መረጃ ዘመደመር
1.02K subscribers
48K photos
1.81K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
#ታግዷል❗️
ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ፣ ዋጋቸው ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ አክሲዮኖች፣ ከ5 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት፣ ከ200 በላይ ቤቶች፣ ከ300 በላይ ተሽከርካሪዎች እና 69 ከባድ ማሽነሪዎች…

በኢትዮጵያ በታክስና ግብር ስወራ፣ በሙስና፣ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኦንላይን ማጭበርበር እና ከሌሎች ከባድ ወንጀሎች ጋር ግንኙነት አለው የተባለ በቢሊየን ብር የሚቆጠር ንብረት መታገዱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።

በ2018 ዓ.ም ብቻ በተከናወነ የምርመራና የሕግ ማስከበር ሥራ፣ በ544 የክስ መዝገቦች ሥር የተካተቱ በርካታ ሀብቶች ታግደው የሕግ ሂደታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህም መሠረት ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ፣ ዋጋቸው ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ አክሲዮኖች፣ ከ5 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት፣ ከ200 በላይ ቤቶች፣ ከ300 በላይ ተሽከርካሪዎች እና 69 ከባድ ማሽነሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና እንዲታገዱ መደረጉን ሸገር አኤፍ አኤም ዘግቧል።

ሥራ ላይ ከዋለ ከአንድ ዓመት በላይ የሆነው አዋጁ የሕገ-ወጥ ሀብት ምንጭን በጥብቅ በመመርመርና በማረጋገጥ፣ ንብረቱ ለመንግሥትና ለሕዝብ ጥቅም የሚወረስበትን ግልጽ ሕጋዊ አሰራር ዘርግቷል።

ሕጉ በጸደቀበት ወቅት እስከ 10 ዓመት ወደ ኋላ ተመልሶ ተጠያቂነት እንዲኖር መፍቀዱ በበርካቶች ዘንድ ከፍተኛ ክርክር አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

በተለመደው የሕግ አሰራር አንድ ንብረት በሕገ-ወጥ መንገድ መገኘቱን ማስረዳት ያለበት ከሳሽ አካል ቢሆንም፤ በዚህ አዋጅ መሠረት ግን «ሀብቴ በሕጋዊ መንገድ የተገኘ ነው» ብሎ የማሳመንና የማስረዳት ሸክሙ ሙሉ በሙሉ የተከሳሹ ነው።

አዋጁ የታወቀ የገቢ ምንጭ ያላቸው ሰዎች ከሚያገኙት ገቢ ጋር ያልተመጣጠነና የተጋነነ የሀብት ልዩነት ሲገኝባቸው ወይም ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሲኖር ምርመራ እንዲደረግባቸው ይደነግጋል።

በተመሳሳይ የታወቀ የገቢ ምንጭ የሌላቸው ግለሰቦች ያፈሩትን ሀብት እንዴትና በምን መንገድ እንዳጠራቀሙት ማስረዳት ካልቻሉ፣ ምርመራ ተካሂዶ ክስ በመመሥረት ንብረቱ እንዲወረስ ያዝል።

በጠቅላይ ዐቃቤ-ሕግ የሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ኃይሌ የአዋጁ ዋና ዓላማ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ሀብት መለየት፣ መመርመር፣ ማገድና የፍርድ ቤት ሂደቱ ሲጠናቀቅ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መውረስ እንደሆነ አስረድተዋል።

በ2018 ዓ.ም የታገዱት ጥሬ ገንዘቦች፣ አክሲዮኖች፣ መሬቶችና ሌሎች ንብረቶች ከጀርባቸው ትላልቅ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ወንጀሎች ያሉባቸው እንደሆኑ የጠቆሙት ምክትል ዳይሬክተሩ፣ የወንጀል ጉዳዮቹ በሕግ ሂደት ውሳኔ ሲያገኙ የውርስ አቤቱታው በይፋ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።

የሀብት ማስመለስ አዋጁ ትግበራ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን፣ ሰሞኑንም የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት የሚያናጉ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 169 ግለሰቦች እንዲሁም በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ የተጠረጠሩ 109 ግለሰቦች ተለይተዋል።

ከእነዚህም መካከል እስካሁን 91 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማስታወቁንም ነው ዘገባው ያመላከተው።
👍1
"እኛ ኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር በገዥ ትርክት ተሸምነን ተቋማዊ ለውጥን እያጠናከርንና ብሔራዊ ጥቅማችንን እያሳካን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የዝናብ ሁኔታ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል  ጥንቃቄዎችን አድርጉ ሲል የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

ኮሚሽኑ የጥንቃቄ መልእክቱን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራ ሲሆን  ህብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የዝናብ ሁኔታ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ያድርግ ሲል አሳስቧል፡፡በዚህም  በወንዝ ዳርቻና ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች የውኃው መጠን ከመጨመሩ በፊት ጥንቃቄ ያድርጉ ብሏል።

በሉላ በኩልም የውኃ መውረጃዎችን መፈተሸ፣ በቤት ዙሪያ ያሉ ቦዮች በቆሻሻ አለመደፈናቸውን ማረጋገጥ እና የልጆችን ውሎ መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።

ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ልጆች ከቤት እንዳይወጡና ወደ ዋና ዋና የጎርፍ መውረጃዎች እንዳይጠጉ መቆጣጠር ይገባል ተብሏል፡፡

አደገኛ የጎርፍ ምልክት በሚታይበት ወቅት በአደጋ ጊዜ ስልክ 939 ላይ በመደወል ያሳውቁ ሲል ኮሚሽኑ አሳስባል።
👍1
😱1
ውሃ መንካት ብርቅ የሆነበት የባህር ዳርቻ

በቻይና ሺንዘን የሚገኘው የዳሜሻ የባህር ዳርቻ በአንድ ቀን እስከ 200 ሺህ የሚደርሱ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የአለማችን የተጨናነቀ ስፍራ በመሆን ይታወቃል። በሞቃታማው ወቅት ቦታው እጅግ ከመጨናነቁ የተነሳ፣ ለመዋኘት የሄዱ ሰዎች ትከሻ ለትከሻ እየተገፋፉ የባህር ውሃውን እንኳን ሳይነኩ የሚመለሱበት አስገራሚ ሁኔታ ይፈጠራል።

ይህ ከትልቅ ኮንሰርት የማይተናነስ የህዝብ ብዛት የፈጠረውን ግፊት እና ቅሬታ ለመቅረፍ ባለስልጣናት እርምጃ ወስደዋል። በዚህም መሰረት ከግንቦት እስከ መስከረም ባለው ጊዜ የባህር ዳርቻውን በቀን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ከ80 ሺህ እንዳይበልጥ ገደብ ተጥሎበታል።
ፍየሎቹ በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ላለመወሰድ ያደረጉት ከባድ ትንቅንቅ

ሁለቱ የቤት እንስሶች በዙሪያቸው ከሚንደረደረው ጎርፍ ከወንዝ መኻል በተገኘ ዛፍ ተጠልለው አምልጠዋል።
🙏2
ኢትዮጵያ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

🇪🇹🇺🇳 ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሚንስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ልታስተናግድ ነው።

ስብሰባው ከነሐሴ 17 እስከ 21 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከ150 በላይ፤ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ከ250 በላይ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤዎችን እና ስብሰባዎችን አስተናግዳለች።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ኑ ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁ ጋር በዚህ ውቧ አራዳ ፓርክ አሳልፉ። ፓርኩ ለወጣቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት ፣ለስፖርተኞች፣ ለነጋዴውና፣ ለአርቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ለተማሪዎች በጠቅላላ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ነው" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
🙏 🙏 🙏
"የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ ያቀደችውን ማሳካት እንደምትችል ለዓለም የምናሳይበት ግዙፍ ሥራ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ሁለት_አይነት_አቀራረቦች!

የየእለት ሕይወታችንን በሁለት መልኩ የመቅረብ ምርጫ አለን፡-

1.   “የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ” (reactive approach)
ይህ አቀራረብ በአካባቢያችን ለሚከናወኑ ሁታዎች፣ ለስሜታችንና ለሰዎች ሁኔታ ምላሽ እየሰጡ መኖርን ያመለክታል፡፡ ይህንን አቀራረብ የሚለማመዱ ሰዎች ለሕወታቸው ቅድመ-እቅድ ሳይኖራቸው ለመጣው ነገር ምላሽ እየሰጡ የሚኖረ ሰዎች ናቸው፡፡ በውጤቱም፣ ራሳቸውን አይመሩም፣ በሰዎች ላይ ተጽእኖ አያመጡም እንዲሁም ምንም አይነት ስራን አቅደው ሰርተው አያሳድጉም፡፡

2.  “የንቁ አቀራረብ” (proactive approach)
ይህ አቀራረብ በሕይወታችን መሆን እና ማከናወን በምንፈልገው ነገር ዙሪያ ሆን ብሎ አቅዶ መንቀሳቀስን ያመለክታል፡፡ ይህንን አቀራረብ የሚለማመዱ ሰዎች ለሕይወታቸው ግልጽ የሆነ ዓላማ ስላላቸው በዚያ ዙሪያ ግብን በማውጣት፣ በመንቀሳቀስና አልፎ አልፎም ግምገማ በማድረግ ይራመዳሉ፡፡ በውጤቱም፣ ራሳቸውን ይመራሉ፣ በሰዎች ላይ መልካም ተጽእኖ ያመጣሉ፣ ስራቸውንም ያሳካሉ፡፡
በሾላ ገበያ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ ተከማችቶ የነበረ የተበላሸ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል ተወገደ 🤔

በየካ ክፍለ ከተማ ሾላ ገበያ አካባቢ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መልኩ ተከማችቶ የነበረ፣ ግምታዊ ዋጋው 8 ሚሊዮን 664 ሺሕ 495 ብር የሚያወጣ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈና የተበላሸ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል መወገዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን አስተወቀ፡፡

ምርቱ በኩላሊት እጥበት ክሊኒክ ስር ያለ መጋዘን በሚል ሽፋን የተከማቸ ቢሆንም፣ ቦታው ከደረጃ በታች የሆነና በየካ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በኩል ምንም ዓይነት እውቅናና የብቃት ማረጋገጫ የሌለው ነው። በመጋዘኑ ውስጥ ከተገኙት 34 የሕክምና መሳሪያዎችና ኬሚካሎች መካከል 14ቱ ሙሉ በሙሉ የአገልግሎት መስጫ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።የተቀሩት 2 የህክምና መሳሪያዎችና የኬሚካል ዓይነቶች ጊዜያቸው ባያልፍም በተገቢው ሁኔታ ባለመያዛቸው ለአገልግሎት የማይውሉ መሆናቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ ለኩላሊት እጥበት ህክምና የሚያገለግሉ ኬሚካሎች በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒትና ኬሚካል ማቃጠያ እንዲወገዱ ተደርጓል። በተደረገው ምርመራም ምርቶቹ እ.ኤ.አ. ከ2021 እስከ 2026 ድረስ ያሉ ቀናትን የሚያሳዩና ለአመታት ጊዜያቸው አልፎ ተከማችተው የቆዩ መሆናቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል፣ አብረዋቸው ከተገኙት ውስጥ ለአገልግሎት ብቁ የሆኑ 18 ዓይነት የሕክምና መሳሪያዎች ሳይወገዱ ቀርተዋል። ከተወሰደው የማስወገድ እርምጃ ጎን ለጎን፣ ከድርጊቱ ጋር ተያያዥነት ያለው ክሊኒክ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዷል።

የግብዓቱ መያዝ በጤና ላይ ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ ስጋት ያስቀረ ሲሆን ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።
2👏1