ውሃ መንካት ብርቅ የሆነበት የባህር ዳርቻ
በቻይና ሺንዘን የሚገኘው የዳሜሻ የባህር ዳርቻ በአንድ ቀን እስከ 200 ሺህ የሚደርሱ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የአለማችን የተጨናነቀ ስፍራ በመሆን ይታወቃል። በሞቃታማው ወቅት ቦታው እጅግ ከመጨናነቁ የተነሳ፣ ለመዋኘት የሄዱ ሰዎች ትከሻ ለትከሻ እየተገፋፉ የባህር ውሃውን እንኳን ሳይነኩ የሚመለሱበት አስገራሚ ሁኔታ ይፈጠራል።
ይህ ከትልቅ ኮንሰርት የማይተናነስ የህዝብ ብዛት የፈጠረውን ግፊት እና ቅሬታ ለመቅረፍ ባለስልጣናት እርምጃ ወስደዋል። በዚህም መሰረት ከግንቦት እስከ መስከረም ባለው ጊዜ የባህር ዳርቻውን በቀን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ከ80 ሺህ እንዳይበልጥ ገደብ ተጥሎበታል።

ፍየሎቹ በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ላለመወሰድ ያደረጉት ከባድ ትንቅንቅ
ሁለቱ የቤት እንስሶች በዙሪያቸው ከሚንደረደረው ጎርፍ ከወንዝ መኻል በተገኘ ዛፍ ተጠልለው አምልጠዋል።

🙏2
ኢትዮጵያ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን
🇪🇹🇺🇳 ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሚንስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ልታስተናግድ ነው።
ስብሰባው ከነሐሴ 17 እስከ 21 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከ150 በላይ፤ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ከ250 በላይ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤዎችን እና ስብሰባዎችን አስተናግዳለች።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ኑ ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁ ጋር በዚህ ውቧ አራዳ ፓርክ አሳልፉ። ፓርኩ ለወጣቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት ፣ለስፖርተኞች፣ ለነጋዴውና፣ ለአርቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ለተማሪዎች በጠቅላላ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ነው" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
🙏 🙏 🙏
🙏 🙏 🙏
#ሁለት_አይነት_አቀራረቦች!
የየእለት ሕይወታችንን በሁለት መልኩ የመቅረብ ምርጫ አለን፡-
1. “የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ” (reactive approach)
ይህ አቀራረብ በአካባቢያችን ለሚከናወኑ ሁታዎች፣ ለስሜታችንና ለሰዎች ሁኔታ ምላሽ እየሰጡ መኖርን ያመለክታል፡፡ ይህንን አቀራረብ የሚለማመዱ ሰዎች ለሕወታቸው ቅድመ-እቅድ ሳይኖራቸው ለመጣው ነገር ምላሽ እየሰጡ የሚኖረ ሰዎች ናቸው፡፡ በውጤቱም፣ ራሳቸውን አይመሩም፣ በሰዎች ላይ ተጽእኖ አያመጡም እንዲሁም ምንም አይነት ስራን አቅደው ሰርተው አያሳድጉም፡፡
2. “የንቁ አቀራረብ” (proactive approach)
ይህ አቀራረብ በሕይወታችን መሆን እና ማከናወን በምንፈልገው ነገር ዙሪያ ሆን ብሎ አቅዶ መንቀሳቀስን ያመለክታል፡፡ ይህንን አቀራረብ የሚለማመዱ ሰዎች ለሕይወታቸው ግልጽ የሆነ ዓላማ ስላላቸው በዚያ ዙሪያ ግብን በማውጣት፣ በመንቀሳቀስና አልፎ አልፎም ግምገማ በማድረግ ይራመዳሉ፡፡ በውጤቱም፣ ራሳቸውን ይመራሉ፣ በሰዎች ላይ መልካም ተጽእኖ ያመጣሉ፣ ስራቸውንም ያሳካሉ፡፡

በሾላ ገበያ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ ተከማችቶ የነበረ የተበላሸ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል ተወገደ 🤔
በየካ ክፍለ ከተማ ሾላ ገበያ አካባቢ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መልኩ ተከማችቶ የነበረ፣ ግምታዊ ዋጋው 8 ሚሊዮን 664 ሺሕ 495 ብር የሚያወጣ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈና የተበላሸ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል መወገዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን አስተወቀ፡፡
ምርቱ በኩላሊት እጥበት ክሊኒክ ስር ያለ መጋዘን በሚል ሽፋን የተከማቸ ቢሆንም፣ ቦታው ከደረጃ በታች የሆነና በየካ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በኩል ምንም ዓይነት እውቅናና የብቃት ማረጋገጫ የሌለው ነው። በመጋዘኑ ውስጥ ከተገኙት 34 የሕክምና መሳሪያዎችና ኬሚካሎች መካከል 14ቱ ሙሉ በሙሉ የአገልግሎት መስጫ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።የተቀሩት 2 የህክምና መሳሪያዎችና የኬሚካል ዓይነቶች ጊዜያቸው ባያልፍም በተገቢው ሁኔታ ባለመያዛቸው ለአገልግሎት የማይውሉ መሆናቸው ተረጋግጧል።
እነዚህ ለኩላሊት እጥበት ህክምና የሚያገለግሉ ኬሚካሎች በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒትና ኬሚካል ማቃጠያ እንዲወገዱ ተደርጓል። በተደረገው ምርመራም ምርቶቹ እ.ኤ.አ. ከ2021 እስከ 2026 ድረስ ያሉ ቀናትን የሚያሳዩና ለአመታት ጊዜያቸው አልፎ ተከማችተው የቆዩ መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል፣ አብረዋቸው ከተገኙት ውስጥ ለአገልግሎት ብቁ የሆኑ 18 ዓይነት የሕክምና መሳሪያዎች ሳይወገዱ ቀርተዋል። ከተወሰደው የማስወገድ እርምጃ ጎን ለጎን፣ ከድርጊቱ ጋር ተያያዥነት ያለው ክሊኒክ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዷል።
የግብዓቱ መያዝ በጤና ላይ ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ ስጋት ያስቀረ ሲሆን ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

❤2👏1
የሐገር መልክ
#Ethiopia | የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን የሕይወት ታሪክ የያዘ አዲስ መጽሐፍ በታሪክ ተመራማሪው ኸድር ታጁ አዘጋጅነትና በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ታትሞ ለንባብ ሊበቃ ነው።
"የሐገር መልክ" በሚል የተሰየመው ይኸው ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ተቀዳሚ ሙፍቲ በሕይወት እያሉ የተጀመረና እሳቸው በሚገኙበት መድረክም ይመረቃል ተብሎ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።
በመጨረሻም ከውልደት እስከ ህልፈተ-ሕይወታቸው ድረስ ከዚህ ቀደም ለአደባባይ ያልበቁ በርካታ ገጽታዎቻቸውንና የታሪክ መረጃዎችን ያካተተ ሙሉ መጽሐፍ ሆኖ ለአንባቢያን መዘጋጀቱን አዘጋጁ ኸድር ታጁ በተለይም ለየኑስ ሚዲያ ገልጿል።

የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ መድፍ ይተኮሳል፡፡
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ስፖርትና ኪነ ጥበባት ስራዎች ማዕከል ነገ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡