ለጋምቤላ የፖሊስ አባላት የተሰጠ ማሳሰቢያ 👇
በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ርቀው የሚገኙ የክልሉ አድማ ብተና ፖሊስ አባላት በሙሉ፤ ኮሚሽኑ የሚከተለውን ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።
ከዛሬ ከመስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እያንዳንዱ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት በየምድብ የሥራ ቦታቸው በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን ።
በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተንቀሳቀሱት አባላትም በአቅራቢያችሁ ለሚገኙ ለወረዳዎች አስተዳደር የፓሊስ መዋቅር በአፋጣኝ ሪፖርት እንድታደርጉ ሆኖ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተው ሪፖርት በማያደርጉ አባላት ላይ ኮሚሽኑ ተገቢውን ጥብቅ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አበክሮ ያስገነዝባል። ለዚህም ተግባር ተፈጻሚነት እንዲሆን በየደረጃው የተመደቡ የአድማ ብተና እና የመደበኛ ፓሊስ አመራሮች ተገቢውን እንዲያደረጉ ጭምር በጥብቅ እናሳስባለን።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
መስከረም 24/2019 ዓ.ም

Forwarded from Z Info. 🏆
ከ22 ነዋሪዎች መካከል አንዱ ሚሊየነር የሆነባት ከተማ። ኒው ዮርክ ሲቲ የአለም ባለጠጎች መገኛ ከተማ ሆናለች።
ከተማዋ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ በአለም ላይ በርካታ ባለሀብቶች የሚኖሩባት የአንደኝነት ደረጃን የያዘች ከተማ በመሆን አውራነቷን አረጋግጣለች።
ከተማዋ የያዘችው ግዙፍ ሀብት እና የባለሀብቶች ብዛት በቁጥር ሲቀመጥ ከፍተኛ ነው።
በዚህም በከተማዋ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያላቸው 384,500 ሚሊየነሮች መኖራቸው ታውቋል።
እንደዚሁም 66 ቢሊየነሮች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ በከተማዋ 3 ትሪሊዮን ዶላር የግል ሀብት አለ ተብሏል።
በሪፖርቱ መሠረት በከተማዋ ከ22 ነዋሪዎች መካከል አንዱ ሚሊየነር ነው።
ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ የከተማዋ ሚሊየነሮች ቁጥር በ 45 በመቶ አድጓል።
በዚህም ኒው ዮርክ እንደ ሳን ፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ፣ ቶኪዮ ሲንጋፖር ያሉ የአለም ግዙፍ ከተሞችን በሀብት መጠን በልጣ በመሪነት ላይ ትገኛለች።
ይህ ሁሉ ትሪሊዮን ዶላር በሚፈስባት ከተማ ውስጥ ሌላ አሳዛኝ እውነታ አለ።
ኒው ዮርክ በአንድ በኩል የአለም ሀብታሞች መገኛ ብትሆንም በሌላ በኩል ለተራው ህዝብ እና ለሰራተኛው ክፍል ከባድ እና ተስፋ አስቆራጭ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ሆናለች ነው የተባለው።
በከተማዋ የመካከለኛ የቤት ኪራይ ዋጋ በወር እስከ 5,000 ዶላር ደርሷል።
ለአነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የሚሆኑ ቤቶች አቅርቦት እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ ተገልጿል።
በከተማዋ ከሚኖሩ ነዋሪዎች መካከል 1/4 የሚሆኑት በድህነት ውስጥ ይኖራሉ ተብሏል።
በአጠቃላይ ኒው ዮርክ በአንድ በኩል የአለም ሀብታሞች መኖሪያ በሌላ በኩል ደግሞ ሰራተኛው በኑሮ ውድነት የሚፈታተንባት ከተማ ሆና ቀጥላለች።

#ኢትዮጵያ_ትችላለች
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ላይ ረጅምና ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ ታሪክ ካላቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ነች፡፡
የኢትዮጵያ የሀገረ መንግስት ግንባታ ታሪክ ከጥንታዊው ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፈ ረጅም እና ውስብስብ ሂደት ነው፡፡
ያለፉት መንግስታዊ ሥርዓቶች በሀገሪቱ ሁለንተናዊ የልማትና ሰላም እንቅስቃሴዎች ውስጥ የየራሳቸው ጥንካሬ እና ውስንነት ቢኖራቸውም በተለይ በብሔረ መንግስት ግንባታ ላይ ከፍተኛ ክፍተቶች መኖራቸውን ምሁራን ያስረዳሉ፡፡
በተለይ ከታሪክ እና ትርክት ጋር በተያያዘ አለመግባባቶች ከመኖራቸውም በላይ፣ እንደ ሀገር የጋራ የሆነ ብሔራዊ ትርክት በመገንባት ረገድ ውስንነቶች ነበሩ፡፡
ከማዕከላዊ መንግስትና ከክልሎች የኃይል ሚዛን ጋር በተያያዘም የመንግስት ሥልጣንን አግባብነት ባለው መልኩ ወደ ታችኛው የስልጣን እርከን ከማውረድና ከማስተዳደር አንፃርም እጥረቶች ነበሩ፡፡
ማዕከላዊው መንግስት ሲጠናከር ክልሎች ይዳከማሉ፤ በተቃራኒው ደግሞ ማዕከላዊ መንግስቱ ሲዳከም ሀገሪቱ ወደ መፈራረስ አደጋ ትገባለች የሚሉ ስጋቶች እንደነበሩም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የብሔር እና የዜግነት ፖለቲካ ውጥረት፣ የመንግስት ተቋማት ገለልተኛ አለመሆን፣ አካታች እና ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር አለመፈጠሩ እና ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ መረከብ የሚያስችል የፖለቲካ ባህል አለማዳበሩ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱ ውስጥ ከተስተዋሉ ውስንነቶች መካከል ዋንኞቹ ናቸው፡፡
ልዩነቶችን በውይይት እና በምክክር ከመፍታት ይልቅ፣ የኃይል እርምጃን ወይም ፖለቲካዊ ማግለልን መምረጥ ለዘመናት የቆየ የሀገረ መንግስት ስብራት ሆኖ መቀጠሉን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬም ከምትፈተንባቸው ዋንኛ የጸጥታ ችግሮች መካከል አንዱ የመንግስት ስልጣንን በኃይልና በጉልበት ለመቀማት የሚደረግ ፍላጎት ሲሆን፣ ዛሬም እንደትናንቱ በጦርነት፤ በመጠፋፋት፤ በሴራና በተንኮል መንግስትን ገልብጠው ህዝብን ለመምራት የሚፈልጉ ኋለ ቀር ኃይሎች አሉ፡፡
ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በባህል፣ በህዝብ ብዛት፣ በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ በስነምህዳራዊ አቀማመጥና በሌሎች ሀብቶች የታደለች ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በሀገረ መንግስት ግንባት ሂደት ውስጥ ያጋጠሟትን እነዚህንና መሰል ተግዳሮቶችን በሰለጠነ መንገድ መክሮና ዘክሮ የሚፈታ መንግስት መመስረት ባለመቻሏ ከጦርነትና ከድህነት አዙሪት መላቀቅ አልቻለችም፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ከኢትዮጵያ ያነሰ የሀገረ መንግስት ግንባታ ታሪክና እድሜ ያላቸው አንዳንድ የዓለም ሀገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ መንግስት፣ ሀገርና ኢኮኖሚ ከመገንባት አልፈው የሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማስፈን በቅተዋል፡፡
በተለይ የለውጡ መንግስት ወደ አመራርነት ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ሀገሪቱ በተለያዩ ዘርፎች ያሉባትን የረጅም ዘመናት ውዝፍ ስብራቶች ለመጠገን ባደረገው ብርቱ ጥረት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር፣ መንግስት በህዝብ ይሁንታና ምርጫ ብቻ እንዲመሰረት፣ የፖለቲካና የሀሳብ ልዩነቶች በምክክር ብቻ እንዲፈቱ ተደርጓል፡፡
ዋንኛ የሀገሪቱ የጸጥታ ችግርና የልዩነት መንስኤ የሆኑትን የታሪክ እና ትርክት ስብራት ለመጠገን በተከናወኑ መሰረተ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች የወል ትርክትን ለመገንባት የሚያስችሉ ጽኑ የመሰረት ድንጋዮች ተቀምጠዋል፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩነቱን አክብሮና አንድነቱን ጠብቆ የሚኖር ማህበረሰብ እየተገነባ በመሆኑ ብዝሃነት የግጭትና የጦርነት መንስኤ መሆኑ ቀርቶ የሀገሪቱ የልማትና የሰላም ጸጋ፣ ሀብትና ምሶሶ ለመሆን በቅቷል፡፡
የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌላውን ብሔር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋና ማንነት የሚያከብር፤ የሚቀበልና ከጥላቻ የጸዳ ትዉልድና ማህበረሰብ እየተፈጠረ መጥቷል፡፡
የሰላምና የልማት ጸር ብቻ ሳይሆኑ እንደ ማህበረሰብ እና ሀገር አብሮ ለመኖር ሲያስቸግሩ የነበሩ ጽንፈኛ፣ ዘረኛ፣ ከፋፋይና አክራሪ እሳቤዎች በወንድማማችነት፣ አብሮነትና እኩልነት እሳቤዎች መተካት ጀምረዋል፡፡
ከተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘም ከፖለቲካዊ ሥርዓቶች ጋር የማይቀያየሩ፣ ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋማትን ለመፍጠር የሚያስችሉ መሰረቶች ተጥለዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን ጨምሮ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ መልክ እየተገነቡ ያሉት መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ብቻ ሳይሆኑ ኢኮኖሚውን የሚያሳልጡና ሀገርን የሚያሻግሩ ናቸው፡፡
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ለመጠፋፋትና ለመገዳደል የሚፈላለጉ፣ ስልጣን ቀረብኝ ብለው ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የሚተባበሩ ሳይሆኑ፣ አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ከተመረጠው መንግስት ጋር ስልጣን ተጋርተው አብረው የሚሰሩና ለሀገራዊ ልማትና ሰላም በጋራ የሚቆሙ ለመሆን በቅተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ሀሳብን በሀሳብ የማሸነፍ አዲስ የፖለቲካ ባህል በመገንባት ላይ ሲሆን፣ የፖለቲካና የሀሳብ ልዩነት እርግማን ሳይሆን በረከት እየሆነ መጥቷል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡና በመገንባት ላይ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችና ሌሎች የልማት ስራዎች፣ ሁሉንም የሀገሪቱን ክፍሎችና ዜጎች ያሳተፉና ማዕከል ያደረጉ መሆናቸው ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ መደላድል ፈጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ በግብፅ፣ በሻዕቢያና ህገወጡ የህወሃት ቡድን ምክንያት ያጣችውን የባህር በር ለማስመለስ እያደረገች ያለው ብርቱ ጥረት የትናንትናውን የታሪክና የኢኮኖሚ ስብራት የሚጠግን ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ከመልክዓ ምድራዊ እስረኝነት ነጻ የሚያወጣ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው አዲሱ መንግስታዊ ሥርዓት ያለፉት ሥርዓቶች የፈጠሩትን በርካታ ስብራቶች የሚጠግንና የሚያክም፣ ለወደፊቱም መሰረት የሚጥል ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ልዕለ ኃያል ሀገር ሆና እንድትወጣ የሚያደርግ ርዕይ የሰነቀ ነው፡፡

የፌዴራል መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል
ኢትዮጵያ ያካሄደችውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ አዲሱን መንግሥት የምትመሠርትበት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች።
በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት ምስረታ ሂደት መከናወኑን ተከትሎ፤ ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት ይመሠረታል።
በዚህ መድረክ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ የመክፈቻ ጉባዔያቸውን ያካሄዳሉ።
በዚህም የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤዎች እና ጠቅላይ ሚኒስትር ይሰይማሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ዛሬ የሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የጀመረቻቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በቁርጠኝነት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኗን የሚያበስር ታላቅ ቀን ነው።

እንኳን ኤርትራና ወያኔና ሱዳን ሌላም ቢጨመር በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ቅንጣት ታክል ስጋት የለብንም። ቅንጣት ታክል። ያን ለመከላከል የሚያስችል ብቃት እየገነባን ነው ያለነው ጊዜው ሲደርስ እንዳስፈላጊነቱን እንገልጻለን እኛ ስጋት የለብንም።
ሰዎች ባረጀ ባፈጀ ስልት ድሮ በሰራ ስልት አሁን ለመጠቀም መሞከር ጠቃሚ አይደለም ምክንያቱም ያኔ ስልቱ የሰራው በሸበጥ፤ በጫፈሬ፤ በላስቲክ ጫማ መሄድ የፈለገ መቅመል የፈለገ መራብ የፈለገ ቢገባውም ባይገባውም ወስኖ የተከተለ ኃይል ነበረ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት በፓርላማ ከተናሩት የተወሰደ
ሰዎች ባረጀ ባፈጀ ስልት ድሮ በሰራ ስልት አሁን ለመጠቀም መሞከር ጠቃሚ አይደለም ምክንያቱም ያኔ ስልቱ የሰራው በሸበጥ፤ በጫፈሬ፤ በላስቲክ ጫማ መሄድ የፈለገ መቅመል የፈለገ መራብ የፈለገ ቢገባውም ባይገባውም ወስኖ የተከተለ ኃይል ነበረ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት በፓርላማ ከተናሩት የተወሰደ
Forwarded from Z Info. 🏆
"ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም" - የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ መነሻ ስትሆን፣ ከሞላ ጎደል አብዛኛው የዓባይ ውሃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ነው፡፡
ወንዙ ለናይል ወንዝ አጠቃላይ የውኃ መጠን 85 በመቶውን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡
በተመሳሳይ ቀይ ባሕር ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ ትስስር ያላት የውኃ አካል መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላት የጠበቀ ቁርኝት ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርብ የተባለው ድንበር ከባሕር ዳርቻው 48 ኪ.ሜ ብቻ ርቀት ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡
በመሆኑም በቀጣናዊ የባሕር ላይ ጉዳዮች እና የደኅንነት መዋቅር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅሞች እና ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ዘላቂ ትስስር ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት ሲል አሳስቧል፡፡
እነዚህ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ዲስኩር፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም ሀገርን በማተራመስ ድርጊቶች ሊቀየሩ እንደማይችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በተላላኪዎች አማካይነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ወይም የጥቃት ድርጊቶች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማይቀይሩት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሕጋዊ ጥቅም፣ ሚና እና ኃላፊነት ሊያሳንሱት አይችሉም ሲል አስምሮበታል፡፡
ኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነትን፣ የጋራ መከባበርን እና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደምትቀጥል ያረጋገጠው ሚኒስቴሩ፤ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና ዋነኛ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለመጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም የቀጣናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን ከግጭት እና አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ ከሚሆንበት (ዜሮ-ድምር) አካሄድ ይልቅ፣ ገንቢ በሆነ ውይይት፣ በአጋርነት እና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው እንዲፈቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ለማሻሻል ከተከናወኑት ተግባራት መካከል በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የላቀ ድርሻ አለው።
ይህ ስትራቴጂ ቴክኖሎጂን ከዘመናዊ አስተዳደር ጋር በማስተሳሰር የመንግስት አገልግሎትን ቀላል ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ የአገልግሎት ስርአት ለመገንባትና ኢትዮጵያን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሸጋገር ጠንካራ መሰረት ጥሏል።
ዛሬ የምናየው የዲጂታል አገልግሎቶች መስፋፋት የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥብ የአገልግሎት ጥራትን የሚያሻሽልና ከመንግስት ጋር ያለውን የዜጎች ግንኙነት የሚያዘምን የለውጥ ጉዞ እየተጠናከረ መምጣቱን ያሳያል።

#አባይ እና #ቀይ_ባህር የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ የሚበይኑ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። አባይ የልማታችን የሀይላችንና የብልፅግናችን ምንጭ ሲሆን ቀይ ባህር ደግሞ የንግዳችን የቀጣናዊ ትስስራችንና የኢኮኖሚ እድላችን ቁልፍ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እነዚህን ሁለት የሀገራችን ስትራቴጂካዊ ሀብቶችና አቅሞች በሰላማዊ በህጋዊና በጋራ ጥቅም መርህ በመጠቀም የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ወደ አዲስ የብልፅግና ምዕራፍ ለማሻገር እየተጉ ይገኛሉ።
ይህም የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት ስትራቴጂካዊ አቅምና ምቹ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በአግባቡ በመጠቀም የህዝባችንን የብልፅግና ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የሚደረግ ታላቅ ሀገራዊ ጥረት ነው።