በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ውልቂጤ ወረዳ ነፍጥ አንግበው የህዝብን ሰላም ሲነሱ እና ልማት ሲያደናቅፉ የነበሩ ሸኔዎች የሰላም አማራጭን በመቀበል የቡድኑን ምክትል መሪ ጃል ቦሬሳ ጨምሮ ዘጠኝ የቡድኑ አባላት ከነ-ሙሉ ትጥቃቸው እጅ መስጠታቸውን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ጸጋየ በርሄ ገልጸዋል።
ዋና አዛዡ ክፍለ ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው ለህዝብና ለሀገር ልማትና ደህንነት ሲባል በጫካ የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላምን መንገድ በመከተል መደበኛ ህይወታቸውን መምራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

Forwarded from Fana Media Corporation S.C (FMC)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በእድገት እና አመራር ልምዶቻቸውን ለመለዋወጥ ለእሳት ዳር ወግ ተቀምጠዋል።
Forwarded from Ethiopian News Agency
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መለያችንና የኢኮኖሚ ዋልታችን በሆነው ቡናችን እያስመዘገብነው ያለውን ስኬት በጥራትና በፍጥነት አጠናክረን መቀጠል አለብን።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የባለድርሻ አካላት የእውቅና መርኃ ግብር ላይ ተገኝተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

👍2
መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን አስታወቀ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባጋራው መረጃ እንዳስታወቀው፤ "በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት፤ የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን" አመላክቷል።
"ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል" ሲል ጠቁሟል።
ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ በውድድር በተሞላበት የአህጉር አቀፍ ሂደት ፣ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ የድርጊት ማዕቀፍ ስር የሚካሄደውን 32ኛው የተሳታፊ አካላት ጉባኤ (ኮፕ32) ለማስተናገድ የአፍሪካ ኅብረትን ድጋፍ ካገኘች በኋላ ነው።
ይህ ውሳኔ ከህዳር 1 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በቤሌም ብራዚል በተካሄደው የኮፕ30 ጉባኤ በሁለተኛው ቀን ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በብራዚል የኮፕ30 ፕሬዝዳንት የተረጋገጠ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት “ከዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት በመተባበር” የመጀመሪያውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በአፋር ክልል ሃይሊ ጎቢ ተራራ ላይ አዲስ የተከሰተው እሳተ ጎመራ
በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ፈንድቷል!
ፍንዳታው ለሰዓታት የቀጠለ እና ከፍተኛ የጭስ እና የአመድ ብናኝ ወደ ሰማይ ለቋል። እንደ እድል ሆኖ ግን በአካባቢው ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም።
የሃይሊ ጉቢ እሳተ ጎሞራ ዳግም መነቃቃት አስገራሚ ክስተት ነበር ። ምክንያቱ ደግሞ እሳተ ገሞራው ምናልባትም ላለፉት 12,000 ዓመታት አንቀላፍቶ ነበር።
ምንም እንኳን ከአካባቢው የተገኘ መረጃ አነስተኛ ቢሆንም፣ እሳተ ጎሞራው ለመጨረሻ ጊዜ ንቁ የነበረው መቼ እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አስቸጋሪ ነው።
ነገር ግን በምስራቅ አፍሪካ ታላቁ የስምጥ ስርዓት ጫፍ ላይ በሚገኘው በዚህ በጣም ንቁ የሆነ የእሳተ ገሞራ ክልል ውስጥ እንደዚህ ያሉት ፍንዳታዎች በርግጥም ይጠበቃሉ።
- ስምጥ ሸለቆ በጣም ግዙፍ እና አፍሪካን ለሁለት እየከፈለ ነው

ለመንግሥት ገቢ መሆን የነበረበትን ከ100 ቢሊየን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ የስፖርት አወራራጅ ድርጅት ባለቤቶችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው÷ በቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶችና ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር በሚባሉ የገንዘብ ክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተባባሪ ተቋማት ዙሪያ ጥናትና ክትትል ሲከናወን ቆይቷል፡፡
ፈቃድ ያላቸውና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በገቡት ውል መሰረት የማይሠሩ፣ በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው በመገኘታቸው ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው እንዲሁም ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው በስፖርት አወራራጅነት ተሰማርተው የነበሩ አካላት በዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ትስስር አማካይነት በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው መገኘታቸው ተገልጿል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ትብብር አማካኝነት 24 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መግለጫው አስታውቋል፡፡
በተለይ በሕጋዊነት ሽፋን ፈቃድ ያወጡት ድርጅቶች ላይ ክትትል ለማድረግ ሙከራ በተደረገበት ወቅት ሁሉም ፈቃድ ሲያወጡ ይዘውት ከነበረው ቢሮ መልቀቃቸውና አድራሻቸውን መሰወራቸው ተረጋግጧል፡፡
የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶቹ ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር ተብለው ከሚጠሩ የፋይናንስ ስርዓቶችን ከሚያሳልጡላቸው የሀገር ውስጥ የክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተቋማት ጋር በመመሳጠር በአጠቃላይ ሲያንቀሳቅሱት ከነበረው የገንዘብ መጠን መንግሥት በተለያዩ የገቢ አማራጮች ማግኘት የነበረበትን 100 ቢሊየን ብር በላይ መሰወራቸው እንደተደረሰበት አመላክቷል፡፡
የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶቹ በተለያዩ የገንዘብ ክፍያ ስርዓቶች አማካይነት የሚሰበስቡትንና የሚያዘዋውሩትን የገንዘብ መጠን ያማከለ ግብር አለመክፈላቸው እንደተደረሰበት የጠቆመው መግለጫው÷ በክሪፕቶከረንሲ እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሃዋላ ገንዘብ ማስተላላፊያ አማራጮች አማካኝነት የሚያገኙትን ገቢ በውጭ ምንዛሪ በመቀየር ሲሰውሩና ከሀገር እንዲወጣ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡
ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር የሚባሉት የሀገር ውስጥ የገንዘብ ክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተቋማቱ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በመውሰድ የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፤ የደንበኛን ምስጢር መጠበቅ የሚል ሙያዊ አሠራርን እንደ ሽፋን ተጠቅመው የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች የሚያንቀሳቅሱትን የገንዘብ መጠን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አስፈፃሚ ተቋማት በመደበቅ ወይም አሳንሶ በማቅረብ በግብር ስወራ እንዲሁም ከፍተኛ የሀገር ሀብትን ወደ ውጭ በማሸሽ ወንጀል ላይ ተሳትፎ እንዳላቸው የአገልግሎቱ መግለጫ አብራርቷል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ገለሠቦች ጭምር ከኢትዮጵያ ውጪ ሆነው ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችው ውክልና በመስጠት ሕገ-ወጥ ድርጊቱን ሲፈጸሙ መቆየታቸው እንዲሁም ውጭ ሀገር የበለጸጉ ሶፍትዌሮች ጥቅም ላይ መዋላቸውና ድርጅቶቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው መሆኑ ወንጀሉን ውስብስብና ለቁጥጥር አስቸጋሪ አድርጎት ቢቆይም የደኅንነት ተቋሙ ከሌሎች የመረጃና የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ስምሪት ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡
በሕገ ወጥ ድርጊቱ ከሀገር ሲሸሽ የነበረው ከፍተኛ ገንዘብ ሽብርተኝነትንና ጸረ ሰላም ቡድኖችን በገንዘብ ለመደገፍ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ለማስመሰል እንዲሁም ለኮንትሮባንድ ንግድ ማካሄጃ እንደሚውል የጠቆመው መግለጫው፤ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመጻረር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞች ስጋት ላይ ለመጣል የሚደረግ እንቅስቃሴ አካል በመሆኑ ዜጎች ማንኛውም አይነት ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ሲመለከቱ ለደኅንነትና ጸጥታ አካላት የሚሰጡትን ጥቆማ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን 96ኛውን የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመረጠች
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን 96ኛውን የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ በሙሉ ድምፅ የተመረጠችው በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ ሲካሄድ በቆየው 93ኛ የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ነው።
ከሦስት ወር በፊት እ. ኤ.አ 2025 በነሐሴ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ ተደርጎ በነበረው 26ኛው የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጂናል ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ቀጣዩን በ2027 የሚካሄደውን 27ኛውን የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጅናል ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ መመረጧ ይታወሳል።

በከፋ ድህነት የተዘፈቁ 10 ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት
(በቀን ከ3 ዶላር በታች የሚኖሩ በፐርሰንት)
1. ኮንጎ ሪፐብሊክ፡ 85.3%
2. ሞዛምቢክ: 82.2%.
3. ማላዊ ፡ 75.4%
4. ብሩንዲ፡ 74.2%
5. ዛምቢያ፡ 71.7%
6. መካከለኛው አፍሪካ ሪፐ. 71.6%
7. ኒጀር: 60.5%.
8. ኡጋንዳ: 59.8%.
9. ዚምባብዌ፡ 49.2%
10. ኬንያ፡ 46.4%
ምንጭ፡- Africa is Home
(በቀን ከ3 ዶላር በታች የሚኖሩ በፐርሰንት)
1. ኮንጎ ሪፐብሊክ፡ 85.3%
2. ሞዛምቢክ: 82.2%.
3. ማላዊ ፡ 75.4%
4. ብሩንዲ፡ 74.2%
5. ዛምቢያ፡ 71.7%
6. መካከለኛው አፍሪካ ሪፐ. 71.6%
7. ኒጀር: 60.5%.
8. ኡጋንዳ: 59.8%.
9. ዚምባብዌ፡ 49.2%
10. ኬንያ፡ 46.4%
ምንጭ፡- Africa is Home