ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#አቢጊያ_ነኝ

#በወሲብ_ወቅት_ብልቴን_ያቃጥለኛል_ያመኛል_ይቆስላል_ይላላጣል

እድሜዬ 25 ሲሆን የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ነበረን፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ በግንኙነት ጊዜ ከእኔ ብልት የሚወጣው ፈሳሽ አይወጣም ነበር፡፡ ይህን ተመርምሬ መድሃኒቱን ተከታትዬ ለተወሰነ ጊዜ ተሻለኝ፡፡ ቀጥሎ የጓደኛዬ ብልት ብልቴ ውስጥ ሲገባ ያቃጥለኛል፣ ያመኛል፣ ይቆስላል፣ ይላላጣል፣… ለአንድ ዓመት እንደዛ ሆነብኝ፡፡ ከዛ ተመርምሬ ዶክተሩ (ሐኪሙ) ይህን ችግር ሊያስከትልብሽ የቻለው ማህፀንሽ ውስጥ ዕጢ ስላለ ነው አለኝ፡፡ ይህን እጢ ሳታስወጭ መፀነስ የለብሽም፡፡ ዕጢውን ካስወጣሽ በኋላም ለመፀነስ ሐኪምን ማማከር አለብሽ ተባልኩኝ፡፡ የኔ ጥያቄ ታዲያ፡-
#1 . ማህፀን ውስጥ ዕጢ ሊፈጠር የሚችለው እንዴት ነው?
#2 . በግንኙነት ጊዜ የሚቆስለው የሚላጠው ዕጢው ሲወጣ ይተውሻል ብላችሁ ታምናላችሁ?
#3 . ከቀዶ ጥገና በኋላ እንደፈለጉ ግንኙነት ማድረግ እና ያለስቃይ ልጅ መውለድ ይቻላል? ይህን ሁሉ የምላችሁ ፍቅረኛዬን ማጣት ስለማልፈልግ ነው፡፡ የማይሆን ከሆነ እወደዋለሁ ግን ምን ላድርግ?
#ምላሽ_ዛሬ_ማታ

#ከዶክተር_አንደበት

@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ
#አቢጊያ_ነኝ #በወሲብ_ወቅት_ብልቴን_ያቃጥለኛል_ያመኛል_ይቆስላል_ይላላጣል እድሜዬ 25 ሲሆን የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ነበረን፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ በግንኙነት ጊዜ ከእኔ ብልት የሚወጣው ፈሳሽ አይወጣም ነበር፡፡ ይህን ተመርምሬ መድሃኒቱን ተከታትዬ ለተወሰነ ጊዜ ተሻለኝ፡፡ ቀጥሎ የጓደኛዬ ብልት ብልቴ ውስጥ ሲገባ ያቃጥለኛል፣…
#የዶ/ር ምላሽ 👆👆👆👆
በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ሆነም ከግንኙነት በፊት ወይም በኋላ በብልትና አካባቢው የሚሰማ ህመም በህክምናው Dys-pareunia በመባል ይታወቃል፡፡ የዚህ ህመም ስሜት ከመጀመሪያው የግብረ ስጋ ግንኙነት ጀምሮ የሚሰማ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመሩ ከብዙ ጊዜያቶች ያለ ህመም ከቆየ በኋላ የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት በማንኛውም ጊዜና ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲመጣ ወይም አልፎ አልፎ ሊከሰት የሚችል የበሽታ አይነት ነው፡፡
ምክንያቱም ከብልትና አካባቢው (ከማህፀን ጭምር) በሚኖሩ ችግሮች እና ከስነ ልቦና ችግር ጋርም የመያያዝ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፡፡
ለዚህ ችግር ተጠያቂ ምክንያቶች ተደርገው የሚነሱ ጉዳዮች፡-
– የሴት ልጅ ግርዛት፣
– የማህፀን በሽታ (ኢንፌክሽን)
– ያረጡ ሴቶች
– የጭንቀት በሽታ
– የድብርት በሽታ፣ እና
– በልጅነት ዕድሜ የተከሰተ የፆታ ጥቃት ወይም አስገድዶ መደፈርን የመሳሰሉ ናቸው፡፡
የዚህን በሽታ ምክንያቶች ዘርዘር አድርገን ስንመለከት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ Vestibulsodyria የተባለው የበሽታ አይነት ሲሆን ከ50 ዓመት በላይ በሆኑት ላይ ደግሞ የብልት መሳሳት (Vulvavaginal atrophy) ይህንን የህመም ስሜት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ያስከትላሉ፡፡
ተራ በተራ የዚህን በሽታ ምክንያቶች እስከ ህክምናቸው ስናይ፡-
1. Vaginismus:- የዚህ ችግር መንስኤ አንዲት ሴት የብልቷና አካባቢ ጡንቻ ሳታስበው በሚፈጠርባት መኮማተር የሚያስከትለው ነው፡፡ ለዚህ ችግርም የስነ ልቦና ችግር እንደ ምክንያት ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ የዚህች ሴት የብልት አካባቢ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት በሚነካበት ወይም የወንዱ ብልት ወደ ብልቷ ሊገባ ሲል የብልቷ ጡንቻዎች ይኮማተራል ወይም ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ አካባቢም ሳይነካ ይህ ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ህክምናውን በተመለከተ ቀስ በቀስ የብልትና አካባቢውን ጡንቻዎች አዕምሮን በማዘዝ ለማላላት በመሞከር የሚደረግ የህክምና አይነት ነው፡፡ በዚህም የብልትን ጡንቻዎች ወይም በብልት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ቀስ በቀስ በአዕምሮ እንዲታዘዙ ማድረግ ስለሚቻል በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜትን መቆጣጠር ይቻላል፡፡
ሌሎች ህክምናዎች ደግሞ Sex therapy የሚባለው የህክምና አይነት ሲሆን ህመሙን ለማለዘብ ጓደኛሞች ቀስ በቀስ ግብረስጋ ግንኙነቱን እንዲያላምዳት ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ጊዜ የጓደኛዋ ብልት ቀስ እያለ ወደ ብልቷ እንዲገባ በመርዳት በሂደት የሚከናወን ድርጊት ሲሆን ወንዱም ያለመ ሰላቸት የሚያከናውነው መሆን ያለበት የህክምና አይነት ነው፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚወሰድ የጡንቻን መላላት የሚያመጣውን መድሃኒት መጠቀም ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህንንም ከሐኪም ጋር በመወያየት መጠቀም ይቻላል፡፡
2. Vulvar vestibulodynia:- ይህም ችግር ልክ እንደ ከላይ እንዳለው አይነት በሽታ ሲሆን ምክንያቱ ግን ተደጋጋሚ የብልት ኢንፌክሽን ወይም አደጋ የሚያስከትለው የበሽታ አይነት ነው፡፡ ህመሙ የሚመጣው የብልት አካባቢ ሲነካ ብቻ ነው፡፡ የላይኛው ግን ሳይነካም ሊመጣ ይችላል፡፡
ህክምናውም የግብረስጋ ከመፈፀም በፊት (ከ10 ደቂቃ በፊት) እና ከፈፀሙም በኋላ የሚቀባ ቅባት በመጠቀም ከህመሙ መላቀቅ ይችላል፡፡ የዚህ ቅባት ስም ዛሎኬን ይባላል፡፡ ወይም ከዚህ ላቅ ያሉ የመድሃኒት አማራጮችን በመርፌ የሚሰጥ መድሃኒት በባለሙያ እርዳታ በብልት አካባቢ በመወጋት ህመሙን መቀነስ ይቻላል፡፡ ይህም በመጀመሪያው ቀን፣ ከሳምንት በኋላ እንደገና ከ15 ቀን በኋላ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ስለሚኖሩ በዚህ አይነት በሽታ የተጠቁ ሴቶች የማህፀን ሐኪምን እርዳታ መጠየቅ አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ምክሮች፡-
– የብልትን አካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣
– ላላ ያለና አለርጂ የማይፈጥር ፓንትና ልብስ ማድረግ፣ ከጥጥ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
– ሽታ፣ ቀለማቸው የሚለቅ፣ ኬሚካል ያላቸውን ልብሶች አለመልበስ፣
– የብልትን አካባቢ ሊጎዱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ብስክሌት መንዳት ማቆም፣
– የብልት ፈሳሽ የሚያስቸግራቸው ሴቶች ፓድ ከማድረግ የውስጥ ሱሪያቸውን ቶሎ ቶሎ መቀየር ይጠበቅባቸዋል፣
– የብልት አካቢን ሞቅ ባለ ውሃ መዘፍዘፍና በተለይም የብልት አካባቢ ድርቀት የሚታይባቸው ከሆነ፣
– የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚደረግበት ጊዜ የአትክልት ዘይት መቀባትም ድርቀቱን ሊያስወግድ ይችላል፣
– የተሰባበረ በረዶ በላስቲክ በማድረግ ብልት ላይ ማድረግ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሚከሰተውን የብልት ማቃጠል ሊያስወግድ ይችላል፡፡
– Oxolate የተባለውን ቅመም የያዙ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬዎች አትክልቶችንና ጥራጥሬዎችን ከምግቦቻቸው ላይ መቀነስ፡፡
1. Vulvovaginal atrophy (የብልት መሳሳት)
ይህ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት ወይም ባረጡ ሴቶች ላይ ይታያል፡፡ ምክንያቱም ኤስትሮጅን የተባለው ሆርሞን እጥረት ሲሆን፣ በዚህ እጥረት የብልት አካባቢ ቅባት ይቀንሳል፡፡ ስለሆነም የብልት አካባቢ መድረቅ ይከሰታል፡፡ በዚህም የተነሳ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ይሰማል፣ የብልት አካባቢ ያቃጥላል፣ የብልት መቁሰልና ከግንኙነትም በኋላ መድማት ይታያል፡፡ የኤስትሮጅን ቅባት በቀን አንድ ጊዜ ለአራት ሳምንታት መቀባት ያስፈልጋል፡፡
2. በቂ የብልት ቅባት አለመኖር
በቁጥር 3 እንዳየነው ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ የሚታይና በቂ የስሜት አለመነሳሳት፣ ከጓደኛ ጋር በተለያየ ምክንያት አለመጣጣም ወይም ያልተፈታ የስነ ልቦና ችግር ሲኖር የአንዳንድ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ችግሮች (የደም ግፊት፣ የድብት በሽታ መድሃት እና ሌሎችም) ይህንን ችግር ያስከትላሉ፡፡
መፍትሄዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ ያሉትንና አጋላጭ ችግሮችን ማስወገድ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት የሚደረግ የፍቅር ጨዋታ ያስፈልጋል፡፡
3. የፊኛና የኩላሊት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- በባለሙያ እርዳታ በመታገዝ ህክምና ማድረግ
4. የብልት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- የብልት ፈንገስ በሽታ ወይም ሌላ የብልት በሽታ መኖር፣ የብልትና አካባቢው ፈሳሽ መኖር፣ መቁሰል፣ ማቃጠል፣ ማሳከክ ሌሎችም ምልክቶች ይኖራሉ፡፡ ህክምና ሳይደረግ የሚፈፀም ግንኙነት ህመም ያስከትላል፡፡ በባለሙያ እርዳታ ህክምና ማድረግ ለበሽታውም ለህመሙም መፍትሄ ያስገኛል፡፡
5. በወሊድ ጊዜ የሚደረግ የብልት መቆረጥ ወይም መለጠጥ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህም ችግር በቀዶ ጥገና መስተካከል አለበት፡፡
6. የማህፀን ዕጢ፡- የማህፀን ዕጢ ያላቸው ሴቶች ከሌላቸው ሴቶች ጋር ሲነፃፀሩ በግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በተለይ ትልቅ የሆነና በማህፀን ጀርባ አካባቢ የወጣ ዕጢ ከሆነ የማህፀን ዕጢውን ማውጣት ከዚህ ችግር ያድናል፡፡
7. የስነ ልቦና ችግር ያላቸው ሴቶች በዚህ ህመም ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተለይ የተቃራኒ ፆታ ጥቃት ከደረሰባቸው፣ በቂ እውቀት (ስለ ግንኙነት) የሌላቸው ከሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት የተሳሳተ ግምት ካላቸው ለዚህ ሰዎችም የስነ ልቦና ህክምና፣
#አቢጊያ_ነኝ

#ጡትዎን_በራስዎ_የመመርመ_ዘዴ
እራስ በራስ ጡትዎን በየጊዜዉ የሚያዩና የሚከታተሉ ከሆነ እራስ በራስ ጡት የመመርመር ዘዴ ይባላል፡፡ ስለጡትዎ ያለዎትን ግንዛቤ ለመጨመር አይንዎንና እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን በመዳሰስና በማየት በቀላሉ ጡትዎ ላይ ያሉ ለዉጦችን መለየት ይችላሉ፡፡
ለምን ይህን ማድረግ ያስፈልጋል?፡ጡትዎን እራስዎ መርምረዉ መገንዘብ ጥቅሙ የጡትዎን ኖርማል/ትክክለኛ የሆነዉን ይዘትና ሁኔታ ለማወቅ ስለሚረዳ ነዉ፡፡ጡትዎ ላይ ትክክለኛ ነገር ያልሆነና የተለወጠ ነገር ካጋጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስለሚያስችልዎትም ነዉ፡፡
የጡት ካንሰርን ጨምሮ የጡትዎን ሁኔታ ሊለዉጡ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እራስን በራስ ጡትን የመመርመር ዘዴ የጡት ካንሰርን ለማወቅ/ለመመርመር የሚተማመኑበት ሁነኛ መንገድ/ዘዴ አይደለም፡፡ ይሁንና ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑ ሴቶች ሪፖርት እንዳደረጉት ከሆነ የጡት ካንሰር የመጀመሪያዉ ምልክት የሆነዉ የጡት ዉስጥ እብጠት/ሴቶች እራሳቸዉ ጡታቸዉን በሚዳብሱበት ወቅት የተገኘ ነዉ፡፡በዚህ ምክንያት የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች የሚመክሩት ሴቶች ኖርማል የሆነዉን የጡታቸዉን ይዘት እንዲያዉቁ ነወ፡፡
እጅዎትን በሰዉነትዎ በጎን በኩል በማድረግና ከወገብ በላይ ራቁት በመሆን በመስታወት ፊት መቆም፡፡ ከዚያን ጡትዎ ላይ የሚከተሉትን ነገሮች/ለዉጦች ካሉ ማየት
• ወደፊት ዘምበል በማለት ጡት ላይ የመሸብሸብ፣ የመሰርጎድ፣የመጠን የቅርፅና በሁለቱ ጡት መካከል የመጠን ልዩነት መኖሩን
• የጡት ጫፍዎ ወደዉስጥ መግባት ያለመግባቱን
• ሁለቱን እጅዎን በዳሌዎ ላይ በመጫን ጡትዎን ማየት/መመርመር
@onlyfemaleb
• እጅዎን ከራስዎ በላይ ከፍ በማድረግና ሁለቱን መዳፍና መዳፍዎን አንድ ላይ መጫን
• ጡትዎን ወደላይ ከፍ ማድረግና በታች በኩል ያሉት የጡት ጠርዞች በሁለቱም በኩል ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ
ከዚያን እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን መመርመር፡ ብዙዉን ጊዜ የሚመከሩ ዘዴዎች
• መንጋለል፡- በጀርባዎ ለመተኛት እንዲመችዎ በአልጋ ላይ ወይም ለጥ ያለ ቦታ መምረጥ
• በሻወር ወቅት፡- ጡትዎንና ጣትዎን ሳሙና በመቀባት በደንብ እንዲያሟልጭ በማድረግ በቀላሉ በቆዳዎ ላይ እንዲሸራተት ማደረግ
ጡትዎን በሚዳስሱበት/በሚመረምሩበት ወቅት ሊከተሉት የሚገባ ምክር
@onlyfemaleb
• የእጅዎን መዳፍ መጠቀም
• ጡትዎን በሚመረምሩበት ወቅት በተለያየ ደረጃ መጫን(አንዳንዴ በስሱ ሌላ ጊዜ በደንብ ጫን በማድረግ)
• በደንብ ጊዜ ወስዶ መመርመር
• የሚመረምሩበትን ዘዴ/ንድፍ አዉቆ መከተል
ዉጤት
በወር አበባ ዑደት ወቅት የሚከሰቱ ለዉጦች ብዙዎቹ ኖርማል ናቸዉ፡፡ በጡትዎ ላይ ለዉጥ ወይም የሆነ እብጠት/የጠጠረ ነገር ቢያገኙ መደናገጥ የለብዎትም፡፡ በጡትዎ የታችኛዉ ጠርዝ ላይ የሚታዩ ጠንከር ያሉ ነገሮች እምብዛም የሚያሳስቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ እድሜዎ በጨመረ ቁጥር የጡትዎ ሁኔታ እየተቀየረ ይመጣል፡፡
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያለብዎ መቼ ነዉ?
@onlyfemaleb
• በጡትዎ ላይ ጠንካራ/ጥጥር የሆነ እብጠት ወይም በብብትዎ ስር ጥጥር የሆነ እብጠት ካለ
• ጡትዎን ሲዳስሱት ወይም ሲያዩት የተለወጠ ከመሰለዎ፡- የመወፈር፣ በዙሪያዉ ካለዉ አካል በተለየ ሁኔታ ማበጥ/መለየት ካለዉ
• የሰረጎደ፣የተሸበሸበ፣ያበጠ ወይም ጠርዝ ያወጣ ነገር በጡትዎ ላይ ከተመለከቱ
• በቅርቡ የተከሰተ ወደ ዉስጥ የገባ የጡት ጫፍ
• የመቅላት፣የመሞቅ፣የማበጥ ወይም ህመም ጡትዎ ላይ ካለ
• የማሳከክ፣ሽፍታ፣ቁስለት ጡትዎ ላይ ካዩ
• ደም የተቀላቀለበት የጡት ፈሳሽ ካለዎ ናቸዉ፡፡
@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ
Video
ወገብሽ ውብ እንዲሆን 👆👆👆
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

እንዴት ናቹልኝ የኔ ውዶች ከዚህ ቀን በኋላ #online የማማከሪያ ሰዓት ዘውትር ሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት
ምን አልባት ስራ አዳሪ በምሆንበት ቀን ላልኖር እችላለው።
ከ online ውጪ ማለትም text ባየሁ ቁጥር ለመመለስ በማንኛው ሰዓት እናንተን ለመርዳት እና ለማገዝ ተዘጋጅቻለው።
#ቤተሰብ
#ትምህርት_እና_ስራ
#ፍቅር
#ጤንነት
#ጓደኝነት
#ሴትነት
#ወሲብ
#እንዲሁም ማንኛውንም ሀሳብ መመካከር እንችላለን መጪው ጊዜ የእኔ እና የአንቺ ነው።
ሚስጥር ጠባቂነቴ እስከ አሁን ባማከርኳቸው እህቶቼ ታይቷል ተመስግኛለው።
#እስካሁንም እጅግ በርካታ ሴቶችን online አማክሬአለው

#አንቺስ??

💯 አንድ % ሚስጥራቹ ይጠበቃል

#በጥያቄያቹ መሰረት
የማማከር አድማስ ሰፋ አድርጌአለው
ወንድ እንዲያማክራቹ ምትፈልጉም በውስጥ መስመር መጠየቅ ትችላላቹ

@onlygirlsb

ላይ ማንኛውንም ሀሳብ ማንሳት መብታቹ ነው።

#share #share
@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ
#አቢጊያ_ነኝ ስለ #ብልት መታጠን መረጃ @onlyfemaleb
#ብልትን_መታጠን
ጉዳት እንዳለው ባለሙያዎች አስጠነቀቁ
አንዲት ካናዳዊት ሴት ብልቷን ለመታጠን ባደረገችው ሙከራ ራሷን ካቃጠለች በኋላ የማህፀን ሀኪሞች ብልትን መታጠን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ አደጋዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።
የ62 ዓመቷን ካናዳዊትን ተሞክሮ ያካተተው ይህ ጥናት ታትሞ የወጣው በካናዳ በሆድና የማሕፀን ጤና ላይ በሚያተኩር ጆርናል ላይ ነበር።
ይህች በጥናቱ ላይ የተሳተፈችው ሴት የብልት መገልበጥ ሕመም ስትሰቃይ የነበረ ሲሆን ቀዶ ሕክምና ሳታደርግ በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ፈውስ ማግኘት እንደምትችል እምነት ነበራት።
• መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው
• ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ?
ብልትን መታጠን፣ በሞቀ ውሃ ላይ መቀመጥ፣ በውሃው ላይ ባህላዊ መድሃኒቶችን መጠቀም እየተለመደ የመጣ ተግባር ነው። በውጫዊ የብልት አካባቢ ያሉ አካላትን ለመንከባከብ በሚል ዘመናዊ በሆኑ የውበት መጠበቂያ ቤቶችና ስፓዎች ሳይቀር ለሚፈልጉ ደንበኞች አገልግሎቱን ይሰጣል።
ይህንን ብልትን የመታጠን ልማድ በሚመለከት ኤል ኤ ታይምስ በአውሮፓዊያኑ 2019 ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት ያደረገ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግውይኔት ፓልትሮው ጉፕ ብራንድ እንዲጠቀሙት ከመከረ በኋላ ግን የበርካቶችን ትኩረት ስቧል።
ባለፈው ዓመት አሜሪካዊቷ ሞዴል ክሪሲይ ቴገን ብልቷን ስትታጠን የሚያሳይ ፎቶግራፏን አጋርታለች።
የውበት መጠበቂያ ቤቶችና ስፓ ማስታወቂያዎችም ብልትን መታጠን እስያና አፍሪካ በዘመናቸው ሁሉ ሲጠቀሙበት የኖሩት መድሃኒት እያሉ ያስተዋውቃሉ፤ እንዲያውም ይህንን ልማድ አንዳንጊዜ 'ዮኒ ስቲሚንግ ' እያሉ ይጠሩታል። ድርጊቱም ብልትን የሚመርዝ ነገርን የማስወገድ ተግባር እንደሆነ ይነገራል።
ባለሙያዎች ግን እነዚህ ድርጊቶች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ይመክራሉ- በወር አበባ ወቅት የሚከሰትን ህመም ያስታግሳል፣ መካንነትን ይከላከላል የሚሉትን ጨምሮ ስለሌሎች ጠቀሜታውና ፋይዳው እስካሁን የወጡ ማረጋገጫዎች አለመኖራቸውን በመጥቀስ።
በሮያል ኮሌጅ የሆድ አካልና ማሕፀን ሕክምና ክፍል አማካሪና ቃል አቀባይ የሆኑት ዶ/ር ቫንሳ ማኬይ የሴቶች ብልት የተለየ እንክብካቤና ከመጠን ያለፈ ፅዳት ያስፈለግዋል መባሉን ' አፈ ታሪክ' ነው ይሉታል። ይሁን እንጂ ሽታ በሌላቸው ሳሙናዎች ውጫዊ የሆነውን የብልት ክፍል ማፅዳት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ።
"የሴቶች ብልት ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎችን ይዟል፤ ባክቴሪያዎቹ እርሱን ለመጠበቅ የተቀመጡ ናቸው " ሲሉ በመግለጫቸው አክለዋል።
በመሆኑም ብልትን መታጠን በውስጡ ያሉ ባክቴሪያዎች ላይ የጤና መናጋት ያስከትላል፤ የ'ፒ ኤች' መጠንንም ሊቀንስ ይችላል፤ ከዚህም ባሻገር ማሳከክ፣ መቆጣት፣ ማቃጠል እና ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።
ይህም ብቻ ሳይሆን በብልት አካባቢ ያለ ለስላሳ ቆዳ [vulva] ላይ ቃጠሎም ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።
• የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ?
በርካታ ሐኪሞችም ብልትን መታጠን የሚያስከትለውን ጉዳት ለማሳየት በካናዳዊቷ ሴት ላይ የሆነውን ሁሉ በተለያየ መልኩ እያጋሩት ይገኛሉ።
የእርሷን አጋጣሚ የጻፉት ዶ/ር ማጋሊ ሮበርት በበኩላቸው ሴትዮዋ በአንድ ቻይናዊ ዶክተር ምክር ብልቷን ለመታጠን ስትሞክር ጉዳቱ እንዳጋጠማት አስረድተዋል።
ይህች ታሪኳ ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን ለማጋራት ፈቃደኛ የሆነችው ሴት፤ ብልቷን ለመታጠን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለ20 ደቂቃዎች ያህል የሞቀ ውሃ ላይ ተቀምጣ ነበር ።
ያጋጠማት ጉዳትም ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ ሲሆን ከጉዳቷ ስታገግም ቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላት ተገልጿል።
በካልጋሪ ከእንብርት በታች ያሉ ክፍሎች ሕክምና የሚያደርጉትና የቀዶ ሕክምና ባለሙያው ዶ/ር ሮበርት እንዳሉት እንደ መታጠን ያሉ ልማዳዊ ህክምናዎች በኢንተርኔትና በወሬ የሚዛመቱ ናቸው ብለዋል።
" የጤና ባለሙያዎች ለሴቶች አማራጭ ሕክምናዎችን እንዳሉ ማስገንዘብ አለባቸው፤ ይህም ጠቃሚ የህክምና ዘዴዎችን እንዲመርጡ ያስችላቸዋል፤ ሊያጋጥማቸው ከሚችል ጉዳትም ይጠበቃሉ" ሲሉ በፅሁፋቸው ላይ አስያየታቸውን ሰጥተዋል።
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የጤና_መረጃ!!!

#በወር_አበባ ጊዜ መመገብ ያለብን እና መመገብ የሌለብን ምግቦች:
መመገብ ያለብን ምግቦች
• አረንጓዴ ቅጠላቅጠል
• ጥቁር ቸኮሌት
• ሙዝ
• የአሳ ስጋ
• ሀብሀብ
• ለውዝ
• በቂ ውሃ እና ፈሳሾችን መውሰድ
መመገብ የሌለብን ምግቦች:
• ቅባታማ ምግቦች
• የታሸጉ ወይም በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች
• ወተት ተዋጽኦ
• የተጠባበሱ ምግቦች
• ፒዛ፣ዳቦ እና የተቀነባበሩ የእህል ዘሮች
• ጨው የበዛባቸው ምግቦች
• ካፊን ያላቸው መጠጦች
• የአልኮል መጠጦች
መልካም ጤንነት!! ሼር
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#የሆድ_ድርቀትን

አስቸግሮሻል??

ዛሬ ማታ መፍትሄ

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
💋 #ስለ_ወንድ💋
#1 አንድ ወንድ ለትክክለኛ ምክንያት ክወደደሽ #sex አይፈልግም አንቺ
እስክትጠይቂው ድረስ

#2 አንድ ወንድ ከመደወሉ በፊት ምን እንደሚልሽ ያቅዳል

#3 ምንም ወንዶች ሰለ ዳሌ እና ጡትሽ ቢያወሩም personality
ወሳኝነት አለው

#4 ወንዶች ሰሜታዊ ናቸው ይደብቁታል እንጂ

#5 አንደ ወንድ በጭራሽ አይቶሽ የማያውቅ ከሆነ አይወድሽም ምናልባት ረጅም ጊዜ chat ካላረጋችሁ 8ወር+

#6 ወንዶች እውነተኛ ሴት ይወዳሉ

#7 ወንዶች ሁሌም ላንቺ ጥሩ ሰው ለመሆነ የሞከራሉ

#8 ወንዶች ከወደዱሽ ጉራ አያበዙም

#9 ወንዶች በቀላሉ ይቀናሉ

#10 ወንዶች በሴቶች ግራ የጋባሉ

#11 ወንድ ልጅ ሰታወሩ አይንሽን በጣም ካየሽ ያልተመቸው ነገር አለ

#12 ወንዶች ሴቶች ሲያለቅሱ ማየት አይወዱም

#13 ምንም ብር ባይኖራችውም ወንዶች የረከሰ ቦታ ሲወስዱስሽ ጥሩ
ስሜት አይሰማቸወም

#14 አብዛኛዎቹ ወንዶች ቆንጆ ሴት ሳይሆን ንጹህናዋን የምትጠብቅ እና
ለሰው የምትቀርብ አይነት ሴት የሚፈልጉት

#15 አንድ ወንድ አልተረዳሽም ሲልሽ ማለት የፈልገው እኔ እንደማሰበው
እያሰብሽ አይደለም ለማለት ፈልጎ ነው

#16 አንድ ወንድ የእውነት ከወደደሽ መጥፎ በህሪሽን በሙሉ የቀበልዋል

#17 ወንዶች በሴቶች ፈገግታ እጅጉን የማረካሉ

#18 ወንዶች እጃቸውን በሴቶች ሲነኩ ደስ የላችዋል

#19 ወንዶች እናታቸውን ይወዳሉ

#20 ወንድን ልጅ ችግሩን ሲነግርሽ ምክር ባትሰጪውም ችግር የለወም
የሚሰማው ሰዉ ብቻ ነው የሚፍልገው

#21 የሴቶች ቁመት ለወንዶች መንም ላይሆን ይችላል ክብደታቸው ግን
ትርጉም አለው
@onlyfemaleb
Brand ቀሚሶች,ጫማዎች,ተመሳሳይ ቦርሳ እና ጫማዎች,የወንድ ሡፎች,Cosmotics,humanhair ሁሉንም በአንድ ላይ ከታች ያለውን link በመጫን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Cherstinfashion
t.me/Cherstinfashion
0934722062
Brand ቀሚሶች,ጫማዎች,ተመሳሳይ ቦርሳ እና ጫማዎች,የወንድ ሡፎች,Cosmotics,humanhair ሁሉንም በአንድ ላይ ከታች ያለውን link በመጫን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Cherstinfashion
t.me/Cherstinfashion
0934722062
#አቢጊያ_ነኝ

#የወር_አበባሽ በሚመጣበት ወቅት የመጀመሪያ ቀን የጠቆረ ጉበት መሰል ደም ይፈስሻል???
አዎ

አይ ☑️
@onlygirlsb

#join
@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ
#የሆድ_ድርቀትን አስቸግሮሻል?? ዛሬ ማታ መፍትሄ @onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#የሆድ_ድርቀትን_ለመከላከል

#Like #Share #Leanchi_becha
የሆድ ድርቀት ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ ችግር ነው፡፡ የሆድ ድረቀት በአመጋገብ፤ በህመም ወይም በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የሆድ ድርቀት የሚከሰትበት ምክንያት አይታወቅም፡፡
የሆድ ድርቀት ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
 የሆድ ድርቀት ማለት በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መውጣት ማለት ነው፡፡
 በተጨማሪም የሆድ መነፋት፤የሆድ ቁርጠት፤ ሰገራ በምንወጣበት ጊዜ የሚሰማ ህመም እና የመሳሰሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፡፡
በተለይ ደግሞ ከሁለት ሳምንት በላይ ችግሩ ከቆየ ወይም ሰገራችን ውስጥ ደም ካየን ወይም ከድርቀት በተጨማሪ የሆድ ህመም ካለ ወደ ሀኪም ቤት መሄድ አለብን፡፡
ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን በመጠቀም የሆድ ድርቀትን ማስታገስ ወይም መከላከል ይቻላል፡፡ ከነዚህ ነገሮች መካከል
1. ውሃ መጠጣት፡- በሰውነታችን ውስጥ ያለው የውሃ መጠን ሲቀንስ የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ሴቶች በቀን ከ8-9 ብርጭቆ ውሃ እና ወንዶች ደግሞ በቀን ከ9-10 ብርጭቆ ውሃ ቢጠጡ ተብሎ ይመከራል፡፡
2. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦች መመገብ፡- በምግቦች ውስጥ የሚገኝ ፋይበር የሚባል ቃጫ መሰል ንጥር ነገር አለ፡፡ ፋይበር በሁለት ይከፈላል
 የማይፈጭ ፋይበር፡- ሳይፈጭ በሰውነታችን ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ሰገራን የማለስለስ እና ከበድ እንዲል እና ከሰውነታችን ቶሎ እንዲወገድ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡  የሚፈጭ ፋይበር፡- እንደዚህ አይነት ፋይበር በሚፈጭበት ጊዜ ከውሃ ጋር ይቀላቀል እና ጄል ወደሚመስል ነገር ሰውነታችን ውስጥ ይቀየራል፡፡ይሄም ሰገራችን በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳል፡፡
 ሁለቱም አይነት ፋይበሮች የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡
3. አፕል ወይም ፖም መመገብ፡-አፕል ውስጥ መፈጨት የማይችለው የፋይበር አይነት በብዛት ይገኛል፡፡ ይሄ አይነት ፋይበር ሰገራችን ቶሎ በሰውነታችን አልፎ እንዲወጣ ያግዘዋል፡፡ በተለይ አፕሉን ሳይላጥ መብላት ነው ያለብን፡፡
3. ቆምጠጥ የሚሉ ፍራፍሬዎች፡- ቆምጠጥ ያሉ ፍራፍሬዎች ማለት እንደ ብርቱካን፤ መንደሪን ወይም ግሬፕ ፍሩት ያሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ፍራፍሬዎች በሁለቱም አይነት ፋይበር የበለፀጉ ስለሆነ የሆድ ድረቀትን ለማስታገስ ይጠቅማሉ፡፡
4. አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፡- እንደ ሰፒናች፤ ብሮኮሊ የመሳሰሉት አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ከፋይበር በተጨማሪ ቫይታሚን ኬ፤ ቫይታሚን ሲ እና ፎሌት የመሳሰሉትን ለጤናችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ይዘዋል፡፡ በነዚህ አትክልቶች ውስጥ ያለው ፋይበር ሰገራን በማለስለስ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
5. ስኳር ድንች፡- አንድ መካከለኛ የስኳር ድንች በውስጡ 3.8 ግራም የሚያህል ፋይበር ይይዛል፡፡ ስለዚህ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ተመራጭ ምግብ ነው፡፡
6. ባቄላ፤ ምስር እና አተር፡- እነዚህ ጥራጥሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የምናገኛቸው ሲሆኑ የማይፈጨውን እና የሚፈጨውን ፋይበር በብዛት ይዘዋል፡፡
7. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሳምንት ውስጥ ለ3 ቀናት ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ማድረግ ሰገራ ከአንጀታችን ውስጥ ቶሎ እንዲያለፍ ይረዳዋል፡፡ ነገር ግን በጣም ከባድ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጠን ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ውሃ በደንብ መጠጣት ይኖርብናል፡፡
ማሳሰቢያ
የጨጓራ ህመም ካለብን ከላይ የተጠቀሱትን ምግቦች ለመመገብ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#የሆድ_ድርቀትን_ለመከላከል

#Like #Share #Leanchi_becha
የሆድ ድርቀት ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ ችግር ነው፡፡ የሆድ ድረቀት በአመጋገብ፤ በህመም ወይም በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የሆድ ድርቀት የሚከሰትበት ምክንያት አይታወቅም፡፡
የሆድ ድርቀት ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
 የሆድ ድርቀት ማለት በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መውጣት ማለት ነው፡፡
 በተጨማሪም የሆድ መነፋት፤የሆድ ቁርጠት፤ ሰገራ በምንወጣበት ጊዜ የሚሰማ ህመም እና የመሳሰሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፡፡
በተለይ ደግሞ ከሁለት ሳምንት በላይ ችግሩ ከቆየ ወይም ሰገራችን ውስጥ ደም ካየን ወይም ከድርቀት በተጨማሪ የሆድ ህመም ካለ ወደ ሀኪም ቤት መሄድ አለብን፡፡
ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን በመጠቀም የሆድ ድርቀትን ማስታገስ ወይም መከላከል ይቻላል፡፡ ከነዚህ ነገሮች መካከል
1. ውሃ መጠጣት፡- በሰውነታችን ውስጥ ያለው የውሃ መጠን ሲቀንስ የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ሴቶች በቀን ከ8-9 ብርጭቆ ውሃ እና ወንዶች ደግሞ በቀን ከ9-10 ብርጭቆ ውሃ ቢጠጡ ተብሎ ይመከራል፡፡
2. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦች መመገብ፡- በምግቦች ውስጥ የሚገኝ ፋይበር የሚባል ቃጫ መሰል ንጥር ነገር አለ፡፡ ፋይበር በሁለት ይከፈላል
 የማይፈጭ ፋይበር፡- ሳይፈጭ በሰውነታችን ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ሰገራን የማለስለስ እና ከበድ እንዲል እና ከሰውነታችን ቶሎ እንዲወገድ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡  የሚፈጭ ፋይበር፡- እንደዚህ አይነት ፋይበር በሚፈጭበት ጊዜ ከውሃ ጋር ይቀላቀል እና ጄል ወደሚመስል ነገር ሰውነታችን ውስጥ ይቀየራል፡፡ይሄም ሰገራችን በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳል፡፡
 ሁለቱም አይነት ፋይበሮች የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡
3. አፕል ወይም ፖም መመገብ፡-አፕል ውስጥ መፈጨት የማይችለው የፋይበር አይነት በብዛት ይገኛል፡፡ ይሄ አይነት ፋይበር ሰገራችን ቶሎ በሰውነታችን አልፎ እንዲወጣ ያግዘዋል፡፡ በተለይ አፕሉን ሳይላጥ መብላት ነው ያለብን፡፡
3. ቆምጠጥ የሚሉ ፍራፍሬዎች፡- ቆምጠጥ ያሉ ፍራፍሬዎች ማለት እንደ ብርቱካን፤ መንደሪን ወይም ግሬፕ ፍሩት ያሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ፍራፍሬዎች በሁለቱም አይነት ፋይበር የበለፀጉ ስለሆነ የሆድ ድረቀትን ለማስታገስ ይጠቅማሉ፡፡
4. አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፡- እንደ ሰፒናች፤ ብሮኮሊ የመሳሰሉት አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ከፋይበር በተጨማሪ ቫይታሚን ኬ፤ ቫይታሚን ሲ እና ፎሌት የመሳሰሉትን ለጤናችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ይዘዋል፡፡ በነዚህ አትክልቶች ውስጥ ያለው ፋይበር ሰገራን በማለስለስ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
5. ስኳር ድንች፡- አንድ መካከለኛ የስኳር ድንች በውስጡ 3.8 ግራም የሚያህል ፋይበር ይይዛል፡፡ ስለዚህ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ተመራጭ ምግብ ነው፡፡
6. ባቄላ፤ ምስር እና አተር፡- እነዚህ ጥራጥሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የምናገኛቸው ሲሆኑ የማይፈጨውን እና የሚፈጨውን ፋይበር በብዛት ይዘዋል፡፡
7. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሳምንት ውስጥ ለ3 ቀናት ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ማድረግ ሰገራ ከአንጀታችን ውስጥ ቶሎ እንዲያለፍ ይረዳዋል፡፡ ነገር ግን በጣም ከባድ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጠን ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ውሃ በደንብ መጠጣት ይኖርብናል፡፡
ማሳሰቢያ
የጨጓራ ህመም ካለብን ከላይ የተጠቀሱትን ምግቦች ለመመገብ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
ማማከር ምትፈልጉ 3 ሴቶች ብቻ
@onlygirlsb
ላንቺ ብቻ via @toolkitbot
#አቢጊያ_ነኝ #የወር_አበባሽ በሚመጣበት ወቅት የመጀመሪያ ቀን የጠቆረ ጉበት መሰል ደም ይፈስሻል??? አዎ አይ ☑️ @onlygirlsb #join @onlyfemaleb
እናንተም እንዳረጋገጣቹልኝ እኔም እራሴ ላይ እንደማየው።

የወር አበባ በሚመጣበት ወቅት የመጀመሪያ ቀን የጠቆረ ጉበት መሰል ደም ለምን ይወጣል

ይህ በብዙዎች ላይ የሚታይ ነገር ነው ። አንዳንዶቹ ተፈጥሮአዊ ስለማይመስላቸው የጤና ችግር እንዳለባቸው አድርገው ሲወስዱትና #በጭንቀት ሲሰቃዩ ይስተዋላል ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ካደረጉት ግንኙነት የተነሳ እርግዝና ተፈጥሮ ድንገት ፅንስ የወረደ ይመስላቸዋል ። ነገር ግን ይህ ቀይ ጉበት የመሰለ ጥቁር ደም ከሁለቱም አይደለም ።

#እና_ምንድን_ነው?

ተብላልቶ የነበረው እንቁላል የወንድን የዘር ፈሳሽ ባለማግኘቱ ይበላሻል ይህ የተበላሸው እንቁላል የወር አበባ ይህን መልክ እንዲይዝ ያደርገዋል ። በእርግጥ ጠረን ያለው ከሆነ ፣ የእመም ስሜቱ ከፍተኛ ከሆነ ኢንፌክሽን ሊሆን ስለሚችል መታየት ያስፈልጋል ።
@onlyfemaleb
ስራ ማስታወቂያ

ነርሲንግ እና ፋርማሲ
በ ዜሮ አመት

እና ሌሎችም

@onlygirlsb