Prana Events
296 subscribers
213 photos
7 videos
43 links
Prana Events is the leading trade fair organizer and event managment company in Ethiopia.

+251 116 184365
+25192 930 8366
Lucky Building 5th floor
www.pranaevents.net

Follow us on
Facebook @pranaeventsplc
Twitter @eventsprana
Telegram @PranaEvents
Download Telegram
ፊንቴክስ የፈርኒቸር የቤተውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች አገልግሎቶችና ቴክኖሎጂ
አለም አቀፍ አውደርእይ እና ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ለ 4ኛ ጊዜ እየተካሄደ ነው
ከሰኔ 8 እስከ 11 በሚካሄደው አውደርእይ የሀገር ውስጥ አምራች ኩባንያዎች ከ 400 በላይ ገዢዎች እንዲሁም ከ 4000 በላይ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እና ጎብኝዎች እንደሚስተናገዱበት ይጠበቃል
በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ትረስትድ ፓርትነርስ .....አቶ አክሊለ በለጠ
የፈርኒቸር የቤት ውበትና የግንባታ አጨራረስ ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተው መንግስት ለኢንዱስትሪው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል
የስራ እድል ፈጠራ ለማበረታታት እና የሀገራችንን ምርት ለማሳደግ ፊንቴክስ የራሱን አስተዋጾ እያበረከተ ነው ብለዋል
በቀጣይ አመታትም ያሉንን ምርቶች የማምረት አቅምና ጥራት ላይ አተኩሮ ይሰራል ነው ያሉት
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አስተባባሪ አቶ አስፋው አበበ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እየመጣ ባለው ለውጥና ዘርፉ ላይ በመሳተፋቹ ትልቅ መነቃቃት ሆኗል ብለዋል።
መንግስት ለንግድ ለፈጠራና ለኢንቨስትመንት ቁርጠኛ ነው ያሉት ሀላፊው አስቻይ ሁኔታን በመፍጠር እረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል ያስፈልጋል ነው ያሉት
በጋራ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ ይገባልም ብለዋል።
የተለያዩ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለድርሻዎች በመድረኩ የተገኙ ሲሆን አውደርእዩንም ከፍተው ጉብኝት አድርገዋል።
ለመሳተፍ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://bit.ly/fintex2023