Prime Media
2.03K subscribers
5.22K photos
77 videos
4 files
1.13K links
Prime Media is an East-African media organization founded to stand for the truth. Follow us here for high quality news updates and entertainment.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ "Liveable and Sustainable Cities: Rejuvenate, Reinvent, Reimagine" በሚል መሪ ቃል በሲንጋፖር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ በርካታ የአለም ከተሞች በተሳተፉበት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ::

ጉባኤው ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና አረንጏዴ በማድረግ ፣ የአየር ብክለትን መከላከል እና የፈጣን ለውጥ ማዕከል በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ስለማኖር በሰፊው እየመከረ የሚገኝ ሲሆን ልምድ ልውውጥ እና መማማርን ማዕከል ያደረገ ጉባኤ ነው::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በC40 አባል ከተሞች አማካይነት በተዘጋጀዉ የፓናል ዉይይት ላይ በመሳተፍ በከተማችን ቀጣይነት ያለው እድገት በማረጋገጥ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ፣ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በተለይ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የተሻለ ከተማን ለመገንባት እየተከናወኑ ባሉ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች በመገንባት፣ የአረንጓዴ ልማት ኢንሼቲቭን በማከናወን ላይ ስለሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዲሁም የሚሰራው ልማት ሁሉ ለሰው ልጆች ተስፋ እና የኑሮ ጫናን የሚያቃልል ይሆኑ ዘንድ ሰው ተኮር ተግባራት በተመለከተ በዝርዝር አስረድተዋል::

ከጉባኤው ተሳትፎ ጎን ለጎን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሲንጋፖር ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴስሞንድ ሊ ፣ ከተለያዩ ከንቲባዎች ፣ ከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በከተሞች ዙሪያ ከሚሰሩ የድርጅት ተወካዮች ጋር በመገናኘት በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ውይይት ለማድረግ ችለዋል::
አትሌት ለሜቻ ግርማ በስቶኮልም የዳይመንድ ሊግ አሸነፈ

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_በስዊድን ስቶኮልም ከተማ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ አሸንፏል።

የርቀቱን የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር ያሸነፈው አትሌት ለሜቻ በ8:01:63 ውድድሩን አጠናቋል።

አትሌት ፍሬው ሳሙኤል በ8:05:78 በሁለተኝነት እንዲሁም አትሌት ጌትነት ዋለ በ8:10:73 የአራተኛ ደረጃን በመያዝ ወድድሩን ፈፅመዋል።

በተያያዘም በሴቶች 1500 ሜትር አትሌት ብርቄ ሀየሎም በ3:59:84 በአራተኝነት አጠናቃለች።

ሀብታሙ ምትኩ
"ማንበብ ባህል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው።

የንባብን ባህል ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው። በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ለ አንድ መቶ ቀናት ንባብን ሲያበረታታ ቆይቷል። ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

መጪው ክረምት ነው። ብዙ ወጣቶች ዕረፍት ላይ ይሆናሉ። ጊዜያቸውን በንባብና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያሳልፉ በብርቱ ልንሠራ ይገባል-" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ፕራይም ሚዲያ (ፕራይም ሚዲያ)_ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ብሎም በኢፌዲሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት ተፈራረሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ በኢስታና ቤተመንግስት በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙ ተመላክቷል።

በተጨማሪም በኢፌዲሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት መፈረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።