Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያየሁት ነገር፤ ሰው የጠራ ራዕይ ካለው ፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሠራ ከሆነ አንድን ነገር ባየው ልክ ማሳካት እንደሚችል ፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር እንደሆነች ነው።
ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮልሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መልክ-አዲስ፥ ተምሳሌተ አዲስ ትውልድ፣ የብልፅግና መንገድ፤

ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ፥ የስኽበት ማዕከል በሆነችዉ አዲስ አበባ፣ በፍጥነትና በጥራት ከተጠናቀቁ መሰረተ - ልማቶች መካከል፥ ወጣቱን በአዕምሮ፤ በአካል እና በስነ-ልቦና የሚገነቡ፤ የከተማዋን ገፅታ የሚቀይሩ፤ በዓለም ተወዳዳሪነትን የሚያጎናፅፉ áŠĽáŠ“ የትዉልዱን መፃኢ ዕድል የሚያመላክቱ፣ ዘመን ተሻጋሪ ዘመናዊ የስፖርት ማዘዉተሪያዎችና መዝናኛዎች በጥራት ገንብታ እንኾ ብላለች። እንዲሁም፤ ለኪነጥበቡ ዕድገት፣ ለተተኪ ከያኒ ምቾት፣ አንፊዎች እና በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ሲኒማ ቤቶች፣ ቴአትር ቤቶች እነኆ ብላለች። ቃል ወደ ተግባር የመቀየር ባህል በውል የታየባቸው የመንግስት እና የህዝብ ድምር ዉጤቶች ናቸዉ፡፡

ኑ! ተጠቀሙባቸው።
❤1
ዛሬ በይፋ መርቀን ሾል ያስጀመርነው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የላቀ የሕክምና ማዕከል ዓለም አቀፍ  ጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሟላ ነው።

በውጪ ሀገራት  ንፁህ እና ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የተሟላላቸዉ የህክምና ማእከላትን ስናይ “ መቼ ይሆን በሃገሬ ይህንን የመሰለ ለባለሙያው፣ ለታካሚው እንዲሁም ለአስታማሚው ጭምር የተመቸ  ዘመናዊ የጤና ማዕከል የሚኖረው?” ለሚለው ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው።

ይህ የላቀ የሕክምና ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን ፦
•  የተኝቶ ህክምና ህሙማን ክፍሎች (IPD)
•  የጨረር  ህክምና አገልግሎቶች
•  ኤም አር አይ፣ ሲቲ-ስካንእና ኤክስሬይ
•  የህፃናት እና የአዋቂዎች ፅኑ ህሙማን ክፍሎች (ICU)
•  የኦክስጅን ማምረቻ ፕላንት
•  የቪአይ ፒ አልጋዎች
•  የኦፒዲ ክፍሎች
•  የኦፕራሲዮን ክፍሎች(OR) እና  የማገገሚያ ክፍሎች እንዲሁም
•  የድንገተኛ ክፍል አልጋዎች
•  በየህክምናው አይነትና በየወለሉ ፋርማሲ እና የመድሃኒት ስቶር
•  ላቦራቶሪ
•  የአስተዳደር ቢሮዎች
•  የማብሰያ ክፍሎች፣ ዋና  ካፊቴሪያ፣ በየወለሉ ለሚገለግሉ ባለሙያዎች  የሚሆኑ ካፊቴሪያዎች
• የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ከውብ ምድረ ግቢ ጋር አካቷል፡፡

ይህን ለማሕበረሰባችን ፋይዳው እጅግ የላቀ የጤና ማዕከል  ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት ፣ አመራሮች እና ባለሙያዎችን በተገልጋዩ  ሕብረተሰብ እንዲሁም በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤2