መረጃ ዘመደመር
1.01K subscribers
48K photos
1.81K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
"ለግብርናው ዘርፍ ወሳኙ ግብዓት ማዳበሪያ በመሆኑ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠራን ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
በመሪዎቿ መቀያየር የማይለወጠው ዘመናትን የተሻገረው የግብፅ ሴራ

ዓባይ ለሰሜን ምሥራቅ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሕይወት እና የኢኮኖሚ ደም ስር ቢሆንም፣ የዘመናት የጂኦ-ፖለቲካዊ ጦርነት እና የዲፕሎማሲ ፍጥጫ አውድማ መሆኑ አልቀረም::

የውኃው 85 በመቶ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ አንዲት ጠብታ ለማታመነጨው ግብፅ ሁሌም እንደ ትልቅ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ትታያለች
ከ162 ዓመታት በኋላ ከባህር ስር የተገኘው የ19ኛው ክፍለ ዘመን ጊነስ ቢራ! 🤔🤔🤔

​በእንግሊዝ ቦይ  ስር ከተሰጠመች ታሪካዊ መርከብ ውስጥ የ162 ዓመት እድሜ ያለው የታሸገ የጊነስ  ቢራ በዋናተኞች ተገኝቷል።

​ይህ የቢራ ጠርሙስ እ.ኤ.አ. በ1864 ከተሰጠመችው 'ሚንዶሮ' ከተባለችው የብሪታንያ የሸራ መርከብ ፍርስራሽ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ ከቪክቶሪያን ዘመን ጀምሮ ከባህር በታች ተጠብቆ ቆይቷል።

​በውስጡ የሚገኘውን የጥንት እርሾ በመመርመር የ19ኛውን ክፍለ ዘመን የጊነስ ቢራ አሰራርና ጣዕም እንደገና ለመስራት ያለመ “ጁራሲክ ቢራ” የተሰኘ የምርምር ፕሮጀክት ተጀምሯል።

​ሳይንቲስቶች ቢራውን መርምረው ለመጠጥ ደህነነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ከገለጹ፣ ቢራውን ያገኘው ዋናተኛ ራሱ ቀምሶ ለመሞከር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጥብቅ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አንድ ወር መሙላቱን አስመልከቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መልዕክት ማምሻውን አስተላልፏል ።

ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ ላለፉት ሰላሳ ቀናት የተካሄደው የምክክር ሂደት ስኬታማና አዲስ የምክክር ባህል እንዲዳብር መሰረት የጣለ እንደነበር ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረና ተፈጥሯዊ የሆኑ አለመግባባቶች ማጋጠማቸውን ጠቁሟል።

በተለይም ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በስም ያልጠቀሳቸው ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላትና አንዳንዶች ሲል የገለጻቸው የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው ብሏል።

ስለሆነም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑና በስፍራው ከሚገኙ ህጋዊ መገናኛ ብዙኃን ከሚወጡ መረጃዎች ውጪ ያሉ ሀሰተኛ ወሬዎችን እንዳይከታተል፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል።

በመጨረሻም ኮሚሽኑ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት በሚፈፅሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህ ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
👍2
እስራኤልን ያስደመመው የኢራን ፈጣን የጦር ማገገም

በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንታት የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ፣ የኢራን ወታደራዊ ኃይል ባሳየው ያልተጠበቀ እና ፈጣን የማገገም ሂደት እስራኤል ከፍተኛ ደንጋጤ እና አግራሞት እንደተፈጠረባት ተገለጸ።

የደህንነት እና የጂኦፖለቲካ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ኢራን በተሰነዘረባት ወታደራዊ ምት ሳቢያ ደክማለች ተብሎ በተገመተበት በአጭር ጊዜ ውስጥ አቅሟን መልሳ በማደራጀት ያሳየችው ፍጥነት የእስራኤልን ወታደራዊ ስትራቴጂስቶች እና የደህንነት ተቋማት አስደምሟል።

ይህ ያልተጠበቀ የኃይል ማገገም በኢየሩሳሌም ከፍተኛ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የጦርነት ሂደት እና የኃይል ሚዛን አዲስ አቅጣጫ ሊያስይዘው እንደሚችል ይገመታል።
1
"ጦርነት የሀገርን ሀብትና የሰው ሕይወት ያጠፋል፤ ሰላም ግን ለልማት መሠረት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ባህርዳር ስታዲየም‼️

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)  መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል።

ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
👍1
"አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ ከቀይ ባህር አባረረን፤ ኢትዮጵያ ለዘመናት ያስከበረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ የጂኦግራፊ እስረኛ ያደረገበት ምክንያት በውስጣችን ያለ ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻት እና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ አይደለም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የውክልና አገልግሎቱን በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወረቀት ነጻ በሆነ ሲስተም ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።

ሜክሲኮ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስር ልዩ እና መደበኛው ቅርንጫፍ ፣አያት አደባባይ ሎሚያድ ሱፐርማርኬት በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራአንድ  እንዲሁም ካዛንቺስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው  ቅርንጫፍ ስምንት እና ቦሌ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራሁለት ጽ/ቤቶች ነው  አገልግሎቱን መስጠት የተጀመረው።

በቅርቡም በሁሉም ቅርጫፎች ተግባራዊ  ለማድረግ እየሰራሁ እገኛለሁ ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገልጋዮች  ምን ይጠበቃል ?

👉https://dars.gov.et:5102 ሊንክ በመጫን መግባት፤

👉 ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም አስፈላጊ ዶክመንቶችን መጫን

👉 ወደተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማቅናት

👉 የተጫነውን መረጃ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን ዶክመንቱ ተመሳክሮ ትክክለኛነቱ  ሲረጋገጥ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ  (signature  pad) በመፈረም የውክልና ሰነዱ በኦንላየን ይላካል።

👉 በሰነዱ መገልገል ሲፈልጉ የሰነዱን ትክክለኛነት በQR Code ማረጋገጥ ይችላሉ።

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ከወረቀትአልባ አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌሳይን  መተግበሪያ አማካይነት የቤተሰብ የጠበቃ እና የአስተዳደር ውክልና አገልግሎት ወደተቋም መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ማግኘት የሚያስችላቸው አሰራር መተግበሩን አስታውሷል።