Forwarded from Tips ... ለአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሰልጣኞች እና ለአሽከርካሪዎች ጠቃሚ መረጃዎች
በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ።
በከተማችን አዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ወንጀል የመፈፀም፣ የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ የመንገድ ትራፊክ ህጎችን የመጣስ ( በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ.) በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉን ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቦ የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸው እና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይከል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል፡፡

Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ለመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፤ ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው።
ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነው። በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለበተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል።
ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው። ሥራው መረጃዎች ተሰብስበው፣ ተቀናብረውና ተተንትነው ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዙ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች እና የመረጃ ማዕከላት መረብ ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው።

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ 15 አርአያ አፍሪካውያን ተርታ ውስጥ ተካተተ
መጽሔቱ 15ተኛ ዓመቱን በማስመልከት ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ ሃሳባቸው፣ ድምጻቸው እና ሥራቸው በአፍሪካ አኅጉር ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊና ዘላቂ ተፅዕኖ ማሳደር የቻሉ አፍሪካውያንን አካቷል።
ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች፣ ስምንት የዓለም ሻምፒዮናዎች፣ 27 የዓለም ሪከርዶችን መስበሩ በስፖርት ዘርፉ የተጠቀሱ የተጎናፀፋቸው ድሎች ባለቤት ሃይሌ ገብረስላሴ።
በንግድ መስክ፤ በ "ኃይሌ እና አለም ኢንተርናሽናል" ኩባንያ ስር በሆቴል፣ በመኪና ማምረቻ፣ በሪል እስቴት እና ግብርና ዘርፎች ተሠማርቶ ያገኘው ስኬት በዝርዝሩ ውስጥ እንዲካተት አስችሎታል።
አሊኮ ዳንጎቴ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ እንዲሁም የቀድሞው የኮትዲቯር እና ቼልሲ አጥቂ ዲዲዬር ድሮግባ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ጉልህ አፍሪካውያን ናቸው ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።

#ከጽናት_በላይ_የሆነ_የሀገር_ጋሻ
የሀገር ሉዓላዊነትና የሕዝብ ደህንነት የሚረጋገጠው በወሬ ሳይሆን በተግባር በሚፈተን ጽኑ ተቋም ነው።
በዘመናዊ እውቀትና በቁርጠኝነት የተገነባው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ ዛሬ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ ስጋቶችን በቅድመ-ዝግጅት የማክሸፍ እና ሰላምን በዘላቂነት የመጠበቅ ሁለንተናዊ አቅም ገንብቷል።
ይህ ሠራዊት የትናንት የጀግንነት ውርስ ብቻ አይደለም፤ የነገዋ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የሰላም ዘበና የፅናት ተወካይ ነው! 🇪🇹💪