Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
ሰሞኑን ጂንካ ላይ የታየው ወረርሽኝ የኢቦላ ዝርያ ግን ከኢቦላም የከፋ መሆኑ ተረጋገጠ‼️
ወረርሹኙ  ማርበርግ የተሰኘ ቫይረስ ( Marburg virus) የሚያስከትለው በሽታ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚንስተር አረጋግጧል።

የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (CDC) ቫይረሱን “እምብዛም የማይከሰት  ግን በጣም የከፋ በማለት ገልፆት ገዳይ ሊሆን ይችላል” ብሏል።

በሽታው ከ ‘ ግብጿ የፍራፍሬ  ለሊት ወፍ’ ( Egyptian fruit bat)  የሚመጣ ሲሆን  በህመሙ ከሚያዙ ሰዎች ግማሽ ያህሉ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ጥናቶች ያሳያሉ።

በሽታዉ የሚተላለፈው በሰውነት ፈሳሽ ንክኪ ፤  ህክምናው ደግሞ እረፍትና ፈሳሽ አብዝቶ መውሰድ (የእገዛ ህክምና) መሆኑ ተዘግቧል።

ህብረተሰቡ የቫይረሱን  መተላለፊያ  መንገድ በመረዳት አስፈላጊውን ጥንቃቄ  ማድረግ ይኖርብናል።
የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች እና ማዳረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ጤና ሚኒስቴር ያወጣውን መረጃ ከላይ ተያይዟል።
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ። በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል። የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው። የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉ።

በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል።