Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
በ20 ብር ስልካቸውን ሱቅ የሚያስቀምጡት ተማሪዎች

የሞባይል ስልካቸውን 20 ብር በመክፈል ሱቅ አስቀምጠው ወደ ክፍል የሚገቡ  ተማሪዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ባደረግነው ቅኝት መመልከት ችለናል።

የትምህርት ሚኒስትር ባወጣው መመርያ መሰረት ማንኛውም ተማሪ የሞባይል ስልክ ይዞ ት/ቤት እንዳይገባ በመመርያው ሰፍሮ ይገኛል።

ይህንንም ተከትሎ ወላጆች ልጆቻቸው ስልክ ይዘው ወደ ት/ቤት እንዳሄዱ እንዲያደርጉም ሲል ነበር ያዘዘው።

ግን ቅኝት ባደረግንባቸው የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በርካታ ተማሪዎች ስልካቸውን ከት/ቤታቸው አቅራቢያ በሚገኙ ሱቆች 20 ብር በመክፈል አስቀምጠው ወደ ክፍል እንደሚገቡ ተመልክተናል።

ተማሪዎቹ ለምሳ በሚለቀቁበት ሰአት ስልካቸውን ተቀብለው ባላቸው ሰአት የማህበራዊ ሚዲያ እንደሚጠቀሙም ተመልክተናል።

እንዲያውም ከምሳ በፊት የነበራቸውን ቆይታ በተመለከተ ለቲክቶክ ሰርተው እንደሚለቁም ለመታዘብ ሞክረናል።

ለሱቅ 20 መክፈል ያልቻሉ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ በምሳ እቃቸው ስልኩን ደብቀው እንደሚገቡም ነው ከአንዳንድ እማኞች የሰማነው።

ባስ ሲል ደግሞ ከአቅም በላይ የሆኑ ውስን ተማሪዎች ስልካቸውን በግልጽ በመያዝ የመምህራን እንቅስቃሴ በመቅረጽ በማህበራዊ ሚዲያ ሲለቁት ይስተዋላል።

ተማሪዎቹ ስልካቸው ሱቅ ማስቀመጥና ይዘው መግባታቸው አይደለም ዋናው ችግር።

ችግሩ ተማሪዎቹ ክፍል ውስጥ የሚያከናውኑት ክዋኔ ነው።

# የውጭ ተከታታይ ፊልሞች መመልከት

# የተለያዩ የእግር ኳስ ውርርድ ጫወታዎች መወራረድ እና ሌሎችም ተግባራቶች እንደሚያደርጉ ነው የሰማነው።

# የወሲብ ፊልሞች መመልከት

እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች እንመልሳቸው

ወላጆች ልጆቻችሁን ወደ ት/ቤት ስትልኩ ምን እንደያዙ ምን ያህል ታረጋግጣላችሁ?

እንዲሁም የቀን የት/ቤት ቆይታቸው ምን መልክ እንደነበረውስ ለማወቅ የምትሄዱበት ርቀት አለ ወይ?

ትምህርት ሚኒስትርስ ያወጣውን መመርያ መሬት ላይ መሩረዱን አረጋግጦ ይሆን?

ይህ ችግርስ እንዳለ ት/ቤቶች ያውቁ ይሆን?

ከተማሪዎቹ 20 ብር ተቀብለው ስልካቸውን የሚያስቀምጡ ባለ ሱቆችስ ይህ መመርያ እንደወጣ ያውቁ ይሆን?

ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂው ማን ነው ትላላችሁ??
ሠራዊታችን በባንዳነት በተሰለፈው ፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰድ ሰላምን እያፀና ነው -
  ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ

ሠራዊቱ የኢትዮዽያ ታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪ በመሆን በባንዳነት በተሰለፈው ፅንፈኛ ቡድን ላይ ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ ሰላምን በዘላቂነት እያፀና መሆኑን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ፤ በሰሜን ጎጃም እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በግዳጅ ላይ የሚገኘውን ኮር የግዳጅ አፈጻጸም የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

ከመስክ ምልከታቸውም በኋላ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ጋር የተወያዩ ሲሆን በሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ በአንድ ክፍለ ጦር የስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ በመገኘትም የስራ መመሪያና ስምሪት ሰጥተዋል።

ሌተናል ጄኔራል መሃመድ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪ በመሆን በባንዳነት የተሰለፈውን ፅንፈኛ ቡድን ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ ሰላምን በዘላቂነት እያፀና ይገኛል ብለዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች በመሽሎክለክ ሕብረተሰቡን በማገትና በመዝረፍ ወንጀል የሚፈፅመውን ፅንፈኛ ቡድን ሰራዊቱ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ተከታትሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አንስተው፤ ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

የታሪካዊ ጠላቶችን ተልዕኮ በመቀበል በክህደት በዜጎች ላይ ወንጀል ለመፈፀም የሚንቀሳቀሰውን ፅንፈኛ ቡድን በየደረጃው የሚገኘው አመራር፣ ሕዝቡና የፀጥታ ሃይሉ በትብብር ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢዎች ሰላምን በማፅናትና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳካት የኢትዮጵያን እድገትና ብልፅግና ማረጋገጥ የሁላችንም አደራ እና ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የሰላምና የጀግንነት ተምሳሌት የሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ክብርና ሉአላዊነት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ዝግጁነት የሚገኝ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አረጋግጠዋል።
በጉራጌ ዞን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስም የተሰየመው ት/ቤት በዛሬው እለት ተመርቋል።

በምስጋና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የዶክተር አብይ አህመድ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋሪያት ከተማ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።

በዚህም የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን የተገነባው ትምህርት ቤት የዞኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል ባለፈ በሀገር ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት አበርክቶው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታም 8 የመማሪያ ክፍሎች፣ ዘመናዊ ቤተመጽሀፍት፣ የአስተዳደር ቢሮ፣ የመምህራን ስታፍና ሌሎችም ያካተተ ነው ተብሏል።

በምረቃ ፕሮግራሙም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣ የምስጋናው የበጎ አድራጎት መስራችና የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው እና የእምድብር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ተገኝተዋል።
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Jaalalli Walloorraa maddu Itoophiyaa maraaf ga'aadha
"ደሴ ከለውጥ በኋላ የሠላም፣ የልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ተምሳሌት ከሆኑ ከተሞቻችን ውስጥ አንዷ እየሆነች ነው" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ዛሬ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አስታውቋል።

"ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ዛሬ እሁድ ህዳር 7  ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣  በኤቲኤም ማሽኖች እንዲሁም በፖስ ማሽኖች እና በኮር ባንኪንግ የሚሰጡ አገልግሎቶች (Core Banking Services) በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳወቅን፣ ለሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን። ብሏል
የ11ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች

📌 ምርጥ ተዋናይት፦ ቃልኪዳን ጥበብ (ትዝታ)

📌 ምርጥ ተዋናይ:- ናታይ ጌታቸው ( ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ አማኑኤል ሀብታሙ (አፊኒ)

📌 የተመልካች ምርጫ፦( ባለ ክራር)

📌 ምርጥ ዳይሬክተር፦  ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ፊልም፦ (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ድምፅ፦ ሐብታም አዲስ (አፊኒ )

📌 ምርጥ ኤዲተር፦ ዳንኤል አንማው (ትዝታ)

📌 ምርጥ ስኮር፦  ስምአገኘኹ ሳሙኤል (አፊኒ)

📌 ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ ኤደን አይሸሹ፣ ፍፁም ካሳሁን እና አብነት አጎናፍር (ጥቁር አደይ)

📌 ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ኤልያስ ተስፋዬ 6 ሰዓት ከለሊቱ

📌 ምርጥ ሜካአፕ፦ ዝናዊት ዘርጋባቸው (አፊኒ )

📌 ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)

📌 ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ክላራ ሙሉጌት (ሁለት ቅጣት)

📌 ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ሳሊም አብዱራህማን (ለፍትህ )

📌 ምርጥ ረ/ተዋናይት፦  ማርታ ጎይቶም (6 ሰዓት ከለሊቱ )

☑️ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፍቅርተ ጌታሁን እና ወለላ አሰፋ

☑️ የሐርሜላ ተሸላሚ፦ ወይዘሮ ወሰኔ ሀይሉ

☑️ ምርጥ አጭር ፊልም፦ በማን ዓይን አሸናፊ መስፍን

ከ16ቱ 5ቱን አዋርድ በመውሰድ ጥቁር አደይ ፊልም ከፊት ይገኛል፣

አፊኒ 4ት በመውሰድ ይከተላል፤

ትዝታ እና 6 ሰዓት ከለሊት ደሞ ሁለት ሁለት አዋርድ በማሸነፍ 3ኛን ይዘዋል።