ ከራሴ ጋር የማደርገውን እጠላዋለው”👈

👤A4P እንግዳ:- “አስራ ስድስት አመቴ ነው ። የሴት ጓደኛ የለኝም ትክክለኛ ጊዜው ነው ብዬም አላስብም።ነገር ግን ብጥብጥ የሚያደርገኝ የሆነ ጠንካራ ወሲባዊ ስሜት አለኝ።
#ማድረግ #የማልፈልገውን #ነገር #እንዳደርግ #ያደርገኛል። በእግዚኣብሄር አምናለው በቤተክርስቲያንም እሳተፋለው። ላወራቸው የምችላቸው ጥሩ ጓደኞችም አሉኝ ሁሉም ግን እንደኔ አይነት ትግል ውስጥ ናቸው።
ቤተሰቦቼ አማኞች እንደመሆናቸውና በቤተክርስቲያን ስላደግኩ ስለውጪው አለም ምንም ኣላውቅም። እግዚኣብሄርንም የእርሱንም ህዝብ እወዳለው ፣ እግዚኣብሄር በሂወቴ አላማ እና እቅድ እንዳለው አውቃለው።

አሁን አሁን ግን በሂወቴ የእግዚኣብሄርን መልካምነት መጠራጠር ጀምሬኣለው።
እግዚኣብሄር በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ወሲባዊ ስሜቴን ለምን እስከማገባ ድረስ ገታ አላረገውም😟? ሚሲ , በእውነት ሃጢያትን ማድረግ ኣልፈልግም።
#ከራሴ_ጋር_የማደርገውን_እጠላዋለው ፣ ራሴን እጠላለው ፣አንዳንዴ ሁሉም አንዲያበቃ እፈልጋለው። ባለፈው አመት ራሱን ያጠፋውን የክፍሌ ተማሪ ሁሌ ትዝ ይለኛል።
እሱም በኔ ሁኔታ ውስጥ ኣልፎ ይሆን እያልኩ ኣስባለው……..
በዚህም ውስጥ እግዚኣብሄር ለኔ መልካም ነው ትያለሽ?
በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ለምንድን ነው በዚህ ውስጥ የማልፈው? …….. አስጠልቶኛል፣ ራሴንም ጠልቻለው ! እርዳታ እሻለሁ

💁A4P፦ ዋው! ይሄ አስራዎቹ ውስጥ እያለው ከምታገልባቸው ሚሊዮን ጥያቄዎች ኣንዱ ነው። ስለዚህ እንዴት እንደሚሰማህ አውቃለው።
በጣም አስፈሪ ነው ኣይደል? 👌እግዚኣብሄር ላንተ መልካም ነው ወይ? መልሴ “ኣዎ ነው።” የሚል ነው ። ምክንያቱም የእግዚኣብሄር ቃል እንደዛ ስለሚል።( መዝ 100፥5, መዝ 136፥1) …….. መልካም መሆን የእርሱ ማንነት ነው።
አዎ እግዚኣብሄር ለኛ መልካም ነው። እናም በሂዎታችን የሚያደርገው ሁሉ ነገር አንድ አጀንዳ ብቻ ነው ያለው እሱም ፍቅር ነው።(መሃልዬ 2፡4)
👉ስለዚህ ለእንደዚህ አይነት ጥያቄ መልስ ስትፈልግ እውነታው ላይ ለመድረስ ከዚህ መነሳት አለብህ ።
አየህ ብዙ ጊዜ ጾታዊ ማንነታችንን ከእኛነታችን ለይተን ለማየት እንሞክራለን እውነታው ግን አብይ የእኛነታችን ተፈጥሮ ነው። ጾታዊ ማንነታችንን ራሱን የቻለ ነገር ሳይሆን የእኛነታችን ግንባታ አካል ነው። እንደውም ጾታዊ ማንነታችንን የስብእናችን ማዕከል ነው ብዬ ነው ማስበው። የእኛነታችን ምሰሶ ነው። 💯

እግዚኣብሄር በርግጥ ለኛ መልካም ከሆነ ለምን ወሲባዊ ስሜታችንን ለምን እስከምናገባ ድረስ ገታ አላረገውም? አግባብ ጥያቄ ነው። 󾠬እንደዛ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ምንም ያልበሰልን እና ሃላፊነት የጎደለን ባሎችና ሚስቶች ፣ኣባቶችና እናቶች እንዲሁም ዜጎች በሆንን ነበር።

አስተውል የአስራዎቹ ዕድሜያችን አግባብ ባልሆኑ ጾታዊ እሴቶች(sexual immoralities ) የምንባክንበት ዕድሜ ሳይሆን በንጽህና መልካም ዘርን የምንዘራበት ጊዜ ሲሆን ከትዳር በኋላ ያለው ጊዜ ደግሞ በአስራዎቹ ዕድሜያችን የዘራነውን የምናጭድበት ነው።
የአስራዎቹ ዕድሜያችንና የ“single” (በእኔ አመልካከት “single” የሚባለው ከ18 ዓመት በላይ ላሉት ነው) ዓመታት እግዚኣብሄር “ምሰሶውን” በ “ፈተና እሳት”🔥🔥 የሚያጠነክርበት ወቅት ነው፣ ስለዚህም ሌሎች ክርስቲያናዊ ባህሪያት ኣብረው ይገነባሉ።

በጾታዊ ጉዳይ የተዘበራረቀ ሂዎት ኖሮት ቃሉን የሚጠብቅ ፣ መልካምና የታመነ ወንድም ወይም የተሰጠ ባልና አባት እስካሁን ኣላገኘሁም። የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖር አይችልም🔑። የውሸት እየኖረ ሰውን ሊያታልል ይችላል። እግዚኣብሄርንና ራሱን ግን ሊያታልል አይችልም። ለሴትም ቢሆን ተመሳሳይ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖራት አይችልም።💯

ለምን? ምክንያቱም ጾታዊ ማንነታችን በትዳር ውስጥ ለአንድ ሰው እንድንሰጥ የተሰጠን በዚያም ውስጥ እንድንረካ ነው።(1ኛ ቆሮ 7፥1-3) ከዚህ ከጾታዊ ማንነታችን ጀርባ ያለውን መሰረታዊ ዓላማ ስናውቅ ሃጥያታዊና ራስወዳድ ነገሮች ይገደላሉ።
👉ነገርግን ለዚህ ዓላማ ጀርባችንን ሰጥተን ጾታዊ ማንነታችንን ለራሳችን ደስታ ፍለጋ ካዋልነው ስብዕናችንን እንረብሻለን። ምክንያቱም ከተፈጠርንበት ዓላማ ዉጪ እየሄድን ሰለሆነ።
󾠬 ለዛም ነው አንዳንድ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ራሳችንን ለማጥፋት የምናስበው ።
👉የተወደድክ ሆይ ፣ እነዚህ በፈተና የተሞሉ ዓመታት መልካም ናቸው ። ምክንያቱም
በእግዚኣብሄር መደገፍንና የእርሱን ጥበቃ የምትማርባቸው አመታት ናቸውና። ለጾታዊ ስሜትህ መልስ ሊሆኑ የሚችሉት ሴቶች ወይም ወሲብ እንዳልሆኑ ትረዳለህ። የሚያስፈልግህ አንድና ብቸኛ ነገር ክርስቶስን ማወቅ እንደሆነ ትማራለህ። ፍላጎቶችህን በራስህ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ለእግዚኣብሄር አንዴት ማቅረብ እንዳለብህ ትማራለህ። 󾠬በዚህም ሂደት ውስጥ ለአንዲት ሴት ብቻ በፍቅር የሚማርክ ልብ ይኖርሃል። ከዚያም ማንንም ሴት በክርስቶሰ እህትህ እንድትሆን በእግዚኣብሄር እንደተፈጠረች ውድ ስጦታ እንጂ እንደ ወሲብ ዕቃ አታይም።
አስተውል፥ ደግነት፣ ሃቀኝነት ፣ ፍትሃዊነት ፣ሁለገባዊነት ፣ጽኑነትና ሌሎችም መልካምና የተመሰገኑ እሴቶች የሆነ ሰው እጁን ጭኖ ሲጸልይልህ አይደለም የሚመጡት። ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እሳት🔥🔥 በሚነደው ጾታዊ ፈተና ውስጥ በድል ማለፍ ስትችል ያኔ ቀስበቀስ በእርግጠኝነት እነዚህን እሴቶች መያዝ ትችላለህ። ግን አስታውስ በቀላሉ አይመጡም ። ሁሉንም ለማግኘት መታገል አለብህ።

እስራኤላውያን ወተትና ማር ወደ ምታፈሰው ምድር እንዴት በትግል እንደገቡ አስታውስ ። ኣዎ እግዚኣብሄር ከእነርሱ ጋር ነበር ቢሆንም ግን መታገል ነበረባቸው።
👉ጾታዊ ፍላጎቶቻችን ለሌሎች የሂወታችን ዘርፎች መሰረት ናቸው። ነገርግን መሰረቱ የሚንቀጥቀጥ ከሆነ ምንም ነገር በላዩ ላይ ሊገነባ አይችልም። እናም መልካም ትዳር እንዲገነባ መሰረቱ እነዚህ እሰቶች መሆን መቻል አለባቸው።
👉ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለብህ ፈተና አንተን ለማጥፋት ሳይሆን እምነትህ ከወርቅ ይልቅ የተፈተነ ይሆን ዘንድ ነው።(1ኛ ጴጥ 1፥7)
🔑🔑ልታደርገው የምትችለው አንድ በጣም ጥሩ ነገር ይህ ነው፦
👉ለዚህ “ጭራቃዊ ” ስሜትህ በሃጥያት የተሞላ መረጃ ይመግበው ዘንድ ለራስህ አትፍቀድለት ። 👉የምታየውንና የምትሰማውን ለይ፣ ከማን ጋር እንደምትውልም ምረጥ። 👉ይህን ፍላጎትህን ከሚመግቡ ነገሮች መሸሽ ብችኛው መጽሃፍቅዱሳዊ መፍትሄ ነው።(1ኛ ቆሮ 6፥18)

አስታውስ ከእግዚኣብሄር ስሞች ኣንዱ “ተዋጊ” የሚል ነው። ተዋጊም ስለሆነ ተስፋቸውን ለመውርስ ከሚታገሉት ጋር ዓላማውን ለመፈጸም ይወዳል።(2ኛ ዜና 16፥9) ስለዚህ መዋጋትህን እስከመጨረሻው እንዳታቆም 👌። ምክንያቱም በመጨረሻ ሚጠብቅህ ድል በመዋጋትህ እንዳትቆጭ የሚያደርግህ ነውና።💯💯


#single #General


እባክዎ ይህን መልዕክት ለሌሎች ያካፍሉ

Be our family 👇👇
@Appeal4purity
@Appeal4purity
@Appeal4purity
ተከፈተ🙈
ተከፈተ🙈
ተከፈተ🙈
🔸የተወዳጁ ቻናል የደስታዬ እልልታ የዩቲዩብ ቻናል ተከፈተ💯
🔸ከታች ያለው ሊንክ በመጫን አሁኑኑ #subscribe ያዱርጉ😊
👇🔻👇🔻👇🔻👇🔻
https://www.youtube.com/channel/UCqihryVzJuniJYSzp6qDevQ
ዶ/ር መስከረም ክፈተው ከ stream of life tv ጋር ስለ ግብረሰዶማውያን ያደረገችው ቃለ መጠይቅ

💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
ሻሎም

ትንሽ ልጅ ትምህርት ቤት ሲሄድ ምሳ ይቋጠርለታል፡፡ ይሄ ልጅ ከእለታት በአንዱ ቀን እናቱ የሚወደውን ምግብ እንደቋጠረችለት ብትነግረው ምግቡን ሊበላ በጣም ይጓጓል፡፡
ስለዚህ መምህር እያለ ሊበላ ይሞክራል፡፡ በምግቡ መዓዛ የተሳበው መምህር ልጁን ከክፍል በማስወጣት ማድረግ ያለበትን ነገር ያደርጋል፡፡

🎷 የዚህ ልጅ ጥፋት ምግብ መብላቱ ሳይሆን ምግቡን ያለጊዜው(ባልተፈቀደለት ጊዜ) መብላቱ ነው፡፡
👇
️"Sex" ማድረግ በራሱ ሀጢያት አይደለም፡፡ ያለጊዜው ማድረግ ግን ሀጢያት ነው፡፡
ትክክለኛ ጊዜው
🤔👇👇

️" መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንፁህ ይሁን"!
ዕብራውያን 13 ፥ 4

👉@ @Appeal4purity 👈
👉 @Appeal4purity 👈
Forwarded from Purity Tube
💢እነዚህ የ #ፖርኖግራፊና#masturbation ሶስት ዋና ዋና #ውሸቶች ናቸው👇👇

⛔️ውሸት1⃣ 👉"ይሄ የመጨረሻህ ነው"

ምንም ያህል ጊዜ የፖርኖግራፊ ፊልም ብታይ 'ይሄ ለመጨረሻ ጊዜ የምታየው ነው' የሚል የውሸት ድምፅ አለ፡፡

👉የመጨረሻህ እንደሆነ ስላመንክ ወደ ድህረገፁ ስትገባ ወይም ዳውንሎድ ስታደርግ ለሰው መናገር አለብኝ ብለህ አታስብም ምክንያቱም 'የመጨረሻ ጊዜህ ነው'

🔴ፖርኖግራፊ ይህ የመጨረሻህ ነው ብሎ ካሳመነህ ለማንም ችግርህን አታወያይም ማንም አይፀልይልህም ማንም አይረዳህም

መጨረሻ የሌለው መጨረሻ

⛔️ውሸት2⃣👉"በፈለግከው ጊዜ ማቆም ትችላለህ"

ፖርኖግራፊና masturbation እንዲህ ይሉሃል

👉" እኛ በሌሎች ትዳሮች ላይ ፣ ሌሎች ጓደኞችህ ላይ፣ ሌሎች ቤተሰቦች ላይ ፣ ሌሎች የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ያደረሰውን ውድቀት ታውቃለህ......አንተ ግን 'ሱስ አልያዘህም' ፡፡ በፈለግከው ጊዜ ማቆም ትችላለህ፡፡ በዚያ ላይ ሌሎች ላይ የሚያደርሰውን አይነት ተፅእኖ አንተ ላይ አያደርስም፡፡ ህይወትህን ፣ ትዳርህን ፣ ቤተክርስቲያንህን ፣ አገልግሎትህን አይጎዳም፡፡
አንተ ነህ እንጂ የምትቆጣጠረው እሱ አይቆጣጠርህም፡፡ "

⛔️ውሸት3⃣ 👉"ትግልህን ለሰው መናዘዝ ብዙ ዋጋ ያስከፍልሃል፡፡ "

👉ፖርኖግራፊና masturbation በሚስጥር እንድትኖር ነው ሚፈልጉት፡፡

ብቻህን ስትሆን የምታደርጋቸው ነገሮች ስለሆኑ ሁሌ ብቻህን ብትሆን ፣ጓደኞች ባይኖሩህ ደስ ነው የሚላቸው፡፡

👉እነዚህ ክፉ ነገሮች የመናዘዝን ዋጋ ችግሩን ከመደበቅ ዋጋ ጋር አመዛዝነህ የመደበቅ ዋጋ ቀላል እንደሆነ እና ብዙ ህመም እንደሌለው ሊያሳምኑህ ይጥራሉ፡፡

👉ይሄን ችግርህን ለሰው ባለማወያየትህ ቤተሰብህን ፣ ትዳርህን ወይም ራስህን እየረዳህ እንደሆነ እንድታስብ ያደርጉሃል

ሚስትህ አይገባትም አትረዳህም (ባልሽ አይረዳሽም) ትዳርህ ይፈርሳል
በሰዎች ያለህን ተቀባይነት ታጣዋለህ የሚል ድምፅ ያሰማሉ፡፡

👉💯ነገር ግን ሃጢያትህን አለመናገር ከዛ ቀንበር እንዳትወጣ ያደርግሃል፡፡ 💯

📌እውነቱ ግን ይህ ነው " እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
(የያዕቆብ መልእክት 5:16)

󾠬ከላይ የተዘረዘሩትን ውሸቶች የምታምን ከሆነ ከዚህ እስራት ለመውጣት የምታደርገውን ትግል ተራራ ያደርግብሃል፡

💁እግዚአብሄር በእነዚህ ድርጊቶች ተበሳጭቶ ፊቱን እንዳዞረብህ ሚሰማህ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡

♥️እንደውም ከዚህ እስራት እንድትወጣ እየታገለልህ ነው፡፡

💢ጌታ ኢየሱስ የሞተውና ሞትንና ሃጢያትን ያሸነፈው አንተን በሃጢያት ላይ አሸናፊ ሊያደርግህ ነው


#General

@Appeal4purity
@Appeal4purity
👁👁የወጣት ወንድ ጠላት👁👁

የወጣት ወንድ ቀጥር አንድ ጠላት ምንድን ነው ከተባለ መልሱ" ሁለቱ አይኖቹ ናቸው" የሚል ይሆናል፡፡

⚠️አዎ! በእግዚአብሔር መንፈስና በቃሉ በሚመሩት በአእምሮውን እና በመንፈሱ እንዲታዘዙ እስካልሰለጠኑ ድረስ ጠላቶቹ ናቸው፡፡

*⃣የወጣት ወንድ አይን ቆንጆ ሴት ሲያይ በቃ እስከዛሬ ስትፈልጋት የነበረችውን ፣ እግዚአብሄርን የምትወድ ፣ የተወደደ ባህሪ ያላት ለጌታ የተሰጠች ሴት ይኸው አገኘሃት ይለዋል ለአእምሮው፡፡

🔴እውነቱ ግን ልጅቷ ቆንጆ መሆኗ ብቻ እንጂ ሌላው ሁሉ ተረት ነው፡፡

እንደዛ ከሆነ ነገሩ ልጁ በገዛ አይኖቹ እየተታለለ ነው ማለት ነው፡፡

🔵ጥበብ ግን እንዲህ ይለዋል " አሁን የምታየው ጊዜያዊ ነው ፣ በአይንህ የማይታይህ ግን ዘላቂ ነው "

💢ጌሪ ቶማስ የተባለ ሰው "The Sacred Search" በሚለው ድንቅ መፅሀፉ ላይ ለወጣቶች ይሄን ፅፏል " አስበኸው አታውቅ እንደሆነ ይህን ልንገርህ ፤ የሴት አካል ከባህሪዋ ይልቅ ፈጥኖ ይቀየራል"

እምም ፤ ሁለቴ እንደታስብ አደረገህ አይደል😊

👉አንድ ወንድ የሴትን ልጅ የተደበቀ ዘላቂ ውበትና መልካም ባህሪ ማየት የሚችልበት አንዱና ብቸኛ ፣ ምርጡና ውጤታማው መንገድ ይህ ነው
👉 ከእግዚአብሔር ቃል መጣበቅ፡፡

💢ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ከጠላትህ ይልቅ ጥበበኛ ያደርግሃል ፤ አንዱ ጠላትህ ደግሞ አይንህ ነው፡፡

💯ይሄን ስታደርግ አእምሮህና መንፈስህ ከአይኖችህ ይልቃሉ፡፡

"ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።"
(መዝሙረ ዳዊት 119:98)

👉ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት የሌለው ሰው ምንም እንኳን በቋሚነት ወደ ቤተክርስቲያን ቢሄድም ማየት የተሳነው ነው፡፡💯

ይሄን በማስተዋል አንብበው
(የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 3)
----------
17፤ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

18፤ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ፡፡"

💢ኩል በጊዜው የአይን ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይጠቀሙበት ነበር፡፡
ዋው! አያችሁ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን?

💯የእግዚአብሔር ቃል ለአይኖችህ ፈውስ ነው💯

💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
⛔️አግቢኝና ጌታን እቀበላለሁ....⛔️

እንግዳ ፦ ከሆነ ሰው ጋር ግንኙነት ጀምሬአለሁ። የማልመው አይነት ሰው ነው፡፡ አያጨስም አይጠጣም አይቅምም። እንደምፈልገው አይነት እንክብካቤ ያደርግልኛል፡፡ እኔ ዳግም የተወለድኩ ክርስቲያን ነኝ እሱ ግን አይደለም፡፡ ማለቴ ወደ ቸርች መሄድ ብዙም አይፈልግም እኔ ግን እንድሄድ ያበረታታኛል፡፡
ባለፈው ሳምንት እንዳገባው ጠየቀኝና ይሄ አመት ሳያልቅ ጌታን እንደሚቀበል ቃል ገባልኝ፡፡ እኔ ግን የሆነ ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት እየተሰማኝ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ምክር ፈልጌ ነበር፡፡

💁A4P፦ ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት??
እኔ ማምነው እግዚያብሄር እየነገረሽ እንደሆነ ነው፡፡ ዳግም የተወለድሽ ክርስቲያን እንደሆንሽ ነግረሽኛል፡፡
ያን እውነት በትክክል የያዝሽው አይመስለኝም፡፡
ወደዚህ ምድር የመጣሽበትን ቀንና ቦታ አንቺ እንዳልወሰንሽ ሁሉ ሁለተኛው ውልደትሽም እንዲሁ ነው በእግዚአብሔር ፍቃድ እንጂ በሰው አይደለም፡፡(ዩሐ 1፥13)

👉ሙታን ሳለን እግዚአብሄር ሲያገኘን ፈልገነው አይደለም፡፡ እርሱ በመጀመሪያ ሲወደን ወደ ልጁም መንግስት ሲያመጣን ወደነው አልነበርም፡፡(ሮሜ 5፥8 ዩሐ 4፥19)

ስለዚህ ጓደኛሽ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዙ ትንሽ የሚያስቅና ከቃሉ ውጪም ነው፡፡ እግዚአብሄር ካልጠራው በቀር ማንም ወደ ኢየሱስ ሊመጣ አይችልም።(ዩሐ 6፥44)
👉ማን ወደ መንግስቱ እንደሚመጣ የሚወስነው እግዚአብሄር እንጂ ሰው አይደለም፡፡ በክርስቶስ ስላላመኑ ሰዎች ለመረዳት 2ኛ ቆሮ 6፥14-18 አንብቢ፡፡

ስለዚህ ምክሬ ይህ ነው፦ ከዚህ ሰው ራቂ!! የሰጠሽን ቀለበት መልሺለትና የራስሽን ኑሮ ቀጥይ፡፡
🔴እሱን በማግባት አዲስ ፍጥረት ልታደርጊው አትችይም፡፡
󾠬ካላመነ ሰው ጋር አትታሰሪ፡፡
🔴 ያን ካላረግሽ በእግዚአብሔር ቃል ላይ እያመፅሽ ነው ያ ደግሞ ብዙ ዋጋ ያስከፍልሻል፡፡ ስለዚህ በጣም ተጠንቀቂ
💯ትዳር ሰርግ እንዳልሆነ አትርሺ፡፡💯 ትዳር የግብረስጋ ግንኙነት ፍቃድም አይደለም ፡፡
󾠬 ትዳር ከምታገቢው ሰው ጋር አንድ የመሆን ጎዳና ነው፡፡ በአካል ብቻ አይደለም ፣ በሁሉ ሁኔታም ጭምር እንጂ፡፡💯

አውቃለሁ ለአንድ ሴት ልጅ በወንድ ልጅ መፈቀር ፣ ያፈቀረችውንም ወንድ ማግባት በጣም ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ግን ከሁሉ በፊት መጀመሪያ በእግዚአብሔር ቃልና ፈቃድ መማረክና መደሰት ነው ያለብን ፡፡ 👉እግዚአብሄርም ደግሞ አያሳፍረንም፡፡ ሁሉን ነገር ሰጥቶናል ነገር ግን በመጀመሪያ ፅድቁነንናመንግስቱን ልንፈልግ ይገባል፡፡ ማቴ 6፥33

#General #youth


👉@Appeal4purity👈
👉@Appeal4purity👈
ፍቅረኛ አለሽ/ህ

ፍቅረኛ አለሽ/ህ? ፍፁም የሆነ ፍቅር ለመጀመር አስበሃል፣ እስከሞት ድረስ የሚወድሽን ለማግኘት፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሚያስብልሽ/ምታስብልህ እና ሚንከባከብሽ/ምትንከባከብህ ሰው ትፈልጊያለሽ/ህ

🛑እንዲህ ያለን ሰው ማግኘት ካገኘህ/ሽ ምታገቢው/ምታገባት ይመስልሻል/ሃል? አታገቢውም ምክንያቱም እሱ ፍፁም ነው አንቺ ደሞ አደለሽም። እንደውም ትሰቅይዋለሽ! አዎ። ሁላችንም ሰቅለነዋል


💢ይሄ እውነቱ ከሆነ ለምን ታድያ ፍቅር ያልጀመሩ ሰዎች ፍፁም የሆነን አጋር ይፈልጋሉ? ይሄ የሁሉም ብቸኛ ሰዎች ህመም ነው። አታስቡ እኔ ራሱ 22 አመቴ እያለ እንዲህ ታምሜ ነበር። ከመዳኔ በፊት አገባው።


ብርሃኔን(ባለቤቴን) እንዳገባው ታድያ ፤ ፍፁም ያልሆነ ሰው ያገባው መስሎ ተሰማኝ እና " ብርሃን ፍፁም ነው ብዬ አስቤ ነበርና እንዳልሆነ ስረዳ ሌላ ፍፁም ለኔ ሚሆን ፍፁም ሰው ሌላ ይኖራል" ብዬ አሰብኩ።

እግዚአብሔር ይባረክ እርሱ ረድቶኝ በዚህ ሃሳብ ስላልተዋጥኩኝ። እግዚአብሔር በምህረቱና በፀጋው ፍፁም ሚባል ሰው ከኢየሱስ በቀር ኖሮ እንደማያውቅ አስተማረኝ፤ እና የኔ ባለቤት የሰው ልጅ መሆን እስከሚችለው ድረስ ፍፁም ነበር።

ኡ…! አስባቹታል ሃሳቤን አምኜ ባሌ ፈትቼ ሌላ ፍፁም ሰው መፈለግ ጀምሬ ቢሆን ኖሮ? ኦህ! እግዚአብሔር ይባረክ ከዛ እብደትና ሞኝነት ያዳነኝ። ነገር ግን ይህን ተመልከቱ፤ ማመን ባንፈልግም እንኴን፤ አስተውለነውም ሆነ ሳናስተዋል፥ ሁላችንም ፍፁም አጋር ምክንያቱም(ሲመስለኝ) በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሲፈጥረን በውስጣዊና ውጫዊ ማንነታችን ፍፁም አርጎን ነበር። ከዛ ግን አዳምና ሄዋን ከፍፁምነት ወደቁ። የኛ ፍፁምነት ገነት ውስጥ ሞቷል ፤ ሁላችን ይሃን በሞት የመጣውን ትልቅ ጠባሳ ተሸክመነዋል።

👉ጠባሳው ፍፁም የመሆንና ፍፁም ፍቅረኛ የማግኘት ነው፥ "ይህች አጥንት ከአጥንቴ፤ ስጋዋ ከስጋዬ" አይነት ፍፁም ፍቅረኛ።(ዘፍ 2÷21_23) ስለዚህ፤ እግዚአብሔር በምህረቱና በፀጋው ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከ። ስለሃጥያታችን ሞተ እኛን ለማፅደቅ ተነሳ። ከዛም እሱ "የኛ ፍፁምነት" ሆነ፣ የኛ ፅድቅ፣ የውስጣችንን ፍፁምነት ያሟላ ሆነ።

ሰምታችኋል? አዎ! ኢየሱስ ክርስቶስ የኛ ፍፁም አጋር ነው። ( ኢሳይያስ 54÷4; ኤርሚያስ 3÷14) እባካችሁ ይሄን አትርሱ።

💢ስለዚህ የፍቅር አጋር እንደሌለው ሰው፤ ምታገቡትን ሰው ከመፈለጋችሁ አስቀድሞ፤ ከውድቀታችን የመጣው ያ ልባችሁ ውስጥ የቀረ ትልቅ ጉድለት ወይም ጠባሳ፤ ፍፁም የመሆንና ፍፁም አጋር የማግኘት ፍላጎት፥ በኢየሱስ መሟላቱን ማረጋገጥ አለባችሁ። ጌታ ፍፁሙ ሰው፥ የልባችሁን ጥማት ባረካ ጊዜ፤ በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ፊት ፍፁም መሆናችሁንና ሙሉ በሙሉ እንደተቀበላችሁ፤ በፍፁሙ አፍቃሪ እንደተፈቀራችሁ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን ሊመጣ ባለውም አለም ከመቃብር ባለፈ ባለው ህይወታችን መወደዳችሁን ታውቃላችሁ።

👉ውዶቼ ሆይ፤ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ካልገባችሁ፥ መጀመሪያ ኢየሱስን ብቻ የፍፁምነት ጥማታችሁን እንዲያረካ ፍቀዱለት። ከዛ እናንተን ለማግኘት እግዚአብሔር የባረከውን/የባረካትን ሰው ጥሩ የፍቅርና የህይወት አጋር ታገኛለችሁ።

የዛሬ 22 አመት ይህን አንብቤ ቢሆን ኖሮ በትዳሬ መጀመሪያ ለባለቤቴ ጥሩ ሚስት ሆኜ በነበርና እንደ ክርስቶስ ፍፁም በሆነ ብዬ ባልተመኘው። መቼስ ይሁን፤ ዛሬ እኔ ተቸግሬ እንደነበረ ለተቸገሩ ትምህርት አርጎኛል።

"ጆሮ ያለው ይስማ" ከማለት ውጪ ምን እላለው


💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
🔴ምክር ላላገቡ ወጣት ሴቶች🔴

👉 ከማያምን ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራችሁ ከሆነ ሁለቴ ማሰብ ሳይጠበቅባችሁ መወሰን ያለባችሁ ውሳኔ ይህ ነው
🚫 ግንኙነታችሁን ማቋረጥ 🚫

👉 በጌታ ካልሆነ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዳር ዳር እያላችሁ ከሆነ (በስልክ ወይም በchat በማውራት ሊሆን ይችላል) ከዚህ ወደ ክፋት ከሚወስድ ጎዳና ለመውጣት ማወላወል አያስፈልግም፡፡
ለማቆም ቆራጥ ሆነሽ መወሰን ነው ያለብሽ

ከላይ ያሉትን ውሳኔዎች መወሰን ያለብሽ
በዚህ ወር አይደለም
በዚህ ሳምንትም አይደለም
ነገም አይደለም
በኋላም አይደለም
🤔ታዲያ መቼ መልሱ #ዛሬ #አሁን ነው‼️

💢ምክንያቱም ከሞት ጋር የተፈራረምሽውን ውል ለማቋረጥ ቀጠሮ አያስፈልገውም አራት ነጥብ ፡፡

በነገራችን ላይ ይህ ምክር ላላገቡ
ወንዶችም የሚሆን ነው😊

ተጨማሪ ምንባቦች👇👇

https://t.me/Appeal4purity/351

💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
Purity Tube pinned «🔴ምክር ላላገቡ ወጣት ሴቶች🔴 👉 ከማያምን ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራችሁ ከሆነ ሁለቴ ማሰብ ሳይጠበቅባችሁ መወሰን ያለባችሁ ውሳኔ ይህ ነው 🚫 ግንኙነታችሁን ማቋረጥ 🚫 👉 በጌታ ካልሆነ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዳር ዳር እያላችሁ ከሆነ (በስልክ ወይም በchat በማውራት ሊሆን ይችላል) ከዚህ ወደ ክፋት ከሚወስድ ጎዳና ለመውጣት ማወላወል አያስፈልግም፡፡ ለማቆም ቆራጥ…»
👁👁 የሰው አይን 👁👁

መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር 1 ዮሐንስ 2 (1 John)
15-16፤ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና 🔴የዓይን አምሮት 🔴ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።

🌟"የአይን አምሮት " ብዙ የመዝናኛ📺 እና🎦የporn ኢንዱስትሪ ዋነኛው የገቢ ምንጭ የሚያገኙት በዚህ ነገር ነው፡፡ በዚህ መንገድ ለአንድ ክርስቲያን ወገን ይቀርባሉ "እስኪ እየው "🎭በማለት እንዲያይ ያደርጉታል ፡፡

🔶🔷የሚቀረው ታሪክ እንግዲህ
🔑ጦርነቱ ያተኮረው በነብስ ለይ ሲሆን አይን ደግሞ ተግባሯን በመቀጠል የለምንም ጥርጣሬ እና ያለምንም ገደብ በትኩረት መመልከትን ትጀምራለች፡፡
_📔መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር
ምሳሌ 27 (Proverbs)
20፤ ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም።

😃የሰው አይን በሚያየው ነገር አይረካም(አይጠግብም );ለምን አሁንም ያያል ?
ከሚያየውም ነገር ደስታ ከሌለው እና ሀሴትን የማያውቅ ከሆነ :-ነገር ግን እጅ 🙌መስጠት,ተሰፋ መቁረጥ እና ጭንቀት ከሆነ ለምን ያያል ?

💸💷$ይህ የሚሊዮን ብር ጥያቄ ነው?
አይደለም !!ምሳሌ 16 (Proverbs)
32፤ ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል።
💮💯 ሠው በመንፈስ ሲመራ አይኑን ይመራል ደግሞም ማየት የሌለበትን አያይም .........



ⓙⓞⓘⓝ us
@Appeal4purity
@Appeal4purity
👋🖐ሻሎም የA4P ቤተሰቦች

⛔️ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለ ኦቲዝም ካላቸው የተዛባ አመለካከት የተነሳ የችግሩን ተጠቂ ከመርዳት ይልቅ ወደ ተባባሰ ችግር ውስጥ ሲከቱት ይስተዋላል፡፡

💢በመሆኑም ሰዎች ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲያገኙ የአቅማችንን ያህል ለመርዳት #family በሚለው አምድ ስር በተከታታይ ክፍሎች ስለ ኦቲዝም ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን አካተን ወደ እናንተ እናደርሳለን እርስዎም ሼር በማድረግ ኃላፊነትዎን ይወጡ

ተባረኩ!!

💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
ኦቲዝም

ክፍል አንድ

📜ኦቲዝም (Autism) የቃሉ መሰረት Autos ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ራስ (Self) ሲሆን፤ ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች ወይም አዋቂዎች ራሳቸውን ከሌላው ማህበረሰብ በማግለል የራሳቸውን አለም እንደሚፈጥሩ ለማመልከት የተወሰደ ቃል ነው፡፡

🛑ኦቲዝም ቋሚ የሆነ የማህበራዊ ተግባቦትና ግንኙነት ችግር ሲሆን፤ አዕምሮ በሚፈለገው ደረጃ በተለያዩ ለመኖር በሚያስፈልጉ ክህሎቶች ማሳደግ እና መበልፀግ ሳይችል ሲቀር ማለት ነው፡፡

👉ኦቲዝም ባብዛኛው ከ2 ዓመት የሚጀምር ወይም የሚታይ ሲሆን ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት ይስተዋላል፡፡

💢 መንስኤው 💢

🛑በእርግጠኝነት የኦቲዝምን በሽታ መነሻነት መናገር ባይቻልም አንዳንድ ጥናጦች እንዳመላከቱት ግን
ልጆች በሚረገዙበት ጊዜ
📌የወላጆች ዕድሜ መግፋት ፣
📌ከዘር ጋር የተያያዙ ችግሮች (genetic problems)
📌በማህጸን ውስጥ ፅንሱ አስፈላጊውን የአዕምሮ እድገት ደረጃ አለመጨረስ

👉በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት
የሚያጋጥሙ አካባቢያዊ ምክንያቶች ማለትም መርዛማ አየር፣ ውኃ፣ ምግብ ይጠቀሳሉ
📌እንዲሁም በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ አደንዛዥ ዕፆችም ይነሳሉ፡፡

💢 ምልክቶቹ 💢

🛑የኦቲዝም ምልክትን በተመለከተ የተለያዩ ነገሮች በተለያየ ደረጃ የተጠቀሱ ቢሆንም በዋናነት ከተነሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
📌የተስተጓጎለ ማህበራዊ ግንኙነት፣ 📌በግንኙነት ጊዜ የዓይን ለዓይን መተያየትን ባብዛኛው አያደርጉም በአንጻሩ የተናጋሪውን አፍ ነው የሚያዩት፣ 📌ቋንቋን ለማዳበር ረዘም ያለ ጊዜ ይፍጅባቸዋል፣
📌የሚሰሙትን ቃላት እና አረፍተ ነገሮች ይደጋግማሉ፣
📌ከተመሳሳይ ዕድሜ ካላቸው ልጆች ጋር ግንኙነት የመመስረት ችግር
ይስተዋላል፣
📌ውስን የሆኑ የሰውነት እንቅስቃሴዎች፣ ሌሎች ልጆችን የሚያጓጓ እና የሚያስደስት ነገር እነሱን አያስደስታቸውም ወይም አያጓጓቸውም፣ 📌ተደጋጋሚ የሆኑ ባሕርያትን ያሳያሉ በዚህም ራሳቸውን ሊጎዱ ይችላሉ ፣
ነገሮች ከተልምዷዊው ሁኔታ ወጣ ሲሉ
አይወዱም፣
📌ለተወሰኑ ድምጾች እና ሽታዎች እጅግ በጣም ስሜታዊ እና ያልተለመደ ምላሽ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

💢በዚህም የአዕምሮ
ዕድገት ውስንነት የሚያጠቃቸው ሰዎች የማህበራዊ ግንኙነታቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው

🛑በተጨማሪም ለተወሰነ ነገር ብቻ ከፍተኛ ትኩረት እና ዝንባሌ ያሳያሉ፡፡

👉እነዚህንም ምልክቶች ለማየት ወላጆች ቀዳሚዎች ናቸው፡፡

ይቀጥላል.......

🙏🙏እባክዎ ለሌሎች እንዲደርስ #ሼር #ሼር_ሼር ያድርጉ🙏🙏

©ዘ-ሳይኮሎጂስት

#family

💢 @Appeal4purity 💢
💢 @Appeal4purity 💢
#በክርስቲያን_ወጣቶች ዙርያ #ሰፊ_ዳሰሳ የሚያደርግ #ቻናል ከፈለጉ ሁለቴ ሳያስቡ ይህን ህብረት ይቀላቀሉ!!

👉 ይታነፁበታል ይማሩበታል!!
👉 በመቀላቀልዎ ፈፅሞ አይፀፀቱም!!
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgngaTYyJjZx-hg
ኦቲዝም

ክፍል ሁለት

🛑ኦቲዝምን በህክምና ለማዳን ይሄ ነው የሚባል የህክምና መፍትሄ ባይኖረውም ሆኖም ግን ልጆችን ምልክቶቹ በታዩባቸው ቀድም ያሉ ጊዜያቶች ባህሪያዊ፣ ስነ-ልቡናዊ እና ተግባቦታዊ ምክክሮችና እና ፕሮግራሞች የልጆቹ የማህበራዊ ግንኙነትን ክህሎት በጥቂቱ
እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡

💯ሌላው በኦቲስቲክ ልጆች ላይ ብቻ ያተኮረ ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆቹን ማስተማር የዐዕምሮ ብቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል በዚህም የወላጆች ከፍተኛ እና ንቁ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው፡፡

*⃣ለኦቲዝም በህክምና የሚታዘዙ
መድኃኒቶች አሉ ሆኖም ግን በሽታውን ሙሉ ለሙሉ የማጥፋት ኃይል የላቸውም ስለዚህም ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘለቄታዊ አይደሉም፡፡

💢እርግጥ ነው ኦቲዝም በአንድ ልጅ ብቻ ላይ ቢያጋጥም እንኳን መላው ቤተሰብ ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ችግር ነው ስለዚህ ልጅዎ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ/ኗ በህክምና ከተረጋገጠ በኋላ በቅድሚ ማድረግ የሚኖርብን ችግሩን መቀበል ነው፡፡

🛑በዚህም ልጆችን ጓዳ ውስጥ ደብቆ ከማስቀረት ይልቅ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የልጆቹን ሁለንተናዊ የሆነ አእምሮኣዊና አካላዊ እድገትን ያፋጥናል፡፡

📎ቀጥሎ ቤት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን ሁኔታዎችን ማሙዋላት ይኖርብናል ለምሳሌ መጫወቻዎች፣ ቤትን ለልጆች ምቹ ማድረግን እና የመሳሰሉትን ሌላው ትምህርት ቤት በሚገቡበት ጊዜ ከመምህራኖቻቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመስረት የየዕለት ልዩነታቸውን እና እድገታቸውን መከታተል ያስፈልጋል፡፡

📰ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ኦቲዝምን ስር ሳይሰድ አውቆ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ልጆቹ ላይ አስደናቂ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል፡፡

☑️እኛ ሀገር ላይም ጥቂት ድርጅቶች በኦቲዝም ዙሪያ ንቃተ ህሊናን ለማዳበር እና ኦቲስቲክ ልጆችን ለመርዳት የተቋቋሙ ተቋማት አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ኒያ ፋውንዴሽን ፎር ጆይ ሴንተር አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ የድርጅቱን አድራሻ ለምትፈልጉ የድህረ ገጽ አድራሻቸውን ይኸው ብለናል http://www.ethioautism.org/
Joy/Home.html አብረን እንጎብኛቸው፡፡

💢ውድ የAppeal4purity ቤተሰቦች እርግጥ ነው ይህን ሁዳድ የሆነ ርዕስ በዚህ አጭር ጽሑፍ መሸፈን አባይን በጭልፋ እንደማለት ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ በጉዳዩ ዙሪያ ሌሎች ሀሳቦቸን እና የሚመለከታቸውን አካላት ወደፊት በሰፊው ይዘን እንደምንመጣ እየጠቆምን የዛሬውን እዚህ ጋ እንቋጨው።

#family

@Appeal4purity
@Appeal4purity
Forwarded from Purity Tube
🏃🏃 ቅዱስ ሽሽት 🏇🏇

💢ከዝሙት ሽሹ፣......1ቆሮ 6፡18

ከእንቅልፍ ያነቃኝ ህልም ነው።በህልሜ አንድ ቤት ውስጥ ላሉ ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል ሳስተምር ቆይቼ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ነኝ።
የቤቱ መውጫ ከሩቅ ይታየኛል ነገር ግን በአጠገቤ ባለው የጓሮ አጥር ጥግ የተገነጠለ ቆርቆሮ አያለሁ።በልቤ ለምን በዚህ በኩል አልወጣም ብዬ ዓሰብኩና ቆርቆሮውን አጥፌ በማእዘኑ ስር ለመሹለክ ስጎነብስ ገና ግማሽ ጎኔ ሳይወጣ አንዳች የሚያካክሉ ውሾች🐶🐶 አየሁ።

መውጣቴን ስቀጥል ከመካከላቸው አንዱ እየተስፈነጠረና እየጮህ ወደ እኔ ሲጋልብ ደንግጬ ተመለስኩና በአጥር መውጣቴን ትቼ በበሩ ለመውጣት ውሰንኩ ፤ ወድያው ከእንቅልፌ ነቃሁ።

💡መብራቱን ሳላበራ የት እንዳለሁ ማሠብ ጀመርኩ። ለአገልግሎት ከወጣሁ አንድ ወር ሆኖኛል። በጀርመን ከተሞች ሳገለግል ከቆየሁ በኋላ ከሹቱትጋርት በባቡር ተሳፍሬ ወደ ሆላንድ ከተማ በሆነች ዘ ሄግ ሁለት ቀናት ቆይቼና አገልግሎቴን ጨርሼ ወደ ጀርመን ለመመለስ ትላንት ምሽት አምስተርዳም ገብቻለሁ። ያደርኩት ዘ ሄግ ኮንፍራንስ ይዞን የመጣው አምስተርዳም ከተማ የሚኖር ወንድም ቤት ነው።አሁን የት እንዳለሁ ተረድቻለሁ።
እናም ጥቂት ህልሙን ካሰላሰልኩ በኋላ ወርጄ ተንበረከኩና ጠላት ከፊቴ ካስቀመጠው ከማናቸውም ወጥመድ እንዲጠብቀኝ ጌታን ተማጽኜ 🙏ተነሳሁ።

ቁርስ እንደበላን ዝነኛዋን አምስተርዳምን እንድያስጎነኘኝ ከአንድ ወንድም ጋር ቀጠሮ መያዜን ትዝ አለኝ።

አስጎብኚዬ ከተማይቱን ‘ከሱ ይልቅ ለሳር! ’ እስከሚባልለት ድረስ ጠንቅቆ ያውቃል። ወደ ጌታ ከመምጣቱ በፊት አደንዛዥ ዕጽ እያጨሰም እያስጨሰም ያልገባበት የጨለማ ጥግ እንደሌለ አጫውቶኛል። ወደ ጌታ ከመጣ በኋላ ተከታታይ ትምህርቶቼን በቴፕ አግኝቶ ስለሰማና ስለተጠቀመ በዚህ አጋጣሚ ከተማይቱን ለማስጎብኘት ፍቅሩን ለመግለጽ ጓግቷል።ከዛም ጉብኝቱ ተያያዝነው።ከጥቂት ቆይታ በኋላ እምብዛም ግራና ቀኝ መታጠፍያ የሌለው አንድ ቀጭን መንገድ ይዘን መውረድ ጀመርን።

አስጎብኚዬም ‘ይህ መንገድ ወደ ቀይ መንገድ ጎዳና የሚወስደው መንገድ ነው፤አምስተርዳም መጥቶ ይህን ሳይጎበኝ የሚሄድ የለም።’

ይሄኔ አንድ ትልቅ የማይታይ እጅ ደረቴ ላይ አርፎ ወደ ኋላ የሚገፋኝ ያህል ተሰማኝ።

ቆም አልኩና “ይህ ቀይ መንገድ ጎዳና ሴቶች በከፊል ዕርቃናቸውን ሆነው በመስታወት ውስጥ የሚታዩበት ነው ?” አልኩና ፈጣን መልስ በሚሻ ድምጽ፤ፊቱ ቅጭም አድርጎ “አዎን ፧ ”አለኝ።

ከዚህ ቀደም እንደሰማሁት ከሆነ ይህ ጎዳና ሴቶች ራቁታቸውን ሆነው ለዝሙት የሚቀሰቅስ እንቅስቃሴ እያሳዩ በመስኮት የሚቆሙበትና ተመልካቾቻቸውን ለወሲብ የሚጋብዝ በዓለም ላይ የታውቀ፤ በሃገሩ ህግ የተደገፈ ዘመናዊ የሴት አዳሪዎች ጎዳና ነው።
ይህን ለማየት ከዓለም 🌏 ዙሪያ የመጡ የትዬለሌ ጎብኚዎች ከፊታችን እየተጋፉ ያልፋሉ። ወድያው የማታው ህልም ትዝ አለኝ።

በልቤ “አገልግሎቴን ጨርሻለሁ በሰላም በገባሁበት በር ብወጣ ይሻለኛል፤አጥር መጣስ አይበጀኝም፤ ይህ የውሾች እንጂ የሰው መንደር አይደለም፤ ጩኧታቸው ልቦናዬን እንዳይረብሽ ለምን እፈቅዳለሁ” አልኩና ወደ አስጎብኚዬ ዞር ብዬ “ ወዳጄ #ይሄ_የእኔ_ክልል_አይደለም ብመለስ ይሻለኛል።”በማለት እግዚአብሔር ክፋትን ከማየት ስለታደገኝ እያመሰገንኩ ወደ ጀርመን ይዞኝ የሚምዘገዘግ ፈጣን ባቡር ለመጠበቅ ባቅራቢያ ባለ ካፌ ተቀምጥኩ።

👉በፍልሚያ ላይ መሸሽ የፈሪነት እንጂ የጅግንነት መግለጫ ተደርጎ አይወሰድም።

💢ፍጣጫው ከዝሙት ጋር ከሆነ ግን ማሸነፊያው መንገድ፤ ድል መንሺያው ስልት #መሸሽ_ብቻ ነው። ስለዚህ ጀግና ሳያመነታ ይሻሻል።

💂💂 የበጎ ወታደር መለያው ጠላትን መጋፈጥ ብቻ ሳይሆን ለጦር ያስከተተውን መታዘዝ ስለሆነ “ሽሽ” ሲባል መሸሹ ጀግና እንጂ ፈሪ አያሰኘውም።

ቤት በእሳት ሲያያዝ🏡🔥🔥 ከአደጋ ለማምለጥ ጅርባ ሰጥቶ መሮጥ እንጂ ማቄን ጨርቄን እያሉ ወደ ቤት መለስ ቀለስ እንደማይባል ሁሉ ከዝሙት ለማምለጥ ከመሸሽ ሌላ ምንም አማራጭ #የለም💯💯

📚ተጨማሪ ንባባት፡ ኤፌ 5፡3 ዕብ 13፡4 ምሳሌ 5፡7-14
ጸሎት🙏🙏🙏
“አቤቱ፡ከዘመኔ ሁሉ ከዝሙትና ወደ ዝሙት ከሚመሩ ነገሮች ጠብቀኝ፤የምሸሽበትን ጸጋ አብዛልኝ፤ አጉል ደፋር ሆኜ ወጥመድ ውስጥ ከመግባት፤ካዘጋጀህልኝ ክብር ከመጉደል ጠብቀኝ።
በተፈጥሮ የሰጠህኝ ማንነት ቅዱስ እንደሆነ አውቄ አንተ ባሳመርኧውና ለክብር በሚሆን መንገድ ብ ቻ በአግባቡ እንድጠቀምበት እርዳኝ ። አሜን።”

#General

📔 ምንጭ፦በ2016 አ᎐አ ፤ ከእፎይ-ታ የጥሞና መጽሃፎች ፤ በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

@Appeal4purity
@Appeal4purity