Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ዛሬ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አስታውቋል።

"ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ዛሬ እሁድ ህዳር 7  ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣  በኤቲኤም ማሽኖች እንዲሁም በፖስ ማሽኖች እና በኮር ባንኪንግ የሚሰጡ አገልግሎቶች (Core Banking Services) በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳወቅን፣ ለሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን። ብሏል
የ11ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች

📌 ምርጥ ተዋናይት፦ ቃልኪዳን ጥበብ (ትዝታ)

📌 ምርጥ ተዋናይ:- ናታይ ጌታቸው ( ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ አማኑኤል ሀብታሙ (አፊኒ)

📌 የተመልካች ምርጫ፦( ባለ ክራር)

📌 ምርጥ ዳይሬክተር፦  ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ፊልም፦ (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ድምፅ፦ ሐብታም አዲስ (አፊኒ )

📌 ምርጥ ኤዲተር፦ ዳንኤል አንማው (ትዝታ)

📌 ምርጥ ስኮር፦  ስምአገኘኹ ሳሙኤል (አፊኒ)

📌 ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ ኤደን አይሸሹ፣ ፍፁም ካሳሁን እና አብነት አጎናፍር (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ኤልያስ ተስፋዬ 6 ሰዓት ከለሊቱ

📌 ምርጥ ሜካአፕ፦ ዝናዊት ዘርጋባቸው (አፊኒ )

📌 ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)

📌 ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ክላራ ሙሉጌት (ሁለት ቅጣት)

📌 ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ሳሊም አብዱራህማን (ለፍትህ )

📌 ምርጥ ረ/ተዋናይት፦  ማርታ ጎይቶም (6 ሰዓት ከለሊቱ )

☑️ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፍቅርተ ጌታሁን እና ወለላ አሰፋ

☑️ የሐርሜላ ተሸላሚ፦ ወይዘሮ ወሰኔ ሀይሉ

☑️ ምርጥ አጭር ፊልም፦ በማን ዓይን አሸናፊ መስፍን

ከ16ቱ 5ቱን አዋርድ በመውሰድ ጥቁር አደይ ፊልም ከፊት ይገኛል፣

አፊኒ 4ት በመውሰድ ይከተላል፤

ትዝታ እና 6 ሰዓት ከለሊት ደሞ ሁለት ሁለት አዋርድ በማሸነፍ 3ኛን ይዘዋል።
የአየር ጤና - ወለቴ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም፡-  የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የስትራቴጂክ አመራር አባላት የአየር ጤና- ወለቴ የመንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ለማፋጠን የሚያስችሉና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ  የመንድ ፕሮጀክቱ በወሰን ማስከበርና ተያያዥ ችግሮች የተነሳ ለረጅም ጊዜ የግንባታ ሂደቱ መጓተቱን አውስተው፤ በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ሂደቱ የሚፋጠንበትን ሁኔታ ለማገዝና ድጋፍ ለማድረግ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር ሙህዲን አክለውም በአሁኑ ወቅት በመንገድ ፕሮጀክቱ የግንባታ ስራ ላይ ማነቆ ሆነው የቆዩ የወሰን ማስከበር ስራዎች መጠናቀቅ በመቻላቸው የስራ ተቋራጩ በሙሉ አቅሙ የግንባታ ስራውን እንዲያከናውን አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን፤ ችግሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን የኮንትራት ውል እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል።
የጀግናው ጊቤ ክፍለጦር ዝግጁነት

💪💪💪💪💪💪💪💪💪
የዞኑን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩን ማጠናከር እንዳለበት ተገለፀ።

በአርሲ ዞን ከፍተኛ የፌዴራል አመራሮች እና የሠራዊቱ አመራሮች የዞንና የወረዳ መስተዳደሮች ከሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በአቦምሳ ከተማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ የመከላከያ ሰራዊታችንን ምት መቋቋም ያልቻለው አሸባሪው የሸኔ ቡድን የውሸት ፕሮፖጋንዳ ከመንዛት ውጭ የኢትዮጵያ ስጋት ሊሆን እንደማይችል ገልፀው የተወርዋሪው ኮከብ ኮር የሰራዊት አባላት መስዋዕትነት በመክፈል በዞኑ የነበረውን የሽብር ስጋት በማምከን ሰላሙ የተረጋገጥ እንዲሆን በማስቻሉ ኮሩ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሀይማኖትና የብሔር ብዝሃነት ያለልዩነት ህዝቦቿን እንዳታስተናግድ ዝቅ ለማድረግ ከውስጥና ከውጭ ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት በውሸት ትርክት ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚለፉ ፀረ ሰላም ሀይሎችን ጀግናው ሰራዊታችን  ከፀጥታ ሀይሉና  ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመቀናጀት የጠላትን ፍላጎት እያመከነ እንደሚገኝም አንስተዋል።

የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመዳፈር አቅም ያጡ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እንደፈረስ እየጋለቡ የሚልኩት የሽብር ቡድንን የሚታገስ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ተናግረው  ሰራዊታችንም ህዝብን ከህዝብ ለማባላት የሚሰሩ የጥፋት ሀይሎችን በመፋለም የሀገርን ሰላም በመስዋዕትነት እያፀና የመጣ ሠራዊት መሆኑን ገልፀዋል።

በዞኑ የተሰማራው የተወርዋሪው ኮከብ ኮር ከዞኑ የፀጥታ ሀይሎችና ከማህበረቡ ጋር በቅንጅት በመስራቱ የዞኑን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ህዝቡ የተለመደውን ድጋፍ በማድረግ እየታየ ያለውን የዞኑን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአርሲ ዞን ዋና  አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር በበኩላቸው የዞኑን ሰላም ለማረጋገጥ ሰራዊቱ  መስዋዕትነት እየከፈለ ያሰፈነውን ሰላም በጥፋት ሀይሎች እንዳይደፈርስ የሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን የዞኑ ህብረተብ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት ሰላምን  የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት ሲሉ አሥገንዝበዋል።