መረጃ ዘመደመር
1.03K subscribers
48.8K photos
1.87K videos
17 files
15.9K links
Download Telegram
#ኦነግ የመንግሥትን የባሕር በር
ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ።

ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የመንግሥትን የባሕር በር የማግኘት ጥረት በቅንነት እንደሚደግፍ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረና ኢኮኖሚዋም እያደገ መሄዱን የገለጠው ኦነግ፣ ለዚህ ደሞ የባሕር በር ማግኘት አማራጭ የለውም ብሏል።

ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች የሀሳብ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅምና ደኅንነት በጋር የሚሠሩበት ጊዜው አሁን ነው ሲል ኦነግ ጥሪ አቅርቧል።
👍1
"ወደ ኤርትራ መሸሽ ወደ ሲኦል እንደመሄድ ነው" TPF

የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ተከማችተው እንደሚገኙ ቲፒኤፍ ይፋ አደረገ፡፡ አመራሮቹ ወደ ኤርትራ እንሻገር አንሻገር በሚለው ዙሪያ ለሁለት ተከፍለዋል ብሏል፡፡

የቲፒኤፍ ኃይል ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫውም የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የት እንዳሉ እንደሚያውቅ ይፋ አድርጓል፡፡ የቡድኑ ቃል አቀባይ በጋዜጣው መግለጫቸው፣ ‹‹የተሸነፈው የሕወሓት ቡድን ባሁኑ ወቅት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ ተሰብስቦ እንደሚገኝ እናውቃለን›› ብለዋል፡፡ የቡድኑ አመራሮች ‘ወደ ኤርትራ እንሻገር’ በሚሉና ‘አንሻገርም’ በሚሉ ኃይሎች ለሁለት ተከፍሎ ከባድ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል ብለዋል፡፡

‹‹በሕይወት እያሉ ደደ ኤርትራ መሸሽ ወደ ሲኦል መሄድ ማለት ነው›› ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ‹‹ስለዚህ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ ተሰብስባችሁ የምትገኙ የፈትለ-ፅዮን ቡድን ታጣቂዎችና ካድሬዎች አገራችሁን ጥላችሁ አትሂዱ፤ የትግራይ መጻኢ ዕድል ብሩህ ነው፤ ተስፋ ሰንቃችሁ፣ ምሕረት እንደሚደረግላችሁ ተረድታችሁ በሃገራችሁ እንድትቆዩ እና ወደ አሃዶቻችሁ በመሄድ እጃችሁን እንድትሰጡ ይመክራል›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መከላከያ ሰራዊቱ አድዋን ተቆጣጥሮ ራማን ለመቆጣጠር ከጫፍ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ የሕወሓት ኃይሎች አክሱም ከተማን ለቀው ወጥተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በአዲግራት ዙሪያ ከባድ ውጊያ ሲደረግ ውሏል፡፡ በርካታ ከባባድ መሳሪያዎችም ተማርከዋል፡፡

መከላከያ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በአዲግራት ዙሪያ ከቀርሳበር እስከ ፊያ ቀሺ በተባለ ቦታ የነበረውን የጠላት ሀይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በርካታ ወታደራዊ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ወደ ፋፂ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡ ህወሃት በዛሬው ዕለት በርካታ ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉበት ሲሆን መድፍን ጨምሮ የተለያዬ ዓይነት ተተኳሽ ተማርኳል።
የ155 ሚ ሜ መድፍ ጥይት
የ130 ሚ.ሜ መድፍ ጥይት
T55 እና T72 ታንኮች ጥይት
የዲሽቃ ጥይት
የብሬን ጥይት
የስናይፐር ጥይት
የክላሽ ጥይት
01 መድፍና
2 ዲሽቃ በቁጥጥር ስር ውሏል።
እስካሁን ለሚዲያ ያልተናገርኩትን አንድ ነገር ልናገር... 👆 👆 👆
የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ

የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ቀባአዴድር) በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ ያካሄደውን ሕዝባዊ ጉባኤ አጠናቋል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እና የህግደፍ መንግሥት በአፋር ሕዝብ ላይ ለፈጸሙት በደልና ሰብአዊ ጥሰት ተጠያቂ እንዲሆኑና ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጥሪ አቀረበ። በተጨማሪም የሕዝቡ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲከበርና በኤርትራውያን ላይ የሚፈጸሙ እስራቶች እንዲቆሙ ጠይቋል።

ድርጅቱ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የፖለቲካና የወታደራዊ አቅሙን ሲገነባ የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡም አዳዲስ ታጋዮችን ማስመረቁንና የባሕር ኃይል አቅሙን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አስታውቆ ነበር። እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ከእስራኤል እገዛ ለማግኘት ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ትኩረት አግኝተዋል። ድርጅቱ ህግደፍ ተደምስሶ የሕዝቡ መብት እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል ገልጿል።

ይህ ጉባኤ የተካሄደው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት ወቅት ነው።

ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኤርትራ ኃይሎች ድንበር አልፈው ወረራ ፈጽመዋል ስትል ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አቅርባለች።
Forwarded from Sheger Times Media️
🔴2 ሺህ ጥይት በአንድ ደቂቃ!

ከአሜሪካ ጦር እስከ ሩሲያ፣ ከቻይና እስከ እስራኤል ጦር ድረስ ታጥቀውታል፣ መልኩ ቢመሳሰልም አይነተ ብዙ ነው፡፡
አንድ የሚያደርገው ነገር ግን አደገኛነቱና ፍጥነቱ ነው፡፡በ1 ደቂቃ ውስጥ በሶስት አፈሙዞቹ ሁለት ሺህ ከባድ ጥይቶችን ይተኩሳል፡፡

ተሸከርካሪ ስርዓት ባላቸው ሶስት አፈሙዞችና በተገጠመለት የኤሌክትሪክ ሞተር እንደ መብረቅ እያስገመገመ በሰከንዶች አንደ ዶፍ ዝናብ በሚያዘንባቸው ጥይቶቹ የዓለማችን ፈጣን መሳሪያ አሰኝቶታል፡፡

በቻይናው ኖሪንኮ ግሩፕ ተመርቶ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እጅ የገባው የዚህ አስፈሪ አደገኛ መሳሪያ ታሪክ እስካሁን በነገርናችሁ የተኩስ ፍጥነቱ ብቻ አያበቃም…..

ሙሉ መሰናዶውን በተከታዩ ሊንክ  ይመልከቱት፡፡
**
 ⬇️
https://youtu.be/h5wwyUcTbn8?si=dri6WvmA74Gg0QZ0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአሁኑ ግጭት መንግስት በፖለቲካም፣ በጦርም፣ በዲፕሎማሲም እራሱን እንዳበቃ አረጋግጠናል

በአሁኑ ወቅታዊ ግጭት መንግስት በፖለቲካው፣ በወታደራዊው መስክ እንዲሁም በዲፕሎማሲው ዘርፍ እራሱን በበቃ ሁኔታ ያዘጋጀና የተቀናጀ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። በተለይም በሁሉም መስክ የበቃ፣ የተጠበቀና ሀገራዊ ሉአላዊነትን የማስከበር ከፍተኛ ብቃት ያለው ሰራዊት መገንባቱን በተግባር ያየንበት ወቅት በመሆኑ፣ ይህ ስኬት ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ሰላምና ዘላቂ እድገት ትልቅ መሰረት ጥሏል ማለት ይቻላል።

ይህንንም ተከትሎ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለመንግስትና ለሀገር እና ለሰራዊቱ ያላቸውን የማይወለወል አቋምና ወታደራዊ አጋርነት በደመቀ ሁኔታ ገልጸዋል። በመላ ሀገሪቱ የተሰበሰበውና እየተደረገ ያለው ሰፊ የህዝብ ድጋፍ የህዝቡን አንድነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ሰራዊቱ ለሀገር የሚያደርገውን መስዋዕትነት ህዝቡ በአንድ ድምፅና በከፍተኛ ኩራት እንደሚደግፈው ማረጋገጫ ሆኗል።
ዶክተሩን ሚስቴን እያማገጣት ነው ብሎ በመጠርጠር በሽጉጥ ተኩሶ ያቆሰለው ባል

በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የተኮሰው ባል በፖሊስ እጅ ከገባ በኋላ የወጣው አስደንግጭ እውነት ግን የመላውን ህዝብ ልብ ሰበረው።​ዶክተር ዳንኤል በሆስፒታሉ ውስጥ በስነ-ምግባሩና በታታሪነቱ የሚታወቅ የስነ-ተዋልዶና የወሊድ ህክምና ስፔሻሊስት ነበር ።

ላለፉት አምስት ወራት ሀና የምትባል ውብ ታካሚውን በከፍተኛ ምስጢርና ትኩረት ይከታተላት ነበር ።​ሀና በከባድና አጣዳፊ የማህጸን ካንሰር (Advanced Reproductive Malignancy) የምትቃጠል ሲሆን "ባሌ እንዳያዝንና እንዳይደነግጥብኝ እውነቱን ደብቅልኝ" ብላ በመለመኗ ዶክተሩ ህክምናዋን በሚስጥር ይከታተል ነበር ።

​ነገር ግን የሀና ባል፣ ሚስቱ ተደጋግማ በምስጢር ወደ ዶክተሩ ክፍል ስትመጣ፣ የስልክ መልእክቶች ሲላላኩ እና ዶክተሩ ለእሷ የሚያሳየውን ልዩ ትኩረት ሲያይ "ዶክተሩ ሚስቴን እያማገጣት ነው" በሚል የሀሰት ጥርጣሬና ቅናት አእምሮው ታወረ።

​አንድ ቀን ማታ ባል በቁጣ ተነሳስቶ የዶክተሩ ቢሮ በር ሰብሮ በመግባት "ሚስቴን አትነካትም! "ብሎ በያዘው ሽጉጥ አራት ጊዜ ተኮሰበት! ዶክተር ዳንኤል ትከሻውና ጎኑ ላይ በወደቁት ጥይቶች ተመቶ በደም አብጦ መሬት ላይ ወደቀ።

​በቦታው የደረሱ የፖሊስ አባላት ባልን በካቴና አስረው ሲወስዱት፣ ባል በወደቀው ዶክተር ላይ ይፎክርና ይሳደብ ነበር ።

​ዶክተር ዳንኤል በደረሰበት ከባድ የጥይት ቁስል አጣዳፊ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት ከሞት አፍፍ ተመለሰ። ፖሊስ ባልን ወደ ህክምና ክፍሉ አምጥቶ ባስገበው ጊዜ፣ ባል ያየው ነገር ግን ህሊናውን ሙሉ በሙሉ አደቀቀው።​በወቅቱ ሀና ከፅኑ ህክምና አልጋዋ ላይ ሆና እያለቀሰች የህክምና ፋይሏን ለባሏ አቀረበችው።

​ዶክተር ዳንኤል በዚያን ቀን ጥይት ከመታቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የራሱን ደምና ከውጭ ሀገር በራሱ ውድ ወጪ ያስመጣውን ብቸኛ የካንሰር ማዳኛ መድኃኒት ለሀና ሰጥቶ ህይወቷን ከሞት አትርፎላት ነበር!

​በጣም ልብ የሚሰብረው ደግሞ፣ ዶክተሩ የተኮሰበትን ባል ሊከሰሰውና ሊያስፈርድበት ሲችል «እሱ ሳያውቅ በቅናትና በፍርሃት ተደናግሮ ነው፤ ሚስቱ አሁን የእሱን እንክብካቤ ትፈልጋለች» በማለት ይቅርታ አድርጎለት ክሱን ሙሉ በሙሉ አነሳለት!

​ባል በእግሩ ስር ወድቆ በእንባ እየታጠበ «ወንድሜን ልገድለው ነበር!» ብሎ ተንሰቀሰቀ። ዛሬ ሀና ከህመሟ ሙሉ በሙሉ አገግማ፣ ከባሏ ጋር ሆና የዚያን ደግ ሀኪም ውለታና መስዋዕትነት በደስታ እያሰቡ ይኖራሉ!

«በጥርጣሬና በቅናት የሚወሰዱ ስሜታዊ እርምጃዎች የሰዎችን ህይወት ያጠፋሉ፤ የህክምና ባለሙያዎች ለታካሚዎቻቸው የሚያደርጉት መስዋዕትነት ሁልጊዜ ከምናስበው በላይ ጥልቅ ነው!»
👍1
Forwarded from Z Info. 🏆
Forwarded from Z Info. 🏆
ዛሬ ከእስራኤል ቤርሳቤህ የተሰማው ዜና የብዙዎችን ልብ የሰበረ ነው 😭 25 ሙሉ ዓመታት አብረው ኖረው፣ ልጆች ወልደው፣ ከተለያዩ ገና 3 ወራቸው ነበር። ነገር ግን... ይህ የፍቺ ጊዜ የውስጥ ቁስልን አላዳነውም። የቀድሞ ባል የቤቱን ቁልፍ ተጠቅሞ ገብቶ፣ የ5 ዓመት ልጃቸው ባለበት ቤት ውስጥ፣ ውዷን እናት እና ጎረቤት አክባሪዋን ናኒያ ሜልዳን በጭካኔ ህይ*ወቷን ነጥቋል። ከዛስ? ራሱ ስልኩን አንስቶ 'ሚስቴን አደጋ አድርሼባታለሁ' ብሎ ለፖሊስ ደወለ። የዚህን አሳዛኝ ክስተት ሙሉ መረጃ እና ትንታኔ አብረን እንይ...

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የ40 ዓመቷ ናኒያ ሜልዳ፣ በእስራኤል ቤርሳቤህ ከተማ በምትገኘው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ሰንበት ማለዳ ላይ በቀድሞ ባለቤቷ በደረሰባት አሰቃቂ ጥቃት ህይወቷ አልፏል። ፖሊስ ወደ ስፍራው ሊደርስ የቻለው ራሱ ጥቃት አድራሹ ስልክ ደውሎ ሪፖርት በማድረጉ ነው። የህክምና ባለሙያዎች በስፍራው ደርሰው እርዳታ በማድረግ ወደ ሶሮካ ሜዲካል ሴንተር ቢወስዷትም፣ ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።
የሟች ዘመዶች እና ጎረቤቶች እንዳሉት አብዛኛው የናኒያ ቤተሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኘው። ጎረቤቶቿ "ሁሌም ፊቷ ላይ ፈገግታ የማይጠፋ፣ ለማህበረሰቡ አሳቢ እና ድንቅ እናት ነበረች፤ በቤታቸው ውስጥም የጸብ ድምጽ ሰምተን አናውቅም" ሲሉ በድንጋጤ ገልጸዋል።

የናኒያ ሜልዳ አሳዛኝ ህልፈት ከፍቺ በኋላ ያለውን የሴቶች የደህንነት ስጋት የሚያሳይ ነው። ፍቺ በወረቀት ላይ ቢጠናቀቅም፣ የቀድሞ አጋር የቤቱን ቁልፍ ይዞ መቅረቱ እና የህግ የጥበቃ ስርአቱ ምን ያህል ክፍተት እንዳለው ያሳያል። 'ሴቶችን ከጥቃት እንጠብቅ' የተሰኘው ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዳሉት፣ ይህ ክስተት ሀገሪቱ በሴቶች ላይ የሚደርስን የቤተሰብ ውስጥ ጥቃት ለመከላከል አሁንም ሰፊ፣ ሀገራዊ እና በበጀት የተደገፈ ስራ እንደሚቀራት የሚያጋልጥ ነው። በተለይም ከ25 ዓመት ረጅም የትዳር ጊዜ በኋላ የሚመጣ ፍቺ፣ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ፣ ጥንዶች ከፍቺ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን የባለሙያ ክትትል ምን ያህል ችላ እንደተባለ ያመላክታል።

ፍቺ የጋብቻ መጨረሻ እንጂ የጥቃት እና የበቀል መጀመሪያ መሆን የለበትም! በተለይ በዲያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ የቤተሰብ ግጭቶች ወደ አላስፈላጊ አደጋ ከማምራታቸው በፊት፣ የስነ-ልቦና ማማከር እና ጥብቅ የደህንነት እርምጃዎች (እንደ የቤት ቁልፍ መቀየር ያሉ ጥንቃቄዎች) ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ የናኒያ ህልፈት ትልቅ ማሳያ ነው። ማንም ሰው የህይወት አደጋ ስጋት ካለው፣ ዝምታን ሰብሮ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ የህይወት እና የሞት ጉዳይ ነው!
ታላቁ የታሪክ ስሕተት የሚታረምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል
#ጊዜው_አሁን_ነው
#አሁንንንንንንን
በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ።

በከተማችን አዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ወንጀል የመፈፀም፣ የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ የመንገድ ትራፊክ ህጎችን የመጣስ ( በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ.) በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉን ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቦ የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸው እና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይከል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል፡፡ 
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ለመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፤ ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው።
‎
‎ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
‎
‎እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነው። በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለበተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል።

‎ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው። ሥራው መረጃዎች ተሰብስበው፣ ተቀናብረውና ተተንትነው ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዙ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች እና የመረጃ ማዕከላት መረብ ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው።