Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሃሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር የመወያየት እድል አግኝተናል። ውይይታችን ስትራቴጂካዊ ትብብራችንን በማጠናከር ለበለጠ የጋራ ርምጃ እድሎችን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር።

On the sidelines of the G20 Summit, I also had the honor of meeting with Sheikh Khaled bin Mohamed bin Zayed Al Nahyan, Crown Prince of Abu Dhabi. The discussions focused on strengthening strategic partnerships and opportunities for collaboration.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My address at the G20 Leaders’ Summit
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር፣ እና በሁለትዮሽ ግንኙነት በትምህርት ፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል። ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር።

Met with President Alexander Stubb of Finland for bilateral discussions on regional issues, multilateral cooperation, and bilateral cooperation in education, climate action, and investment opportunities in Ethiopia amid the country’s economic opening. The meeting reaffirmed our commitment to strengthen bilateral ties and advance mutually beneficial collaboration.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የኢትዮ-አውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ለማላቅ ከአውሮፓ ኅብረት ምክርቤት ፕሬዝደንት አንቶኒዮ ኮስታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በተለያዩ ዘርፎች ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር አቋማችንን እንደገና አጽንተናል።

Building on Ethio-EU existing relations, I held a bilateral meeting with António Costa, President of the European Council. We reaffirmed our commitment to deepening cooperation between Ethiopia and the European Union across multiple areas.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተከናወኑ ባሉ ትብብሮች መጠናከሩን ቀጥሏል። በዚህ ረገድም ከፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ትብብሮቻችን ስላሉበት ደረጃ ተነጋግረናል።

Ethiopia-France relations continue to strengthen through ongoing engagements. Accordingly, President Macron and I had the opportunity to meet on the sidelines of the G20 Leaders’ Summit for a productive catch-up.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ውይይታችን በቁልፍ የጋራ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ትስስራችንን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመፈለግ ያለንን ፍላጎት ገልጸናል።

Good to meet with Chancellor Friedrich Merz today. We exchanged views on key areas of mutual interest and expressed our shared intention to explore ways to strengthen ties.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ ትብብር፣ የጋራ ትኩረት በሚሹ የባለብዙወገን ጉዳዮች ብሎም ትብብራችንን በሚያጠናክሩ እና ዘላቂ እድገትን በሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተወያይተናል።

Had a constructive meeting with Norway’s Prime Minister Jonas Gahr Støre, focusing on climate action cooperation, multilateral issues of shared concern, and opportunities for investment to strengthen our partnership and drive sustainable growth.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
በቡድን ሃያ መሪዎች ስብሰባ ፍሬያማ እና ትርጉም ያላቸው ተጨማሪ ውይይቶችን ከህንድ፣ ቬይትናም፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር አካሂደናል።

A productive and substantive day at the G20 Leaders’ Summit with additional engagements with fellow leaders from India, Vietnam, South Korea and Australia as well.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር መልካም ውይይት አድርገናል። በሁለቱም ሀገሮቻችን ቅድሚያ በምንሰጠው በንግድ እና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ባተኮረ የግብርና ማዘመን ሥራ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተነጋግረናል።

Good conversation with Vice President Gibran Rakabuming Raka of Indonesia at the G20 Summit. We explored ways to strengthen the cooperation of the two countries on trade and agricultural modernization with a focus on food sovereignty, which is a priority for both countries.
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተገናኝተን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ጠንካራውን እና ለረጅም ዘመናት የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደፊት ማራመድ በማስፈለጉ ላይ ተወያይተናል።

Met with Sir Keir Starmer, Prime Minister of the United Kingdom for exchanges on the need to take forward the strong and longstanding bilateral relations between two countries.