ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
ላንቺ ብቻ

ጥሎክ ለሄደ ሰዉ አንተን የማይፈልግህ ሰዉ አንተ ሳይሆን ማልቀስ ማንባት ያለብህ እሱ እራሱ ነዉ ነገሩ እንዲ ነዉ .........
አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል
ጓደኞቹ እንዲነግራት ቢያበረታቱትም ደፍሮ ማድረግ አልቻለም በቃ እሷን እያሰበ
በትምህርቱ እየደከመ ሳቅ ጨዋታ እያስጠላው ሰውነቱ እየቀነሰ ጭንቀታም
መሆኑ እጅግ ያሳሰባቸው ጓደኞቹ በስንት መከራ አግባብተው እንዲነግራት
ያደርጉታል
እናም ሲፈራ ሲቸር በጣም እንደሚወዳት ይነግራታል እሷም ቀብራራ ነገር
ነበረችና እንዲህ አለችው <<ውይ በጣም ይቅርታ እንኳን የፍቅር ጥያቄህን
ልቀበልህ ይቅርና በአለም ላይ ማንን ትጠያለሽ ብባል አንተን ነው የምለው እና
ይሄን ጥያቄ ደግመህ እንዳታነሳብኝ >>
ልጁም ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግቶና ፈገግ ብሎ ወደ ጓደኞቹ ይመለሳል።
ጓደኞቹም ፈገግታውን ሲያዩ ልጅቷ የፍቅር ጥያቄውን እንደተቀበለችው አምነው
በደስታ ተቀበሉት አንደኛው ጓደኛው <<እሺ አለችህ አይደል በጣም ደስ ይላል>>
ሲለው ወጣቱ ልጅ
<<አረ በፍፁም እንደውም በአለም ላይ እንደኔ የምትጠላው ሰው እንደሌለ ነው
የነገረችኝ>>አላቸው ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው <<ታድያ እንዴት አላዘንክም እንዴት
አልተከፋህም?>> አሉት እሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ሲል መለሰላቸው
<<ለምን እከፋለሁ ለምንስ አዝናለሁ? እኔ እኮ ያጣሁት በአለም ላይ ከምንም
በላይ የምትጠላኝን ልጅ ነው። እሷ ግን ያጣችው በአለም ላይ ከምንም በላይ
የሚወዳትን ሰው ነው ስለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንም መከፋትም ያለባት እሷ
ናት>> አላቸው።
ይሄ ታሪክ የሁላችንም ነው አንድ የምንወደው ሰው ጥላቻውን ሲያሳየን ወይም
ሲርቀን እንከፋለን እናዝናለን እናለቅሳለን ግን ይሄን ማድረግ ያለበት ያ ትቶን
የሄደ ሰው ነው እንጂ እኛ አልነበርንም።

@onlyfemaleb
#ላንቺ ብቻ:

❤️የእውነት #የሚወድሽ ፈጥኖ ወደ አልጋ አይወስድሽም! ❤️
👇 👇
🌷 @onlygirlsb 🌷
🔹 @onlyfemaleb
#ዛሬ ማታ ስለ ድንግልና እናወራለን።

@onlyfemaleb

#share #share
የሴት ልጅ #ድንግልና ክብሯ ውበቷና ኩራቷ ነው!

@onlygirlb
♦️ @onlyfemaleb ♦️
🔅🔅 ድንግልና 🔅🔅
#መግቢያ
👉ኢትዮጵያ ውስጥ ድንግልና ከፍተኛ ዋጋ አለው። ድንግል ሆና ያገባች ሴት የባልዋ ኩራት ነች ምክንያቱም ሌላ ወንድ አታዉቅማ። በአሁን ጊዜ ግን የሩጫ ሪከርድ ከመስበር ይልቅ ድንግልናን መገርሰስ እንደ
ጀብድ (ስኬት) ከሚታዩት ነገሮች አንዱ ሆንዋል። አዳዶች ኢትዩጲያዊ ባህል እዲሁም እምነትን አሽቀንጥረዉ ጥለዉ ድንግልና ክብር ሳይሆን መቆመሪያ የገንዘብ ማግኛ አድርገዉታል። የድንግልና ዋጋ (ክብር) ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ድንግሎችን
ለማበላሽት የሚመኝና የሚለፋ ወንድ ብዙ ነዉ።
👉በዚያው ልክ ለተለያዩ
ሴቶች ድንግልና ልዩ ትርጉም አለው። አንዳንዶች ድንግልናቸውን
ያስረከቡበትን ምሽት ወይ በጸጸት አልያም በደስታ ያስታውሱታል።
አንዳንዶች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደፍረው ለዓመታት
ከማይወጡበት የስነልቦና ቀውስ ውስጥ በስቃይ ይዋኛሉ።
አንዳንዶች ለድንግልና ልዩ ትርጉምና ክብር በመስጠት ይዘውት ይቀበራሉ። አንዳንድ ሴቶች ድንግልና ሳይኖራቸው “ድንግል ነኝ” በማለት ለድንግልና የሚስገበገቡ ወንዶችን ያታልላሉ ይህን የሚያደርጉት ከተሳካላቸው የሚፈልጉትን ወንድ ለማጥመድ ሲሉ ነው፤ ካልተሳካላቸው ግን የሚደርስባቸው ገጠመኝ ጥሩ አይሆንም።
👉ድንግልና በተለያዩ ምክንያቶች ሊገረሰስ ይችላል። በጎ እና መልካም በሆነ በሕጋዊ ጋብቻ፣ በጠለፋ ፣ ተገዶ በመደፈር፣ ከጋብቻ በፊት በሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ይገረሰሳል።
👉ለነገሩ ጠለፋና ተገዶ መደፈር ልዩነት የላቸውም። ልጅቱ
የምትጠለፈው ያለፍቃድዋ ስለሆነ፣ ከተጠለፈች በኋላ
ድንግልናዋን ካጣች፣ ተገዳ እንደተደፈረች ይቆጠራል። በርግጥ አንዳንድ ጠላፊ፣ ለልጅቱ ወላጆች የጋብቻ ጥያቄ በመላክ፣ ፈቃድ አግኝቶ እስኪያገባት ድረስ በፍትወት ላይደርስባት ይችላል።
ወጣም ወረደ ጠለፋና አስገድዶ መድፈር ብዙም ልዩነት የላቸውም። አስገድዶ መድፈርን እንደ ጀብዱ የሚቆጥር ሰው ካለ
ደግሞ የሥነ ልቦና ችግር ያለበት በመሆን ህክምና ያሻዋል።
👉ብዙውን ጊዜ ድንግልናን መገርሰስ እንደ ክብር የሚያወሩት በሕጋዊ መገድ ያገቡ ወንዶች ሲሆኑ ልክ ናቸዉ። ሌላኛዎቹ እንደ ጀብድ የሚያዩት ደግሞ በፍቅር አሳበው የፈለጓትን ያገኙ ጎረምሶች ናቸው። አሁን አሁን “እንትናን እኮ አሸነፍኩዋት!” እያሉ መጎረር በወጣት ወንዶች ዘንድ የተለመደ ሆኖዋል። በጎልማሶችም ዘንድ ድንግሎች ብርቅ ናቸው። “እከሊት እኮ ድንግል ናት” ሲባል ሰምቶ
የማይቀነዝር ወንድ ጥቂት የሚባል አይደለም። በሐሳቡ ለሱ
የሚታየው፣ ድንግልናዋን ወስዶ፣ በደሟ ታጥቦ፣ “ይኸውና የደሙ
ሻሽ” እያለ እርካታው ሲወጣለት ሊንጠባረር እንጂ “ድንግልናዋን እንዲያ ስገረስስ እሷን ምን ይሰማት ይሆን?” ብሎ ለመጠየቅ ከቶ አይጨነቅም።
👉እንደ ሕንድ ባሉ ሀገሮች ደግሞ ድንግሎች ከመንደራቸው
እየተሰረቁ በከፍተኛ ዋጋ ለቡና ቤቶች ይሸጣሉ። ይህም
የሚሆንበት ምክንያት “ድንግሎች ጎልማሳውን ወጣት ያደርጋሉ”
የሚሉት አጉል እምነት ስላላቸው ነው። በተጨማሪም ድንግሎች
ወሲብ ፈጽመው አለማወቃቸው ከኤድስ ነጻ ለመሆናቸው እንደ
ማስተማመኛ ስለሚወሰድም ነው። የሚያሳዝነው ግን
የሚደፍሯቸውን ወንዶች ከኤድስ ነጻ ይሁኑ አይሁኑ የሚጠይቃቸው
የለም፣ ገንዘባቸውን ከፍለው የሚፈልጓትን ድንግል እስካገኙ
ድረስ።
👉ድንግልናቸውን ከወሲብ ውጭ የሚያጡ ብዙ ሴቶችም አሉ። ለድንግልና ተጠያቂ የሆነችው የቆዳ ሽፋን ስስ ከመሆኗ የተነሳ በከባድ እንቅስቃሴ ልትቀደድ ትችላለች። ሴቶች ገመድ ዝላይ
ሲጫወቱ ወይም ብስክሌት ሲነዱ ያጧታል ይህ ማለት ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅሙ ደም ላይፈስ ይችላል ግን መጀመሪያቸዉ እንደሆነ ያስታዉቃል።
👉ስለዚህ ድንግልናን በሚያከብር ማህበረሰብ ውስጥ ሲኖሩ፣ ድንግልናን ሳይዙ
መገኘት የሚያስከትለው መዘዝ ደግሞ ራሱን የቻለ ስቃይ አለው።
👉አንዳንድ ሴቶች ድንግልናቸውን እስኪያስረክቡ ድረስ ያቁነጠንጣቸዋል። ሁኔታውን ለማየት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ይጓጓሉ። “ያማል”፣ “አያምም” የሚል አሉባልታ ስለሚሰሙ፣ ያን ስሜት በራሳቸው ሰውነት ለማጣጣም ይቋምጣሉ። ሌሎች ደግሞ የሚያምኑትን፣ የሚወዱትንና የሚያገቡትን ወንድ
እስከሚያገኙ ድረስ ከወሲብ ታቅበው ድንግልናቸውን በክብር
መያዝ የሚመርጡ አሉ። እነዚኛዎቹ የፈለገውን ጊዜ ይውሰድ ለጋብቻ የሚሆናቸውን ወንድ ለመጠበቅ የቆረጡ ጀግኒት ናቸው። አንዳንዶች ደግሞ በሐይማኖት ምክንያት፣ በድንግልና ጸንተው ፈጣሪን
እያገለገሉ ለመኖር ይወስናሉ።
👉ድንግልና ይህን ያህል ዋጋ ያለው ነገር ቢሆንም አንዳንድ ወንዶች ግን የሚያፈቅሯት ሴት ያለፈ የህወት ታሪኳን በፀጋ ተቀብለው ለፍቅር መስዋትነት የሚከፍሉ ናቸዉ።
👉እንደዚህ ዓይነት ወንዶች ድንግል የሆነች ጓደኛ ስታጋጥማቸው ወሲብ ለመፈጸም ወይም “ድንግልናዋን ለመገርሰስ” አይቸኩሉም። ደምን ሳይሆን ፍቅርን ነውና የሚፈልጉት። ለነሱ ከወሲብ ይልቅ የሚቀድመው ፍቅር ነው። የግብረሥጋ ግንኙነት ሳይፈጽሙ ጓደኛቸውን ለማርካት ይሞክራሉ። እሷ በራሷ ጊዜ ድንግልናዋን በጋብቻ ለመስጠት እስክትወስን ድረስ አያጨናንቋትም፣ አይገፋፏትም። ግንኙነታቸው ካልቀጠለም በሰላም ይለዩዋታል።
ቀድሞውኑ ለድንግልናዋ ሳይሆን እሷን ብለው ነውና የቀረቧት።
👆ይህ አቁዋም የወንዶች ሁሉ ቢሆን ብዬ እመኛለወ። ሴቶችም በድንግናቸዉ ሊኮሩ ይገባል።

ድ ን ግ ል ና ታላቅ ሚስጥር ነዉ።
ክብር እንጂ ሸክም አይደለም!!!
👍👍👍👍 @onlyfemaleb
😂© #ላንቺ_ብቻ 😂:
የሙሉ 30 ደቂቃ ሜካፕ ተቀብታ
ስትጨርስ ምን ብትል ጥሩነው

ውበት ማለት ውስጣዊ😂😂😂
#ላንቺ_ብቻ

በኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡- በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡

በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡

አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡

ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው?
በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት?

1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት
2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ
3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ
4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው
5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር
6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና
7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት
ጥቅሙ፡-
• በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል
ጉዳቱ፡-
1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም
2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ
3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል
4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው
5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ
****ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@onlyfemaleb

ተቀላቀሉ
#ላንቺ_ብቻ
ለሴት እህቶች ጠቃሚ ምክር

● በፌስቡክ ወይም ቴሌግራም ሀይ ብሎ ቴክስት ላከልሽ
● ሳትመልሺ ወደ ፕሮፋይሉ አቀናሽ
● ጥሩ መኪና አለው አለባበሱም ሆነ አቋሙ ያምራል
● በድጋሚ ሀይ አለሽ
● አሁን ግን በደስታ መለሽለት
● መልእክት መለዋወጥ ተጀመረ
● በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ተያዘ
● ጥሩ ለበስሽ ሽቶ ሜክአፕ ብቻ ተውበሻል
● ተገናኛችሁ
● ውድ የሆነ መዝናኛ ቦታ ወሰደሽ
● ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ጀመራችሁ
● እጆችሽን በፍቅር ያሻሽሻል በቀልዶች ያስቅሻል
● አይኖችሽን በፍቅር አይን ተመልክቶ ፈገግታ ይመግብሻል
● ብዙ ትውውቅ ያላችሁ ያህል ተሰማሽ
● ክፍል እንድትይዙ ጠየቀሽ ተስማማሽ
● ምቾት እንዲሰማሽ አደረገሽ
● በፍቅር በስሱ ከንፈሮችሽን መሳም ጀመረ
● ትክክል አለመሆኑ ቢገባሽም ደስታ ተሰምቶልሻ
● በእርጋታ ወደ አልጋው ወሰደሽ
● ለመቃወም አቅሙን አጣሽ
● ሌላው ቢቀር መከላከያ ለመጠቀም ሀሳብ አቀረብሽ
● በስሜት ጦፎ ስለነበር ሊሰማሽ አልቻለም
● አንቺም ተሸነፍሽ
● ፍልሚያውን ወደድሽው እርካታም አገኘሽ
● ከፍሪጅም ቀዝቃዛ ውሃ አምጥቶ እራሱ አጠጣሽ
● የሚያሳይሽ ክብር እጅጉን ማረከሽ
● ራስሽን ዕድለኛ አድርገሽም ቆጠርሽ
● የምትፈልጊው አይነት ወንድ እንዳገኘሽ ተሰማሽ
● ልብስሽን ለባበስሽ
● ወደ ታክሲ መሳፈሪያም አደረሰሽ
● ጉንጮችሽን ስሞ የደስታ ጊዜ ማሳለፉን ገለፀልሽ
● ለጉዞሽም ገንዘብ በእጅሽ አስጨበጠሽ
● ከልብሽ ፈገግ በማለት ነገ እንገናኝ ፍቅር አልሽው
● እሱ ግን መልስ አልሰጠሽም
● በደስታ ፈገግ እንልዳሽ ተጉዘሽ እቤት ደረስሽ
● በሰላም እቤት እንደደረስሽ መሴጅ ላክሽለት
● ኦንላየን ቢሆንም መልስ አልመለሰልሽም
● ግራ ተጋብተሽ በድጋሚ ፃፍሽለት
● አሁንም መልስ የለም
● ከደቂቃዎች በኃላ ከፌቡ ጓደኞችሽ ሊስት አጣሽው
● ብሎክ መደረግሽ ታወቀሽ
● ቀን ሳምንት ወራት አለፉ
● ህምመ ይሰማሽ ጀመር ድካም ክብደት መቀነስ
● ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ አደረግሽ
● ከቆይታ በኃላ ነርሷ የምርመራ ውጤት ይዛ መጣች
● ኤችአይቪ ፖዘቲቭ እና እርጉዝ እንደሆንሽ ተነገረሽ
● እንዴት?
● ከእውነታው ጋር ተጋፈጥሽ
● ጭንቀት ነገሰብሽ በፍርሃት ተዋጥሽ
● ተስፋቢስነት ስሜት አልባነት ተሰማሽ
● ሞት ወደ አንቺ መቃረቡ ተገለጠልሽ
● ሁኔታዎች ወደ ኃላ ተመልሰው ብታድሻቸው ተመኘሽ
● እረፍዷል
● ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ፀሎት አደረስሽ
® ይህችን ሴት አትሁኚ
® በስሜታዊነት አትመሪ
® በሀብት በንዋይ ሰውን አትመዝኚ
©® ሴት ልጅሽ እንድትሆንልሽ የምትመኚያ አይነት ሴት ሁኚ©®

🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ሴቶች ሆይ ትክክለኛውን ወንድ ጠብቁ
ያላችሁበት ሁኔታ አያስገድዳችሁ
የደቂቃዎች ስህተት የህይወት ዘመን ህመም ያመጣልና ፤ ይልቁንስ ከነገሮች ታግሳቹ የናንተን ትክክለኛ ሰው ጠብቁ!!!!
ወንዶች ሁሉ አንድ አይነት አይደሉም !!
የናንተ ወንድ ይለያል ፤ ከራሱ ይልቅ ለናንተ ያስባል!!
ፍላጎታችሁን ያከብራል!!
እራሱን ሳይሆን እናንተን ያስቀድማል!!
ትክክለኛው ሰው ሲመጣ ውስጣችሁን ይሰማችኋል!!
ክብር ለጠንካራ ሴቶች
ክብር ለእውነተኛ ወንዶች
ክብር በዚህ ሁሉ ከባድ ሁኔታ ውስጥ አልፈው ጠንካራ እናት ለሆኑት

@onlyfemaleb
#የወር_አበባዬ ተዛብቶብኝ ነበር ምን ላድርግ??

@onlyfemaleb
ምላሹን ዛሬ ማታ
አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?
ስለ ወር አበባ መዛባት
እነሆ ቃል
በገባነው መሰረት መረጃውን ይዘን መጥተናል፡፡ ይሄኛው
ክፍል ሁለት ነው፡፡
የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ
ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡
1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች
• የፍሰት መጠን መብዛት
• የፍሰት መጠን ማነስ
• መቅረት
• የቀኑ መዛባት
• ቶሎ ቶሎ መምጣት
2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች
የፍሰት መጠን መብዛት- ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው
መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና
መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣
የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ
መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡
መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣
ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን
ይችላል።
የፍሰት መጠን ማነስ፡- ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ
ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ
ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)
መቅረት፡- ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ
መቅረት፤ መንስኤዎቸሁም
• እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን
መዛባት
• ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ
ሊሆኑ ይችላሉ።
ቀኑን ማዛባት፡- ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
መንስኤዎች፡- የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር
ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡- ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ
የሚመጣ ከሆነ ነው።
መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣
ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ
ይችላሉ።
መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል። ችግር
ከገጠምዎት የተሻለ መፍትሄ ለማግኘት ወደ ህክምና ቦታ
ሄዶ ምርመራ ማድረግና ተገቢውን ህክምና መከታተል።

@onlyfemaleb
#ላንቺ_ብቻ

በእጮኝነት ጊዜያችሁ እጮኛችሁን #ለማቆየት ብላችሁ ያልሆናችሁትን ነኝ ብሎ ከመናገር ተቆጠቡ።


👅 #እውነትን_ተናገሩ

Join us here 👉 @onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ:
#የፍቅር_ግንኙነትን_ረጅም_ጊዜ_ለማቆየት_ሚረዱ_ነጥቦች
አንደኛውና ዋነኛው ነገር
#ኩርፊያን ማቆም ነው ትንሽዋ
ነገር ምትገነው በኩርፊያ ም/ክ ነው በምንም ነገር
ከማኩረፍም ሆነ ከመበሳጨት በፊት ተነጋገሩ።
☞ሁለተኛው ነገር ምንም ነገር አትመዝኚ/ን ለምን
አይደውልም ለምን ቴክስት አይፅፍም ……………ለምን
ሚለውን ነገር ባጠቃላይ ከአይምሮዋቹ አሶጡት ምንም ነገር
አትመዝኑ ሁሉም የሆነበት የራሱ ም/ክ አለ።
ሶስተኛው እና ግን ቀዳሚዊ ነገር ለሁሉም ነገር አትቸኩሉ
በአንዴው ስለ አንድ ሰው ማንነት ሳታውቁ አበድንልህ
ሞትንልህ አትበሉ በስተመጨረሻ ስለ አፍቃሪያቹ ስሰሙ
መጨረሻው መዘዙ ለናተው ነው።
☞ለወሲብ አትቸኩሉ ከስጋዊ እርካታ በፊት ልባዊ ፍቅራቹን
ማጠንከር አለባቹ ወሲብ አስቀድማቹ ኃላ ፍቅራቹን ረስታቹ
ሁሌም ለስጋዊ እርካታቹ ብቻ መገናኘት ትጀምራላቹ
በመጨረሻም ግንኙነታቹ ይፈርሳል።
ሌላው ደሞ ሁሌም እንደምለው #ትኩረት #ትኩረት #
ትኩረት ትኩረት አስፈላጊው ነገር ነው ለአጋራቹ ትኩረት እና
ጊዜ ስጡ።
☞ካለሱ ወይም ካለስዋ መኖር አልችልም ብላቹ አስቡ
ባሰባቹ ቁጥር ለአፍቃሪያቹ ትልቅ ቦታ እየሰጣቹት ትመጣላቹ
ቅናትን አጥፉ
ወሬ አትስሙ
በሆዳቹ ቂም ከመያዛቹ በፊት መነጋገር ልመዱ
☞ይሄ ቢሄድ ያይመጣል ምትሉትን ሁሉ ከሀሳባቹ አውጡ
ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ዝም ብላቹ 10ፍቅረኛ
ከመያዝ ይልቅ ለህይወታቹ ሚያስፈልገውን ሰው መርጣቹ
መስዋት ብትከፍሉለት ይሻላል።
ወንድሜ እህቴ መለያየትን እንደመፍትሄ አትውሰጂ/ድ
መለያየት መፍትሄ አይደለም ፍቅር እንደ ህፃን ልጅ ነው
በትግስትና በእንክብካቤ ነው ማደግ ያለበት ትግስት ይኑራቹ
ያለፈውን አታስታውሱ ባለፈ ሚዛን አትመዝኑ።

#share #share

አድርጊው

@onlyfemaleb
#የወር_አበባ_ህመም_ህክምና!

አንዳንድ የጤና ባለሙያዎ ከሆርሞን የተሰራ የወሊድ
መቆጣጠሪያ እንክብል ያዛሉ። እነዚህ እንክብሎች የእንቁላል
መፈልፈልን (ኦቪውሌሽን) (Ovulation) ይከላከላሉ
በተጨማሪም በወር አበባ ጊዜ የሚከሰትን ቁርጠት ወይም
ህመምን ይቀንሳሉ። 97% የሚሆኑት ሃኪሞች
እንደሚስማሙበት የወር አበባን ለመቀነስ በአፍ የሚወሰድ
የወሊድ መከላከያ እንክብል ህክምና ከጤና አንፃር
አስተማማኝና ተቀባይነት ያለው ቢሆንም አብዛኛዎቹ ሴቶች
ግን ይህን አያውቁም።
በለንደን አንድ ኮሌጅ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው
የቻሞሚል ሻይ የወር አበባ ህመምን በመከላከል ረገድ ፍቱን
እንደሆነ አረጋግጠዋል።
ከበሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የወር አበባ ህመም ምንም
የራሱ የሆነ የጐንዮሽ ጉዳት ወይም አደጋ ቢኖረውም በቀዶ
ጥገና መስተካከል ይችላል።
ተጨማሪ የወር አበባ ህመምን የሚያስታግሱ
መፍትሄዎች እነሆ፦
• በሙቅ ወይም ለብ ባለ ውሃ መዘፍዘፍ።
• የታችኛውን የሆድ ክፍል ማሞቂያ በመጠቀም ማሞቅ።
• ዮጋ ስፖርት።
• ማሳጅ።
• መመሰጥ (ሜዲቴሽን)።
• አኩፓንክቸር።
• ተጨማሪ ምግቦች (ቫይታሚን ኢ፣ ቲያሚን፣ ኦሜጋ - 3)
የወር አበባ ህመም ችግር ያለባት አንድ ሴት በቂ የሆነ
እረፍትና እንቅልፍ ብቻ ሳይሆን መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ
እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባታል።
የወር አበባ ህመም መከላከያዎች
የወር አበባ ህመምን ለመከላከል የሚመከሩ
#የመፍትሄ
እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ።
2. የፋት፣ አልኮል፣ ካፌይን፣ ጨውና ጣፋጭ ነገር
አወሳሰድዎን መገደብ ወይም መቀነስ።
3. በመደበኛ ሁኔታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን መሥራት።
4. ጭንቀትና ሃሳብን መቀነስ።
5. ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ያቁሙ።
6. የዮጋ ስፖርት።
7. አኩፓንክቸር።
አሁን ላይ የተሰሩ ጥናቶች
በአብዛኛዎቹ ሴቶች ዘንድ በየወሩ የሚከሰተው የወር አበባ
ህመም ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስና ተቅማጥን ካስከተለ በኋላ
የህመም ስሜቱ ይቆማል ነገር ግን ጥናት አድራጊዎች
መሠረት የተለመድ ለወንድ የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚታዘዙ
መድሃኒቶች በጥቂቱም ቢሆን ከዚህ ህመም እፎይታ
እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።
ሌላው ጥናት አድራጊዎች የሚጠቁሙን ነጥብ በአፍ
የሚወሰድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን በተለምዶ
የወር አበባ ኡደትን መሠረት አድርጐ ከሚታዘዝልን ትዕዛዝ
በተለየ ሁኔታ እነዚህን እንክብሎች በተከታታይ መውሰድ
ከመካከለኛ እስከ ከባድ የወር አበባ ህመምን
እንደሚያስታግሱ ተናግረዋል።
መልካም ጤንነት!!
@onlyfemaleb
#የወር_አበባ_ተፈጥሯዊ_ጸጋ ነው።
የመተንፈስ ወይም የመመገብ ያህል ከተፈጥሮ ሂደቶች አንዱ
ነው። የምድርን እኩሌታ የያዙት ሴቶች ወርሀዊ ዑደትም ነው።
ሆኖም ስለ ወር አበባ ማውራት እንደ ሀጢያት ይቆጠራል።
ከወር አበባ ጋር የተያያዙ የተዛቡ አመለካከቶችም የትለሌ
ናቸው።
ከደቡብ እስያ ሴቶች አንድ ሦስተኛው የወር አበባ
ከማየታቸው በፊት ስለ ወር አበባ ምንነት እንደማያውቁ
ዩኒሴፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 የሰራው ጥናት
ያመለክታል። ከኢራናውያን ሴቶች 48 በመቶዎቹ እንዲሁም
ከህንዳውያን ሴቶች አስር በመቶ የሚሆኑት የወር አበባ በሽታ
እንደሆነ ያስባሉ።
በዓለም ላይ በሚልዮን የሚቆጠሩ እንስቶች የወር አበባ
በሚያዩበት ወቅት ይገለላሉ። ሀፍርትም ይሰማቸዋል።
የግንዛቤ ክፍተቱን ከግምት በማስገባት ዋሽ ዩናይትድ የተባለ
የተራድኦ ድርጅት በየአመቱ ግንቦት 28 ዓለም አቀፍ የወር
አበባ ንጽህና ቀን እንዲከበር አድርጓል። ስለ ወር አበባ ርዕሰ
ጉዳይ ማውራትን ለማስለመድ ስለ ሂደቱ ማወቅ የመጀመሪያ
እርምጃ ሊሆን ይችላል።
የወር አበባ ዑደት እንዴት ይፈጠራል?
ስለ ወር አበባ ምንነት ማስገንዘብ ስለ ዑደቱ ያለው
አመለካከት እንዲቃና መንገድ ይከፍታል። የወር አበባ ከአስር
እስከ 14 ዓመት አንስቶ ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚዘልቅ
ዑደት ነው።
የወር አበባ ወርሀዊ ዑደት የሚፈጠረው በየ28 ቀን ልዩነት
ሲሆን፣ ወደ ጽንስነት ያልተለወጠ እንቁላል ፈርሶ በደም
መልክ የሚወጣበት ሂደት ነው። የ28 ቀን ዑደቱ ሁለት
ደረጃዎች አሉት።
የመጀመሪያው የወር አበባ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ያሉትን
ሁለት ሳምንታት ያካትታል። በዚህ ወቅት ከሴቶች መራቢያ
ህዋስ በአንዱ እንቁላል ማደግ ይጀምራል። የእንቁላሉን
እድገት የሚያፋጥን ሆርሞንም ይመረታል።
ወደ አስራ አራተኛው ቀን አካባቢ እንቁላሉ ሲያድግ በማህጸን
ቧምቧ አድርጎ ወደ ማህጸን ይወርዳል። እንቁላሉ ከወንድ ዘር
ጋር ከተዋሃደ የእርግዝና ሂደት ይጀመራል። ውህደቱ
ካልተፈጠረ እንቁላሉ ከሁለት ወይም ከሦስት ቀናት በኋላ
ሞቶ ይወገዳል።
የዑደቱ ሁለተኛ ደረጃ በአስራ አራተኛው ቀን ጀምሮ በሀያ
ስምንኛው ቀን ይጠናቀቃል። በሀያ አምስተኛው ቀን በማህጸን
ውስጥ የሚመረተው የሆርሞን መጠን ቀንሶ ከሦስት እስከ
ሰባት ቀን ደም ይፈሳል።
በዚህ መንገድ የሚፈጠረው የወር አበባ ወርሀዊ ሂደትን
ይከተላል።
ለምን በወር አበባ ወቅት ህመም ይከሰታል?
በወር አበባ ወቅት ምቾት የማይሰማቸው ሴቶች አሉ። አንድ
ሦስተኛ ያህሉ ሴቶች ደግሞ ያማቸዋል። ከህመሞቹ ራስ
ምታት፣ የጀርባ ህመም፣ ሆድ ቁርጠትና ማቅለሽ ይጠቀሳሉ።
ለ24 ሰዓት ሊቆዩም ይችላሉ።
ምክንያቱን ለማብራራት ቢያስቸግርም አቅም ማነስ
የሚከሰትበትም ጊዜ አለ።
የወር አበባ ህመም መጠን ያለፈ የማህጸን ውስጥ የደም
እጢ ውጤት ነው። ይህም የማህጸን ጡንቻ መወጠርና
መላላት የሆድ ቁርጠት ያስከትላል። ህመሙ ከወር አበባ
አንድ ወይም ሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ ለቀናት ይዘልቃል።
አንዳንድ ሴቶች ላይ ከቀናት ሊያልፍም ይችላል።
ዲስሜኖሪያ የተሰኘው ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ፍተኛ የሆድ
ቁርጠት እድሜ ሲጨምር ሊከሰት ይችላል። በዘር
የመተላለፍ ባህሪም አለው። በማህጸን ውስጥ መሆን
ያለባቸው ህዋሶች ከማህጸን ውጪ ሲሆኑ ኢንዶሜትርዮሲስ
ይባላል። ከአስር ሴቶች በአንዷ ሊከሰትም ይችላል።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ተቀላቀሉ
@onlyfemaleb

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ስለ ጡት ካንሰር ዛሬ ማታ

@onlyfemaleb
#የጡት_ካንሰር_ህመም_ ምልክቶች
ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር
አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው
ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም
በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡
የጡት ካንሰር መነሻ መንስኤዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ
ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለህመሙ
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎችን በከፊል እንደሚከተሉት
ቀርበዋል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
1. እድሜ
በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት
የህይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50
ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
2. በዘር
ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን
በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት
ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
3. ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
4. ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን
እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
5. ጡት ያለማጥባት
6. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
7. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
8. ሲጋራ ማጨስ
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች
1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ
አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው
ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን
ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን
ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን
ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ
ተገቢ ነው፡፡
3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት
4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ
ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት
(ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ
መገልበጥ አያካትትም
5. የህመም ስሜት
አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡
ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም
ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል
የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው
ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው(Lymph node ) በተላበው
አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል
ይችላል፡፡
የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ
ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች
በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት
ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም
አይት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ
ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ
መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

@onlyfemaleb