መረጃ ዘመደመር
1.03K subscribers
48.8K photos
1.87K videos
17 files
15.9K links
Download Telegram
የቅዳሴ ስነ-ስርዓት ወቅት፣ የኢየሱስ ምስል ያለበት መስቀል በላያቸው ላይ የወደቀባቸው አንድ ካህን ህይወታቸው አለፈ።

በኢኳዶር ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቄስ ቅዳሴ ላይ እያሉ መስቀል በላያቸው ላይ በመውደቁ ሕይወታቸው አልፏል፤ በወቅቱም ሥነ ሥርዓቱ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ ነበር።

በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋራ አንድ ምስል እንዳሳየው፣ በጓያኪል የሚገኘው የ«ፐርፔቱኦ ሶኮሮ» ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አባት ፓትሪሲዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ቅዳሜ ዕለት ለምእመናኑ ንግግር እያደረጉ ሳለ፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለው የክርስቶስ ምስል ወድቆ በእሳቸው ላይ ሲያርፍ ያሳያል።

የጓያኪል ሊቀ ጳጳስ እሁድ ዕለት አባ ሞሊናሪ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በጻፉት ጽሁፍ እንዳረጋገጡት “በቤተክርስቲያኑ ቄስ ሆነው ያገለገሉት የተወደዱት አባ ፓትሪሺዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ወደ አባታችን ቤት መሄዳቸውን እናሳውቃለን።”፥ “የዘላለም ዕረፍት ይሁንለት፣ ጌታ ሆይ። የዘላለም ብርሃንም በእርሱ ላይ ይብራ። በሰላም ያድርሰው። አሜን።” ሲሉ መልዕክት አጋርተዋል።
የ19 ዓመቱ ኤርትራዊ ሚስጥሩን ለ AI ነግሮ የተፈጠረውን አስደንጋጭ መጨረሻ ተመልከቱ 👆👆👆
በጀግናው ጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራውና ባለፉት አመታት በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያሳየች የምትገኘው ኢትዮጵያ ሀገራችኝ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥና በምግብ ራሷን ለመቻል ለግብርና ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ቀን ከሌት ተግታ እየሰራች ትገኛለች።

የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ የመስኖ ልማትን ማስፋፋት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና የምግብ አቅርቦትን ማረጋጋት የዚህ ጥረት ዋና አቅጣጫዎች ናቸው።

ይህም የምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባለፈ የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራና ለዘላቂ ሀገራዊ ብልፅግና ወሳኝ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

የምግብ ሉአላዊነት የሀገራዊ ነፃነትና የዘላቂ ብልፅግና መሰረት መሆኑን በሚገባ የሚያውቀውና የሚረዳው የለውጡ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
በምግብ ራስን መቻል የሀገርን ክብርና ነፃነት ከማጠናከር ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የስራ እድልን ለማስፋፋትና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው።

በምግብ ራሷን የቻለች የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠችና ለዜጎቿ የተሻለ ነገ የምትገነባ ኢትዮጵያን መፍጠር በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት ካስቀመጣቸው የልማት አላማዎች መካከል ዋነኛው ነው።

የለውጡ መንግስት ህልምና ራዕይ ድህነትን ድል የነሳች በምግብ እራሷን የቻለች ከተረጂነት ወደ ረጂነት የተሸጋገረች እድገት ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምድረ እውን ማድረግ ነው
#ከቴክኖሎጂ_የተኳረፈችው_ሀገር!

“ሲም ካርድ ከማግኘት ወርቅ ማውጣት ይቀላል፣ ገንዘብ ቢያስፈልግዎት ከኤቲኤም እወስዳለሁ ማለት ዘበት ነው፣ ኤቲኤም ማሽን የሚባል የለምና፣ ባለንበት ዘመን ሲም ካርድ ለማግኘት በቱሪዝም ሚኒስቴር በኩል ሰነዶችን ማቅረብ ግድ የሚልባት የዓለማችን ብቸኛዋ ሀገር ሳትሆን አትቀርም፡፡”

ይህን የሚሉት “ከዓለም የተገለለችና የተቆለፈች፣ በድሮ ዘመን ላይ የቆመች” ሲሉ የሚጠሯት ሀገረ ኤርትራ ላይ የተገኙ በሚሊየኖች ተከታይ ያላቸው ተጓዥ ጋዜጠኛና ዩቱበሮች ናቸው፡፡

ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ፍትሕ ( #ህግደፍ ) ብቸኛው ፓርቲ የሆነባት፣ 19 89 ዓ.ም የጸደቀው ሕገ መንግሥትም በተግባር ያልዋለባት፣ የዚህችን ሀገር ዋና ከተማ “ትንሿ ሮም” ሲሉ ጠርተው ሀገሪቱን “አፍሪካዊቷ ሰሜን ኮሪያ” ያሏት እነዚሁ ጋዜጠኛና ዩቱበሮች ስለዚህች ሀገር ያዩትንና የታዘቡትን ሲናገሩ ለሰማ እውነት ነው ብሎ ለማመን የሚከብድ ጭምር ነው፡፡

ኤርትራን የጎበኙ ጋዜጠኞች ምልከታን የሚያሳየውን መሰናዶ በተከታዩ የመሿለኪያ ትዩብ ሊንክ ይመልከቱት!! 👇👇👇

https://www.youtube.com/@Meshualekia
የ #No_More_ስጋ ዘመቻ በአዲስ አበባ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ትልቅ መነጋገሪያ እየሆነ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከልክ ያለፈ የስጋ ዋጋ ጭማሪ ለመቃወም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተጀመረው “የስጋ ዋጋ ይቀንስ no more ስጋ” የተሰኘ የቦይኮት ንቅናቄ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል።

ዘመቻው በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን፣ የዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነውን የዋጋ ጭማሪ በመቃወም ድምፃቸውን እያሰሙበት ይገኛሉ።

ሸማቾች የስጋ ቤቶች የጣሉትን ተገቢ ያልሆነ ዋጋ እንዲያስተካክሉ ግፊት ለማድረግ፣ ጥያቄው እስኪመለስ ድረስ ስጋ አለመግዛትና ፍጆታን ማቆም እንደ አማራጭ እንዲወሰድ እየጠየቁ ይገኙበታል

የከተማ አስተዳደሩ የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስድም፣ በተለይ በትልልቅ የሉካንዳ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች የሚቀርበው የስጋ ዋጋ ማርገብ አልቻለም።

በአንዳንድ ታዋቂ የከተማዋ ስጋ ቤቶች የአንድ ኪሎ ግራም ስጋ ዋጋ እስከ 6 ሺህ ብር መድረሱ መነገሩ የህብረተሰቡን ቁጣ አባብሶታል።

ይህንን ተከትሎ የዘመቻው ተሳታፊዎች ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ጥራጥሬና አትክልት ምርቶች እንዲያዞር ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው። ይህ የዲጂታል አንድነት በስጋ አቅራቢዎችና ሻጮች ላይ የገበያ ግፊት በመፍጠር ዋጋውን ወደ መደበኛ እንዲያመጣው ይጠበቃል።

ምን ይመስላችኋል? በከተማችን የታየውን የዋጋ ጭማሪ ለመቋቋም እንዲህ ያሉ የቦይኮት ዘመቻዎች ምን ያህል ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ?

🥩 🥩 🥩
❤1
የለውጡ መንግስት የመደመር እሳቤን በተግባር በመተርጎም የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከር ልማትን ለማፋጠንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በተለያዩ ዘርፎች ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል። የመደመር እሳቤ ልዩነቶቻችንን እንደ ጥንካሬ በመቀበል በጋራ አላማና በትብብር ለሀገራዊ ሰላም ለዘላቂ ልማትና ለጋራ ብልፅግና እንድንሰራ የሚያበረታታ የሀገር ግንባታ እሳቤ ነው።

በዚህ እሳቤ ኢትይጵያን እየመሩ የሚገኙት ጠ/ሚ/ዶ/ር/ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን ወደ ልማትና ብልፅግና ለማሸጋገር በተለያዩ ዘርፎች ለውጦችን ለማምጣት እየሰሩ ይገኛሉ።

ይህም ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የልማት አቅሞችን በማስፋፋትና የዜጎችን ተሳትፎ በማበረታታት የተሻለች የበለፀገችና ለሁሉም ዜጎቿ ተስፋ የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ጉዞ ነው።
ግብርና ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ አመራር መሰረቱን ወደ አምራች ኢንዱስትሪም እያሰፋ ነው። በጠ/ሚር ዐቢይ ሃሳብ አመንጪነት ወደ ስራ የገባው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲነቃቃ እና እድገት እንዲያስመዘግብ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በግብአት እጥረት እና በቴክኒክ ችግር ከስራ ውጭ ሆነው የነበሩ ከ800 በላይ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው ባሻገር በአጠቃላይ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ምርታማነት በከፍተኛ መጠን አድጓል።

በዚህም በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በብዛት ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ መገኘትም ተችሏል።