Estifanos Getahun
1.06K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብያለው።

ውይይታችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለንን ግንኙነት ለጋራ ነጋችን ወሳኝ በሆኑ መስኮች በጋራ ለመሥራት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አንድ ጠቃሚ ርምጃ ነው። በተለይም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር ትብብር ላይ ያደረግናቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት ብሎም በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው።

ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችንም ክብር ይሰማናል። በላቀ ተግባራዊ ትብብር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን በማልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በገንዘብ ልውውጥ ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ደኅንነት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለንን ትብብር ለመጠቀም እጅግ ሰፊ አቅም አለን።
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ያደረጉት ጉብኝት ...
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ያደረጉት ጉብኝት : እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያደረጉላቸው አቀባበል!!

#aa_prosperity
#addisababa #Ethiopia
Singapore Ministry of Manpower
Singapore Airlines
#singapore
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥ እና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

Taking time to learn from one another through a fireside chat entitled “Building Nations, Bridging Worlds,” with Prime Minister Lawrence Wong as he shares the successes and lessons from Singapore’s growth. I’m grateful for Prime Minister Wong’s insights on nation building governance and leadership, economic transformation.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ዛሬ ጠዋት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዘዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰንን አግኝቼ በቀጠናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።

I welcomed General Dagvin R. M. Anderson, Commander of the U.S. Africa Command, this morning for a constructive exchange on regional security and opportunities for enhanced cooperation.