Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ። በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል። የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው። የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉ።

በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ስለ አፍሪካ መልካም ገጽታ የሚሰራው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አኮን ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ ሥራዎቹ ዎዴ ማያ በመባል የሚታወቀው ጋናዊው ወጣት በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች እና በሰው ዘር መገኛዋ አፋር ተገኝቶ ያደረገውን ጉብኝት እንደሚከተለው አጋርቷል።

ሙሉ ዘጋቢ ፊልሙ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/N-9ziUnJVeE?si=IA_NzGC1Jwq0YQCK
1