Estifanos Getahun
1.06K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥ እና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

Taking time to learn from one another through a fireside chat entitled “Building Nations, Bridging Worlds,” with Prime Minister Lawrence Wong as he shares the successes and lessons from Singapore’s growth. I’m grateful for Prime Minister Wong’s insights on nation building governance and leadership, economic transformation.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ዛሬ ጠዋት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዘዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰንን አግኝቼ በቀጠናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።

I welcomed General Dagvin R. M. Anderson, Commander of the U.S. Africa Command, this morning for a constructive exchange on regional security and opportunities for enhanced cooperation.
Miidhaa dubartootarra gahu ittisuun itti gaafatamummaa lammii hunaati!
=
Ayyaanni guyyaa Riibaanii Adii sadarkaa Addunyaatti yeroo 34ffaa akka Biyyaafi Naannoo Oromiyaatti yeroo 20ffaaf  mata duree "Hawaasa miidhaa obsuu hin dandeenye ijaarsa dhalootaaf!" jedhuun Magaala Adaamaatti deemsa lafootiin kabajamaa jira.

Guyyaan Riibaanii Adii (White Ribbon Day)  dhimma yakka dubartootaa fi daa'imman irratti raawwatamu balaaleffachuu fi hubannoo uumuu kaayyeffatee kan kabajamu sochii addunyaalessaa yoo ta'u, keessumaa dhiirotaan miidhaa dubartootaarra ga'u dhaabsisuuf kan Akka Addunyaattis akka biyya keenyaattis kan eegaledha.

Mootummaan Naannoo Oromiyaas, Miidhaa dubartootaafi daa'ïimmanirra ga'u hir'isuuf imaammata, qajeelfamootaafi inisheetiiviiwwan garaagaraa hojirra oolchuun fooyya'insi gaarii akka dhufu xiyyeeffannoon hojjechaa jira.

Federaalizimii Sabdaneessi Wabii  Keenya!
1
በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ውልቂጤ ወረዳ ነፍጥ አንግበው የህዝብን ሰላም ሲነሱ እና ልማት ሲያደናቅፉ የነበሩ ሸኔዎች የሰላም አማራጭን በመቀበል የቡድኑን ምክትል መሪ ጃል ቦሬሳ ጨምሮ ዘጠኝ የቡድኑ አባላት ከነ-ሙሉ ትጥቃቸው እጅ መስጠታቸውን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ጸጋየ በርሄ ገልጸዋል።

‎ዋና አዛዡ ክፍለ ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው ለህዝብና ለሀገር ልማትና ደህንነት ሲባል በጫካ የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላምን መንገድ በመከተል መደበኛ ህይወታቸውን መምራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
Forwarded from Ethiopian News Agency
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሶስተኛዉ የኢጋድ ሚዲያ አዋርድ
#አሁን 👆 #LIVE

ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤዝ ኮርስ ስራ እየተከናወነ ነው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በእድገት እና አመራር ልምዶቻቸውን ለመለዋወጥ ለእሳት ዳር ወግ ተቀምጠዋል።
Forwarded from Ethiopian News Agency
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መለያችንና የኢኮኖሚ ዋልታችን በሆነው ቡናችን እያስመዘገብነው ያለውን ስኬት በጥራትና በፍጥነት አጠናክረን መቀጠል አለብን።

ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የባለድርሻ አካላት የእውቅና መርኃ ግብር ላይ ተገኝተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
👍2
መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን አስታወቀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባጋራው መረጃ እንዳስታወቀው፤ "በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት፤ የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን" አመላክቷል።

"ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል" ሲል ጠቁሟል።

ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ በውድድር በተሞላበት የአህጉር አቀፍ ሂደት ፣ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ የድርጊት ማዕቀፍ ስር የሚካሄደውን 32ኛው የተሳታፊ አካላት ጉባኤ (ኮፕ32) ለማስተናገድ የአፍሪካ ኅብረትን ድጋፍ ካገኘች በኋላ ነው።

ይህ ውሳኔ ከህዳር 1 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በቤሌም ብራዚል በተካሄደው የኮፕ30 ጉባኤ በሁለተኛው ቀን ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በብራዚል የኮፕ30 ፕሬዝዳንት የተረጋገጠ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት “ከዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት በመተባበር” የመጀመሪያውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
በአፋር ክልል ሃይሊ ጎቢ ተራራ ላይ አዲስ የተከሰተው እሳተ ጎመራ 
በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ፈንድቷል!

ፍንዳታው ለሰዓታት የቀጠለ እና ከፍተኛ የጭስ እና የአመድ ብናኝ ወደ ሰማይ ለቋል። እንደ እድል ሆኖ ግን በአካባቢው ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም።

የሃይሊ ጉቢ እሳተ ጎሞራ ዳግም መነቃቃት አስገራሚ ክስተት ነበር ። ምክንያቱ ደግሞ እሳተ ገሞራው ምናልባትም ላለፉት 12,000 ዓመታት አንቀላፍቶ ነበር።

ምንም እንኳን ከአካባቢው የተገኘ መረጃ አነስተኛ ቢሆንም፣ እሳተ ጎሞራው ለመጨረሻ ጊዜ ንቁ የነበረው መቼ እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አስቸጋሪ ነው።

ነገር ግን በምስራቅ አፍሪካ ታላቁ የስምጥ ስርዓት ጫፍ ላይ በሚገኘው በዚህ በጣም ንቁ የሆነ የእሳተ ገሞራ ክልል ውስጥ እንደዚህ ያሉት ፍንዳታዎች በርግጥም  ይጠበቃሉ።

- ስምጥ ሸለቆ በጣም ግዙፍ እና አፍሪካን ለሁለት እየከፈለ ነው
ለመንግሥት ገቢ መሆን የነበረበትን ከ100 ቢሊየን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ የስፖርት አወራራጅ ድርጅት ባለቤቶችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው÷ በቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶችና ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር በሚባሉ የገንዘብ ክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተባባሪ ተቋማት ዙሪያ ጥናትና ክትትል ሲከናወን ቆይቷል፡፡

ፈቃድ ያላቸውና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በገቡት ውል መሰረት የማይሠሩ፣ በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው በመገኘታቸው ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው እንዲሁም ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው በስፖርት አወራራጅነት ተሰማርተው የነበሩ አካላት በዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ትስስር አማካይነት በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው መገኘታቸው ተገልጿል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ትብብር አማካኝነት 24 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መግለጫው አስታውቋል፡፡

በተለይ በሕጋዊነት ሽፋን ፈቃድ ያወጡት ድርጅቶች ላይ ክትትል ለማድረግ ሙከራ በተደረገበት ወቅት ሁሉም ፈቃድ ሲያወጡ ይዘውት ከነበረው ቢሮ መልቀቃቸውና አድራሻቸውን መሰወራቸው ተረጋግጧል፡፡

የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶቹ ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር ተብለው ከሚጠሩ የፋይናንስ ስርዓቶችን ከሚያሳልጡላቸው የሀገር ውስጥ የክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተቋማት ጋር በመመሳጠር በአጠቃላይ ሲያንቀሳቅሱት ከነበረው የገንዘብ መጠን መንግሥት በተለያዩ የገቢ አማራጮች ማግኘት የነበረበትን 100 ቢሊየን ብር በላይ መሰወራቸው እንደተደረሰበት አመላክቷል፡፡

የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶቹ በተለያዩ የገንዘብ ክፍያ ስርዓቶች አማካይነት የሚሰበስቡትንና የሚያዘዋውሩትን የገንዘብ መጠን ያማከለ ግብር አለመክፈላቸው እንደተደረሰበት የጠቆመው መግለጫው÷ በክሪፕቶከረንሲ እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሃዋላ ገንዘብ ማስተላላፊያ አማራጮች አማካኝነት የሚያገኙትን ገቢ በውጭ ምንዛሪ በመቀየር ሲሰውሩና ከሀገር እንዲወጣ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡

ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር የሚባሉት የሀገር ውስጥ የገንዘብ ክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተቋማቱ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በመውሰድ የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፤ የደንበኛን ምስጢር መጠበቅ የሚል ሙያዊ አሠራርን እንደ ሽፋን ተጠቅመው የቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች የሚያንቀሳቅሱትን የገንዘብ መጠን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አስፈፃሚ ተቋማት በመደበቅ ወይም አሳንሶ በማቅረብ በግብር ስወራ እንዲሁም ከፍተኛ የሀገር ሀብትን ወደ ውጭ በማሸሽ ወንጀል ላይ ተሳትፎ እንዳላቸው የአገልግሎቱ መግለጫ አብራርቷል፡፡

የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ገለሠቦች ጭምር ከኢትዮጵያ ውጪ ሆነው ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችው ውክልና በመስጠት ሕገ-ወጥ ድርጊቱን ሲፈጸሙ መቆየታቸው እንዲሁም ውጭ ሀገር የበለጸጉ ሶፍትዌሮች ጥቅም ላይ መዋላቸውና ድርጅቶቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው መሆኑ ወንጀሉን ውስብስብና ለቁጥጥር አስቸጋሪ አድርጎት ቢቆይም የደኅንነት ተቋሙ ከሌሎች የመረጃና የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ስምሪት ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

በሕገ ወጥ ድርጊቱ ከሀገር ሲሸሽ የነበረው ከፍተኛ ገንዘብ ሽብርተኝነትንና ጸረ ሰላም ቡድኖችን በገንዘብ ለመደገፍ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ለማስመሰል እንዲሁም ለኮንትሮባንድ ንግድ ማካሄጃ እንደሚውል የጠቆመው መግለጫው፤ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመጻረር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞች ስጋት ላይ ለመጣል የሚደረግ እንቅስቃሴ አካል በመሆኑ ዜጎች ማንኛውም አይነት ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ሲመለከቱ ለደኅንነትና ጸጥታ አካላት የሚሰጡትን ጥቆማ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በመግለጫው አመላክቷል፡፡