Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት በመለወጥ መሃል ከተማ ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዛውሯል። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የግንባታ ለውጥ እና ዘመናዊ የመሥሪያ ሥፍራ ጥበብን በማሳየት ለሠራተኞቹ እጅግ ምቹ የሆነ ስፍራንም መፍጠር ችሏል። ተቋሙ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሕይወታችንን በፍጥነት በመቅረጽ ውስጥ ያለውን ስፍራ በሚያንፀባርቅ እና ሀገራችንም በዚህ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በንቁነት መሳተፏን በሚያረጋግጥ መንገድ ከፍታ ላይ ደርሷል። ኢንስቲቲዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ሲሆን በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ትላልቅ የመረጃ ቋቶች፣ የመረጃ ፍለጋ፣ ሮቦቲክስ እና ኢመርሲቭ ቴክኖሎጂዎች አቅሙን በማጎልበት ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የተጀመረው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርት አፕ መዐከል ደግሞ ይኽንን ከባቢ የበለጠ ያጠናክረዋል። ዜጎች ሀሳብ ብቻ ይዘው በመምጣት ፕሮቶታይፕ ለመፍጠር፣ ለማባዛት ብሎም ከግሉ ዘርፍ ኢንቬስተሮች ጋር እንዲገናኙ እድል ያመቻቻል። እስከ አሁን 200 ሀሳብ ፈጣሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያየሁት ነገር፤ ሰው የጠራ ራዕይ ካለው ፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሠራ ከሆነ አንድን ነገር ባየው ልክ ማሳካት እንደሚችል ፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር እንደሆነች ነው።
ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮልሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)