መረጃ ዘመደመር
1.01K subscribers
48K photos
1.81K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
ወደኋላ ከመሄድ ወደፊት መውደቅ ይሻላል።

ወደፊት መውደቅ ወደ ዓላማ ለመድረስ መንገድ ይቀንሳል። ወደኋላ መሄድ ግን ከዓላማ ያርቃል። ዋናው ወደፊት መሆኑ ነው።

እየተከራከሩም፣ እየተጨቃጨቁም፣ እያስፈራሩምም፣ እየዘለፉም - ዋናው መመካከሩ ነው። "እተዋለሁ፣ እወጣለሁ" የሚለው መንገድ በኢትዮጵያ ታሪክ አዋጥቶ አያውቅም። "አኩራፊ ልጅ ምሳው እራቱ ነው" የሚል ሕዝብ ነው።

ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ከትምህርት ቤት ደወል ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመባቸው ያሉት የትግራይ ታዳጊዎች

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሥነ ልቦና፣ በቁሳቁስ እና በሞራል ከፍተኛ ዝግጅት የሚያደርጉበት ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እና ነጋቸውን በዕውቀት ለመገንባት የሚያልሙበት ልዩ ወቅት ላይ ይገኛሉ።

በየክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን እና የመማሪያ ቁሳቁሶቻቸውን አዘጋጅተው አዲስ የዕውቀት ምዕራፍ ለመጀመር በጉጉት የሚጠበቁበት ጊዜም ነው።

ነገር ግን ይህ ደስታ እና የትምህርት ጅማሮ ለትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች እውን ሊሆን አልቻለም።

የክልሉ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ፣ ከሰላማዊ ሕይወት እና ከብሩህ ተስፋ ይልቅ በሞት እና በሕይወት መካከል በሚወዛወዝ አሰቃቂ እና መሪር እውነታ ውስጥ ይገኛሉ።

የከሰረው የህወሓት ቡድን ክልሉን ብቻ ሳይሆን የወጣቶችን እና የታዳጊዎችን የነገ ተስፋ በግልጽ እያደናቀፈ ነው።

የቡድኑ አምባገነናዊ እና ግትር አካሄድ ክልሉን ወደአልተቋጨ ቀውስ እና ምስቅልቅል ከመምራቱም በላይ የአዲሱን ትውልድ ሕይወት እና ጊዜ በከንቱ እያባከነ ይገኛል።

ወጣቶች ዕውቀት፣ ክህሎት እና የሥነ ልቦና ዝግጁነት የሚያገኙበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ በፖለቲካዊ ሴራ እና ግጭት ምክንያት ሕልማቸው አደጋ ተጋርጦበታል።

የትግራይ ታዳጊዎች የትምህርት ቤት ደወል ከመስማት ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመባቸው የከፋ የሥነ ልቦና ጫና እና የተስፋ መቁረጥ አደጋ ተደቅኖባቸዋል።

ይህ ደግሞ በነገው ትውልድ ሥነ ልቦና ላይ የሚተው ጠባሳ በቀላሉ የሚጠገን አይደለም።

ሕገ ወጡ ህወሓት የሀገር ተስፋ የሆኑትን ታዳጊዎች እና ወጣቶች ከትምህርት፣ ከዕድገት እና ከዘመናዊ ዕውቀት የማራቅ እኩይ ተግባሩን እየገፋበት ነው።

ይህ የከሰረው ቡድን የክልሉን ሥልጣን እና የገዛ ፖለቲካዊ ሕልውናውን ብቻ ለማስቀጠል በሚያደርገው እኩይ እና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ የትግራይን አዲሱን ትውልድ ለባሰ ጨለማ እና ለድህነት አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።

ወጣቶች እና ታዳጊዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምር እና በዕውቀት መበልጸግ በሚገባቸው ወሳኝ ወቅት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው እንዲጨልም መደረጉ የክልሉን የወደፊት ዕድገት ብቻ ሳይሆን የሀገርንም የነገ ተስፋ የሚጎዳ ታሪካዊ ስህተት ነው።

የትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ከፖለቲካዊ ቁማር እና ለሥልጣን ከሚደረግ እልህ ይልቅ ሰላም፣ ትምህርት፣ ሥነ ልቦናዊ እፎይታ እና ብሩህ አድማስ ያስፈልጋቸዋል።
ዩክሬን 600 ድሮኖችን በሩሲያ ላይ አዘነበች።

ዩክሬን ዛሬ ለሊት ወደ 600 የሚጠጉ ድሮኖችን በመተኮስ በሞስኮ እና በዙሪያዋ ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ሰነዘረች። 

በጥቃቱ በፖዶልስክ እና በዶሞዴዶቮ የሚገኙ የሎጂስቲክስ መጋዘኖች (የሩሲያው ትልቅ የኦንላይን ገበያ ዋይልድቤሪስን ጨምሮ) በእሳት ተቃጥለዋል።

​የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያኒን ድርጊቱን በቅርብ ጊዜያት ከተሰነዘሩት ትልልቅ ጥቃቶች አንዱ ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የሩሲያ ባለስልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ ሌሊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በሰነዘረችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የረጅም ርቀት ጥቃት አዲስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል።
"የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ባህል ሆኖ መቀጠል አለበት" ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ

"በኢትዮጵያ እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ቀጣይነት ኖሮት ውይይት እንደ ባህል መወሰድ አለበት" ሲሉ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ ተናግረዋል።

“ብሔርተኝነት” የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ እና ፖለቲከኛው ዶክተር ብርሃኑ ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በምክክሩ ከሚታዩ ችግሮች ትምህርት በመውሰድ ሂደቱን የተሻለ አሳታፊ እና ገለልተኛ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተጨማሪም፤ ሀገር የሚገነባው “በምክክር” እንደሆነ እና ዜጎች ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚችሉት “በስምምነት ብቻ” መሆኑን አንስተዋል።

ሰላማዊ መንገድን በመከተል ሀገር መገንባት የሚፈልጉ የፖለቲካ ኃይሎች በምክክሩ መሳተፍ እንዳለባቸው ጠቁመው፣ የፖለቲካ ልሂቃን ድርድር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

"ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚልን ሁሉ ማካተት እንዳለበት" የሚል ሐሳብ ያነሱት ዶክተር ብርሃኑ የችግሩ ዋና መንስኤ ህዝቡ ሳይሆን የፖለቲካ ልሂቃን በመሆናው፤ ዜጎች በራሳቸው መንገድ በምክክር ሂደቱ በመሳተፍ ችግሮቹን መፍታት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ያሳደግን ሲሆን፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማምረት አቅማችን አሁን ላይ ወደ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ ችለናል፡፡

በተለይ ዛሬ የመረቅናቸዉ ደግሞ የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር አለም የደረሰበትን እጅግ የረቀቁ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዘላቂነት ፈርቀዳጅ ሚና አላቸዉ።

አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ አዲስ ፥ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ በማድረግ እና አገልግሎትን የሚያሳልጡ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ከዛሬ አልፎ ለትውልድ የምታሸጋግር ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
ምክክር ያስፈለገው እኮ የሀሳብ ልዩነት ስላለ ነው ። ልዩነት ደግሞ ተፈጥሯዊ እንጂ ወንጀል አይደለም። ልክ አይመርጡም ሲሉ እንደመረጥነዉ÷ አይተክሉም ሲሉ እንደተከልነዉ÷ አይወያዩም ሲሉ እየተወያየን ነው ።

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው !
Solomon Dibaba ያስቀመጣት አጭር ግን ግልፅና ግዙፍ የጋራ መልዕክት

ከ OBN Afaan Oromoo እስከ AMN-Addis Media Network የደመቀ ጉዞ ማለት ይኼ ነው