"አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ ከቀይ ባህር አባረረን፤ ኢትዮጵያ ለዘመናት ያስከበረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ የጂኦግራፊ እስረኛ ያደረገበት ምክንያት በውስጣችን ያለ ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻት እና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ አይደለም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#እንድታውቁት
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የውክልና አገልግሎቱን በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወረቀት ነጻ በሆነ ሲስተም ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።
ሜክሲኮ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስር ልዩ እና መደበኛው ቅርንጫፍ ፣አያት አደባባይ ሎሚያድ ሱፐርማርኬት በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራአንድ እንዲሁም ካዛንቺስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው ቅርንጫፍ ስምንት እና ቦሌ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራሁለት ጽ/ቤቶች ነው አገልግሎቱን መስጠት የተጀመረው።
በቅርቡም በሁሉም ቅርጫፎች ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራሁ እገኛለሁ ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።
ከተገልጋዮች ምን ይጠበቃል ?
👉 በ https://dars.gov.et:5102 ሊንክ በመጫን መግባት፤
👉 ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም አስፈላጊ ዶክመንቶችን መጫን
👉 ወደተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማቅናት
👉 የተጫነውን መረጃ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን ዶክመንቱ ተመሳክሮ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ (signature pad) በመፈረም የውክልና ሰነዱ በኦንላየን ይላካል።
👉 በሰነዱ መገልገል ሲፈልጉ የሰነዱን ትክክለኛነት በQR Code ማረጋገጥ ይችላሉ።
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ከወረቀትአልባ አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌሳይን መተግበሪያ አማካይነት የቤተሰብ የጠበቃ እና የአስተዳደር ውክልና አገልግሎት ወደተቋም መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ማግኘት የሚያስችላቸው አሰራር መተግበሩን አስታውሷል።

ኢራን አሜሪካውያን ወታደሮችን ለሚገድሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ሽልማት አዘጋጀች‼
የኢራን ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ማንኛውም አሜሪካዊ ወታደርን ማርኮ ወይም ገድሎ የሚያመጣ ኢራናዊ 30,000 ዶላር የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጠው አስታውቀዋል። አሚር ሀታሚ የተባሉት ባለሥልጣን አያይዘውም ይህ ገንዘብ የሚሸፈነው “በኢራን ሕዝብ” ድጋፍ እንደሆነ ገልጸዋል።
የኢራን ባለሥልጣናት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል ቀደም ሲልም የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀታቸው ይታወሳል። ባለፈው ግንቦት 15 ከፍተኛው የፓርላማ አባል ኢብራሂም አዚዚ እንደገለጹት፣ ትራምፕን ለሚገድል አካል እስከ 50 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ሽልማት የሚያካትት የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን አሳውቀው ነበር።

የ"ጽምዶ ጥምረት" የተለያየ እኩይ ፍላጎት ያላቸው የጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ስብስብ ነው
የ"ጽምዶ ጥምረት" የተለያየ እኩይ ፍላጎት ያላቸው የጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ስብስብ ነው አሉ የኤርትራ ሰማያዊ አብዮት ግንባር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዳዊት ተፈሪ፡፡
የማዕከላዊ ኮሚቴው አባል እንዳሉት፤ “ጽምዶ” የተሰኘው የጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ህብረት ባልተጣጣሙ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተመሠረተና በፌደራል መንግሥት ላይ ባላቸው ተቃውሞ ብቻ የተጣመረ ስብስብ ነው፡፡
በዚህ ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና አካላትን ከመሠረቱ የሚያገናኛቸው የጋራ ራዕይ የለም፤ ብቸኛ ዓላማቸው በኢትዮጵያ የሚገኘውን ማዕከላዊ መንግሥት መጣል ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጥምረቱ የቅርብ ጊዜ ዋና ስልት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ሁለገብ ጫናዎችን አጠናክሮ መቀጠልና የተለያዩ ተቃዋሚ ኃይሎችን በማስተባበር የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት መሆኑን አመልክተዋል።
ዋና ግባቸው መንግሥትን በቋሚነት ማወክና የማዳከም ሥራ መስራት ሲሆን፤ መንግሥትን በመጉዳት በዚህ ጥምረት የሥልጣን ለውጥ ማምጣት ይቻላል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የጽምዶ ስልት በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አባላቱን ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ወደ ሰፊ ግጭት ሊያስገባ የሚችል ወታደራዊ ምላሽ የማግኘት ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።
ቡድኑ መንግሥትን ወደ ግጭት ማስገባት ካልቻለ፤ ከፍተኛ የውስጥ ቅሬታና እርስ በርስ የሚጋጩ ተቃርኖዎች ሊገጥሙት እንደሚችሉ አንስተዋል፡፡
የጥምረቱ አባላት የጋራ ለሆነ የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ዓላማ ሳይሆን እናሳካዋለን ብለው ለሚያስቡት ጊዜያዊ ግቦች ብቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
የአሁኑ ትብብራቸው በዋናነት በአጭር ጊዜ ፍላጎቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፉት ግጭቶች ትምህርት መውሰድ እንዳለበትና ተቃዋሚ ቡድኖች የግጭቱን ሁኔታና አካሄድ እንዲወስኑ ዕድል መስጠት እንደሌለበት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ለቀይ ባሕር ደህንነት ዋስትና፤ የካይሮ ፍርሃት እና የአዲስ አበባ ‘ገቢር-ነበብ' ፖሊሲ
ቀይ ባሕር አፍሪካን ጨምሮ የተለያዩ አህጉራትን የሚያገናኝና የዓለምን ከፍተኛ የንግድና የነዳጅ ፍሰት የሚያስተናግድ ቁልፍ የጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማዕከል ነው።
ይህ የውኃ መስመር ለዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ባለው ከፍተኛ ድርሻ ምክንያት የብዙ ሀገራትን ትኩረት ይስባል።
በአሁኑ ወቅትም የሁቲ አማፂያን በየዕለቱ በሚፈጽሙት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ሳቢያ ከፍተኛ የደህንነት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።
ይህ አይነቱ ስጋት የዓለምን ኢኮኖሚ እያናጋ ባለበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ የካይሮ እና የሌሎች የቀጣናው ሀገራት መከላከል ላይ ብቻ ያተኮረ እና የተላላኪነት ባህሪ የተጫነው አካሄድ የደህንነት ክፍተቱን ይበልጥ አስፍቶታል።
ይህንን ክፍተት ለመሙላት የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና ‘ገቢር-ነበብ’ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቀጣናዊ መረጋጋትን ለመመለስ ብቸኛው አማራጭ እየሆነ መጥቷል።
የየመኑ የሁቲ ታጣቂዎች በባብል ኤል-መንደብ እና በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት የአለም አቀፍ የባህር ትራንስፖርት ደህንነትን ዋነኛ ስጋት አድርጎታል።
በርካታ ግዙፍ የጭነት መርከቦች መንገዳቸውን በመቀየር በደቡብ አፍሪካ በኩል ለመዞር በመገደዳቸው የትራንስፖርት ወጪ እና የጊዜ መራዘም አስከትሏል።
ይህ የሁቲ አደገኛነት የአለም ሀያላን ሀገራት በቀጣናው ላይ ያላቸውን የደህንነት ስጋት እጅግ አግዝፎታል። ይሁን እንጂ፣ ግብፅ ከቀይ ባህር እና ከስዊዝ ቦይ ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ቢኖራትም፣ ችግሩን አስቀድሞ የመከላከል እና የማስቆም ወታደራዊም ሆነ ስትራቴጂካዊ ብቃት አላሳየችም።
የካይሮ እና የጎረቤት ሀገራት ፖሊሲ ችግር ከተከሰተ በኋላ በሚደረግ ያረጀ ምላሽ እና የውጭ ሀያላንን ፍላጎት በማስፈጸም ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ ትልቅ የደህንነት ክፍተት ፈጥሯል። ይህ የአቅም ማነስ ደግሞ የአለም አቀፍ ንግድ መናጋትን ይበልጥ አባብሶታል።
ከቅርብ አመታት ወዲህ አዲስ አበባ የምትከተለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከባህላዊው ‘ችግርን የመከላከል’ ስትራቴጂ ወጥቶ፣ በቀጣናው ላይ ቀድሞ የመገኘት እና የደህንነት ስጋቶችን አስቀድሞ የመቅረጽ ‘ገቢር-ነበብ’ ባህሪን የተላበሰ ነው።
ይህ ፖሊሲ በሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ይቆማል።የመጀመሪያው ቀድሞ የመገኘት ስትራቴጂ ሲሆን፥ ይህም ስጋቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከመምጣታቸው በፊት በምንጫቸው ላይ ስልታዊ ተጽዕኖ ማሳደርን ያለመ ነው።
ሁለተኛው ምሰሶ ቀጣናዊ ትስስር እና የጋራ ደህንነት ሲሆን፥ የኢኮኖሚ ትስስርን ከደህንነት ዋስትና ጋር አጣምሮ መራመድን ይፈልጋል።
ሶስተኛው ደግሞ የሀይል ሚዛን ጥበቃ ነው።በቀጣናው ላይ የሚታየውን የሀያላን ሀገራት ፍላጎት ለቀጣናው ሰላም በሚጠቅም መልኩ ማቀናጀትን ያካትታል።
የፖለቲካ እና የደህንነት ተንታኞች እንደሚስማሙበት፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት ግዙፍ የህዝብ ቁጥር፣ ጠንካራ እና የተፈተነ መደበኛ ሰራዊት እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ እምብርት መሆኗ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ሚና እንዲኖራት ያስገድዳታል።
ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመውጣት የምታደርገው ጥረት እና የምትገነባው ዘመናዊ የባህር ኃይል የኢኮኖሚ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ ያላትን አቅም የምታሳይበት ስልታዊ እርምጃ ነው።
ጠንካራ የባህር ኃይል ያላት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረጓ እንደ ሁቲ ያሉ የሽብር ስጋቶችን እና የባህር ላይ ወንበዴነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመከላከል ዋነኛው ዋስትና ነው።
የአሜሪካ፣ የቻይና፣ የአውሮፓ ህብረት እና የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀይ ባህር ላይ የየራሳቸው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት አላቸው። በአሁኑ ወቅት ሀያላኑ ሀገራት የሚፈልጉት የንግድ መስመራቸው እንዳይዘጋ የሚጠብቅ፣ አስተማማኝ ወታደራዊ አቅም ያለው እና ሉዓላዊ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችል ቀጣናዊ አጋር ነው።
የኢትዮጵያ ‘ገቢር-ነበብ’ ፖሊሲ ከእነዚህ ሀያላን ሀገራት ፍላጎት ጋር ፍጹም ይጣጣማል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለዓለም አቀፍ ንግድ መረጋጋት እና ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም አስተማማኝ ምሰሶ መሆን የሚችል በመሆኑ ነው።
በአጠቃላይ የቀይ ባህር ደህንነት ያለ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ወቅታዊው የሁቲ ቀውስ በግልጽ አሳይቷል።
ካይሮ እና ሌሎች የቀጣናው ሀገራት የከሸፈ አካሄዳቸው ደህንነቱን ማስጠበቅ ባቃታቸው በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ ‘ገቢር-ነበብ’ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የባህር በር ጥያቄ ለአለም አቀፍ ፀጥታ መረጋገጥ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ምላሽ ነው።
አዲስ አበባ በቀጣናው የምታሳየው ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ብስለት የቀይ ባህርን መፃኢ እድል የሚወስን ዋናው መፍትሄ ነው።

ወደኋላ ከመሄድ ወደፊት መውደቅ ይሻላል።
ወደፊት መውደቅ ወደ ዓላማ ለመድረስ መንገድ ይቀንሳል። ወደኋላ መሄድ ግን ከዓላማ ያርቃል። ዋናው ወደፊት መሆኑ ነው።
እየተከራከሩም፣ እየተጨቃጨቁም፣ እያስፈራሩምም፣ እየዘለፉም - ዋናው መመካከሩ ነው። "እተዋለሁ፣ እወጣለሁ" የሚለው መንገድ በኢትዮጵያ ታሪክ አዋጥቶ አያውቅም። "አኩራፊ ልጅ ምሳው እራቱ ነው" የሚል ሕዝብ ነው።
ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ከትምህርት ቤት ደወል ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመባቸው ያሉት የትግራይ ታዳጊዎች
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሥነ ልቦና፣ በቁሳቁስ እና በሞራል ከፍተኛ ዝግጅት የሚያደርጉበት ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እና ነጋቸውን በዕውቀት ለመገንባት የሚያልሙበት ልዩ ወቅት ላይ ይገኛሉ።
በየክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን እና የመማሪያ ቁሳቁሶቻቸውን አዘጋጅተው አዲስ የዕውቀት ምዕራፍ ለመጀመር በጉጉት የሚጠበቁበት ጊዜም ነው።
ነገር ግን ይህ ደስታ እና የትምህርት ጅማሮ ለትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች እውን ሊሆን አልቻለም።
የክልሉ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ፣ ከሰላማዊ ሕይወት እና ከብሩህ ተስፋ ይልቅ በሞት እና በሕይወት መካከል በሚወዛወዝ አሰቃቂ እና መሪር እውነታ ውስጥ ይገኛሉ።
የከሰረው የህወሓት ቡድን ክልሉን ብቻ ሳይሆን የወጣቶችን እና የታዳጊዎችን የነገ ተስፋ በግልጽ እያደናቀፈ ነው።
የቡድኑ አምባገነናዊ እና ግትር አካሄድ ክልሉን ወደአልተቋጨ ቀውስ እና ምስቅልቅል ከመምራቱም በላይ የአዲሱን ትውልድ ሕይወት እና ጊዜ በከንቱ እያባከነ ይገኛል።
ወጣቶች ዕውቀት፣ ክህሎት እና የሥነ ልቦና ዝግጁነት የሚያገኙበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ በፖለቲካዊ ሴራ እና ግጭት ምክንያት ሕልማቸው አደጋ ተጋርጦበታል።
የትግራይ ታዳጊዎች የትምህርት ቤት ደወል ከመስማት ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመባቸው የከፋ የሥነ ልቦና ጫና እና የተስፋ መቁረጥ አደጋ ተደቅኖባቸዋል።
ይህ ደግሞ በነገው ትውልድ ሥነ ልቦና ላይ የሚተው ጠባሳ በቀላሉ የሚጠገን አይደለም።
ሕገ ወጡ ህወሓት የሀገር ተስፋ የሆኑትን ታዳጊዎች እና ወጣቶች ከትምህርት፣ ከዕድገት እና ከዘመናዊ ዕውቀት የማራቅ እኩይ ተግባሩን እየገፋበት ነው።
ይህ የከሰረው ቡድን የክልሉን ሥልጣን እና የገዛ ፖለቲካዊ ሕልውናውን ብቻ ለማስቀጠል በሚያደርገው እኩይ እና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ የትግራይን አዲሱን ትውልድ ለባሰ ጨለማ እና ለድህነት አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።
ወጣቶች እና ታዳጊዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምር እና በዕውቀት መበልጸግ በሚገባቸው ወሳኝ ወቅት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው እንዲጨልም መደረጉ የክልሉን የወደፊት ዕድገት ብቻ ሳይሆን የሀገርንም የነገ ተስፋ የሚጎዳ ታሪካዊ ስህተት ነው።
የትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ከፖለቲካዊ ቁማር እና ለሥልጣን ከሚደረግ እልህ ይልቅ ሰላም፣ ትምህርት፣ ሥነ ልቦናዊ እፎይታ እና ብሩህ አድማስ ያስፈልጋቸዋል።

ዩክሬን 600 ድሮኖችን በሩሲያ ላይ አዘነበች።
ዩክሬን ዛሬ ለሊት ወደ 600 የሚጠጉ ድሮኖችን በመተኮስ በሞስኮ እና በዙሪያዋ ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ሰነዘረች።
በጥቃቱ በፖዶልስክ እና በዶሞዴዶቮ የሚገኙ የሎጂስቲክስ መጋዘኖች (የሩሲያው ትልቅ የኦንላይን ገበያ ዋይልድቤሪስን ጨምሮ) በእሳት ተቃጥለዋል።
የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያኒን ድርጊቱን በቅርብ ጊዜያት ከተሰነዘሩት ትልልቅ ጥቃቶች አንዱ ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የሩሲያ ባለስልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ሌሊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በሰነዘረችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የረጅም ርቀት ጥቃት አዲስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል።