#ስምምነት‼️
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደረገ።
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደርጓል።
ስምምነቱ የክልሉ መንግሥት ለሰላም የሰጠው አማራጭ አንዱ አካል የኾነ እና ለቀጣይ የሕዝብ ሰላማዊ እፎይታ መሠረት የሚጥል ነው ተብሏል።
በሁለቱ ወገኖች ስምምነት በአደራዳሪነት የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ተሳትፈዋል።
የሰላም ስምምነቱ በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መካከል ተደርጓል።
በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ ከጦርነት ያተረፈም ኾነ በጦርነት የተጠናቀቀ ግጭት ባለመኖሩ ይህ ድርድር ለክልሉ ሕዝብ ሰላም መነሻ እና ለሰላም የተሰጠ ተግባር ነው ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ብዙ ሰው ይሄን አለባበስ ከሐይማኖት ወይም ከሞራል እና ባህል አንፃር እያየ "የፈረንጆች ባህል" አድርጎ ሲፅፍ አያለሁ። ፈረንጅ ሁሉ እንደምታስቡት አይደለም። ባይፃፍም፣ እንደኛ አምላኩን እየጠራ ባይምል ባይገዘትም የሞራል ህግ አለው። እንደአገር ያቆማቸው ያ ነው! ሚዲያውና ህዝቡ መንገዱም አኗኗሩም የየቅል ነው። የቀለጠው የሆሊውድ መንደር እንኳን በነፃነት ስም እንደእንስሳ በየሜዳው አይጨማለቅም። ባይፃፍም የሞራል ህግ አለው። ለምሳሌ ይሄን አለባበስ ኦስካርን ጨምሮ ሌሎች የሽልማት መድረኮችና የቀይ ምንጣፍ ዝግጅቶች ላይ ለብሶ መገኘት የሚያስጨበጭብ ይመስላችኋል? ከጎን ያለውን አንብቡት። ይህ አለባበስ የዋና ቦታወች፣ የምሽት መጠጥና ጭፍራ ቤቶች ውስጥ የሚለበስ "ርካሽ" ነው ይለናል ፈረንጅ ራሱ። ይህን የፃፍኩት ልጅቱን ለመውቀስ ወይም መነጋገሪያ የመሆን ፍላጎቷን በመዘንጋት አይደለም! ነገ የሚመጡ ልጆች መራቆትን ፈረንጅኛ ፣ ከፍ ማለት አድርገው እንዳይወስዱት፤ አለባበሱ በዋጋም በእይታም በማቴሪያልም ርካሽና ሞገሱ የተገፈፈ መሆኑን ለማሳየት ነው።
ስለዋጋው... ቀሚሱ ከ6- 9 ዶላር ሲሆን ለአጠቃላይ መረዳት መካከለኛ የቡና መጠጫ ዋጋ ነው። በዚህ መንገድ መነጋገሪያ ለመሆን መሞከር ጥሩ መንገድ አይመስልም።
©አሌክስ አብርሃም

የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊዮን ዶላር አፀደቀ
ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን የተቀናሽ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ልዩ አቅርቦት የገንዘብ ድጋፍ የሚከተሉትን ድጎማዎችን አጽድቋል፦
🇪🇹 ለኢትዮጵያ 181.5 ሚሊዮን ዶላር፣
🇩🇯 ለጅቡቲ 29.71 ሚሊዮን ዶላር እና
🇸🇸 ለደቡብ ሱዳን 1.96 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።
የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ሁለት በሦስቱም አገራት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን እንደሚኖሩት የተገለፀ ሲሆን በዚህም፦
🔸 ኢትዮጵያ ውስጥ የ67 ኪሜ የፍጥነት መንገድ ግንባታ እና የዲጂታል የትራንስፖርት ሥርዓቶች ማስፈፀምን ያካትታል።
🔸 በጅቡቲ በ18 ኪሜ የድኪል-ሙሉድ ክፍል (መስመር) ማሻሻያ ላይ ያተኩራል።
🔸 በደቡብ ሱዳን የ280 ኪሜ የካፖዬታ-ቦማ-ራአድ መንገድን ለማሻሻል የሚያስፈልጉ ጥናቶችን የማዘመን ሥራ ትሠራለች።
👉 በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ 50 እና በጅቡቲ 15 ኪሎ ሜትሮች ተለዋጭ መንገዶች የማሻሻያ የፕሮጀክቱ አካል መሆናቸውንም ባንኩ በድረ-ገፁ አስታውቋል።

#የውድቀት_አዋጅ!
እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?!
በመጀመሪያ
ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡
ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡
የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ - ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡
ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ - ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ - ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል?
የትምህርት ስረአታችን ማጥ ውስጥ ነው!
በሙስና ተጨማልቀናል!
የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡
በመጨረሻ
ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤
ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡:
Via - በድሉ ዋቅጅራ (phd)

❤1
“በጦርነት ተጀምሮ በጦርነት ያለቀ ታሪክ የለም ፤ ሕዝቡም ውጊያውን ከዚህ በላይ መሸከም አይችልም” - ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ