Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
"እስራኤል የኢትዮጵያን የወደብ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትደግፋለች" በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ

እስራኤል የኢትዮጵያን የዓባይ ውሃ አጠቃቀም እና የወደብ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትደግፋለች ሲል በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ አብዛኛው የኤምባሲው ሥራ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማራመድ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ስለዚህ አንዱ ብሔራዊ ጥቅም ከዓባይ ውሃ አጠቃቀም እና ከኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ በዋናነት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

"በታሪክ ወደኋላ ተመልሰን ስናይ እስራኤል ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንዳትሆን ስትሰራ ነበር" ያሉት አምባሳደሩ፤ "ይህም ለኢትዮጵያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለራሷም ብላ የምታደርገው ነበር።" ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ከወደብ ተጠቃሚነት በተገፋች ቁጥር ቀይ ባህር የአረብ ሀገራት የበላይነት ይነግስበታል፡፡ ይህ ደግሞ ጉዳቱ ለእስራኤልም ጭምር ነው" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እስራኤል ከቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በወታደራዊ ስልጠና ኢትዮጵያን ስታግዝ እንደነበር በመግለጽም፤ በወቅቱ "ነበልባል" የተሰኘ ጦር በእስራኤሎች መሰልጠኑን አስታውሰዋል። በተጨማሪም አየር ኃይልን የማጠናከር ሥራ በእስራኤል መሰራቱን ገልጸዋል።

"ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተነጠለች ነጻ ሀገር መሆኗን ተከትሎም፤ ኢትዮጵያ ከሁለት ወደቦች ማለትም ከምጽዋ እና አሰብ ባለቤትነት ወደ ወደብ አልባ ሀገርነት ተቀየረች" ብለዋል።

በተጨማሪም በደርግ ጊዜም ሆነ እ.ኤ.አ ከ1973 በኋላ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተቋርጦ እንደነበር ያስታወሱት አምባሳደር ተስፋዬ፤ ሆኖም ከወታደራዊው ደርግ መንግሥት ጋር ይፋ የማይወጣ በወታደራዊና በመረጃ ልውውጥ የመተባበር ግንኙነት እንደነበር ተናግረዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ በሕጋዊ፣ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ጥረት እያደረገች መሆኑን በማንሳት፤ ኤምባሲው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህን የኢትዮጵያን ጥያቄ በማስረዳት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ስለዚህ "በእስራኤል በኩል ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄዋን የመቃወም ሁኔታ የለም" ሲሉ ከአሐዱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህንንም ሲያብራሩ፤ "ኢትዮጵያ እንደገና መልሳ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ ብትመጣ አንደኛ ወዳጅ ሀገር ናት፤ በተጨማሪም እስራኤል ኢትዮጵያን መግቢያ በር አድርጋ ስለምትመለከታት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንድታግዛት ትፈልጋለች" ብለዋል።

"እስራኤላውያን ኢትዮጵያን የሚያዩበት መንገድ የተለየ ነው" ያሉት አምባሳደር ተስፋዬ፤ "በተጨማሪም በአፍሪካ ሕብረት የተመልካችነት ድርሻን መልሶ ለማግኘት የእኛን ድጋፍ ይሻሉ" ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ የልማት አቅም ያላት ሀገር በመሆኗ፤ 'በዚህ ውስጥ በመሳተፍ እኛም እንጠቀማለን' ብለው እንደሚያስቡ አብራርተዋል፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያን ጥያቄዎች የመደገፍ እንጂ ለምን እና እንዴት? የሚለውን ነገር አያነሱም ሲሉ ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ አሁን ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ የእስራኤል መንግሥት ይደግፈዋል ግን አሁን በኢትዮጵያ ጉዳይ መግለጫ መስጠት አይችልም" ያሉት አምባሳደሩ፤ "ሁኔታው እያደገ ሲሄድ ድጋፉን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ጉዳይ እየተነጋገርን ነው" ብለዋል።

አምባሳደር ተስፋዬ አክለውም፤ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጾች መጀመሪያ ግድቡ እንዳይሰራ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ግንባታውን አጠናቃ ማስመረቋን አስታውሰዋል።

"ግብጾች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች መሰረተ ቢስ ናቸው" ያሉም ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የሄደችበት መንገድ እንዲሁም ጉዳዩን በበቂ ሁኔታ በዓለም አቀፍ መድረኮች እያስረዳች ስለመጣች 'አሁን ድርድሩ ውጤት ስላላመጣልን ትተነዋል' የሚል አቋም መያዛቸውን አስረድተዋል።

"ከዚያ ውጪ ግን በዚህ ዓመት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደብዳቤ ጽፈው ነበር ለዚያም አጥጋቢ መልስ ተሰጥቷል" ብለዋል።

"በዚህም ዓለም የእኛ እውነት እየገባው ነው" ያሉ ሲሆን፤ ዋናው ነገር ግድቡ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ነው። የተወሰኑ ተግዳሮቶች ይኖራሉ እነሱን ደግሞ በተለመደው መልኩ እየተቋቋምን ራሳችንን እያጠነከርን እንሄዳለን ብለዋል።

በሌላ በኩል በእስራኤል የሚገኙ ቤተ-እስራኤላውያ ከ175 ሺሕ እስከ 180 ሺሕ እንደሚገመቱ የገለጹት አምባሳደሩ፤ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

በእስራኤል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ባህላዊ መገለጫ የሆኑ መደብሮች እና ሬስቶራንቶች መኖራቸውን ገልጸው፤ በእነርሱም አማካኝነት የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች፣ አልባሳት እና ቋንቋ የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ እስራኤላዊያን በተለያዩ የልማት እና የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እንደሚሳተፉ በማንሳት፤ ኤምባሲው በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም እድሎችን ለእስራኤላውያን የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ይህም የሁለቱን ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት ይበልጥ እያጠናከረው እንደሚገኝ ነው ብለዋል፡፡
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እንደሚቀጣ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጠው ቃል ገለጸ።

ቢሮው " ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው " ብሏል።

" ከዚህ በኋላ ግን ባለው መመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ " ሲል አስጠንቅቋል።

ቢሮ " ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል " ብሏል።

" ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል " ያለው  ቢሮው " ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን " ሲል ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
አዲስ የትምህርት ደንብ‼️ እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።

ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።

ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።

የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።

ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።
ስለ እሱ እናውራ
ከስኬቷ ጀርባ ስላለው ስለ ዝምተኛው ባለሙያ

#Ethiopia | ከስኬቷ ጀርባ ስላለው ስለ ዝምተኛው ባለሙያ፥ ስለ አሰልጣኟ፥ ስላልተዘመረለት ባለቤቷ፥ ስለ ልጆቿ አባት፥ ስለ እሱ እናውራ

የባንክ አውቶቢስ፥ የስፖርተኞቹ ሰርቪስ የፍቅር በር ከፈተላቸው

ከ27 አመት በፊት እሷ የንግድ የባንክ ሯጭ፥ እሱ ደግሞ የክለቡ የ C ቡድን ተጫዋች ሆነው ተዋወቁ፥ መሰረት ደፋር እና ቴዎድሮስ ሀይሉ

በአንዱ ቀን ከልምምድ በኋላ የኳሱና የአትሌቲክሱ ቡድን አባላት ምሳ ለመመገብ በአንድ አውቶቢስ ወደ ክለቡ ሲመለሱ መሰረት እሱ ካለበት አጠገብ ተቀመጠች፤ በፈገግታ ተቀበላት፤ ከጎኑ ወንበር የተጋራችው ግራ ጎኑ ትሆናለች ብሎ ግን አላሰበም

ገና በመጀመሪያ ቀን ትውውቃቸው ውሃ ሰጣት፤ ውሃ አጣጩ እንደምትሆን ግን አልገመተም፤ ተግባቡ፤ ደጋግመውም ተገናኙ፤ ጓደኛሞች ሆኑ

ታሳዝነዋለች...

በቻለው አቅም ያግዛታል፤ ከክለቡ ምግብ ቀንሶ በቱታው ኪስ ደብቆ ይዞላት ይሄዳል፤ ሳንድዊች እየሰራ ያቀብላታል

መሰረት ያኔ የ250 ብር ወርሃዊ ደሞዝተኛ ነበረች፤ የአትሌቲክስ ፍቅርና ችሎታ ብቻ እንጂ ኢኮኖሚያዊ አቅም የሌላት ምስኪን፥ ከደሞዟ ቀንሳ ለቤተሰቧ የምትሰጥ ተስፈኛ አትሌት፥ ባቄላ እየሸጠች እናቷን የምትረዳ ልባም ወጣት፥ እናም ያዝንላታል

ይንከባከባታል....

ሰውነቷ እንዲጠነክር የላም ወተት ተከራይቶላት አቅመኛ እንድትሆን ያግዛታል

በሌላኛው ቀን ደግሞ ከራሱ ቀንሶ በሶ እየበጠበጠ ጃንሜዳ ይዞላት ይሄዳል፤ ከልምምድ በኋላ ሁለቱ ስፖርተኞች አረፍ ብለው በሷቸውን እየተጎነጩ ይመካከራሉ

ባለው አቅም ሁሉ ያግዛታል...

መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ እድል ያገኘች ጊዜ ለኤምባሲ የምትከፍለው ብር አጠራት፤ እያለቀሰች አማከረችው፤ ሳቋን እንጂ እንባዋን ማየት የማይፈልገው ቴዲ ሁለቴ ማሰብ ሳይፈልግ እናቱ በስጦታ ያበረከቱለትን የአንገት ሃብል ሸጠውና ብሩን ሰጣት፤ ጉጉቷ ተሳክቶ ሄደች፤ በድል ተመለሰች

ከአንገቱ የማይጠፋው ሃብል አለመኖሩን የተረዱት እናቱ 'ልጄ ዱርዬ ሆነ፥ ሱስ ጀመረ፥ ቁማር ውስጥ ገባ' ብለው ከቤት አባረሩት፤ ይባስ ብሎ ከባንክ እግር ኳስ ተጫዋችነቱም ተቀነሰ፤ ወጣቱ ቴዲ ግን ቅድሚያ ለመሲ አለ

ያበረታታል፥ ደጀን ይሆንላታል...

ሙሉ ትኩረቱን ለእሷ አድርጎ የአትሌቲክስ አሰልጣኝነት ኮርስ ወስዶ መሰረት- መሰረት እንዲኖራት እየጣረ ለስኬቷ መልፋቱን ቀጠለ፤ በኦሊምፒክ ሁለት ወርቅና አንድ ብር ስታጠልቅ፥ በአለም ሻምፒዮና ሁለት ወርቅ አንድ ብርና ሁለት ነሀስ ለሃገሯ ስታመጣ፥ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አራት ወርቅ አንድ ብርና አንድ ነሀስ ስታገኝ በጥቅሉ በሩጫ ህይወቷ 183 ውድድር አድርጋ 161 ስታሸንፍ በእያንዳንዱ ዱካዋ የእሱ አሻራ ታትሞበታል፤ ስትበደል ቀዳሚ ተሟጋቿ፥ ስትደክም ከፊት ያለ አበርቺዋ፥ ስትገፋ ድምፅዋ ሆኖ ሁለት አስርት አመታትን ተሻግሯል፤ ክብረወሰን ስትሰብርና የአለም ኮከብ አትሌት ተብላ የንግስና ዘውድ ስትጭን ቀዳሚ ደስታ ተጋሪዋ፥ በሴራ ስትገለል እንባ አባሽ አጋሯ ሆኖ ከርሟል

የመሰረት ባል ቴዲ አሁንም ወጣት አትሌቶችን እያሰለጠነ ለኦሊምፒክና ለአለም ሻምፒዮና እያበቃ ይገኛል፤ ታላላቅ አትሌቶችን አሰልጥኗል፤ አሁን የእነ መዲና ኢሳ፣ ሳሙኤል ፍሬው፣ ፋንታዬ በላይነህና ሌሎች በርካታ አትሌቶች አሰልጣኝ ነው

አሁንም ይሳሳላታል..

የመሲና የቴዲ በአውቶቢስ ጉዞ ከጎን በመቀመጥ የጀመረው ትውውቅ በ2004 ወደ ትዳር አድጎ ሶስት ልጆችን አፍርተው ሁለት ተጨማሪ ልጆችን አሳድገው እዚህ ደርሰዋል፤ ልክ እንደ ድሮው አሁንም ያዝንላታል፥ ይንከባከባታል፥ ያግዛታል፥ ያበረታታል፥ መከታ ይሆንላታል፥ ዛሬም ይሳሳላታል፥ መሰረትም እንደዛው

ስለ እሱ ነው ያወራነው፤ ስለ ውሃ አጠጪው፥ ስለ ወተት ተከራዩ፥ ስለ በሶ አቅራቢው፥ ስለ ሃብል ሻጩ፥ ስለ አሰልጣኙ፥ ስለ ባልና አባቱ፥ ስለ መሰረት- መሰረት፥ አዎ ስለ ቴዎድሮስ ሀይሉ

የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋር ዛሬ ዕሮብ ህዳር 10 የልደት ቀኗ ነው፤ ስለ እሷ ብዙ ተብሏል፤ ሀገርን በአለም አደባባይ ከፍ አድርጋ፥ ሰንደቋን በኩራት አሰቅላ፥ መዝሙሯን አዘምራ ኢትዮጵያን አስጠርታለች፤ እናም ለኢትዮጵያ እንኳን ተወለድሽላት፤ ከትናንት ጅማሬዋ እስከ አሁኑ ክብሯ አብሯት ላለው ሁሌ ከአፏ ለማይጠፋው ከመጋረጃ ጀርባ ለተደበቀው ለባለቤቷ ቴዎድሮስ ሀይሉ ደግሞ እንዲህ እንላለን፤ ለመሰረት- መሰረት ስለሆንክ እናመሰግናለን፥ ላንተም እንኳን ተወለደችልህ!

©️ታምሩ ዓለሙ 🙏
"አፋር ምንጊዜም የኢትዮጵያ ድንበር ጠባቂ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ምንጭ፣ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነ ሕዝብ ነው።

በአፋሮች ውብ ከተማ ሠመራ-ሎጊያ ሲካሄድ የቆየውን 10ኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ዛሬ በደማቅ ሁኔታ አጠናቀናል"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
🔥1
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተጠናከረ ግንኙነት ለጋራ ብልጽግና

Strengthening Our Ties for Mutual Prosperity

#EthiopiaMalaysia60
Mootummaan Damee qonnaatif xiyyeeffannaa adda kenneen diinagdee damdaneessa, saffisaa fi fayyadamummaa uummataa mirkaneessan iddoo hundatti lafa qabsiisuf xiyyeeffannaa addaatin hojjachaa turee jira.
Gama kanaan, damee Qonnaa ammayyeessuun wabii nyaataa mirkaneessuu, alergii guddisuu, oomishaalee alaa galan kan biyya keessatiin bakka buusuufi carraa hojii bal'aa uumuuf hojii hojjetamaa jiruunbu’aa qabatamaan mul’achaa dhufee jira.
ጃፓን ውስጥ በሰደድ እሳት ምክንያት 170 ቤቶችን ያቀፈ ሙሉ ሰፈር አመድ ሆነ

በኦይታ ከተማ ግዙፍ የእሳት አደጋ ተከሰተ። እሳቱ አንድን ሕንፃ ከዋጠ በኋላ በደቂቃዎች ውስጥ ሙሉውን ሰፈር አዳረሰ። ኃይለኛ ነፋስ እሳቱን በጣም በፍጥነት በማሰራጨቱ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ከ12 ሰአታት በላይ ለማጥፋት ታግለዋል። አንድ ሰው ጠፍቷል።

​የአደጋ መከላከል  ስርዓቱ በዓለም ላይ ካሉት ፈጣን ከሚባሉት አንዱ እንደሆነ በሚታሰብባት ጃፓን ውስጥ እንኳን እንዲህ ዓይነቱ ሰፊ አደጋ ብርቅ ነው ሲል ኤጀንሲው አክሎ፣ ሮይተርስ ዘግቧል።
"ኢትዮጵያ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የዲፕሎማሲ አካሄዷን ለማሳደግ ጎልታ የምትታይበት እድል ከፍተኛ ነው" - ዶክተር ቀነዓ ያደታ

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለመደበኛ እና ለአጭር ኮርስ ሰልጣኞች ሀገራዊና ቀጠናዊ አሁናዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ትምህርት የሰጡት በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአሰራር ስርዓት በዓለም አቀፍ እይታ ያለው ተፅእኖ ምን እንደሚመሥል አሥገንዝበዋል።

ሀያላን ሀገራት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ሀገራትን የመጠምዘዝ አዝማሚያ ቢኖርም ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ጥቅሟን ለማስጠበቅ የዲፕሎማሲ አካሄዷን በማሳደግ ቀጠናው ላይ ጎልታ የምትታይበት እድል ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በውስብስብ የዓለም አቀፋዊና ቀጠናዊ የደህንነት ጉዳይ ውስጥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ሥለመሆኑ ያነሱት ዶክተር ቀነዓ ሀገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን እና ፍላጎታቸውን ለማስጠበቅ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ያሳድጋሉ ብለዋል።

በአፍሪካ ቀንድ በተለያዩ በጎሮቤት ሀገራት እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊያን ቀድማ ያቀነቀነችው ሀገር ከመሆንዋም ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከመሰረቱትም አንዷ ናት ብለዋል።

የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ትኩረት ሠጥቶ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድን በተከተለ አግባብ መንቀሳቀስ ጥቅሙ የላቀ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ቀነዓ ያደታ ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዙሪያ ያበረከተችው ከፍተኛ አስተዋፆኦ መልካም ስም እንዲኖራት ያሥቻለ እንደሆነም አሥገንዝበዋል።

ሀብትን፣ ማንነትን፣ ፖለቲካን እና ሀይልን መሰረት አድርጎ የተሰራ ሥራ ለግጭት መነሻ በመሆኑ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አሥረድተዋል።