♱ ᴏʀᴛʜᴏᴅᴏx ǫᴜᴏᴛᴇ ♱
3.59K subscribers
559 photos
40 videos
336 links
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ :- @Chkuvara & @Rider16
Download Telegram
በሰላም አሳድሮ አዉሎ በሰላም ለዚህ ሰአት ያደረሰን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ነገንም እንድናይ እሱ ይርዳን 🙏
🙏8423
ከተኛ አንበሳ ይልቅ ዞርዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል

እንንቃ መነሳት አለብን ከተኛንበት ሀጢያት መነሳት አለብን መስራት አለብን መለወጥ አለብን የሰዉ ወሬ ትተን  መስራት አለብን እራሳችንን እንገንባ ተነሳ ከሀጢያት አልጋ

         መልካም እለተ ቅዳሜ
36🙏10
🙏265🥰1
🥰 ዛሬ ቀኑ 5 ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው 🤗

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ

አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል

በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ
ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል
መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል

ለፅንሰትከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ

ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ

ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።

የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው አይለየን አሜን🙏❤️
🥰239🙏4
እንኳን አደረሳቹ ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ጳዉሎስ አመታዊ ክብረ በአል እንዴሁም ለቅዱሱ ለአባታችን ለአብነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ በአል በሰላም አደረሳቹ ካባቶቻችን በረከት ረድኤት ይጠብቀን ሀገራችንን መሀሏን ገነት ዳሯን እሳት ያድርግልን መልካም በአል
44🙏15
ስም____ትርጉም
1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ
2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ
3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ
4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር
17 ዲና፦ፈረደ
18 ማኑሄ፦እረፍት
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ
21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል
22 ሐና፦ ስጦታ
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ
25 ቶማስ፦ፀሐይ
26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ
27 ማትያስ፦ፀሐይ
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና
30 ኖኅ፦ደስታ
31 ሴም፦ተሾመ
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው
36 እሴይ፦ዋጋየ
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው
42 ዮናስ፦ርግብ
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ
44 ራኄል፦በግዕት
45 ዕዝራ፦ረዳቴ
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት
51 ሶምሶን፦ፀሐይ
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
53 ማርታ፦እመቤት
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር
59 ሄኖስ፦ሰው
60 ሰሎሜ፦ሰላም
61 ሩሐማ፦ምሕረት
62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል
63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ
65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ
66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል
67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል
68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ
70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል
71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል
72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር
73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ
74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!
75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል
76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት
77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ
79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ
80 ሣራ፦ልዕልት
81 ስምዖን፦ሰማ
82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል
85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል
86 አስቴር፦ኮከብ
87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው
89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ
90 አብራም፦ታላቅ አባት
91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት
92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው
93 አክዐብ፦የአባት ወንድም
94 ባሮክ፦ቡሩክ
95 አዳም፦መልካሙ
96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
97 ባርቅ፦መብረቅ
98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው
99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል
100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ
101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል
102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት
103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ
105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው
106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው
107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል
108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል
111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል
113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው
114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ
115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ
116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ
117 ኬብሮን፦ኅብረት
118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል
119 ኤደን፦ደስታ
120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል
122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ
123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ
124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው
125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው
126 ዮሴፍ፦ይጨምር
127 ዮናስ፦ርግብ
128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል
130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው
131 ምናሴ፦ማስረሻ
132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል
133 ዲቦራ፦ንብ
134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው
136 ጽዮን፦አምባ
137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
                   
                        
32
ሰዓሊለነ ማርያም🥹🤲
ኀበ ወልድኪ መድኃኔዓለም🙏
🙏403
እንኳን አደረሳቹ ለቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም በጤና አደረሳቹ ቅድስት ሥላሴ የአብርሀም ቤት እንደ ገቡ ሥላሴዎች የእኛም ቤት ይግቡ በልባችን በሕይወታችን በኖሯችን ይግቡ ከቅድስት ሥላሴ በረከት ረድኤት አይለየን ሀገራችንን ሰላም ያድርጉልን ለሁላቹህም መልካም በአል ይሁንላቹ 🙏
33🙏20
ፊሊጲሲዩስ 1÷27

በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።
24
It's alright God...
It's okay...
I trust you..🤎

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
      ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss ɪᴛ ♡
       
      
#sʜᴀʀᴇ & #ʟɪᴋᴇ
41🥰6
ሰዓሊለነ ማርያም🥹🤲
ኀበ ወልድኪ መድኃኔዓለም🙏
27🎉1
ሰዓሊለነ ማርያም🥹🤲
ኀበ ወልድኪ መድኃኔዓለም🙏
16🙏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ንስሓ በየቀኑ ለመግባት ይህንን ተማሩ || መምህር ዘበነ ለማ
13
መረረም ጣፈጠም
ራስን ማጥፋት መፍቴ አይሆንም

ወጣቶች ሆይ እራሳችሁን ገድቡ
አይዞችሁ  እግዚያብሄር አለ 🙏
🙏277
የጥቅስ ቻናላችን ይቀላቀሉ👇

@Sam_Quotes
@Sam_Quotes
ሰዓሊለነ ማርያም🥹🤲
ኀበ ወልድኪ መድኃኔዓለም🙏
15
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህይወት ብዙ ነገር ታስተምረናለች ።

መቻልን...
ወድቆ መነሳትን...
አልቅሶ መሳቅን...
አግኝቶ ማጣትን...
ወዶ መለየትን...
ፈልጎ አለማግኘትን...ሁሉንም ከባድ ነገር ሲጀመር የሚያቅተን የማንችለው የማይረሳ መስሎን.....ግን የሆነ ቀን ቀስ በቀስ የተቀደደው ገፅ በአዲስ ገፆች እየተተካ ያዘንበትና ልባችንን የሰበረውን ታሪክ በእርሳስ እንደተፃፈና በላጲስ እንደሚጠፋ ፅሁፍ ሙልጭ ሲልልን እናስተውላለን.....
  ........... አንድ ቀን ላይም የማንንም እጅ ሳንይዝ ደስተኛ እንሆናለን.......🤍

#ቅዱስ_አማኑኤል ከሁሉ ነገር በላይ ነው! ዛሬ ላይ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፍን ሊሆን ይችላል ነገር ግን እመኑኝ በእግዚአብሔር ታምነን በትዕግስት ይሄን ጊዜ ካሳለፍን የእርሱ ጊዜ ስትመጣ.......... እርሱ በየሄድንበት ሁሉ ሞገስ ይሆነናል! የነካነውን ሁሉ ይባርክልናል! ከእራሳችን አልፈን ለብዙዎች የምንተርፍ ያደርገናል! የመመስገኛው ምክንያት እንሆናለን! ምርጡ ዕቃው ያደርገናል!

......... ዝም ብዬ እቆማለው ሰልፉን ላንተ እለቃለው በእምነት ወደ አንተ አያለው ጌታ ሆይ  ድልህን እጠብቃለው አዎ የኔ አማኑኤል  ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ ነው! ክብርና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን 🙏 🤍
🙏2718
45🙏7
ደና አመሻቹ ሰላም እግዚአብሔር ከሁላቹጋ ይሁን እና ዛሬ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ መጥቻለዉ መቼስ ትሰሙኛላቹ ብዬ አስባዉ?

ዛሬ መንገድ እየሂድኩ አንድ ወጣት ሴት ቁጭ ብላ ታለቅሳለች በጣም አሳዘነችኝ ተጋ ብዬ ምን ሆነሽ ነዉ ብዬ ጠየኳት እሷም እያለቀሰች እንዴ አለችኝ ቤተሰብ አለኝ ወንድምም አለም እህትም አለኝ ግን የሚያዳምጠኝ ሰዉ የለም ዉስጤ ተስፋ ቁርጧል ነገሮች ሁሉ ይበላቹብኛል ብቸኝነት ይሰማኛል የሚያየኝ ሁሉ ይጠላኛል አለችኝ የምሪነዉ የምላቹ እንባዋ ማቋረጫ የለም ዉስጤን በጣም ነዉ የተሰማኝ ።
አሁን እራሴን ላጠፋ እየሂድኩ ነዉ አለችኝ ለምን እላታለዉ የማልፈለግበት ቦታ የሚያዳምጠኝ የሚረዳኝ ሰዉ  የለኝም ቤተሰብ እንዳሌለዉ ሰዉ ነዉ የምኖረዉ ብኖርስ ምን እጠቅማለዉ አለችኝ ማርያምን ነዉ የምላቹ ይሂን ያህል ክፉ መሆናችንን አየዉ የምርነዉ የምላቹ ሌላዉ ይቅር እስቲ  እንደማመጥ አንናናቅ እንከባበር  ሰዉ በሰዉነቱ እናክብር የሳቀ ሰዉ ሁሉ ደስ ብሎት አደለም ዉስጡ ባዶነት የሚሰማዉ ስንት ሰዉ አለ እግዚአብሔርን ሁሉንም ሰዎች በፍቅር ፈገግ ብለን እንቀበላቸዉ እንረዳቸዉ እግዚአብሔር ይሂንን አይቶ እኮ ነዉ ዝናቡን ያቆመዉ አጠገባችንን ያሉትን ሰዉ ያላዳመጥን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን  ሂደን አዳምጠን ወደ ፀሎቴ ተመልከት እንለዋለን ፀሎታችን እንዴሰማ አጠገባችን ያሉትን ሰዎች እንስማቸዉ ።

እባካቹህን ስለ እግዚአብሔር ብላቹ አጠገባቹ ያሉትን ሰዎች አዳምጧቸዉ እግዚአብሔር የዛሬ የእናንተን ፀሎት ይሰማል ምንም አታርጉላቸዉ ግን በቃ አዳምጧቸዉ  ሀሳብም ካላቹ መናገር ይቻላል ።

       እ   ን   ደ   ማ   መ   ጥ
🙏
🙏257👍4🔥1🕊1
“ሰይጣን ካልፈተነህ ንቆሃል ማለት ነው፤
ስለዚህ በርትተህ ጸልይ።’’

🤍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🤍
43
I know ማንም ሰው ባይኖረኝ
ቅዱስ ሚካኤል እንዳለልኝ🤎

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
      ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss ɪᴛ ♡
       
      
#sʜᴀʀᴇ & #ʟɪᴋᴇ
90🥰5🤗5🔥1