ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
@Sellers and buyer
@ዱባይ ገበያ
@ available on hand
contact @Elu_jo
https://t.me/joinchat/AAAAAEPylbBjUwNq9_KGHQ
በዓል እንዴት እያለፈ ነወ?

@onlygirlsb

ንገሩኝ እስኪ
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስታይልሽ እንዴት አይነት ነው?

🎀ሚኒስከርት ይመችሻል?

🎀ሱሪ ነው ምታዘወትሪው?

🎀ብራስሌት ደስ ይልሻል?

🎀የራስሽ ምርጫ የሆኑ ጌጣጌጦች አሉሽ?
ለማንኛውም ምርጧ ሴት የሚያምርባትን የምታውቀዋ ናት። ስለዚህ አንዲት ጠንካራ ሴት እንደምታደርገው ለውጫዊ አስተያየት ደንታ ሳይኖርሽ ራስሽን መግለፅ አለብሽ።

እመኚኝ፡ መጪው ጊዜ አሪፍ ነው።

#share @onlyfemaleb
#ጤናሽ

ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ጠቃሚ የሆኑ 5 የምግብ አይነቶች

በአለማችን 350 ሚልዮን ሰዎች በጭንቀትና በድብርት እንደሚጠቁ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡ የተለያዩ ቫይታሚን፣ ንጥረ ነገሮችን (Minerals)፣ ጤናማ የቅባት አይነት የያዙ ምግቦች እንዲሁም ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ያግዛሉ ይላል #የሜዲካል_ዴይሊ_ዘገባ፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱት የምግብ አይነቶች ከጭንቀትና ድብርትን ከማስወገድ ባሻገር ለጤናማ አእምሮ ስርዓትም አጋዥ ናቸው፡፡

1⃣ የዕህል ምግቦች

ሴሮቶኒን (Serotonin) የተሰኘው ንጥረ ነገር ንቁ እንዲንሆንና ዘና እንድንል የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ሜላቶኒን ደግሞ ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓት አንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የዕህል ምግቦች ሴሮቶኒን እና ሜላቶኒን በአግባቡ በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖር በማድረግ ጭንቀትና ድብርትን ለመቀነስ ድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡

2⃣ ኮሮሪማ

ኮሮሪማ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርግ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የተሰኘ (Antioxidants) በውስጡ ይገኛል፡፡ በተለይም ኮሮሪማን በጥሬው መመገብ ከጭንቀትና ድብርት በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያግዝ ዘገባው ያስረዳል፡፡

3⃣ እንጆሪ 🍓

እንጆሪን መመገብ እራስን እስከማጥፋት ድረስ የሚያደርሰውን የጭንቀትና የድብርት አይነት ጭምር ለማስወገድ ጠቃሚ መሆኑን በቅርቡ የተደረገ ጥናት ያትታል፡፡ እንጆሪ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጨምሮ በቫይታሚን ሲ የበለጸገ በመሆኑ ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ተመራጭ ምግብ መሆኑን ዘገባው ገልጿል፡፡

4⃣ እርጎ 🥤 እና እንቁላል 🥚

እርጎና እንቁላል ጭንቀትና ድብርትን ማስወገድ የሚችሉ ምጣኔያቸውን የጠበቁ የፕሮቲንና የካርቦሃይድሬት ምጣኔ ያካተቱ የምግብ አይነት ናቸው፡፡ እርጎና እንቁላል የደም ስኳር መጠን ሚዛኑን ጠብቆ እንዲሄድም በማድረግም ጭምር ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ሚናቸውን ይወጣሉ፡፡

5⃣ ጥቁር ቸኮሌት 🍫

ጥቁር ቸኮሌት ዶፓማይን (Dopamine) የተሰኘ አይምሮዋች የደስታ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ ንጥረ ነገር አካቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የደስታ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገውን እንዶሮፊንስም (Endorphins) ጭምር በውሰጡ ይገኛል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሰውነታችንን የኮሊስትሮል መጠን የመቀነስ ሚናም ሲለሚጫወት ጭንቀትና ድብርትን የማስወገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የሜዲካል ዴይሊ ዘገባ ያስረዳል፡፡

♨️ ለሌሎች ሼር ያድርጉ❗️
@onlyfemaleb
BOSS COLLECTION
High quality products
Contact @janajan1
Call 0921273990
https://t.me/BOSS_COLLECTION
#አቢጊያ_ነኝ
👩🏽‍🦰👱🏽‍♀️የፀጉር መርገፍ👱🏽‍♀️👩🏽‍🦰

የፀጉር መርገፍ በጭንቅላታችን ላይ ያለን ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ አካላቶቻችን ላይ ያለን ፀጉር ያጠቃልላል፡፡

ለዛሬ የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን እና የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡

#መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

👉🏾 በዘር፡- ሴቶች ላይ የፀጉር መሸሽ እና መሳሳት
👉🏾 ሰውነታችንን በሚያጠቁ በሽታዎች፡- የታይሮይድ ህመሞች፣ የካንሰር ህመሞች
👉🏾 መድሃኒቶች፡- የካንሰር ህክምናዎች
እጅግ በጣም የሚያጠብቅ ሹሩባ
👉🏾 የአእምሮ ጭንቀት
👉🏾 ለፀጉር እድገት የምንጠቀማቸው ግብአቶች

ስለመንስዔው ማወቅ የፀጉር መርገፍን እንዴት መከላከል እንዳለብን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል፡፡

🗒 #ፀጉራችን ከመርገፉ በፊት የምናያቸው ምልክቶች...🗒

-የፀጉር መሳሳት
-በአንዳንድ የፀጉራችን ክፍል ውስጥ ባዶ የሆኑ ቦታዎች መኖር
-ፀጉራችንን በምናበጥርበት ወይም በምንታጠብበት ጊዜ የሚታይ የፀጉር መርገፍ

የፀጉር #መርገፍን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያሉብን ነገሮች

-ለፀጉር የምንጠቀማቸው ግብአቶች ከተፈጥሮ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ
-ሹሩባ በምንሰራበት ወቅት ላላ አድርጎ መሰራት
-ጭንቀታችንን ለቅርብ ለምንለው ሰው ማውራት
-በበሽታዎችና በመድሃኒቶች የሚመጡ የፀጉር መርገፎችን ከሃኪማችን ጋር በመነጋገር ማስተካከያዎችን ማድረግ
-እንደ ፊታችን ሁሉ ፀጉራችንንም መንከባከብ

ፀጉራችንን እንዴት #መንከባከብ ይኖርብናል?

👉🏾 #ማንኛውም ነገር ለማደግ ግብአት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለፀጉርም ግብአት ያስፈልጋል፡፡ ፀጉራችንን በንፅህና መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚመቸንን ሻምፖ እና ኮንዲሽነር በመሞከር ፀጉራችን ላይ የሚመጣውን ለውጥ ማስተዋል፤ የምንጠቀማቸው ግብአቶች ሰልፌት የሌላቸው መሆኑን በእቃው ላይ የሚፃፈውን ንጥረ ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡

👉🏾 #ለፀጉራችን የሚስማማንን ቅባት መለየት፤ ፀጉር ከሰው ሰው ስለሚለይ እኛም ለፀጉራችንን የሚስማማንን ፀጉር በምናየው ለውጥ መወሰን ይኖርብናል፡፡
ለፀጉራችን ቢያንስ በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ማለትም አቮካዶ፣ እርጎ፣ ቅቤን ፀጉር ላይ በመቀባት መንከባከብ ይኖርብናል።

@onlyfemaleb

#join #join #join

በቀጣይም ብዙ የጤና መረጃዎችን እነግርሻለው።
ላንቺ ብቻ
Photo
#አቢጊያ_ነኝ

#የቆዳ_ሸንተረርን_ማጥፋት_ይችላል ?
ሁሉም ሰው የቆዳ ሸንተረር ቢጠፋልኝ ብሎ ያስባል። ቆዳ ላይ የሚፈጠር ሸንተረር ጤና ላይ የሚፈጥረው ችግር ባይኖርም ለእይታ አይስብም።
የቆዳ ሸንተረር ሙሉ በሙሉ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ነገር ግን ከግዜ በኋላ ትልቀቱ እየቀነሰ ይመጣል።

#መንስኤዎች
ሸንተረር የሚፈጠረው ቆዳችን በፍጥነት በሚያድግበት ግዜ ነው። ሰውነት በሚያድግበት ፍጥነት ቆዳ አብሮ መለጠጥ ሲያቅተው ሸንተረር ይፈጠራል። እነዚህ ሸንተረሮች በህክምናው ቋንቋ ስትሪያ(stria) ተብለው ይጠራሉ።
ኮላጅን ቆዳ ተላጣጭ እንዲሆን የሚረዳ ፕሮቲን ነው። ቆዳ በቂ ኮላጅን ከሌለው በሚለጠጥበት ግዜ ሸንተረር ይፈጠራል።
የሚከተሉት ምክንያቶች የሸንተረር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፦
#በፍጥነት ክብደት መጨመር
#እርግዝና
#ሰውነትን ማጎልመስ
#ከፍተኛ የሰውነት ስቴሮይድ
#ሸንተረር በዘርም የሚተላለፍ ክስተት ነው።

#ማን_ላይ_ይከሰታል ?
ሸንተረር ይበልጥ በሴቶች ላይ ይፈጠራል። በተለይ በእርግዝና ግዜ። በልጅ ምክንያት ሆድ ሲለጠጥ ሸንተረር ሊወጣ ይችላል።
ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ ክብደት ስትቀንስ ሸንተረሩ አብሮ ሊቀንስላት ይችላል።
ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ጭማሪ የሚያመጡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል። በልጅነት እድሜም ልጆች በፍጥነት በሚያድጉበት ግዜ ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል።
ሸንተረር በሚከተሉት የሰውነት አካላት ላይ ሊፈጠር ይችላል፦
#እጅ
#ጀርባ
#ጡት
#መቀመጫ
#ዳሌ
#ትከሻ
#ሆድ
#መፍትሄዎች
ሸንተረርን ያጠፋሉ ተብለው የሚሸጡ በርካታ ክሬሞች እና መድሃኒቶች አሉ። ውጤታማነታቸው ግን አጠያያቂ ነው።
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የእከክ_በሽታ_መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች
እከክ በአይን የማይታዩ “ሳርኮፕተስ” በሚባሉ ተዋስያን አማካኘነት የሚመጣ የቆዳ በሽታ ነው፡፡
ይህ የቆዳ በሽታ በበሽታው ከያዘው ጋር በጋራ ልብስ መልበስ፤በጋራ በመተኛትና እንዲሁም በንኪኪ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ሊተላለፍ የሚችል በሽታ ነው፡፡
የበሽታው ምልክቶች
-በከፍተኛ ሁኔታ የማሳከክና በቆዳ ላይ ሽፍታን ማሳየት
-ማሳከኩም በተለይ ማታ ላይ ያይላል
-የበሽታው ነብሳት በቆዳችን ውስጥ ለመራባት በሚመቻቸው ትንሽ መስመር ውስጥ እንቁላል በመጣል ይራባሉ፡፡
በመሆኑም እንቁላሉ ወደ ላይኛው ቆዳ ላይ በመውጣት ትናንሽ መግል የያዘ ሽፍታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
የሚያሳክኩት የሰውነታችን ክፍሎችም፡-
 ብብት
 በየመገጣጠሚያ አካላት
 በክርን
 ተረከዝ
 ጡት እና
 በመራቢያ አካላትና ጉልበት አካላ አካባቢ ነው፡፡
በህጻናት ላይ ደግሞ
 በጸጉር ቆዳ፤በፊት ላይ፤አንገት፤እጅና እግር አከባቢ በከፍተኛ ይከሰታል፡፡
የእከክ በሽታን ባለመታከም ምክንያት ሊደርሱ የሚችሉ በሽታዎች
 እከክን ባለመታከም ሌሎች በተለያዩ ባክቴሪያዎች የሚመጡ ለቆዳ በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል
 በተጨማሪም የበሽታ መከላከል አቅማቸው አናሳ/ የወረደ ሰዎች፤ ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ እና ካንሰር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ በአስከፊ ሁኔታ ሙሉ የሰውነት ቆዳን ሊያዳርስ ይችላል፡፡
#በሽታውን ለመከላከል
• ከቤተሰብ ውስጥ ቀድሞ የተያዘውን ሰው ቶሎ ማሳከም
• ልብስ በጋራ/ተቀባብሎ አለመልበስ
• በበሽታው የተያዘ ሰው ታክሞ እስከሚድን ድረስ የአካል ንክኪ አለማድረግ
• የእከክ በሽታ ከታከምን በቀላሉ ሊያድን ቢችልም በሃኪም የተሰጡን መድሓንቶችና ተያያዥ ምክሮች በአግባቡ መጠቀም/ ስራ ላይ መዋል ይገባል፡፡

@onlyfemaleb

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስለ #ብልት መታጠን መረጃ
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#የማህፀን_ውስጥ_እጢ

የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለው የማሕፀን ውስጥ ዐዥባጭ
ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡ የማህፀን ውስጥ ዕጢ
ወደ ማኅፀን ካንሰርነት የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ከማሕፀን ግድግዳ ጡንቻዎች የሚነሳ ሲሆን የሴሎች ጤናማ ባልሆነ
ሆኑታ ሲከፈሉ የሚመጣ ሆኔታ ነው፡፡ ይህ የማሕፀን ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ ወይንም
በዝግታ የሚያድግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመልሶ በራሱ ሊጠፈም
ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ በሴቶች ላይ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ምክንያት ከ4 ሴቶች ሦስቱ
በሕይወት ዘመናቸው የማሕፀን ዕጢ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን
ምልክት ስለማያሳዩ እንዳላቸውም የማወቅ ዕድል የላቸውም፡፡ በአብዛኛው የሚገኘው
በድንገት በሚደረግ ምርመራ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ምልክቶች
የማኅፀን ዕጢ በአብዛኛው ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች
ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እንዚህ ናቸው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ መብዛት
• ከሰባት ቀናት በላይ የሚቆይ የወር አበባ ማየት
• ማሕፀን አካባቢ ግፊት መሰማት ወይንም ሕመም
• ቶሎ ቶሎ የውሃ ሽንት መምጣት
• የሆድ ድርቀት
• የጀርባ እና የዕግር ሕመም ስሜት
• አልፎ አልፎ ከፍተኛ የሆነ ሕመም (አጣዳፊ) የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሚሆነው
የደም ዝውውር በሚቀንስ ጊዜ/በሚቋረጥ ጊዜ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ለምን ይከሰታል
ይህ ነው የሚባል ዕርግጥ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ጥናቶች የሚያመለክቷቸው
ከሆርሞኖች እና የጀኔቲክ ሁኑታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ነው፡፤
ለማሕፀን ዕጢ ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች
• ከዘር፡- እናት ወይንም እሕት የማሕፀን ዕጢ ወደ ዘር ካላቸው ተጋላጭነትን
ይጨምራል፡፡
• ጥቁር ዘር፡- ጥቁር ሴቶች በአብዛኘው ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡
• በልጅነት የወር አበባን ያዩ ከሆነ እና አመጋገብ ናቸው፡፡
የማኅፀን ዕጢ ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ ባይሆንም የደም ማነስ እና ምቾት
ማጣትን ግን ሊያስከትል ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ እና እርግዝና
የማሕፀን ዕጢ በአብዛኛው እርግዝናን የማይቃረን ቢሆንም አንዳንዴ ዕጢው
በሚገኝበት ቦታምክንያት በጥቂት ሰዎች ላይ እርግዝናን እንዳይፈጠር መንስዔ
ይሆናል፡፡ ይህ በመሆን ጊዜ ሐኪምን በማማከር ከእርግዝና በፊት መደረግ ያለባቸውን
ቅድመ ሆኔታዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• የማያቋርጥ የማሕፀን አካባቢ ሕመም ካለ
• ከፍተኛ ሕመም ያላቸውና በብዛት የሚያስቸግሩ የወር አበባ ጊዜያት
• ከወር አበባ ፅዳት ውጪ የደም መፍሰስ
• በግብረ ስጋ ግኝኑነት ጊዜ የሕመም ስሜት ከተሰማዎተግ
• የሆድ ዕብጠት ካለዎዘ
• የውኃ ሽንትን ማስወገድ መቸገር
እጅግ ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ የማኅፀን አካባቢ ሕመም ካለዎትና ከፍተኛ የደም መፍሰስ
የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
Forwarded from Najwa
Najwa Henna design
💐You think it, I ink it
Henna is the expression of beauty without wordsLet me make you glow on special day for
Wedding👰
Nikah💍
Parties 💃
Birthdays 🎂
Holliday's....for more information you can contact me by this no 0923776030
@NajwaNasir
https://t.me/hennabynajwa
#አቢጊያ_ነኝ

#በወሲብ_ወቅት_ብልቴን_ያቃጥለኛል_ያመኛል_ይቆስላል_ይላላጣል

እድሜዬ 25 ሲሆን የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ነበረን፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ በግንኙነት ጊዜ ከእኔ ብልት የሚወጣው ፈሳሽ አይወጣም ነበር፡፡ ይህን ተመርምሬ መድሃኒቱን ተከታትዬ ለተወሰነ ጊዜ ተሻለኝ፡፡ ቀጥሎ የጓደኛዬ ብልት ብልቴ ውስጥ ሲገባ ያቃጥለኛል፣ ያመኛል፣ ይቆስላል፣ ይላላጣል፣… ለአንድ ዓመት እንደዛ ሆነብኝ፡፡ ከዛ ተመርምሬ ዶክተሩ (ሐኪሙ) ይህን ችግር ሊያስከትልብሽ የቻለው ማህፀንሽ ውስጥ ዕጢ ስላለ ነው አለኝ፡፡ ይህን እጢ ሳታስወጭ መፀነስ የለብሽም፡፡ ዕጢውን ካስወጣሽ በኋላም ለመፀነስ ሐኪምን ማማከር አለብሽ ተባልኩኝ፡፡ የኔ ጥያቄ ታዲያ፡-
#1 . ማህፀን ውስጥ ዕጢ ሊፈጠር የሚችለው እንዴት ነው?
#2 . በግንኙነት ጊዜ የሚቆስለው የሚላጠው ዕጢው ሲወጣ ይተውሻል ብላችሁ ታምናላችሁ?
#3 . ከቀዶ ጥገና በኋላ እንደፈለጉ ግንኙነት ማድረግ እና ያለስቃይ ልጅ መውለድ ይቻላል? ይህን ሁሉ የምላችሁ ፍቅረኛዬን ማጣት ስለማልፈልግ ነው፡፡ የማይሆን ከሆነ እወደዋለሁ ግን ምን ላድርግ?
#ምላሽ_ዛሬ_ማታ

#ከዶክተር_አንደበት

@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ
#አቢጊያ_ነኝ #በወሲብ_ወቅት_ብልቴን_ያቃጥለኛል_ያመኛል_ይቆስላል_ይላላጣል እድሜዬ 25 ሲሆን የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ነበረን፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ በግንኙነት ጊዜ ከእኔ ብልት የሚወጣው ፈሳሽ አይወጣም ነበር፡፡ ይህን ተመርምሬ መድሃኒቱን ተከታትዬ ለተወሰነ ጊዜ ተሻለኝ፡፡ ቀጥሎ የጓደኛዬ ብልት ብልቴ ውስጥ ሲገባ ያቃጥለኛል፣…
#የዶ/ር ምላሽ 👆👆👆👆
በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ሆነም ከግንኙነት በፊት ወይም በኋላ በብልትና አካባቢው የሚሰማ ህመም በህክምናው Dys-pareunia በመባል ይታወቃል፡፡ የዚህ ህመም ስሜት ከመጀመሪያው የግብረ ስጋ ግንኙነት ጀምሮ የሚሰማ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመሩ ከብዙ ጊዜያቶች ያለ ህመም ከቆየ በኋላ የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት በማንኛውም ጊዜና ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲመጣ ወይም አልፎ አልፎ ሊከሰት የሚችል የበሽታ አይነት ነው፡፡
ምክንያቱም ከብልትና አካባቢው (ከማህፀን ጭምር) በሚኖሩ ችግሮች እና ከስነ ልቦና ችግር ጋርም የመያያዝ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፡፡
ለዚህ ችግር ተጠያቂ ምክንያቶች ተደርገው የሚነሱ ጉዳዮች፡-
– የሴት ልጅ ግርዛት፣
– የማህፀን በሽታ (ኢንፌክሽን)
– ያረጡ ሴቶች
– የጭንቀት በሽታ
– የድብርት በሽታ፣ እና
– በልጅነት ዕድሜ የተከሰተ የፆታ ጥቃት ወይም አስገድዶ መደፈርን የመሳሰሉ ናቸው፡፡
የዚህን በሽታ ምክንያቶች ዘርዘር አድርገን ስንመለከት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ Vestibulsodyria የተባለው የበሽታ አይነት ሲሆን ከ50 ዓመት በላይ በሆኑት ላይ ደግሞ የብልት መሳሳት (Vulvavaginal atrophy) ይህንን የህመም ስሜት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ያስከትላሉ፡፡
ተራ በተራ የዚህን በሽታ ምክንያቶች እስከ ህክምናቸው ስናይ፡-
1. Vaginismus:- የዚህ ችግር መንስኤ አንዲት ሴት የብልቷና አካባቢ ጡንቻ ሳታስበው በሚፈጠርባት መኮማተር የሚያስከትለው ነው፡፡ ለዚህ ችግርም የስነ ልቦና ችግር እንደ ምክንያት ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ የዚህች ሴት የብልት አካባቢ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት በሚነካበት ወይም የወንዱ ብልት ወደ ብልቷ ሊገባ ሲል የብልቷ ጡንቻዎች ይኮማተራል ወይም ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ አካባቢም ሳይነካ ይህ ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ህክምናውን በተመለከተ ቀስ በቀስ የብልትና አካባቢውን ጡንቻዎች አዕምሮን በማዘዝ ለማላላት በመሞከር የሚደረግ የህክምና አይነት ነው፡፡ በዚህም የብልትን ጡንቻዎች ወይም በብልት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ቀስ በቀስ በአዕምሮ እንዲታዘዙ ማድረግ ስለሚቻል በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜትን መቆጣጠር ይቻላል፡፡
ሌሎች ህክምናዎች ደግሞ Sex therapy የሚባለው የህክምና አይነት ሲሆን ህመሙን ለማለዘብ ጓደኛሞች ቀስ በቀስ ግብረስጋ ግንኙነቱን እንዲያላምዳት ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ጊዜ የጓደኛዋ ብልት ቀስ እያለ ወደ ብልቷ እንዲገባ በመርዳት በሂደት የሚከናወን ድርጊት ሲሆን ወንዱም ያለመ ሰላቸት የሚያከናውነው መሆን ያለበት የህክምና አይነት ነው፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚወሰድ የጡንቻን መላላት የሚያመጣውን መድሃኒት መጠቀም ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህንንም ከሐኪም ጋር በመወያየት መጠቀም ይቻላል፡፡
2. Vulvar vestibulodynia:- ይህም ችግር ልክ እንደ ከላይ እንዳለው አይነት በሽታ ሲሆን ምክንያቱ ግን ተደጋጋሚ የብልት ኢንፌክሽን ወይም አደጋ የሚያስከትለው የበሽታ አይነት ነው፡፡ ህመሙ የሚመጣው የብልት አካባቢ ሲነካ ብቻ ነው፡፡ የላይኛው ግን ሳይነካም ሊመጣ ይችላል፡፡
ህክምናውም የግብረስጋ ከመፈፀም በፊት (ከ10 ደቂቃ በፊት) እና ከፈፀሙም በኋላ የሚቀባ ቅባት በመጠቀም ከህመሙ መላቀቅ ይችላል፡፡ የዚህ ቅባት ስም ዛሎኬን ይባላል፡፡ ወይም ከዚህ ላቅ ያሉ የመድሃኒት አማራጮችን በመርፌ የሚሰጥ መድሃኒት በባለሙያ እርዳታ በብልት አካባቢ በመወጋት ህመሙን መቀነስ ይቻላል፡፡ ይህም በመጀመሪያው ቀን፣ ከሳምንት በኋላ እንደገና ከ15 ቀን በኋላ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ስለሚኖሩ በዚህ አይነት በሽታ የተጠቁ ሴቶች የማህፀን ሐኪምን እርዳታ መጠየቅ አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ምክሮች፡-
– የብልትን አካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣
– ላላ ያለና አለርጂ የማይፈጥር ፓንትና ልብስ ማድረግ፣ ከጥጥ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
– ሽታ፣ ቀለማቸው የሚለቅ፣ ኬሚካል ያላቸውን ልብሶች አለመልበስ፣
– የብልትን አካባቢ ሊጎዱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ብስክሌት መንዳት ማቆም፣
– የብልት ፈሳሽ የሚያስቸግራቸው ሴቶች ፓድ ከማድረግ የውስጥ ሱሪያቸውን ቶሎ ቶሎ መቀየር ይጠበቅባቸዋል፣
– የብልት አካቢን ሞቅ ባለ ውሃ መዘፍዘፍና በተለይም የብልት አካባቢ ድርቀት የሚታይባቸው ከሆነ፣
– የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚደረግበት ጊዜ የአትክልት ዘይት መቀባትም ድርቀቱን ሊያስወግድ ይችላል፣
– የተሰባበረ በረዶ በላስቲክ በማድረግ ብልት ላይ ማድረግ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሚከሰተውን የብልት ማቃጠል ሊያስወግድ ይችላል፡፡
– Oxolate የተባለውን ቅመም የያዙ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬዎች አትክልቶችንና ጥራጥሬዎችን ከምግቦቻቸው ላይ መቀነስ፡፡
1. Vulvovaginal atrophy (የብልት መሳሳት)
ይህ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት ወይም ባረጡ ሴቶች ላይ ይታያል፡፡ ምክንያቱም ኤስትሮጅን የተባለው ሆርሞን እጥረት ሲሆን፣ በዚህ እጥረት የብልት አካባቢ ቅባት ይቀንሳል፡፡ ስለሆነም የብልት አካባቢ መድረቅ ይከሰታል፡፡ በዚህም የተነሳ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ይሰማል፣ የብልት አካባቢ ያቃጥላል፣ የብልት መቁሰልና ከግንኙነትም በኋላ መድማት ይታያል፡፡ የኤስትሮጅን ቅባት በቀን አንድ ጊዜ ለአራት ሳምንታት መቀባት ያስፈልጋል፡፡
2. በቂ የብልት ቅባት አለመኖር
በቁጥር 3 እንዳየነው ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ የሚታይና በቂ የስሜት አለመነሳሳት፣ ከጓደኛ ጋር በተለያየ ምክንያት አለመጣጣም ወይም ያልተፈታ የስነ ልቦና ችግር ሲኖር የአንዳንድ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ችግሮች (የደም ግፊት፣ የድብት በሽታ መድሃት እና ሌሎችም) ይህንን ችግር ያስከትላሉ፡፡
መፍትሄዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ ያሉትንና አጋላጭ ችግሮችን ማስወገድ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት የሚደረግ የፍቅር ጨዋታ ያስፈልጋል፡፡
3. የፊኛና የኩላሊት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- በባለሙያ እርዳታ በመታገዝ ህክምና ማድረግ
4. የብልት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- የብልት ፈንገስ በሽታ ወይም ሌላ የብልት በሽታ መኖር፣ የብልትና አካባቢው ፈሳሽ መኖር፣ መቁሰል፣ ማቃጠል፣ ማሳከክ ሌሎችም ምልክቶች ይኖራሉ፡፡ ህክምና ሳይደረግ የሚፈፀም ግንኙነት ህመም ያስከትላል፡፡ በባለሙያ እርዳታ ህክምና ማድረግ ለበሽታውም ለህመሙም መፍትሄ ያስገኛል፡፡
5. በወሊድ ጊዜ የሚደረግ የብልት መቆረጥ ወይም መለጠጥ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህም ችግር በቀዶ ጥገና መስተካከል አለበት፡፡
6. የማህፀን ዕጢ፡- የማህፀን ዕጢ ያላቸው ሴቶች ከሌላቸው ሴቶች ጋር ሲነፃፀሩ በግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በተለይ ትልቅ የሆነና በማህፀን ጀርባ አካባቢ የወጣ ዕጢ ከሆነ የማህፀን ዕጢውን ማውጣት ከዚህ ችግር ያድናል፡፡
7. የስነ ልቦና ችግር ያላቸው ሴቶች በዚህ ህመም ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተለይ የተቃራኒ ፆታ ጥቃት ከደረሰባቸው፣ በቂ እውቀት (ስለ ግንኙነት) የሌላቸው ከሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት የተሳሳተ ግምት ካላቸው ለዚህ ሰዎችም የስነ ልቦና ህክምና፣
#አቢጊያ_ነኝ

#ጡትዎን_በራስዎ_የመመርመ_ዘዴ
እራስ በራስ ጡትዎን በየጊዜዉ የሚያዩና የሚከታተሉ ከሆነ እራስ በራስ ጡት የመመርመር ዘዴ ይባላል፡፡ ስለጡትዎ ያለዎትን ግንዛቤ ለመጨመር አይንዎንና እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን በመዳሰስና በማየት በቀላሉ ጡትዎ ላይ ያሉ ለዉጦችን መለየት ይችላሉ፡፡
ለምን ይህን ማድረግ ያስፈልጋል?፡ጡትዎን እራስዎ መርምረዉ መገንዘብ ጥቅሙ የጡትዎን ኖርማል/ትክክለኛ የሆነዉን ይዘትና ሁኔታ ለማወቅ ስለሚረዳ ነዉ፡፡ጡትዎ ላይ ትክክለኛ ነገር ያልሆነና የተለወጠ ነገር ካጋጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስለሚያስችልዎትም ነዉ፡፡
የጡት ካንሰርን ጨምሮ የጡትዎን ሁኔታ ሊለዉጡ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እራስን በራስ ጡትን የመመርመር ዘዴ የጡት ካንሰርን ለማወቅ/ለመመርመር የሚተማመኑበት ሁነኛ መንገድ/ዘዴ አይደለም፡፡ ይሁንና ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑ ሴቶች ሪፖርት እንዳደረጉት ከሆነ የጡት ካንሰር የመጀመሪያዉ ምልክት የሆነዉ የጡት ዉስጥ እብጠት/ሴቶች እራሳቸዉ ጡታቸዉን በሚዳብሱበት ወቅት የተገኘ ነዉ፡፡በዚህ ምክንያት የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች የሚመክሩት ሴቶች ኖርማል የሆነዉን የጡታቸዉን ይዘት እንዲያዉቁ ነወ፡፡
እጅዎትን በሰዉነትዎ በጎን በኩል በማድረግና ከወገብ በላይ ራቁት በመሆን በመስታወት ፊት መቆም፡፡ ከዚያን ጡትዎ ላይ የሚከተሉትን ነገሮች/ለዉጦች ካሉ ማየት
• ወደፊት ዘምበል በማለት ጡት ላይ የመሸብሸብ፣ የመሰርጎድ፣የመጠን የቅርፅና በሁለቱ ጡት መካከል የመጠን ልዩነት መኖሩን
• የጡት ጫፍዎ ወደዉስጥ መግባት ያለመግባቱን
• ሁለቱን እጅዎን በዳሌዎ ላይ በመጫን ጡትዎን ማየት/መመርመር
@onlyfemaleb
• እጅዎን ከራስዎ በላይ ከፍ በማድረግና ሁለቱን መዳፍና መዳፍዎን አንድ ላይ መጫን
• ጡትዎን ወደላይ ከፍ ማድረግና በታች በኩል ያሉት የጡት ጠርዞች በሁለቱም በኩል ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ
ከዚያን እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን መመርመር፡ ብዙዉን ጊዜ የሚመከሩ ዘዴዎች
• መንጋለል፡- በጀርባዎ ለመተኛት እንዲመችዎ በአልጋ ላይ ወይም ለጥ ያለ ቦታ መምረጥ
• በሻወር ወቅት፡- ጡትዎንና ጣትዎን ሳሙና በመቀባት በደንብ እንዲያሟልጭ በማድረግ በቀላሉ በቆዳዎ ላይ እንዲሸራተት ማደረግ
ጡትዎን በሚዳስሱበት/በሚመረምሩበት ወቅት ሊከተሉት የሚገባ ምክር
@onlyfemaleb
• የእጅዎን መዳፍ መጠቀም
• ጡትዎን በሚመረምሩበት ወቅት በተለያየ ደረጃ መጫን(አንዳንዴ በስሱ ሌላ ጊዜ በደንብ ጫን በማድረግ)
• በደንብ ጊዜ ወስዶ መመርመር
• የሚመረምሩበትን ዘዴ/ንድፍ አዉቆ መከተል
ዉጤት
በወር አበባ ዑደት ወቅት የሚከሰቱ ለዉጦች ብዙዎቹ ኖርማል ናቸዉ፡፡ በጡትዎ ላይ ለዉጥ ወይም የሆነ እብጠት/የጠጠረ ነገር ቢያገኙ መደናገጥ የለብዎትም፡፡ በጡትዎ የታችኛዉ ጠርዝ ላይ የሚታዩ ጠንከር ያሉ ነገሮች እምብዛም የሚያሳስቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ እድሜዎ በጨመረ ቁጥር የጡትዎ ሁኔታ እየተቀየረ ይመጣል፡፡
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያለብዎ መቼ ነዉ?
@onlyfemaleb
• በጡትዎ ላይ ጠንካራ/ጥጥር የሆነ እብጠት ወይም በብብትዎ ስር ጥጥር የሆነ እብጠት ካለ
• ጡትዎን ሲዳስሱት ወይም ሲያዩት የተለወጠ ከመሰለዎ፡- የመወፈር፣ በዙሪያዉ ካለዉ አካል በተለየ ሁኔታ ማበጥ/መለየት ካለዉ
• የሰረጎደ፣የተሸበሸበ፣ያበጠ ወይም ጠርዝ ያወጣ ነገር በጡትዎ ላይ ከተመለከቱ
• በቅርቡ የተከሰተ ወደ ዉስጥ የገባ የጡት ጫፍ
• የመቅላት፣የመሞቅ፣የማበጥ ወይም ህመም ጡትዎ ላይ ካለ
• የማሳከክ፣ሽፍታ፣ቁስለት ጡትዎ ላይ ካዩ
• ደም የተቀላቀለበት የጡት ፈሳሽ ካለዎ ናቸዉ፡፡
@onlyfemaleb