Estifanos Getahun
1.06K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
ዛሬ 26 ሺህ ቤቶችን ለአገራችን የመጀመሪያ በሆነ የግንባታ ቴክሎጂ በላፍቶ ሳይት ስራ አስጀምረናል።

በዚህ ዓመት ከያዝናቸው ዋነኛ እቅዶች መካከል ቀዳሚው ለከተማችን ነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ነው።

በመሆኑም በዚህ ዓመት ከ100 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን በርካታ ተግባራትን እያከናወንን ሲሆን፣ እቅዳችንን በጥራትና በፍጥነትን እውን ለማድረግ ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን Cold-Formed Steel (CFS) የግንባታ ቴክኖሎጂን መጠቀም አንድ አማራጭ አድርገን ዛሬ ስራ አስጀምረናል።

ይህ ቴክኖሎጂ በሌላው ዓለም የተለመደ ሲሆን፣ ቤቶችንም ሆነ ህንፃዎችን በፋብሪካ ውስጥ የሚገጣጠሙ ብረቶችን በመጠቀም ወለልን፣ ግድግዳና ጣሪያን ጨምሮ ሁሉንም ክፍል በፍጥነትና በጥራት ማምረት የሚያስችል አሰራር ነው።

የዚህን የቴክኖሎጂ ፋብሪካ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ የተከልን ሲሆን፣ በፈጠራና ፍጥነት መርህ ግንባታን ከሳይት ወደ ፋብሪካ በመቀየር የግንባታ ፍጥነትን በማሳደግ፣ ወጪን በመቀነስና ጥራትን በማሻሻል አንጻር ተመራጭ ነው።

አስተዳደራችን እንደወትሮው የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በጠንካራ የፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ ዲስፕሊን እና በ24/7 የስራ መርሃ ግብር ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቆ ለታለመለት አላማ እንዲውል ያደርጋል።

ይህን ከከተማችን አልፎ ለአገር ጠቃሚ የሆነ ቴክኖሎጂን ወደ አገር ይዘዉ የመጡትን የሌጋሲ ሆም ድርጅት ባለቤት ኢንጂነር ያሬድ አፈወርቅን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ክቦርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ