መረጃ ዘመደመር
1.03K subscribers
48.8K photos
1.87K videos
17 files
15.9K links
Download Telegram
24 ቢሊዮን ዶላር‼️

እስካሁን ከህወሃት የተያዘው የጦር መሳሪያ መጠን 24 ቢሊዮን ዶላር ግምት እንዳላቸው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ወታደራዊ አባሪ ዛሬ በተደረገ ጉብኝት ላይ ተናግረዋል።

⚠️ ዋና ዋና የተያዙ መሳሪያዎች
📍በርካታ ሞሃጀር ድሮኖች፣ የካሚካዜ ድሮኖች፣ የድሮን ተተኳሽ
📍ረጅም እና አጭር ርቀት ሚሳኤሎች
📍ትላልቅ እና መካከለኛ መድፍ እና ተተኳሾች
📍ሞርታሮች፣ ፀረ-ታንክ፣ኮርኔት ሚሳኤሎች
📍ዲሽቃ፣በርካታ ጠመንጃዎች፣ የእጅ ቦምቦች፣ ስናይፐር፣ዠ
የሰውና የመኪና ፈንጂዎች...ይገኙበታል።
ባለፉት ዓመታት በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር/ ዐቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የዲሞክራሲ ባህልን ለማሳደግና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል።

ሰላም ያለ ዲሞክራሲ አይጸናም ዲሞክራሲም ያለ ሰላም እውን አይሆንም። ይህንን በሚገባ የተረዳው የለውጡ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የዜጎችን መብት ለማክበር የህዝብ ተሳትፎን ለማሳደግና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በመፍጠር ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።
የግብርና ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ለምግብ ዋስትና ለስራ እድል ፈጠራና ለዘላቂ ብልጽግና ወሳኝ መሰረት ነው።

በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር/ ዐቢይ አህመድ የሚመራው የመደመር መንግስት የሀገራችንን የግብርና አቅም በማሳደግ ምርታማነትን በማሻሻል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስፋፋትና ያሉንን የተፈጥሮ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም የምግብ ዋስትናዋን የተጠናከረ የኢኮኖሚ ነፃነቷ የተረጋገጠና ዘላቂ ብልፅግናዋን የተጎናፀፈች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።

ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋነኛ መሰረት ከመሆኑም በላይ ለበርካታ ዜጎቻችን የስራ እድል የሚፈጥር ለኢንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ የሚያቀርብ የወጪ ንግድ ገቢን የሚያሳድግና የሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገትን የሚደግፍ ወሳኝ ዘርፍ ነው።
ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ሀቅ ነው።

ቀይ ባህርና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ቀይ ባህር ያለ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ያለ ቀይ ባህር ሙሉ አትሆንም።

ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ ከተራ የጂኦግራፊ ጉዳይ በላይ ነው። ከታሪካችን ከኢኮኖሚያችን ከንግዳችንና ከቀጠናዊ ትስስራችን ጋር የተሳሰረ የሀገራዊ ጥቅማችን ወሳኝ አካል ነው።

ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም ነው።ቀይ ባህርና ኢትዮጵያ በታሪካዊ ትስስርና በጂኦግራፊያዊ ቅርበት የተሳሰሩ ናቸው። ይህ ትስስር ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ለአለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪነትና ለቀጠናዊ ትብብር ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ነው።

በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራው ኢትዮጵያ ሀገራችን በህዝብ ብዛቷ በኢኮኖሚያዊ እምቅ አቅሟና በቀጠናዊ ተሳትፎዋ የቀጠናው ወሳኝ ሀገር ናት።

ስለዚህም ከአለም አቀፍ ገበያዎች ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር የወጪና የገቢ ንግዷን ለማስፋፋት የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስና የሀገራዊ ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ የባህር በር ወሳኝ ነው።
"ወጣቶችን ከእድገት ጉዞ ለይቶ ማየት አይቻልም የመደመር መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል" - ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሊ
"ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል" - ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሊ
በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ በላይ የካሳ ክፍያ ክስ የተመሠረተበት የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጄክት ክስ የመጨረሻ ውሳኔ አገኘ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ግንባታው በ2013 ዓ.ም. የተቋረጠው ፕሮጄክቱ ከዓመታት የክስ ሂደት በኋላ መስከረም 13/ 2019 ዓ.ም. የመጨረሻ ውሳኔ ማግኘቱን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የባቡር መስመሩን እንዲገነባ ውል ያሰረው 'ያፒ መርከዚ ኢነሳት' የተባለው የቱርክ ኩባንያ ደረሰብኝ ባለው የግንባታ መጓተት፣ ውድመት እና ዝርፊያ ከወለድ ጋር 1.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ክስ በለንደን ዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት አቅርቦ ነበር።

ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ 👉🏾 https://bbc.in/4jU6IqU
ባንቺ ኃጢአት ነው ይህን ልጅ የወለድሽው እንዳይሉሽ ብዬ ነው ለ21 ዓመታት ያልመጣሁት” — ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ (እግረኛው ሚዲያ)

በማህበራዊ ሚዲያ እና በይዘት ፈጠራው ዘርፍ የሚታወቀው የ“እግረኛው ሚዲያ” መስራች እና ባለቤት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ፣ ከረጅም 21 ዓመታት የናፍቆት፣ የሐዘን እና የልብ ስብራት ርቀት በኋላ ከወላጅ እናቱ ጋር በድጋሚ ተገናኝቷል።

ይህ ሁሉ ዓመት እናቱን ሳያይ የቆየበት ምክንያት ሲገለጽ የብዙዎችን ልብ የነካ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው ወደ እናቱ ላለመመላለስ የወሰነው በራሱ ምክንያት በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ዘንድ የሚደርስባቸውን ነቀፋ፣ ስድብ እና የህሊና ጫና ለማስቀረት እንደነበር ተናግሯል። "በኔ ምክንያት እንዳይሰድቡሽ፣ ቡና መጠጫ እንዳያሳጡሽ..." በማለት የተናገረው ስሜታዊ ቃልም ለእናቱ ያለውን ጥልቅ አክብሮት እና ፍቅር ያሳየ ነበር።

* እናትየው በነበሩበት የርቀት ጊዜያት ልጃቸውን በቅርብ የሚያዩበት ብቸኛ ማስታገሻ የልጃቸው የዩቲዩብ ሚዲያ ስራዎች ነበሩ። ምሽት ላይ “እስኪ አምጡልኝ ልየው” በማለት ስክሪን ላይ በመመልከት ቀናትን በናፍቆት ያሳልፉ እንደነበር በስሜት ገልጸዋል።

* የዕንባ እና የሐዘን ቀናት አብቅተው ሁለቱ እናት እና ልጅ ፊት ለፊት የተገናኙበት ቅጽበት ታላቅ ደስታን ፈጥሯል።

* እናቲቱ ልጃቸውን አቅፈው ሲስሙ “ከእንግዲህ ፈጣሪን አላማርርም” በማለት ከልጃቸው መገኘት በላይ ምንም የሚመኙት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

ሰው ከሰው ጋር የሚራራቀው ሁልጊዜ በክፋት ወይም በጠብ አይደለም፤ አልፎ አልፎ እናቱን ከሰዎች ምላስ እና ስድብ ለመጠበቅ ሲል ህመሙን አቅፎ 21 ዓመት ሙሉ ራሱን የሚስዋ ልጅም አለ!

ይህ አጋጣሚ የቤተሰብ ፍቅርን፣ የትዕግስትን ዋጋ እና በውስጥ ተደብቀው የቆዩ ጥልቅ ቁስሎች በጊዜ ሂደት እንዴት ወደ እውነተኛ ይቅርታ እና ደስታ እንደሚቀየሩ የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነው።

“ ታተይ እንኳን ደስ አለሽ”

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
«ማብላት የሚያጸድቅ እንዳይመስላችሁ፤ ተሰብሰባችሁ ሰንበቴ ስለጠጣችሁ፣ ዝክሩን ስለዘከራችሁት... የለም፤ ደግነቱስ ሞልቷል ክርስቶስ የለም። ከውስጥ ክርስቶስ አይታይብህም ውሸትክን ነው፤ ትጠነቁላለህ፣ ቂም አለብህ፣ ታመነዝራለህ አድመኛ ነህ፤ ከላይ ግን ጻድቅ መሠለህ ትታያለህ። ​ማህበር ትጠጣለህ፣ ነጫጭ ትለብሳለህ፣ ታስቀድሳለህ፣ ከኪዳን ትገኛለህ፣ ከማህበሩም ትገኛለህ ግን ተንኮለኛ ነህ። ክርስቶስ ከውስጥ የለም፤ ተኩላ ነህ፣ ​እናንተን ብቻ እንዳይመስላችሁ እኔን ጨምሮ ማለቴ ነው! ግን እኔ መጨመሬ እናንተን አያጸድቃችሁም፣ እግዚአብሔር ሁላችንንም ንጹህ ልቦና ይስጠን።» ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን