#የውድቀት_አዋጅ!
እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?!
በመጀመሪያ
ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡
ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡
የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ - ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡
ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ - ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ - ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል?
የትምህርት ስረአታችን ማጥ ውስጥ ነው!
በሙስና ተጨማልቀናል!
የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡
በመጨረሻ
ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤
ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡:
Via - በድሉ ዋቅጅራ (phd)

❤1
“በጦርነት ተጀምሮ በጦርነት ያለቀ ታሪክ የለም ፤ ሕዝቡም ውጊያውን ከዚህ በላይ መሸከም አይችልም” - ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ
የተደበቀው_አስፈሪ_እውነት!
የ “TikTok Creative Award” (ሽልማት)አደገኛ ደወል!
✍️ ዶ/ር በረከት አማኑኤል
ከሰሞኑ የተከናወነው የ “TikTok Creative Award” ደማቅ አልባሳት ቅንጦትና አፍራሽ ተግባራት የታዩበት ሊያሳየን ያልቻለው አንድ አስፈሪ እውነት የሀገራችንን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን ነው።
ጥያቄው፡- እየሸለምን ያለነው ሀገር ገንቢዎችን ወይስ ጊዜ ገዳዮችን? የሚለው ነው። ከበለፀጉት ሀገራት ተሞክሮ አንፃር ሲታይ፣ የዘንድሮው ሽልማት ለወጣቱ ያስተላለፈው መልእክት እጅግ አደገኛ ነው።
Has to be banned!!
#ለምን?
1. የቻይናን ጥበብ ወይስ የቻይናን ቆሻሻ? (The Double Standard) የቲክቶክ ባለቤት የሆነችው ቻይና፣ ዓለምን በቴክኖሎጂ የተቆጣጠረችው በመጨፈር አይደለም።
ቻይና ለገዛ ወጣቶቿ የምትፈቅደው የቲክቶክ ቅጂ (Douyin)፣ ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚያሳየው የሳይንስ ሙከራዎችን፣ የሮቦቲክስ ፈጠራዎችን እና የአገር ፍቅር ታሪኮችን ብቻ ነው።
#ለምን?
ምክንያቱም “ነገን የሚረከበው ትውልድ ጭንቅላት በዕውቀት እንጂ መደንዘዝ የለበትም” ብለው ስለሚያምኑ ወደኛ ሲመጣ ግን ነገሩ ተገላቢጦሽ ነው።
ሽልማታችን የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የመፅሀፍ እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ወደ ዳር ገፍቶ “ቀልድን”የጀግንነት ማማ ላይ ሰቀለ። ቻይና ለልጆቿ የዕውቀት ወተት ስትግት፣ እኛ ለልጆቻችን በመዝናኛ የተለወሰ መርዝ እየሰጠን ይሆን? ይህንን ቆም ብለን ልንጠይቅ ልንመረምር ይገባል።
2. “Creative” gፈጠራ) ወይስ “Viral” (ማነጋገሪያ)? ቃላትን በትክክል እንጠቀም። “ፈጠራ” (Creativity) ማለት የህዝብን ችግር የሚፈታ፣ አዲስ እሴት የሚጨምር እና ትውልድን የሚያሻግር ስራ ነው።
ስልክን አገላብጦ በመቅረጽ በሺዎች የሚቆጠሩ “ላይክ”ማግኘት ታዋቂነት (Popularity) እንጂ ፈጠራ (Creativity) ሊሆን አይችልም።
ባደጉት ሀገራት ሽልማት የሚሰጠው ለይዘት ጥራት እና ለሚያመጣው ለውጥ ነው።
እኛ ጋር ግን መስፈርቱ የቁጥር ጨዋታ ሆነ። ሳይንስን፣ ህክምናን እና ትምህርትን የሚያስተላልፉ ቻናሎች እንደ ሁለተኛ ሲታዩ፣ ቀላል መዝናኛዎች የክብር ዙፋን ላይ ተቀምጠዋል። እውቀት በ “ላይክ”ብዛት አይለካም፤ እውነትም በ “ሼር” ብዛት አይረጋገጥም።
3. ለወጣቱ የተላለፈው አደገኛ መልእክት (The Wrong Role Models) አንድ ወጣት ይህንን ሽልማት ሲመለከት አእምሮው ውስጥ የሚቀረፀው ምንድን ነው?
"ለካ ክብር ለማግኘት ተምሮ ዲግሪ መያዝ፣ ሌሊት ተቀን ለሀገር የሚጠቅም ምርምር ማድረግ ወይም መፅሀፍ መጻፍ አይጠበቅብኝም።"
"ለካ አቋራጭ መንገድ አለ! ስልኬ ላይ ብጨፍር፣ በቅጽበት 'የዓመቱ ምርጥ' ተብዬ እሸለማለሁ።"
ይህ አስተሳሰብ የስራ ባህልን (Work ethic) የሚገድል መርዝ ነው። አሜሪካን፣ ጃፓንን እና ጀርመንን የገነቡት ፊታቸው በላብ የረጠበ ኢንጂነሮች ሐኪሞች ሙህራኖች ና ገበሬዎች እንጂ፣ ካሜራ ፊት የሚሽሞነሞኑ አይደሉም።
ወጣቱን ትምህርት እና የሥራ ጎዳና አውጥተን፣ ወደ አቋራጭ መንገድ እየገፋነው ነዉ አገርንም ጭምር!
4. የባህል ወረራ በሽልማት ስም
ሽልማቱ ላይ የታየው የአለባበስ እና የቅንጦት ትርኢት፣ የኢትዮጵያን ወጣት ማንነት የሚወክል ነበር? ወይስ የሆሊውድን "Red Carpet" ለመኮረጅ ?
#Dr.BEREKET EMMANUEL
MD, Author
Founder @influential youth Ethiopia CEO

❤2