Estifanos Getahun
1.05K subscribers
47.8K photos
1.79K videos
14 files
15.8K links
Download Telegram
የክብር ዶክተሬት መጠሪያ አይሆንም‼️
የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች በመጠሪያነት መጠቀም የማይቻል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።
በትናንትናው እለት የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያ መመላከቱን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ፤

በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰው ይሁን እንጂ የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አብራርተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት መስጠት የሚችሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ እንዲሁም የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን በየትኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መጠቀም እንደማይችል መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው መላኩ ይታወቃል።
ት/ት ሚኒስቴር
ክፍለ ጦሩ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የሚንቀሳቀሰውን ሸኔ ከጥቅም ውጪ ማድረጉን አስታወቀ።

በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሀብሩ ወረዳ ቀበሌዎች ለአፈናና ለዘረፋ ሲንቀሳቀስ በነበረው ሸኔ ላይ የደቡብ ዕዝ  ነበልባል ክፍለጦር በወሰደው እርምጃ አስራ አምስት የሽብር ቡድኑን አባላት መምታቱን አሥታውቋል።

የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ለታ እንበሴ በዘረፋና እገታ ህዝብን የሚያሰቃየው አሸባሪው ቡድን የመደምሰስ ተልእኮ ቀጣይነት እንዳለው ገልፀው በተጠና መልኩ በተደረገው ስምሪትም አስር ሲደመሰስ አምስት የሽብር ቡድኑ አባላት መማረካቸውን ገልፀዋል። ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ መሳሪያ እና ተተኳሽም ገቢ ተደርጓል።

የ6ኛ ዕዝ መብረቅ  ክፍለ ጦር በምስራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረታ ወረዳ በጽንፈኛው ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች የቡድኑ አባላት መመታታቸው ተገልጿል።

‎የመንግስት እና የህዝብን ንብረት ለመዝረፍ አልሞ የተነሳው  ጽንፈኛ ቡድን ላይ 11 ሲደመሰስ የተለያዩ መሣሪያዎች እና ተተኳሾች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ዘገባው የክፍለጦሮች ነው።
"የትውልድና የሀገር ግንባታ የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ ነው።

ዛሬ ከሐይቅ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ጎን ለጎን በባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ደረጃውን በመጠበቀ መልኩ የተገነባውን ገበታ ለትውልድ ሐይቅ ቁጥር 1 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀናል፡፡

ትምህርት ቤቱ ሀገርን ከፍ የሚያደርጉ ልጆችን የሚያፈራ እንዲሆን በአግባቡ መጠቀም ይገባል"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
10ኛው የከተሞች ፎረም መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በሰመራ ሎጊያ በምስል፡ 👌👌👌