ፑቲን የወታደራዊ ደንብ ልብስ በመልበስ ለምዕራባውያን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፓሲፊክ ውቅያኖስ የጦር መርከቦች ወታደራዊ ልምምድ አካል በሆነው "ቫርያግ" የጦር መርከብ ላይ ተገኝተው ለምዕራባውያን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጡ።
ፑቲን በስፍራው ባደረጉት ንግግር የኔቶ (NATO) በፓሲፊክ ቀጠና ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴውን ማሳደግ እና አዳዲስ ጥበቃዎች መመስረት በቀጠናው የግጭት ስጋትን እያበዛው ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ምዕራባውያን አገራት የሩሲያ የንግድ መርከቦችን ለመያዝ ወይም ለመውረስ የሚሞክሩ ከሆነ ሞስኮ ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቀዋል። ይሁን እንጂ የሩሲያ ምላሽ የግድ ክስተቱ በተከሰተበት ቀጠና ብቻ ላይወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ፑቲን ሩሲያ ለጃፓን ስጋት እንዳልሆነች እና ምንም ዓይነት የቦታ ይገባኛል ጥያቄ እንደሌላት ገልጸው፣ ሆኖም ቶኪዮ ሩሲያን በወታደራዊ ሰነዶቿ ውስጥ እንደ ዋና ስጋት መፈረጇን ተችተዋል።
ከሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በተካሄደው የፓሲፊክ ውቅያኖስ ልምምድ ላይ 60 የጦር እና የሰርጓጅ መርከቦች፣ 30 አውሮፕላኖች እና ከ13,000 በላይ ወታደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ብቻ የሆነው ዋልያ፦ ቁጥሩ እየጨመረ ነው
በመላው ዓለም ቢዞር በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኘው ዋልያ፣ አሁን ቁጥሩ ከ270 ወደ 306 አድጓል።

"ለግብርናው ዘርፍ ወሳኙ ግብዓት ማዳበሪያ በመሆኑ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠራን ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
በመሪዎቿ መቀያየር የማይለወጠው ዘመናትን የተሻገረው የግብፅ ሴራ
ዓባይ ለሰሜን ምሥራቅ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሕይወት እና የኢኮኖሚ ደም ስር ቢሆንም፣ የዘመናት የጂኦ-ፖለቲካዊ ጦርነት እና የዲፕሎማሲ ፍጥጫ አውድማ መሆኑ አልቀረም::
የውኃው 85 በመቶ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ አንዲት ጠብታ ለማታመነጨው ግብፅ ሁሌም እንደ ትልቅ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ትታያለች

ከ162 ዓመታት በኋላ ከባህር ስር የተገኘው የ19ኛው ክፍለ ዘመን ጊነስ ቢራ! 🤔🤔🤔
በእንግሊዝ ቦይ ስር ከተሰጠመች ታሪካዊ መርከብ ውስጥ የ162 ዓመት እድሜ ያለው የታሸገ የጊነስ ቢራ በዋናተኞች ተገኝቷል።
ይህ የቢራ ጠርሙስ እ.ኤ.አ. በ1864 ከተሰጠመችው 'ሚንዶሮ' ከተባለችው የብሪታንያ የሸራ መርከብ ፍርስራሽ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ ከቪክቶሪያን ዘመን ጀምሮ ከባህር በታች ተጠብቆ ቆይቷል።
በውስጡ የሚገኘውን የጥንት እርሾ በመመርመር የ19ኛውን ክፍለ ዘመን የጊነስ ቢራ አሰራርና ጣዕም እንደገና ለመስራት ያለመ “ጁራሲክ ቢራ” የተሰኘ የምርምር ፕሮጀክት ተጀምሯል።
ሳይንቲስቶች ቢራውን መርምረው ለመጠጥ ደህነነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ከገለጹ፣ ቢራውን ያገኘው ዋናተኛ ራሱ ቀምሶ ለመሞከር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጥብቅ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አንድ ወር መሙላቱን አስመልከቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መልዕክት ማምሻውን አስተላልፏል ።
ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ ላለፉት ሰላሳ ቀናት የተካሄደው የምክክር ሂደት ስኬታማና አዲስ የምክክር ባህል እንዲዳብር መሰረት የጣለ እንደነበር ገልጿል።
ይሁን እንጂ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረና ተፈጥሯዊ የሆኑ አለመግባባቶች ማጋጠማቸውን ጠቁሟል።
በተለይም ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በስም ያልጠቀሳቸው ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላትና አንዳንዶች ሲል የገለጻቸው የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው ብሏል።
ስለሆነም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑና በስፍራው ከሚገኙ ህጋዊ መገናኛ ብዙኃን ከሚወጡ መረጃዎች ውጪ ያሉ ሀሰተኛ ወሬዎችን እንዳይከታተል፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል።
በመጨረሻም ኮሚሽኑ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት በሚፈፅሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህ ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

👍2
እስራኤልን ያስደመመው የኢራን ፈጣን የጦር ማገገም‼
በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንታት የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ፣ የኢራን ወታደራዊ ኃይል ባሳየው ያልተጠበቀ እና ፈጣን የማገገም ሂደት እስራኤል ከፍተኛ ደንጋጤ እና አግራሞት እንደተፈጠረባት ተገለጸ።
የደህንነት እና የጂኦፖለቲካ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ኢራን በተሰነዘረባት ወታደራዊ ምት ሳቢያ ደክማለች ተብሎ በተገመተበት በአጭር ጊዜ ውስጥ አቅሟን መልሳ በማደራጀት ያሳየችው ፍጥነት የእስራኤልን ወታደራዊ ስትራቴጂስቶች እና የደህንነት ተቋማት አስደምሟል።
ይህ ያልተጠበቀ የኃይል ማገገም በኢየሩሳሌም ከፍተኛ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የጦርነት ሂደት እና የኃይል ሚዛን አዲስ አቅጣጫ ሊያስይዘው እንደሚችል ይገመታል።

❤1
"ጦርነት የሀገርን ሀብትና የሰው ሕይወት ያጠፋል፤ ሰላም ግን ለልማት መሠረት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ባህርዳር ስታዲየም‼️
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።
በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል።
ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።

👍1
"አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)