ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#ላንቺ_ብቻ

በእጮኝነት ጊዜያችሁ እጮኛችሁን #ለማቆየት ብላችሁ ያልሆናችሁትን ነኝ ብሎ ከመናገር ተቆጠቡ።


👅 #እውነትን_ተናገሩ

Join us here 👉 @onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ:
#የፍቅር_ግንኙነትን_ረጅም_ጊዜ_ለማቆየት_ሚረዱ_ነጥቦች
አንደኛውና ዋነኛው ነገር
#ኩርፊያን ማቆም ነው ትንሽዋ
ነገር ምትገነው በኩርፊያ ም/ክ ነው በምንም ነገር
ከማኩረፍም ሆነ ከመበሳጨት በፊት ተነጋገሩ።
☞ሁለተኛው ነገር ምንም ነገር አትመዝኚ/ን ለምን
አይደውልም ለምን ቴክስት አይፅፍም ……………ለምን
ሚለውን ነገር ባጠቃላይ ከአይምሮዋቹ አሶጡት ምንም ነገር
አትመዝኑ ሁሉም የሆነበት የራሱ ም/ክ አለ።
ሶስተኛው እና ግን ቀዳሚዊ ነገር ለሁሉም ነገር አትቸኩሉ
በአንዴው ስለ አንድ ሰው ማንነት ሳታውቁ አበድንልህ
ሞትንልህ አትበሉ በስተመጨረሻ ስለ አፍቃሪያቹ ስሰሙ
መጨረሻው መዘዙ ለናተው ነው።
☞ለወሲብ አትቸኩሉ ከስጋዊ እርካታ በፊት ልባዊ ፍቅራቹን
ማጠንከር አለባቹ ወሲብ አስቀድማቹ ኃላ ፍቅራቹን ረስታቹ
ሁሌም ለስጋዊ እርካታቹ ብቻ መገናኘት ትጀምራላቹ
በመጨረሻም ግንኙነታቹ ይፈርሳል።
ሌላው ደሞ ሁሌም እንደምለው #ትኩረት #ትኩረት #
ትኩረት ትኩረት አስፈላጊው ነገር ነው ለአጋራቹ ትኩረት እና
ጊዜ ስጡ።
☞ካለሱ ወይም ካለስዋ መኖር አልችልም ብላቹ አስቡ
ባሰባቹ ቁጥር ለአፍቃሪያቹ ትልቅ ቦታ እየሰጣቹት ትመጣላቹ
ቅናትን አጥፉ
ወሬ አትስሙ
በሆዳቹ ቂም ከመያዛቹ በፊት መነጋገር ልመዱ
☞ይሄ ቢሄድ ያይመጣል ምትሉትን ሁሉ ከሀሳባቹ አውጡ
ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ዝም ብላቹ 10ፍቅረኛ
ከመያዝ ይልቅ ለህይወታቹ ሚያስፈልገውን ሰው መርጣቹ
መስዋት ብትከፍሉለት ይሻላል።
ወንድሜ እህቴ መለያየትን እንደመፍትሄ አትውሰጂ/ድ
መለያየት መፍትሄ አይደለም ፍቅር እንደ ህፃን ልጅ ነው
በትግስትና በእንክብካቤ ነው ማደግ ያለበት ትግስት ይኑራቹ
ያለፈውን አታስታውሱ ባለፈ ሚዛን አትመዝኑ።

#share #share

አድርጊው

@onlyfemaleb
#የወር_አበባ_ህመም_ህክምና!

አንዳንድ የጤና ባለሙያዎ ከሆርሞን የተሰራ የወሊድ
መቆጣጠሪያ እንክብል ያዛሉ። እነዚህ እንክብሎች የእንቁላል
መፈልፈልን (ኦቪውሌሽን) (Ovulation) ይከላከላሉ
በተጨማሪም በወር አበባ ጊዜ የሚከሰትን ቁርጠት ወይም
ህመምን ይቀንሳሉ። 97% የሚሆኑት ሃኪሞች
እንደሚስማሙበት የወር አበባን ለመቀነስ በአፍ የሚወሰድ
የወሊድ መከላከያ እንክብል ህክምና ከጤና አንፃር
አስተማማኝና ተቀባይነት ያለው ቢሆንም አብዛኛዎቹ ሴቶች
ግን ይህን አያውቁም።
በለንደን አንድ ኮሌጅ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው
የቻሞሚል ሻይ የወር አበባ ህመምን በመከላከል ረገድ ፍቱን
እንደሆነ አረጋግጠዋል።
ከበሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የወር አበባ ህመም ምንም
የራሱ የሆነ የጐንዮሽ ጉዳት ወይም አደጋ ቢኖረውም በቀዶ
ጥገና መስተካከል ይችላል።
ተጨማሪ የወር አበባ ህመምን የሚያስታግሱ
መፍትሄዎች እነሆ፦
• በሙቅ ወይም ለብ ባለ ውሃ መዘፍዘፍ።
• የታችኛውን የሆድ ክፍል ማሞቂያ በመጠቀም ማሞቅ።
• ዮጋ ስፖርት።
• ማሳጅ።
• መመሰጥ (ሜዲቴሽን)።
• አኩፓንክቸር።
• ተጨማሪ ምግቦች (ቫይታሚን ኢ፣ ቲያሚን፣ ኦሜጋ - 3)
የወር አበባ ህመም ችግር ያለባት አንድ ሴት በቂ የሆነ
እረፍትና እንቅልፍ ብቻ ሳይሆን መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ
እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባታል።
የወር አበባ ህመም መከላከያዎች
የወር አበባ ህመምን ለመከላከል የሚመከሩ
#የመፍትሄ
እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ።
2. የፋት፣ አልኮል፣ ካፌይን፣ ጨውና ጣፋጭ ነገር
አወሳሰድዎን መገደብ ወይም መቀነስ።
3. በመደበኛ ሁኔታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን መሥራት።
4. ጭንቀትና ሃሳብን መቀነስ።
5. ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ያቁሙ።
6. የዮጋ ስፖርት።
7. አኩፓንክቸር።
አሁን ላይ የተሰሩ ጥናቶች
በአብዛኛዎቹ ሴቶች ዘንድ በየወሩ የሚከሰተው የወር አበባ
ህመም ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስና ተቅማጥን ካስከተለ በኋላ
የህመም ስሜቱ ይቆማል ነገር ግን ጥናት አድራጊዎች
መሠረት የተለመድ ለወንድ የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚታዘዙ
መድሃኒቶች በጥቂቱም ቢሆን ከዚህ ህመም እፎይታ
እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።
ሌላው ጥናት አድራጊዎች የሚጠቁሙን ነጥብ በአፍ
የሚወሰድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን በተለምዶ
የወር አበባ ኡደትን መሠረት አድርጐ ከሚታዘዝልን ትዕዛዝ
በተለየ ሁኔታ እነዚህን እንክብሎች በተከታታይ መውሰድ
ከመካከለኛ እስከ ከባድ የወር አበባ ህመምን
እንደሚያስታግሱ ተናግረዋል።
መልካም ጤንነት!!
@onlyfemaleb
#የወር_አበባ_ተፈጥሯዊ_ጸጋ ነው።
የመተንፈስ ወይም የመመገብ ያህል ከተፈጥሮ ሂደቶች አንዱ
ነው። የምድርን እኩሌታ የያዙት ሴቶች ወርሀዊ ዑደትም ነው።
ሆኖም ስለ ወር አበባ ማውራት እንደ ሀጢያት ይቆጠራል።
ከወር አበባ ጋር የተያያዙ የተዛቡ አመለካከቶችም የትለሌ
ናቸው።
ከደቡብ እስያ ሴቶች አንድ ሦስተኛው የወር አበባ
ከማየታቸው በፊት ስለ ወር አበባ ምንነት እንደማያውቁ
ዩኒሴፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 የሰራው ጥናት
ያመለክታል። ከኢራናውያን ሴቶች 48 በመቶዎቹ እንዲሁም
ከህንዳውያን ሴቶች አስር በመቶ የሚሆኑት የወር አበባ በሽታ
እንደሆነ ያስባሉ።
በዓለም ላይ በሚልዮን የሚቆጠሩ እንስቶች የወር አበባ
በሚያዩበት ወቅት ይገለላሉ። ሀፍርትም ይሰማቸዋል።
የግንዛቤ ክፍተቱን ከግምት በማስገባት ዋሽ ዩናይትድ የተባለ
የተራድኦ ድርጅት በየአመቱ ግንቦት 28 ዓለም አቀፍ የወር
አበባ ንጽህና ቀን እንዲከበር አድርጓል። ስለ ወር አበባ ርዕሰ
ጉዳይ ማውራትን ለማስለመድ ስለ ሂደቱ ማወቅ የመጀመሪያ
እርምጃ ሊሆን ይችላል።
የወር አበባ ዑደት እንዴት ይፈጠራል?
ስለ ወር አበባ ምንነት ማስገንዘብ ስለ ዑደቱ ያለው
አመለካከት እንዲቃና መንገድ ይከፍታል። የወር አበባ ከአስር
እስከ 14 ዓመት አንስቶ ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚዘልቅ
ዑደት ነው።
የወር አበባ ወርሀዊ ዑደት የሚፈጠረው በየ28 ቀን ልዩነት
ሲሆን፣ ወደ ጽንስነት ያልተለወጠ እንቁላል ፈርሶ በደም
መልክ የሚወጣበት ሂደት ነው። የ28 ቀን ዑደቱ ሁለት
ደረጃዎች አሉት።
የመጀመሪያው የወር አበባ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ያሉትን
ሁለት ሳምንታት ያካትታል። በዚህ ወቅት ከሴቶች መራቢያ
ህዋስ በአንዱ እንቁላል ማደግ ይጀምራል። የእንቁላሉን
እድገት የሚያፋጥን ሆርሞንም ይመረታል።
ወደ አስራ አራተኛው ቀን አካባቢ እንቁላሉ ሲያድግ በማህጸን
ቧምቧ አድርጎ ወደ ማህጸን ይወርዳል። እንቁላሉ ከወንድ ዘር
ጋር ከተዋሃደ የእርግዝና ሂደት ይጀመራል። ውህደቱ
ካልተፈጠረ እንቁላሉ ከሁለት ወይም ከሦስት ቀናት በኋላ
ሞቶ ይወገዳል።
የዑደቱ ሁለተኛ ደረጃ በአስራ አራተኛው ቀን ጀምሮ በሀያ
ስምንኛው ቀን ይጠናቀቃል። በሀያ አምስተኛው ቀን በማህጸን
ውስጥ የሚመረተው የሆርሞን መጠን ቀንሶ ከሦስት እስከ
ሰባት ቀን ደም ይፈሳል።
በዚህ መንገድ የሚፈጠረው የወር አበባ ወርሀዊ ሂደትን
ይከተላል።
ለምን በወር አበባ ወቅት ህመም ይከሰታል?
በወር አበባ ወቅት ምቾት የማይሰማቸው ሴቶች አሉ። አንድ
ሦስተኛ ያህሉ ሴቶች ደግሞ ያማቸዋል። ከህመሞቹ ራስ
ምታት፣ የጀርባ ህመም፣ ሆድ ቁርጠትና ማቅለሽ ይጠቀሳሉ።
ለ24 ሰዓት ሊቆዩም ይችላሉ።
ምክንያቱን ለማብራራት ቢያስቸግርም አቅም ማነስ
የሚከሰትበትም ጊዜ አለ።
የወር አበባ ህመም መጠን ያለፈ የማህጸን ውስጥ የደም
እጢ ውጤት ነው። ይህም የማህጸን ጡንቻ መወጠርና
መላላት የሆድ ቁርጠት ያስከትላል። ህመሙ ከወር አበባ
አንድ ወይም ሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ ለቀናት ይዘልቃል።
አንዳንድ ሴቶች ላይ ከቀናት ሊያልፍም ይችላል።
ዲስሜኖሪያ የተሰኘው ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ፍተኛ የሆድ
ቁርጠት እድሜ ሲጨምር ሊከሰት ይችላል። በዘር
የመተላለፍ ባህሪም አለው። በማህጸን ውስጥ መሆን
ያለባቸው ህዋሶች ከማህጸን ውጪ ሲሆኑ ኢንዶሜትርዮሲስ
ይባላል። ከአስር ሴቶች በአንዷ ሊከሰትም ይችላል።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ተቀላቀሉ
@onlyfemaleb

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ስለ ጡት ካንሰር ዛሬ ማታ

@onlyfemaleb
#የጡት_ካንሰር_ህመም_ ምልክቶች
ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር
አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው
ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም
በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡
የጡት ካንሰር መነሻ መንስኤዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ
ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለህመሙ
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎችን በከፊል እንደሚከተሉት
ቀርበዋል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
1. እድሜ
በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት
የህይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50
ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
2. በዘር
ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን
በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት
ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
3. ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
4. ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን
እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
5. ጡት ያለማጥባት
6. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
7. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
8. ሲጋራ ማጨስ
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች
1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ
አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው
ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን
ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን
ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን
ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት
4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ
ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት
(ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ
መገልበጥ አያካትትም
5. የህመም ስሜት
አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡
ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም
ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል
የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው
ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው(Lymph node ) በተላበው
አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል
ይችላል፡፡
የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ
ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች
በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት
ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም
አይት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ
ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ
መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

@onlyfemaleb
📌 #ማስጠንቀቂያ 📌
#ለእህቶቻችንን... እባካችሁ የምትገዙት
#የኮስሞቲክስ
አይነቶች
#1ጥራቱን የጠበቀ
#2የአገልግሎት ጊዜው
አለማለፉን
#3ምርቶቹ ከምን ከምን እንደተሰሩ ማረጋገጥ
ይኖርባችኃል:: እንዲሁም ምርቶቹን ከገዛችሁ በሁዋላ
ፊታችሁ ላይ ከማድረጋችሁ በፊት በ ትንሹ እጃችሁ ላይ
በመሞከር እና ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባችኃል::

#ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ



@onlyfemaleb



#ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ #ተቀላቀሉ
ዛሬ ማታ ስለ#ኪንታሮት

@onlyfemaleb
የኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና)ይህ መረጃ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች
ይደርስ መልካም ንባብ…
የቂ.. ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ
ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ
ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡
1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid)
በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ
2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው
ቆዳ ላይ የሚገኝ
ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው
50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን
ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ
ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡
ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች
• ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
• ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ
• የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ)
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• ዕርግዝና
• የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው
• በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች
እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡
የኪንታሮት ምልክቶች
• ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም
• በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ
• ሕመም ወይንም አለመመቸት
• በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡
ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት
ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል
ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት
ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል
አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር
ያስፈልጋል፡፡
• ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ
የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ
መሄድ ይገባዎታል፡፡
• ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና
እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ
ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን
ናቸዉ?
• አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ
በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች
መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን
ያስከትላል፡፡
• ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን
ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች
መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡
በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ
ለውጦች
• ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት
ጊዜ መዘፍዘፍ
• ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ
መታጠብ
• ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም
• እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም
• ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም
ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ
ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ
እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ
ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል?
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር -
አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ
ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡
• ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ -
#እስኪ አስቢው

#እኔ_እና_አንቺ የሌለንበት ቤት በዓሉ በዓል በዓል አይልም እኮ #እኛ_እኮ_ውድ ነን።

#መልካም በዓል ለክርስትና እምነት ተከታዮች

#onlyfemaleb

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇#share #share #share

#join #join #join


@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb