Finally Scholarships in Turkey 🇹🇷 Without IELTS 2026 Opened Now!
Apply Link: https://montessoriline.com/how-to-apply-for-scholarships-in-turkey-without-ielts/
Host Country: Turkey
University: Turkish Universities
Degree Levels: Bachelor’s, Master’s, PhD
Scholarship Coverage: Fully Funded
Eligible Nationalities: All International Students
Application Deadline: Varies depending on the university/program

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ለዜጎች ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች በመስጠት እንዲሁም በትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ፣ በቪዛ እና ሌሎች የይለፍና የጉዞ ሰነዶችን ለደንበኞች በመስጠት ረገድ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸዉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።
በሩብ ዓመቱ ከ545ሺ በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠቱን የገለጹት ወይዘሮ ሰላማዊት አገልግሎቱ የዲጂታል አገልግሎትን በማሻሻል እንዲሁም የፓስፖርትና ቪዛ ስርዓት በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱ ለዜጎች በተሻለ ጥራትና ፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ነዉ የተናገሩት።
ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ከቪዛ አገልግሎት ጋር ተያይዞም 321ሺ በላይ ቪዛ ሰጥቷል። ከዚህም ባለፈ 11,250 ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እንዲሁም 5,161 የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ጊዜያዊ እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ በመስጠት የተሳካ የእቅድ አፈፃፀም ማስመዝገቡምንም ጠቅሰዋል ዋና ዳይሬክተሯ በሪፖርታቸዉ።
በአየር እና በየብስ ድንበር አለማቀፍ ስታንዳርዶችን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት መሰጠቱም ነው የተጠቀሰው።
ከአገልግሎት ተደራሽነት በተጨማሪ የውጭ ዜጎችን እና የድንበር ቁጥጥር ስራ በማጠናከር የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት ለመጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ያብራሩት ወይዘሮ ሰላማዊት በሩብ አመቱ 860 ሀሰተኛ ሰነድ ይዘው ፖስፖርት ለመውሰድ የሞከሩ የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር አውሎ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆን መቻሉንም በሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በ2018 ዓ.ም በአንደኛ ሩብ ዓመት አስራ አንድ ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከአስር ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልጸዋል። ይህም ከዕቅዱ 96 በመቶ በላይ ማሳከት መቻሉን በሪፖርታቸዉ ጠቅሰዋል።
የቋሚ ኮሚቴዉ አባላትም ከአገልግሎት ተደራሽነት፣ ስራዎችን በቴክኖሎጂ የታገዙ ከማድረግ፣ የአገልግሎት ፈላጊዎችን እርካታ እዉን ከማድረግ፣ ከሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቷል።
የቋሚ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ነገዎ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዜጎችን መብት በጠበቀ መልኩ ጊዜዉን የዋጁ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፎችን በመክፈትና ተደራሽነትን በማሳደግ እና መመሪያዎችን በማዘጋጀት የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያደርገዉ ጥረት ሌሎች ተቋማት አርዓያ መሆን የሚችል በመሆኑ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አዲሱን የኢፓስፖርት ሲስተም ወደ ክልሎት ማስፋት፣ በሃሰተኛ ሰነድ አገልግሎት የማግኘት ሙከራ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር፣ አልፎ አልፎ የሚያጋጥምን የኔትዎርክ መቆራረጥ መፍትሄ ማበጀት እንዲሁም የድንበር አስተዳደር ማዘመን እና ዘመናዊ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን መዘርጋት አገልግሎቱ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራባቸዉ አሳስበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Forwarded from Seyoum Teshome (Seyoum Teshome)
እንጀራ እና ዳቦ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ መከልከሉ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ መከልከሉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ፦
- ሳሙና
- በረኪና
- ፍሊት
- የአይጥ መርዝ
- የፅዳት ኬሚካሎች እና ሌሎችም ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ እንዳልሆነ በመግለፅ ይህ ክልከላ መወሰኑን ገልጿል።
ክልከላው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነ እንደሆነ አመልክቷል።
እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑን አሳውቋል።
እንጀራ እና ዳቦ ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
ህብረተሰቡ ለጤናው ሲል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

የተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጨ ከታች ያለዉን ምስል ማጋራቷን ተከትሎ ትችቶች እየቀረበባት ይገኛል። ከተቺዎቿ አንዱ አቶ አሳፍ ሀይሉ እንዲህ ሲል ሀሳቡን አጋርቷል።
👇👇👇
"በእኛ ባህል እንዲህ ዓይነቱ ባለትዳርና የልጆች እናት ሆኖ ጭንን ለአደባባይ ማስጣት ልክ አይደለም!
መመናቀር ዘመናዊነት አይደለም! ሊሆንም አይችልም! በተለይ ለሀበሻ ሴት!"
በማለት የህግ ባለሙያና ጦማሪ አሳፍ ሀይሉ አስተያየቱን ሰጥቷል።
የእናንተንም አስተያየት በጨዋ ደንብ አስቀምጡ‼️

Forwarded from Oromia Prosperity Party /OPP/ 🌾
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Mul'ata badhaadhina biyyaa dhugoomsuuf hojiilee misoomaa fayyadamummaa hawaasaa mirkaneessan ariitii, baay'inaa fi qulqullinaan raawwatamaa jiru.
#Badhaadhina
#Badhaadhina
የሳዑዲ መንግስት ተቺ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጊ ከተገደለ ከዓመታት በኃላ የሳዑዲ አረቢያ ልዑል አሜሪካ ገቡ።
የሳዑዲ አረቢያ ገዥ በዋይት ሀውስ ማክሰኞ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር የሚያደርጉት ጉብኝት ለአስርት አመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል የዘለቀውን በነዳጅ እና ደህንነት ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ በንግድ፣ ቴክኖሎጂ እና በኒውክሌር ሃይል ላይ ያለውን ግንኙነት ለማስፋት ያለመ ነው። እ.ኤ.አ. በ2018 በሳዑዲ አረቢያ መንግስ ጀማል ኻሾጊ በኢስታንቡል ውስጥ በሳዑዲ ወኪሎች ከተገደለ እና አለም አቀፍ ግርግርን ካስከተለ በኋላ አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሳልማን ወደ አሜሪካ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉዞ ይሆናል።
የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት አልጋ ወራሹ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ታዋቂውን ተቺ የሆነውን ካሾጊን መያዝን ወይም መገደልን አፅድቀዋል ሲል ደምድሟል። ኤምቢኤስ በሚል ስም በሰፊው የሚታወቁት አልጋ ወራሽ ልዑሉ ግድያውን ማዘዛቸውን አልተቀበሉም ነገር ግን መንግስታቸው ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አምኗል።
ከሰባት ዓመታት በኋላ የዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ እና የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገር መሪ ውዝግቡን ቋጭተው ወደፊት መሄድን ይፈልጋሉ። ትራምፕ በግንቦት ወር ሳዑዲ አረቢያን በጎበኙበት ወቅት የ600 ቢሊዮን ዶላር የሳውዲ የኢንቨስትመንት ገንዘብን ለማግኘት ይፈልጋሉ። በጉዞው ወቅት በሳዑዲ አረቢያ ስለሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።
የሳውዲ አረቢያ መሪ በአካባቢው ውጥረት ውስጥ የደህንነት ዋስትናዎችን እየፈለጉ ይገኛል። እንዲሁም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ለማሳደግ እና በሲቪል የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ስምምነት ላይ መድረስን ይፈልጋሉ ። በናይፍ አረብ ዩንቨርስቲ የደህንነት ሳይንስ አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አዚዝ አልጋሺያን “በካሾጊ ግድያ ላይ የተከፈተ ገጽ ግን አለ” ብለዋል።

"እስራኤል የኢትዮጵያን የወደብ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትደግፋለች" በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ
እስራኤል የኢትዮጵያን የዓባይ ውሃ አጠቃቀም እና የወደብ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትደግፋለች ሲል በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ አብዛኛው የኤምባሲው ሥራ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማራመድ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።
ስለዚህ አንዱ ብሔራዊ ጥቅም ከዓባይ ውሃ አጠቃቀም እና ከኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ በዋናነት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
"በታሪክ ወደኋላ ተመልሰን ስናይ እስራኤል ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንዳትሆን ስትሰራ ነበር" ያሉት አምባሳደሩ፤ "ይህም ለኢትዮጵያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለራሷም ብላ የምታደርገው ነበር።" ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ከወደብ ተጠቃሚነት በተገፋች ቁጥር ቀይ ባህር የአረብ ሀገራት የበላይነት ይነግስበታል፡፡ ይህ ደግሞ ጉዳቱ ለእስራኤልም ጭምር ነው" ሲሉ አስረድተዋል፡፡
እስራኤል ከቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በወታደራዊ ስልጠና ኢትዮጵያን ስታግዝ እንደነበር በመግለጽም፤ በወቅቱ "ነበልባል" የተሰኘ ጦር በእስራኤሎች መሰልጠኑን አስታውሰዋል። በተጨማሪም አየር ኃይልን የማጠናከር ሥራ በእስራኤል መሰራቱን ገልጸዋል።
"ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተነጠለች ነጻ ሀገር መሆኗን ተከትሎም፤ ኢትዮጵያ ከሁለት ወደቦች ማለትም ከምጽዋ እና አሰብ ባለቤትነት ወደ ወደብ አልባ ሀገርነት ተቀየረች" ብለዋል።
በተጨማሪም በደርግ ጊዜም ሆነ እ.ኤ.አ ከ1973 በኋላ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተቋርጦ እንደነበር ያስታወሱት አምባሳደር ተስፋዬ፤ ሆኖም ከወታደራዊው ደርግ መንግሥት ጋር ይፋ የማይወጣ በወታደራዊና በመረጃ ልውውጥ የመተባበር ግንኙነት እንደነበር ተናግረዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ በሕጋዊ፣ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ጥረት እያደረገች መሆኑን በማንሳት፤ ኤምባሲው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህን የኢትዮጵያን ጥያቄ በማስረዳት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ስለዚህ "በእስራኤል በኩል ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄዋን የመቃወም ሁኔታ የለም" ሲሉ ከአሐዱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህንንም ሲያብራሩ፤ "ኢትዮጵያ እንደገና መልሳ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ ብትመጣ አንደኛ ወዳጅ ሀገር ናት፤ በተጨማሪም እስራኤል ኢትዮጵያን መግቢያ በር አድርጋ ስለምትመለከታት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንድታግዛት ትፈልጋለች" ብለዋል።
"እስራኤላውያን ኢትዮጵያን የሚያዩበት መንገድ የተለየ ነው" ያሉት አምባሳደር ተስፋዬ፤ "በተጨማሪም በአፍሪካ ሕብረት የተመልካችነት ድርሻን መልሶ ለማግኘት የእኛን ድጋፍ ይሻሉ" ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ የልማት አቅም ያላት ሀገር በመሆኗ፤ 'በዚህ ውስጥ በመሳተፍ እኛም እንጠቀማለን' ብለው እንደሚያስቡ አብራርተዋል፡፡
ስለዚህ የኢትዮጵያን ጥያቄዎች የመደገፍ እንጂ ለምን እና እንዴት? የሚለውን ነገር አያነሱም ሲሉ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ አሁን ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ የእስራኤል መንግሥት ይደግፈዋል ግን አሁን በኢትዮጵያ ጉዳይ መግለጫ መስጠት አይችልም" ያሉት አምባሳደሩ፤ "ሁኔታው እያደገ ሲሄድ ድጋፉን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ጉዳይ እየተነጋገርን ነው" ብለዋል።
አምባሳደር ተስፋዬ አክለውም፤ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጾች መጀመሪያ ግድቡ እንዳይሰራ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ግንባታውን አጠናቃ ማስመረቋን አስታውሰዋል።
"ግብጾች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች መሰረተ ቢስ ናቸው" ያሉም ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የሄደችበት መንገድ እንዲሁም ጉዳዩን በበቂ ሁኔታ በዓለም አቀፍ መድረኮች እያስረዳች ስለመጣች 'አሁን ድርድሩ ውጤት ስላላመጣልን ትተነዋል' የሚል አቋም መያዛቸውን አስረድተዋል።
"ከዚያ ውጪ ግን በዚህ ዓመት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደብዳቤ ጽፈው ነበር ለዚያም አጥጋቢ መልስ ተሰጥቷል" ብለዋል።
"በዚህም ዓለም የእኛ እውነት እየገባው ነው" ያሉ ሲሆን፤ ዋናው ነገር ግድቡ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ነው። የተወሰኑ ተግዳሮቶች ይኖራሉ እነሱን ደግሞ በተለመደው መልኩ እየተቋቋምን ራሳችንን እያጠነከርን እንሄዳለን ብለዋል።
በሌላ በኩል በእስራኤል የሚገኙ ቤተ-እስራኤላውያ ከ175 ሺሕ እስከ 180 ሺሕ እንደሚገመቱ የገለጹት አምባሳደሩ፤ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
በእስራኤል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ባህላዊ መገለጫ የሆኑ መደብሮች እና ሬስቶራንቶች መኖራቸውን ገልጸው፤ በእነርሱም አማካኝነት የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች፣ አልባሳት እና ቋንቋ የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰራ አብራርተዋል።
በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ እስራኤላዊያን በተለያዩ የልማት እና የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እንደሚሳተፉ በማንሳት፤ ኤምባሲው በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም እድሎችን ለእስራኤላውያን የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ይህም የሁለቱን ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት ይበልጥ እያጠናከረው እንደሚገኝ ነው ብለዋል፡፡

Forwarded from FDRE TVT Institute
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM