Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
ዛሬ በይፋ መርቀን ስራ ያስጀመርነው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የላቀ የሕክምና ማዕከል ዓለም አቀፍ  ጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሟላ ነው።

በውጪ ሀገራት  ንፁህ እና ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የተሟላላቸዉ የህክምና ማእከላትን ስናይ “ መቼ ይሆን በሃገሬ ይህንን የመሰለ ለባለሙያው፣ ለታካሚው እንዲሁም ለአስታማሚው ጭምር የተመቸ  ዘመናዊ የጤና ማዕከል የሚኖረው?” ለሚለው ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው።

ይህ የላቀ የሕክምና ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን ፦
•  የተኝቶ ህክምና ህሙማን ክፍሎች (IPD)
•  የጨረር  ህክምና አገልግሎቶች
•  ኤም አር አይ፣ ሲቲ-ስካንእና ኤክስሬይ
•  የህፃናት እና የአዋቂዎች ፅኑ ህሙማን ክፍሎች (ICU)
•  የኦክስጅን ማምረቻ ፕላንት
•  የቪአይ ፒ አልጋዎች
•  የኦፒዲ ክፍሎች
•  የኦፕራሲዮን ክፍሎች(OR) እና  የማገገሚያ ክፍሎች እንዲሁም
•  የድንገተኛ ክፍል አልጋዎች
•  በየህክምናው አይነትና በየወለሉ ፋርማሲ እና የመድሃኒት ስቶር
•  ላቦራቶሪ
•  የአስተዳደር ቢሮዎች
•  የማብሰያ ክፍሎች፣ ዋና  ካፊቴሪያ፣ በየወለሉ ለሚገለግሉ ባለሙያዎች  የሚሆኑ ካፊቴሪያዎች
• የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ከውብ ምድረ ግቢ ጋር አካቷል፡፡

ይህን ለማሕበረሰባችን ፋይዳው እጅግ የላቀ የጤና ማዕከል  ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት ፣ አመራሮች እና ባለሙያዎችን በተገልጋዩ  ሕብረተሰብ እንዲሁም በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2
የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት 👆 👇

6 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ሕይወታቸው ሲያልፍ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ የለም ተባለ

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የማርበርግ በሽታ መከሰቱን ከታወቀበት ህዳር 3 ጀምሮ የበሽታዉ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸዉ የተባሉ ሰዎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስቴሩ እስካሁን ድረስ 17 የላብራቶሪ ናሙና ወስዶ የመረመረ ሲሆን፤ በሶስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ስድስት ሰዎች የበሽታዉን ምልክት አሳይተዉ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በላብራቶሪ የተረጋገጠዉ ግን ሶስት ሰዎች ላይ መሆኑን እና እነሱም ህይወታቸዉ ማጣታቸዉን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ እንደሌለ ያረጋገጡት ሚኒስትሯ በሽታዉን ለመከላከልም የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና ተቋማት መቋቋማቸዉን እና የላብራቶሪ ግብአቶችና ባለሙያዎች ወደ ቦታዉ መላካቸውን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ቁሳቁሶችና መድኃኒቶችን የማሟላት ዝግጅት መጠናቀቁና ግብአት የማሟላትና የማሰራጨት ስራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በበሽታዉ ህይወታቸዉን የሚያጡ  ሰዎች ቢኖሩ እንኳን የቀብር ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሚሰጠዉ መመሪያ መሰረት መፈጸም እንደሚኖርበትም ጠቁመዋል።

#Marburg_virus
ኬንያ የሳይበር ጥቃት ተፈጽሞባታል።

በኬንያ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ፅህፈት ቤት ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴሮች ድረ-ገጽ ተጠልፎ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዳግም ተመልሷል።

በዚህ የተቀናጀ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት ጨምሮ የጤና፣ የትምህርት፣ የስራ፣ የአካባቢ፣ የሃገር ውስጥ፣ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች ድህረገጽ መጠለፉ ተነግሯል።

ድረ-ገጾቹ መጠለፋቸውን ተከትሎ በድሀረገፆቹ ላይ "Access denied by PCP", "We will rise again", "White power worldwide", and "14:88 Heil Hitler" የሚል ፅሁፍ ታይቷል።

ድህረገፆቹ ከተጠለፉ በኋላም መንግስት በኦንላይን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አቋርጦ ቆይቷል።

የመከላከያ እና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቃቱ ሰለባ አልሆኑም ሲባል ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን እስካሁን የለም።

በ2023 በኬንያ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ የነበረ ሲሆን የሱዳን የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር።

ዘገባው የኬንያንስ ነው።
1
Finally Scholarships in Turkey 🇹🇷 Without IELTS 2026 Opened Now!
Apply Link: https://montessoriline.com/how-to-apply-for-scholarships-in-turkey-without-ielts/
Host Country: Turkey
University: Turkish Universities
Degree Levels: Bachelor’s, Master’s, PhD
Scholarship Coverage: Fully Funded
Eligible Nationalities: All International Students
Application Deadline: Varies depending on the university/program
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ለዜጎች ፈጣን እና ተደራሽ  አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን  የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች በመስጠት እንዲሁም በትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ፣ በቪዛ እና ሌሎች የይለፍና የጉዞ ሰነዶችን ለደንበኞች በመስጠት ረገድ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸዉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።  

በሩብ ዓመቱ ከ545ሺ በላይ  ፓስፖርት  ለዜጎች መሰጠቱን የገለጹት ወይዘሮ ሰላማዊት አገልግሎቱ  የዲጂታል አገልግሎትን በማሻሻል እንዲሁም የፓስፖርትና ቪዛ  ስርዓት በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱ ለዜጎች በተሻለ ጥራትና ፍጥነት ተደራሽ  እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ  መሆኑንም ነዉ የተናገሩት።

ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ከቪዛ አገልግሎት ጋር ተያይዞም 321ሺ በላይ ቪዛ ሰጥቷል። ከዚህም ባለፈ 11,250 ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እንዲሁም 5,161 የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ጊዜያዊ እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ በመስጠት የተሳካ የእቅድ አፈፃፀም ማስመዝገቡምንም ጠቅሰዋል ዋና ዳይሬክተሯ በሪፖርታቸዉ።

በአየር እና በየብስ ድንበር አለማቀፍ ስታንዳርዶችን በጠበቀ  መልኩ በጉዞ ሰነድ  ከ 2 ሚሊዮን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች  አገልግሎት መሰጠቱም ነው የተጠቀሰው።

ከአገልግሎት ተደራሽነት በተጨማሪ የውጭ ዜጎችን እና የድንበር ቁጥጥር ስራ በማጠናከር የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት ለመጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ያብራሩት ወይዘሮ ሰላማዊት በሩብ አመቱ  860 ሀሰተኛ ሰነድ ይዘው ፖስፖርት ለመውሰድ የሞከሩ የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር አውሎ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆን መቻሉንም በሪፖርታቸው ጠቁመዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በ2018 ዓ.ም በአንደኛ ሩብ ዓመት አስራ አንድ ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከአስር ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን የአገልግሎቱ  ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልጸዋል። ይህም ከዕቅዱ 96 በመቶ በላይ ማሳከት መቻሉን በሪፖርታቸዉ ጠቅሰዋል።

የቋሚ ኮሚቴዉ አባላትም ከአገልግሎት ተደራሽነት፣ ስራዎችን በቴክኖሎጂ የታገዙ ከማድረግ፣ የአገልግሎት ፈላጊዎችን እርካታ እዉን ከማድረግ፣ ከሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቷል።

የቋሚ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ነገዎ  የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  የዜጎችን መብት በጠበቀ መልኩ ጊዜዉን የዋጁ  አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፎችን በመክፈትና ተደራሽነትን በማሳደግ  እና መመሪያዎችን በማዘጋጀት  የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያደርገዉ ጥረት  ሌሎች ተቋማት አርዓያ መሆን የሚችል በመሆኑ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አዲሱን የኢፓስፖርት ሲስተም ወደ ክልሎት ማስፋት፣ በሃሰተኛ ሰነድ አገልግሎት  የማግኘት ሙከራ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር፣ አልፎ አልፎ የሚያጋጥምን የኔትዎርክ መቆራረጥ መፍትሄ ማበጀት እንዲሁም የድንበር አስተዳደር ማዘመን እና  ዘመናዊ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን መዘርጋት አገልግሎቱ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራባቸዉ አሳስበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
Forwarded from Seyoum Teshome (Seyoum Teshome)