መረጃ ዘመደመር
1.04K subscribers
48.8K photos
1.87K videos
17 files
15.9K links
Download Telegram
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ለመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፤ ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው።
‎
‎ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
‎
‎እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነው። በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለበተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል።

‎ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው። ሥራው መረጃዎች ተሰብስበው፣ ተቀናብረውና ተተንትነው ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዙ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች እና የመረጃ ማዕከላት መረብ ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው።
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጉብኝት
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ 15 አርአያ አፍሪካውያን ተርታ ውስጥ ተካተተ

መጽሔቱ 15ተኛ ዓመቱን በማስመልከት ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ ሃሳባቸው፣ ድምጻቸው እና ሥራቸው በአፍሪካ አኅጉር ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊና ዘላቂ ተፅዕኖ ማሳደር የቻሉ አፍሪካውያንን አካቷል።

ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች፣ ስምንት የዓለም ሻምፒዮናዎች፣ 27 የዓለም ሪከርዶችን መስበሩ በስፖርት ዘርፉ የተጠቀሱ የተጎናፀፋቸው ድሎች ባለቤት ሃይሌ ገብረስላሴ።

በንግድ መስክ፤ በ "ኃይሌ እና አለም ኢንተርናሽናል" ኩባንያ ስር በሆቴል፣ በመኪና ማምረቻ፣ በሪል እስቴት እና ግብርና ዘርፎች ተሠማርቶ ያገኘው ስኬት በዝርዝሩ ውስጥ እንዲካተት አስችሎታል።

አሊኮ ዳንጎቴ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ እንዲሁም የቀድሞው የኮትዲቯር እና ቼልሲ አጥቂ ዲዲዬር ድሮግባ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ጉልህ አፍሪካውያን ናቸው ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።
#ከጽናት_በላይ_የሆነ_የሀገር_ጋሻ

የሀገር ሉዓላዊነትና የሕዝብ ደህንነት የሚረጋገጠው በወሬ ሳይሆን በተግባር በሚፈተን ጽኑ ተቋም ነው።
በዘመናዊ እውቀትና በቁርጠኝነት የተገነባው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ ዛሬ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ ስጋቶችን በቅድመ-ዝግጅት የማክሸፍ እና ሰላምን በዘላቂነት የመጠበቅ ሁለንተናዊ አቅም ገንብቷል።

ይህ ሠራዊት የትናንት የጀግንነት ውርስ ብቻ አይደለም፤ የነገዋ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የሰላም ዘበና የፅናት ተወካይ ነው! 🇪🇹💪
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና ጥገኝነት ተላቆ ወደ ኢንዱስትሪም እንዲሰፋ በማድረግ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ የሚመራው መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ፣ የሀገር ውስጥ የግብዓት አቅርቦት እንዲሻሻል በመደረጉ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች በመመቻቸታቸው የምርት መጠንና ጥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አድጓል።

በዚህም በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪ መቆጠብ፤ በውጭ ገበያ ተወደዳሪ የሆኑ ምርቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ከመቻሉ ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል።
#ታሪካዊ_ወዳጅነት_በላቀ_አመራር_ሲታደስ!

ኢትዮጵያ እና እስራኤል ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።

ዛሬ ደግሞ ይህ ታሪካዊ ትስስር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዲፕሎማሲ ችሎታ፣ ዕውቀትና መሪነት አዲስ ምዕራፍ ይዟል!

ሁለቱ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የሰላም ውጥረቶች ዙሪያ ያላቸውን አጋርነት በጽኑ መሠረት ላይ እያደሱ ይገኛሉ።
#የዲፕሎማሲ_ከፍታ_እና_የሀገር_ተሰሚነት!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ባደረጉት ሁለትዮሽ ግንኙነትና በወቅታዊ ቀጠናዊ ልማቶች ዙሪያ ያደረጉት ሰፊ ምክክር፣ የጠ/ሚ ዐቢይን ስልታዊ የዲፕሎማሲ አመራር በግልጽ ያሳየ ነው!

በጋራ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ላይ ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያረጋገጡት ቁርጠኝነት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ከፍተኛ ተሰሚነትና የፖለቲካ ክብደት ያረጋግጣል።
በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ አመራር በአፍሪካ ግዙፍ የሆነ ኢኮኖሚ የገነባችው እንዲሁም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ዋስትና የሆነ በባህር ሃይል ጭምር የተዋቀረ መከላከያ ሃይል የገነባችው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ሀገር ሆናለች።

ሃያላኑ የዓለም ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር የንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ወታደራዊ ትብብር የመመስረት ፍላጎት እያሳዩ ነው። ይህ ለሀገሪቱ ትልቅ የዲፕሎማሲ አቅም ፈጥሯል።

ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ ትላንት ከሃያሏ እስራኤል ጠ/ሚር ቤኒያሚን ናታኒያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የዚህ ማሳያ ነው።