Estifanos Getahun
1.06K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
ዛሬ 26 ሺህ ቤቶችን ለአገራችን የመጀመሪያ በሆነ የግንባታ ቴክሎጂ በላፍቶ ሳይት ስራ አስጀምረናል።

በዚህ ዓመት ከያዝናቸው ዋነኛ እቅዶች መካከል ቀዳሚው ለከተማችን ነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ነው።

በመሆኑም በዚህ ዓመት ከ100 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን በርካታ ተግባራትን እያከናወንን ሲሆን፣ እቅዳችንን በጥራትና በፍጥነትን እውን ለማድረግ ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን Cold-Formed Steel (CFS) የግንባታ ቴክኖሎጂን መጠቀም አንድ አማራጭ አድርገን ዛሬ ስራ አስጀምረናል።

ይህ ቴክኖሎጂ በሌላው ዓለም የተለመደ ሲሆን፣ ቤቶችንም ሆነ ህንፃዎችን በፋብሪካ ውስጥ የሚገጣጠሙ ብረቶችን በመጠቀም ወለልን፣ ግድግዳና ጣሪያን ጨምሮ ሁሉንም ክፍል በፍጥነትና በጥራት ማምረት የሚያስችል አሰራር ነው።

የዚህን የቴክኖሎጂ ፋብሪካ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ የተከልን ሲሆን፣ በፈጠራና ፍጥነት መርህ ግንባታን ከሳይት ወደ ፋብሪካ በመቀየር የግንባታ ፍጥነትን በማሳደግ፣ ወጪን በመቀነስና ጥራትን በማሻሻል አንጻር ተመራጭ ነው።

አስተዳደራችን እንደወትሮው የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በጠንካራ የፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ ዲስፕሊን እና በ24/7 የስራ መርሃ ግብር ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቆ ለታለመለት አላማ እንዲውል ያደርጋል።

ይህን ከከተማችን አልፎ ለአገር ጠቃሚ የሆነ ቴክኖሎጂን ወደ አገር ይዘዉ የመጡትን የሌጋሲ ሆም ድርጅት ባለቤት ኢንጂነር ያሬድ አፈወርቅን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ክቦርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
ሦስት ኢትዮጵያውያን የ15ኛው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሔት
የ2025 ዓመት ምርጥ ግለሰቦች ሽልማቶችን አሸነፉ


ከአጠቃላይ 12 "ፐርሰንስ ኦፍ ዘ ይር" አሸናፊዎች ውስጥ የተካተቱት ሦስቱ ኢትዮጵያውያን፣ በሚከተሉት ምድቦች  የዓመቱ መሪዎች መሆናቸውን መጽሄቱ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።

▫️ የአፍሪካ የግብርና ልማት የዓመቱ መሪ ፦ ግርማ አመንቴ፣ የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር

▫️ የአፍሪካ የመንግሥት ዘርፍ መሪ ዓመቱ መሪ፦ ደበሌ ቀበታ፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ  ኮሚሽን ኮሚሽነር እና

▫️ የአፍሪካ የዓመቱ የበጎ አድራጎት ሰው፦ ሳሙኤል ታፈሰ፣ ሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕና የሰንሻይን ፊላንትሮ ፋውዴሽን መሥራች።
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር እ.ኤ.አ በ2027 አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ 32 በማዘጋጀት ረገድ በጋራ ስለምንሰራባቸው መንገዶች ተወያይተናል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ብሎም ዋና ፀሃፊው ከቡድናቸው ጋር በመሆን ኮፕ 32 ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እተማመናለሁ።

I had a fruitful discussion with the Executive Secretary of UN ECA Claver Gatete on the needs and modalities of working together to deliver a truly African COP in 2027. I am confident that the Economic Commission for Africa with the ES and his team will contribute immensely in making COP 32 a remarkable success for Africa.
መቀሌ ከተማ የታጣቂ ኃይሎቹ 👇

📌የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያን

📌 የድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ፣

📌 የትግራይ ቴሌቪዥን ሠራተኞችን አስወጥተው በቁጥጥራቸው ስር ካስገቡ በኋላ የሚድያዎቹ ስርጭት ተቋርጧል።

📌የከተማዋን መውጫና መግቢያ በሮች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ይገኛሉ።

📌 የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በቁጥጥራቸው ስር ማስገባታቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
#ስምምነት‼️
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደረገ።
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደርጓል።

ስምምነቱ የክልሉ መንግሥት ለሰላም የሰጠው አማራጭ አንዱ አካል የኾነ እና ለቀጣይ የሕዝብ ሰላማዊ እፎይታ መሠረት የሚጥል ነው ተብሏል።

በሁለቱ ወገኖች ስምምነት በአደራዳሪነት የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ተሳትፈዋል።

የሰላም ስምምነቱ በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መካከል ተደርጓል።

በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ ከጦርነት ያተረፈም ኾነ በጦርነት የተጠናቀቀ ግጭት ባለመኖሩ ይህ ድርድር  ለክልሉ ሕዝብ ሰላም መነሻ እና ለሰላም የተሰጠ ተግባር ነው ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
ብዙ ሰው ይሄን አለባበስ ከሐይማኖት ወይም ከሞራል እና ባህል አንፃር እያየ "የፈረንጆች ባህል" አድርጎ ሲፅፍ አያለሁ። ፈረንጅ ሁሉ እንደምታስቡት አይደለም። ባይፃፍም፣ እንደኛ አምላኩን እየጠራ ባይምል ባይገዘትም የሞራል ህግ አለው። እንደአገር ያቆማቸው ያ ነው! ሚዲያውና ህዝቡ መንገዱም አኗኗሩም የየቅል ነው። የቀለጠው የሆሊውድ መንደር እንኳን በነፃነት ስም እንደእንስሳ በየሜዳው አይጨማለቅም። ባይፃፍም የሞራል ህግ አለው። ለምሳሌ ይሄን አለባበስ ኦስካርን ጨምሮ ሌሎች የሽልማት መድረኮችና የቀይ ምንጣፍ ዝግጅቶች ላይ ለብሶ መገኘት የሚያስጨበጭብ ይመስላችኋል? ከጎን ያለውን አንብቡት። ይህ አለባበስ የዋና ቦታወች፣ የምሽት መጠጥና ጭፍራ ቤቶች ውስጥ የሚለበስ "ርካሽ" ነው ይለናል ፈረንጅ ራሱ። ይህን የፃፍኩት ልጅቱን ለመውቀስ ወይም መነጋገሪያ የመሆን ፍላጎቷን በመዘንጋት አይደለም! ነገ የሚመጡ ልጆች መራቆትን ፈረንጅኛ ፣ ከፍ ማለት አድርገው እንዳይወስዱት፤ አለባበሱ በዋጋም በእይታም በማቴሪያልም ርካሽና ሞገሱ የተገፈፈ መሆኑን ለማሳየት ነው።

ስለዋጋው... ቀሚሱ ከ6- 9 ዶላር ሲሆን ለአጠቃላይ መረዳት መካከለኛ የቡና መጠጫ ዋጋ ነው። በዚህ መንገድ መነጋገሪያ ለመሆን መሞከር ጥሩ መንገድ አይመስልም።

©አሌክስ አብርሃም