Estifanos Getahun
1.06K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
1
እንኳን ደስ አለን!

በእግር ኳስ ስፖርት የጀመርነው ፕሮጀክት ፍሬ በማፍራት ላይ ነው። ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ ሲካሄድ በነበረው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ከ17 ዓመት በታች ውድድር፣ ብሔራዊ ቡድባችን የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት ከ 22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ችሏል። ይህ ድል የእግር ኳስ ስፖርት ወዳድ ለሆነው ህዝባችን የዘመናት ቁጭት በቅርቡ መልስ እንደሚያገኝ ያሳየ ነው።

ቀይ ቀበሮዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት ለዘርፉ የሰጠነው ትኩረት ውጤት እያፈራ መሆኑን ማሳያ ነው።

በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መላው የቡድኑ አባላትን፣ የኢትዮዽያን ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

via - ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
የሁለት ሰዎችን ህይወት አጥፍቶ የተሰወረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሽ እሱ ያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነህ ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡

ተከሳሽ ከባለቤቱ ጋር በኪራይ ከሚኖሩበት ቤት ህዳር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሲሆን ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ በሚል ቂም በቀል በመነሳሳት ሟችን አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ለጊዜው ይሰወራል፡፡

ተከሳሹ በዚሁ ብቻ አላባቃም ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ባለቤቱን ከገደለበት መኖሪያ ግቢ ተመልሶ በመምጣት ከእዚህ ቀደም ከባለቤቱ ጋር በሚፈጠረው ፀብ ያሸማግል የነበረን አለባቸው አየለ የተባለን ጎረቤቱን በሟች ባለቤቱ ይጠረጥረው ነበርና መሳሪያ በመተኮስ በስምንት ጥይት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአካባቢው ሊሰወርም ችሏል፡፡

የወንጀሉ መፈፀም መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍሉ የወንጀል ስፍራው ላይ በመገኘት የሟች አለባቸው አየለን አስከሬን በማንሳትና ከአካባቢው በሰበሰበው መረጃ መነሻነት የሟች መኖሪያ ቤት ሲከፈት የሐመልማል አለምነህ አስከሬን ሊገኝም ችሏል፡፡

ፖሊስ ከወንጀሉ መፈፀም በመነሳት ተገቢውን የሰውና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን በመከታተል ተጠርጣሪውን ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት መኖሪያ ቤት የግድያ ወንጀሉን ከፈፀመበት መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡
"ሚናን ለይቶ ለመፍትሔ መቆም ሰላምን ያረጋግጣል" ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
#Baay’isuu: Muuxannoowwan gaggaarii fi milkaahinoota argaman karaa qindaa’een babal’isuu;