ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#የጡት_ካንሰር_ህመም_ ምልክቶች
ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር
አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው
ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም
በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡
የጡት ካንሰር መነሻ መንስኤዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ
ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለህመሙ
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎችን በከፊል እንደሚከተሉት
ቀርበዋል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
1. እድሜ
በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት
የህይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50
ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
2. በዘር
ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን
በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት
ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
3. ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
4. ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን
እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
5. ጡት ያለማጥባት
6. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
7. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
8. ሲጋራ ማጨስ
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች
1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ
አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው
ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን
ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን
ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን
ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት
4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ
ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት
(ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ
መገልበጥ አያካትትም
5. የህመም ስሜት
አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡
ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም
ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል
የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው
ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው(Lymph node ) በተላበው
አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል
ይችላል፡፡
የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ
ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች
በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት
ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም
አይት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ
ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ
መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

@onlyfemaleb
📌 #ማስጠንቀቂያ 📌
#ለእህቶቻችንን... እባካችሁ የምትገዙት
#የኮስሞቲክስ
አይነቶች
#1ጥራቱን የጠበቀ
#2የአገልግሎት ጊዜው
አለማለፉን
#3ምርቶቹ ከምን ከምን እንደተሰሩ ማረጋገጥ
ይኖርባችኃል:: እንዲሁም ምርቶቹን ከገዛችሁ በሁዋላ
ፊታችሁ ላይ ከማድረጋችሁ በፊት በ ትንሹ እጃችሁ ላይ
በመሞከር እና ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባችኃል::

#ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ



@onlyfemaleb



#ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ
ዛሬ ማታ ስለ#ኪንታሮት

@onlyfemaleb
የኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና)ይህ መረጃ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች
ይደርስ መልካም ንባብ…
የቂ.. ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ
ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ
ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡
1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid)
በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ
2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው
ቆዳ ላይ የሚገኝ
ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው
50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን
ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ
ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡
ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች
• ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
• ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ
• የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ)
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• ዕርግዝና
• የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው
• በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች
እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡
የኪንታሮት ምልክቶች
• ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም
• በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ
• ሕመም ወይንም አለመመቸት
• በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡
ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት
ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል
ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት
ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል
አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር
ያስፈልጋል፡፡
• ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ
የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ
መሄድ ይገባዎታል፡፡
• ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና
እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ
ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን
ናቸዉ?
• አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ
በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች
መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን
ያስከትላል፡፡
• ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን
ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች
መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡
በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ
ለውጦች
• ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት
ጊዜ መዘፍዘፍ
• ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ
መታጠብ
• ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም
• እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም
• ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም
ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ
ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ
እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ
ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል?
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር -
አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ
ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡
• ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ -
#እስኪ አስቢው

#እኔ_እና_አንቺ የሌለንበት ቤት በዓሉ በዓል በዓል አይልም እኮ #እኛ_እኮ_ውድ ነን።

#መልካም በዓል ለክርስትና እምነት ተከታዮች

#onlyfemaleb

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇#share #share #share

#join #join #join


@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
ቆንጆ